South Ethiopia Region Prosperity Party - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • South Ethiopia Region Prosperity Party - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ

South Ethiopia Region Prosperity Party - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ South Ethiopia Region Prosprity Party Branch Office

በደቡብ ኢትዮዽያ ክልል በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ በተደረገባቸው ምርጫ ጣቢያዎች መራጩ ህብረተሰብ እየተመለከተ ይገኛል።
02/06/2026

በደቡብ ኢትዮዽያ ክልል በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ በተደረገባቸው ምርጫ ጣቢያዎች መራጩ ህብረተሰብ እየተመለከተ ይገኛል።

02/06/2026

ኢትዮጵያ!🇪🇹
መርጣለች፤ ፀንታለች ፤ አሸንፋለች!

01/06/2026

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-

• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

Uummanni Itoophiyaa dinqisiisaafi ajaa'ibsiisaadha! Uumaa malee uummata keenya guutummaan beekuufi gamaaggamuu kan danda'u eenyu? Aadaa gabbataa, uummata biyya jaallatuufi fedhiisaa waloo eeguu danda'u ta'uusaa filannoo baranaatiin irradeebiidhaan addunyaatti agarsiiseera. Guyyaa seena-qabeessa har'aatiin:
- Qorriifi dukkanni halkani kan isaani hin sodaachifne,
- Aduun saafaafi bokkaan tasaa kan isaan jilbeenfachiifne,
- Cidhi, gaddi, da'umsiifi taateewwan hawaasummaa kanbiroon kan isaan dhorkine,
- Hiriironni dhedheeroon kan isaan hin nuffisiifne,
- Qaama miidhamtummaan sagalee kennuuf kan isaan hin daangessine,
- Dhukkubniifi dullumni abdii biyyaa arguuf kan isaan hin dhowwine,
- Daa'imasaanii kichuu bor biyya dhaalu baatanii filuun kan isaan hin dadhabsiifne
- Hundumaa caalaa lammiilee iyyiifi sodaachiifni diinaa isaan hin dhaabsifne,
Ciminni bu'aa bayii hedduu keessatti agarsiiftan gatii diimokraasiifi jiraachuu biyyatiif kanfalame waan ta'eef galata guddaatu malaafi.

Uummata kana tajaajiluun carroomuu waan ta'eef filatamtoonni warra isin kabajan kabajjanii uummata sirna diimookraasiif gatii baase kana qulqullummadhaan tajaajiluuf isin haa gahu.

The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.

On this historic day:

* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;

The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.

It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.

01/06/2026

ኢትዮጵያን በድምፃቸው ለማፅናት የተጉ ዜጎች በምንም አይነት ውስጥ ሆነው የመራጭነት መብታቸውን እየተጠቀሙ ነው።

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

01/06/2026

እዉነትም ኢትዮጵያ 🇪🇹 እየመረጠች ነው!

ከአካል ጉዳተኛ እስከ ሀገር መሪ ሁሉንም እኩል ያሳተፈዉ ምርጫ

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አገራችን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማፅናትና ሕዝባዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጉዞ በግልጽ ያሳየ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው!

01/06/2026

ኢትዮጵያ_እየመረጠች_ነው!!

ዛሬ የወላጅ አባታቸውን ቀብር ፈጽመው ''ከአገር የሚበልጥ ምንም ነገር የለም" በማለት ድምፃቸውን የሰጡት የሀረር ከተማ ነዋሪ ወ/ሮ ቅድስት

የድምፅ መስጠት ሂደት እስከ ምሽት 6:00 ድረስ ተራዝሟል፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!
01/06/2026

የድምፅ መስጠት ሂደት እስከ ምሽት 6:00 ድረስ ተራዝሟል፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

01/06/2026

"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ጉዞ የሚያሳይ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው" ሲሉ የወላይታ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር አመራሮች ገለጹ ግንቦት 24/2018 ዓ.ምበመላው ኢትዮጵያ ዛሬ እየ...
01/06/2026

"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ጉዞ የሚያሳይ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው" ሲሉ የወላይታ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር አመራሮች ገለጹ

ግንቦት 24/2018 ዓ.ም

በመላው ኢትዮጵያ ዛሬ እየተካሄደ ያለው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገሪቱ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እየተመዘገበ ያለውን እድገት የሚያሳይ ታሪካዊ ክንውን መሆኑን የወላይታ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ወሕዲግ) አመራሮች ገልጸዋል።

የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ጎበዜ ጎአ እንደገለጹት፣ የዘንድሮው የድምፅ መስጫ ሂደት ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ምርጫዎች ጋር ሲነጻጸር በብዙ መስፈርቶች የተሻለ ሆኖ ታይቷል። በተለይም ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያለምንም ጫናና ጭቆና በነፃነት በምርጫው ሂደት መሳተፋቸው የኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ግንባታ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና የወላይታ ሶዶ ከተማ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ቶራ በበኩላቸው፣ ዜጎች የፈለጉትን ፓርቲ በነፃነት የሚመርጡበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ እጅግ የሚያበረታታ ለውጥ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም ኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ልምምዷን እያጠናከረች ወደ ተሻለ ፖለቲካዊ ባህል እየተሸጋገረች መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሚልኪያስ አንታ በበኩላቸው፣ የዘንድሮው ምርጫ ከቀደሙት የምርጫ ሂደቶች በተሻለ መልኩ የዲሞክራሲ ግንባታና የሀገረ መንግሥት ሥርዓት ጥንካሬን የሚያሳይ ተስፋ ሰጪ ለውጥ ማሳየቱን አስታውቀዋል።

አመራሮቹ እንደገለጹት፣ ዜጎች የሚፈልጉትን ፓርቲ በነፃነት የሚመርጡበት ዲሞክራሲያዊ ምኅዳር ይበልጥ እየሰፋ እንዲሄድ የሚመኙ ሲሆን፣ ይህ ዓላማ እውን እንዲሆን ሁሉም ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የድርሻቸውን በኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የወሕዲግ አመራሮች፣ የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምን የሕዝብን ውሳኔ እና በድምፅ ሳጥን የተገለጸውን ፈቃድ በአክብሮት ለመቀበል ሙሉ ዝግጁነት እንዳላቸው ገልጸው፣ የዲሞክራሲ ባህል እንዲጠናከር ሁሉም ወገኖች በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት ተራዘመ ግንቦት 24፣ 2018  የድምፅ መስጠት ሒደቱ ከ12 ሰዓት በፊት ሰልፍ ይዘው የቆዩ መራጮች እስኪመርጡ ይቀጥላል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምር...
01/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት ተራዘመ

ግንቦት 24፣ 2018

የድምፅ መስጠት ሒደቱ ከ12 ሰዓት በፊት ሰልፍ ይዘው የቆዩ መራጮች እስኪመርጡ ይቀጥላል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፡፡

በዛሬው ዕለት ከጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ በነቂስ በመውጣት ድምጹን እየሰጠ ይገኛል፡፡

Address

S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Region Prosperity Party - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share