Humbo Woreda Prosperity Party Office Youths Wing = የወጣቶች ክንፍ

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • Humbo Woreda Prosperity Party Office Youths Wing = የወጣቶች ክንፍ

Humbo Woreda Prosperity Party Office Youths Wing = የወጣቶች ክንፍ በብልጽግና እሳቤ ወጣቶች የዛሬውም የነገውም ሁለንተናዊ ሃገራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ባለበት ነው

በሁምቦ ወረዳ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በወጣቶች ንቁ ተሳትፎ በላቀ መነሳሳት እየተከናወነ ይገኛልሁምቦ፤ ሚያዝያ 6/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ 7ኛው ሀገራዊ ጠቅ...
14/04/2026

በሁምቦ ወረዳ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በወጣቶች ንቁ ተሳትፎ በላቀ መነሳሳት እየተከናወነ ይገኛል

ሁምቦ፤ ሚያዝያ 6/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ታስቦ እየተከናወነ ያለው የመራጮች ምዝገባ ሂደት በወጣቶች አደረጃጀት መሪነት ተጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ።

በወረዳው ስር በሚገኙ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የሚካሄደው ይህ የምዝገባ ሂደት፣ ወጣቱ የሀገር ግንባታ ባለቤትነቱን በተግባር እያረጋገጠበት የሚገኝ መድረክ ሆኗል። የወረዳው ወጣቶች በ"1 ለ 10" እና በ"1 ለ 3" አደረጃጀቶቻቸው አማካኝነት መራጩ ሕዝብ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ የመራጭነት ካርዱን እንዲወስድ የቀስቃሽነትና የአስተባባሪነት ሚናቸውን በከፍተኛ ኃላፊነት እየተወጡ ይገኛሉ።

የወረዳው የወጣቶች ክንፍ አመራሮች እንደገለጹት፣ ወጣቱ በምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ከመጠበቅ ጀምሮ፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ወደ ምዝገባ ጣቢያዎች መጥተው ካርዳቸውን እንዲወስዱ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ነው። በተለይም በገጠር ቀበሌዎች የሚገኘው መራጭ ሕዝብ ስለ ምርጫው አስፈላጊነትና ድምፅ የመስጠት መብቱ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ በየቤቱ የሚደረገው ቅስቀሳ ውጤታማ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ የምዝገባ ሂደት ስኬታማ መሆን የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ሥርዓት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ሲሆን፣ የወረዳው ነዋሪዎችም የወጣቱን ጥሪ ተቀብለው በነቂስ በመውጣት ካርዳቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ። የምዝገባ ሂደቱ በሁሉም ጣቢያዎች ያለምንም የፀጥታ ስጋትና በታላቅ የሕዝብ ተሳትፎ እየተከናወነ መሆኑ የወረዳውን ሰላማዊነትና የሕዝቡን የፖለቲካ ንቃት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

በቀሪዎቹ የምዝገባ ቀናትም ማንኛውም ዕድሜው ለምርጫ የደረሰ ዜጋ ካርዱን በመውሰድ ዜጋዊ ግዴታውን እንዲወጣና ለሀገሪቱ ብልጽግና የበኩሉን አሻራ እንዲያኖር ጥሪ ቀርቧል።

!!


በሁምቦ ወረዳ በወጣቶች ክንፍ መሪነት ደማቅ የ"ይምረጡኝ" የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደሁምቦ፤ መጋቢት 22/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት፣...
31/03/2026

በሁምቦ ወረዳ በወጣቶች ክንፍ መሪነት ደማቅ የ"ይምረጡኝ" የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ

ሁምቦ፤ መጋቢት 22/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት፣ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የብልጽግናን ድል የሚያበስር እንዲሆን የታለመ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ።

በቅስቀሳው ላይ የወረዳው ወጣቶች፣ ደጋፊዎችና የፓርቲው አባላት በተገኙበት የብልጽግና ፓርቲ መለያ ምልክት የሆነውን "የስንዴ ነዶ" ከፍ በማድረግ ፓርቲው ላለፉት ዓመታት ያስመዘገባቸውን የልማት ስኬቶችና የቀጣይ የብልጽግና ተስፋዎችን የሚያንጸባርቁ መፈክሮች ተደምጠዋል።

በዕለቱ የሁምቦ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ሀብታሙ ታደመ ለመላው የወረዳው ወጣቶችና መራጭ ሕዝብ ጥሪ አቅርበዋል። ወጣት ሀብታሙ ባስተላለፉት መልዕክት፦

"ወጣቱ የለውጥ ኃይል ብቻ ሳይሆን የብልጽግና ጉዟችን ዋና የጀርባ አጥንት ነው። ዛሬ በዚህ አደባባይ ወጥተን የምናደርገው ቅስቀሳ የፓርቲያችንን ምልክት ስንዴ ነዶን ለማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገርነት ለመቀየር የጀመርነውን ታላቅ ጉዞ ዳር ለማድረስ ቃል የምንገባበት ጭምር ነው" ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም፣ ወጣቱ በምርጫው ዕለት በነቃ ተሳትፎ ድምፁን ለብልጽግና ፓርቲ በመስጠት፣ የወረዳውንና የሀገሪቱን ሰላም፣ ልማትና አንድነት ማስጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል። "ምልክታችን የስንዴ ነዶ የሰላም፣ የጥጋብና የሥራ ምልክት ነው፤ በመሆኑም ብልጽግናን በመምረጥ ለተሻለችና ለበለጸገች ኢትዮጵያ የድርሻችንን እንወጣ" ሲሉ ጥሪያቸውን አጠናክረዋል።

በቅስቀሳው ላይ የተሳተፉ ወጣቶች በበኩላቸው፣ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የሥራ ዕድሎችንና የልማት ፕሮጀክቶችን ወደ ወረዳው እያመጣ መሆኑን ጠቅሰው፣ በምርጫው ዕለት ፓርቲያቸውን በከፍተኛ ድምፅ ለማሸነፍ ዝግጁ መሆናቸውን በደማቅ መነሳሳት ገልጸዋል።

ይህ የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ-ግብር "ብልጽግናን ይምረጡ!" በሚል መሪ ቃል በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ታውቋል።

!
!
!

ዜና፦ የሁምቦ ወረዳ ወጣቶች የከተራና የጥምቀት በዓላትን በድምቀት ለማክበር የጽዳትና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አከናወኑሁምቦ፤ ጥር 10/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ የከተራ እና ...
18/01/2026

ዜና፦ የሁምቦ ወረዳ ወጣቶች የከተራና የጥምቀት በዓላትን በድምቀት ለማክበር የጽዳትና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አከናወኑ

ሁምቦ፤ ጥር 10/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ የከተራ እና የጥምቀት በዓላትን በሰላም እና በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

በላይኛ ሁምቦ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የሚገኙ የወጣት አደረጃጀቶች በዓሉን ምክንያት በማድረግ ታላቅ የጽዳት መርሃ-ግብር አከናውነዋል። ወጣቶቹ የጥምቀተ ባሕር አካባቢን በማጽዳት፣ ባነሮችን በማዘጋጀትና ባንዲራዎችን በመስቀል አካባቢውን ለበዓሉ ዝግጁ እያደረጉ ይገኛሉ።

"በዓሉ የዩኔስኮ ቅርስ እንደመሆኑ በድምቀት ይከበራል" — ወጣት ሀብታሙ ታደመ

በመረሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሁምቦ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወጣት ሀብታሙ ታደመ ባስተላለፉት መልዕክት፦ የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ የዓለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ ታላቅ የአደባባይ በዓል መሆኑን ገልጸው፣ በዓሉ ይዘቱን ሳይለቅ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ወጣቱ በንቃት እየተሳተፈ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም ከከተራ ቀን ጀምሮ በዓላቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቁ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

ኃላፊው አክለውም ወጣቶች የበዓሉን ድምቀት ከመጠበቅ ባለፈ፣ አካባቢን በመጠበቅና ለእንግዶች መልካም አቀባበል በማድረግ ረገድ ያላቸውን ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ይህ የቅድመ ዝግጅት ሥራ በዓሉ በሃይማኖታዊ ሥርዓቱ መሠረት በሰላም እንዲከበር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል።

#ሁምቦወረዳ #ከተራ #ጥምቀት2018 #የወጣቶችተሳትፎ #የዩኔስኮቅርስ

ወጣቶች የድህረ እውነት ዘመንን ተረድተው ሚዲያን በሚዛናዊነት በመጠቀም ገዢ ትርክቶችን ለማስረጽ ታሪካዊ ኃላፊነት አለባቸው፦ወጣት ሚካኤል ዋዳወላይታ ሶዶ፤ታህሳስ 10/2018 የክልሉ ብልፅግና...
19/12/2025

ወጣቶች የድህረ እውነት ዘመንን ተረድተው ሚዲያን በሚዛናዊነት በመጠቀም ገዢ ትርክቶችን ለማስረጽ ታሪካዊ ኃላፊነት አለባቸው፦ወጣት ሚካኤል ዋዳ

ወላይታ ሶዶ፤ታህሳስ 10/2018 የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ከወላይታ ዞን ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ ለወጣቶች ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ሚካኤል ዋዳ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቱ የሀገር ተረካቢ ሳይሆን ባለቤት መሆኑን በፅኑ ያምናል ብለዋል።

ያለወጣቶች ተሳትፎ ብልፅግናን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት ወጣት ሚካኤል፥ ወጣቱ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ግንባር ቀደም ሚናውን እንደሚጫወትም ተናግረዋል።

ወጣቱ ነጠላ ትርክትን ሳይሆን ገዢ ትርክትን ለማጽናት መንቀሳቀስ እንደሚገባም ያሳሰቡት ወጣት ሚካኤል፥ ወጣቱ ሚዲያን ለገዢ ትርክት ግንባታ መጠቀም እንዳለበት አሳስበዋል።

እንደሀገር ብሎም እንደክልል የተጀመሩ ስራዎችን ለማስቀጠል የወጣቱ ሚና የላቀ እንደሆነም የተናገሩት ወጣት ሚካኤል፥ ለዚህም ወጣቱ በሀሳብና በሌሎች መደገፍና ማገዝ እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል መልካም ስራዎችን በሚያጎለብትና ህብረብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ሚዲያን መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለትውልድ ግንባታ፣ ለሀገር ገጽታ ግንባታ መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት፥ ለዚህም ወጣቱ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መውጣት እንዳለበትም አሳስበዋል።

ወጣቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ መጠቀምና ማጋራት እንዳለባቸው ያሳሰቡት ወ/ሮ ሰላማዊት፥ በወጣቱ ክንፉ የሚወርዱ ተልዕኮውን በብቃት ለመፈጸም መትጋት እንዳለባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ታደለ ሜጋ በበኩላቸው በዞኑ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ ተጠቅመው የተለያዩ በጎ ስራዎችን መሰራታቸውን ገልፀዋል።

ይህንን አጠናክረን በማስቀጠል ሚዲያን ለገዢ ትርክት ግንባታ፣ ለህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትን፣ አንድነትንና አብሮነትን ለማጽናት መጠቀም ይጠብቅብናል ብለዋል።

በመድረኩ የክልልና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የወረዳና ከተማ የወጣት ክንፎች፣ የዞን ማዕከል የወጣቶች ክንፍ ብልፅግና ህብረት ሰብሳቢዎች እና ሌሎችም እየተሳተፉ ናቸው።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ታደለ ሜጋ ጊፋታ በዓል በዓለም ቅርስነት በመመዝገቡ ለወጣቶች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉኃላፊው የወላይ...
10/12/2025

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ታደለ ሜጋ ጊፋታ በዓል በዓለም ቅርስነት በመመዝገቡ ለወጣቶች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ኃላፊው የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት በመመዝገቡ ለመላው ወላይታ ወጣቶች እና እንድሁም ለወላይታ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጊፋታ የወላይታ ህዝብ የአዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት ትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) የተመዘገበው ድርጅቱ 2ዐኛው የኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርስ ጥበቃ የመንግስታት ኮሚቴ ስብሰባ ከታህሳስ 8 እስከ 13፣ 2ዐ25 ድረስ በህንድ ሀገር በኒው ዴሊ ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው ጉባኤ ነው ብለዋል፡፡

በዓሉ በዩኔስኮ በመመዝገቡ ለወጣቶች፣ ለአጠቃላይ ሕዝብና ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም ያለውና ለህብረብሔራዊ አንድነትና ገዢ ትርክትን ለመገንባት ፋይዳው የጎላ እንደሆነም ተናግረዋል።

የወላይታ ብሔር የበርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ባለቤት ነው ያሉት ኃላፊው፥ ከማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል አንዱ እንደሆነም አስረድተዋል።

የጊፋታ በዓል በተለያዩ ስፍራዎች ተራርቀው የሚገኙ የቤተሰብ አባላት፣ ዘመድ አዝማድና በተለያዩ ማህበራዊ መስተጋብሮች የተጣመሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከቤተሰብ ጋር በመሆን በጋራ የሚያከብሩት የአብሮነትና የአንድነት ማሣያ በዓል መሆኑንም ገልጸዋል።

መላዉ የወላይታ ወጣቶችና ህዝብ ይህንን የአባቶቻችንን አኩሪና ብርቅዬ ባህል ሳይበረዝና ሳይከለስ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንዲተላለፍና ከነሙሉ ክብሩ ተጠብቆ እንድቆይ የሁል ጊዜ ትጋታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ያላሰለሰ ድጋፍና ትብብር እንዲሁም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱት ወጣቶች በሙሉ ልባዊ ምስጋናን አቅርበዋል።

11/11/2025
ወጣቱ ሙስናን በመታገል ግንባር ቀደም በመሆን ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ታደለ ሜጋ ገለጹወላይታ ሶዶ፣ጥቅምት 29/2018 ዓ....
08/11/2025

ወጣቱ ሙስናን በመታገል ግንባር ቀደም በመሆን ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ታደለ ሜጋ ገለጹ

ወላይታ ሶዶ፣ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ከዞኑ ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር "ሙስናን በመከላከል የወጣቶች ሚና" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ
የአሠልጣኞች ሥልጠና ለክንፍ አመራሮች እና አስተባባሪዎች ሰጥቷል።

በሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ለወጣቶቹ የሥራ መመሪያ የሰጡት የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ታደለ ሜጋ እንደገለጹት ወጣቱ ሙስናን በመታገል ግንባር ቀደም በመሆን ሚናውን ሊወጣ ይገባል።

የሥልጠና መድረኩ ወደ ታች ስወርድ ብዙሃን ወጣቶች የሚገኙበት በመሆኑ ያለ ምንም መንጠባጠብ እንዲፈጸሙ በትግል ሊመራ ይገባል ሲሉ ወጣት ታደለ።

የዞኑ ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስተባባሪ አቶ አሰላ ተካ እንደገለጹት ያለ ወጣቱ ተሳትፎ የሙስና ትግል ግቡን እንደማይመታ በመግለጽ በመሬት ወረራ፣ በፎርጅድ ደረሰኝ፣ በአላግባብ የወጣቶች የሥራ ስምርት እንዲሁም ከሐሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ጋር በተያያዘ ትግል ሊደረግባቸው የሚገቡ መስኮች ናችው።

ሙስና የህዝባችንን ተጠቃሚነት ብሎም የወጣቱን ተጠቃሚነት የሚያቀጭጭ በመሆኑ ወጣቱ ለራሱ ተገንዝቦ ሌላውን የማስገንዘብ ሥራ በትኩረት ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአሠልጣኞች ሥልጠና ተሳታፊ ወጣቶች ሙስና የብልጽግና ፓርቲ ቀይ መስመር ነው ሲሉ የሙስና ወንጀል በማጋለጥ ትግል ማድረግ እንደሚችሉ አንስተዋል።

በታችኛው መዋቅር የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የማጠናከር ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ እንዲሁም ወጣቱ ራሱን ከሙስና በማፅዳት ትግሉን ከራስ መጀመር እንዳለበት አንስተዋል።

በትምህርት ቤቶች በተለይም በወጣቶች ላይ ሙስና በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ሊሠራ ይገባል ሲሉ በማንሳት ወጣቱ የበይ ተመልካች ሳይሆን ከኮሚሽኑ ጎን በመቆም ትግሉን ሊያጧጡፍ ይገባል ብለዋል ወጣቶቹ።

ሙስና በሚፈጽሙ አካላት ላይ የሚወሰደው ርምጃ አስተማሪ መሆን እንደሚገባ በማንሳት ከተናጠል እንቅስቃሴ ይልቅ የባለ ድርሻ አካላት ቅንጅት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

ሠልጣኞቹ የሙስና ትግል በተደራጀ መረጃ እና ማስረጃ በመታገዝ ሊፈጸም እንደሚገባ በማንሳት የማህበረሰቡን አመለካከት በመቀየር ሙስናን እንዲጠየፍ የማድረግ ሥራ በትኩረት እንዲሠራ ጠይቀዋል።

የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ከዞኑ ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለክንፍ አመራሮች እና አስተባባሪዎች የአሠልጣኞች ሥልጠና መድረክ እያካሄደ ነው...
08/11/2025

የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ከዞኑ ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለክንፍ አመራሮች እና አስተባባሪዎች የአሠልጣኞች ሥልጠና መድረክ እያካሄደ ነው።

ሥልጠናው "ሙስናን በመከላከል የወጣቶች ሚና" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሲሆን ሁሉም የወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት አመራሮች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

ሁምቦ፣ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ከዞኑ ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለክንፍ አመራሮች እና አስተባባሪዎች የአሠልጣኞች ሥልጠና መድረክ እያካሄደ ነው።

ሥልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ታደለ ሜጋ ወጣቶች በሌሎችም ተግባራት የመንግሥት ሥራ እንዲሳለጥ ግንባር ቀደም ሚናቸውን ሲወጡ እንደነበረ አንስተዋል።

ሙስና የወጣቶችን ተጠቃሚነት እጅጉን የሚጎዳ በመሆኑ መዋጋትምና በመከላከሉ ወጣቶች የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ ወጣት ታደለ ተናግረዋል።

በአሠልጣኞች ሥልጠና ያገኙትን ዕውቀት ወደታች በማውረድ ትግሉን የማፋፋም ሥራ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ኃላፊው።

የዞኑ ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስተባባሪ አቶ አሰላ ተካ ለወጣቶቹ በሰጡት ማብራሪያ ሙስና የልማት እና የዕድገት የካንሠር ነው በመግለጽ የወጣቶችን ተጠቃሚነት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ወጣቶች ትግሉን እንዲቀላቀሉ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

የሙስና አደገኛነቱ የሚመነጨው መረጃንና ማስረጃን በማጥፋት የሚነሳ ሲሆን የአገር ስጋት የሆነ ተግባር ነው ሲሉም ተናግረዋል።

አቶ አሰላ እንደተናገሩት እንደ አፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት ሆኖ ሳለ ተጠቃሚነቱን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ወጣቶች አምርረው ሊታገሉ ይገባል።

የሙስና ትግሉ ዋና ዓላማው ሙስናን የሚጠየፍ ማህበረሰብ መፍጠር ነው ሲሉም ተናግረዋል።

03/11/2025

የወጣቶችን ጥያቄ የሚመልሰው ባንክ…

ሙፈሪያት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የወላይታ ዞን ቀይ መስቀል ማህበር ቅ/ጽ/ቤት  ለዞኑ ወጣቶች ክንፍ አመራሮች የበጎ ፈቃደኞች ማጠናከሪያ ሥልጠና ሰጠሁምቦ፤ጥቅምት 22/2025 ዓ.ም የወላይታ ዞን ቀይ መስቀል ማህበር ቅ/ጽ/...
01/11/2025

የወላይታ ዞን ቀይ መስቀል ማህበር ቅ/ጽ/ቤት ለዞኑ ወጣቶች ክንፍ አመራሮች የበጎ ፈቃደኞች ማጠናከሪያ ሥልጠና ሰጠ

ሁምቦ፤ጥቅምት 22/2025 ዓ.ም የወላይታ ዞን ቀይ መስቀል ማህበር ቅ/ጽ/ቤት ከዞኑ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር "ሰብዓዊ አገልግሎት ለትውልድ" የበጎ ፍቃደኞች ማጠናከሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።

የወላይታ ዞን ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አማኑኤል አይዛ በሥልጠናው ባስተላለፉት መልዕክት በዞኑ የወጣቶች ክንፍ በበጎ ፍቃደኝነት እና በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር በተለይ በክረምት እና በጋ በጎ ፍቃድ ወጤታማ ተግባራትን ማከናወናቸውን ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም ወጣቶች የማህበሩ የወደፊት ብቻ ሳይሆኑ የአሁኑም የለውጥ መሪ ተዋናይ ናችሁ፣ የበጎ ፈቃደኝነትን አገልግሎት በብቃትና በሥነ-ምግባር በመምራት፣ ለቀጣዩ ትውልድ የሰብዓዊነት ድልድይ የመሆን ወሳኝ ታሪካዊ ሚና አላችሁ በማለት ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ጃራና ጃርሳ የወላይታ ዞን ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የበጎ ፋቃደኞች አባላት ዘርፋ ኃላፊ ሥልጠናው ለዞኑ ቀይ መስቀል ቅ/ጽ/ቤት ሰብዓዊ ተልዕኮ ዘላቂነት ወሳኝ መሆኑን አንስተው ወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት በብቃት፣ በቁርጠኝነትና በሥነ-ምግባር በመምራት፣ የቀይ መስቀልን መርሆዎች ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ አለባችሁ ብለዋል።

አክለውም ወጣቱ ለሰብዓዊነትና ለበጎ ፍቃድኝነት በግምባር ቀደምትነት የሚሰልፍ ኃይል እንደመሆኑ መጠን እንደዞን በሁሉም መዋቅሮች የሚገኙ የክንፍ አባላትን በማስተባበር ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፍ ወጣት ታደሌ ሜጋ የቀይ መስቀል እንቅስቃሴ መሠረት በጎ ፈቃደኞች ናቸው፤ በተለይም የወጣቶች ክንፍ አባላት! የለውጡ ሞተሮች መሆናቸውን ገልፀዋል።

የበጎ ፈቃደኝነትን አገልግሎት በብቃት፣ በቁርጠኝነትና በሥነ-ምግባር በመምራት፣ ለቀጣዩ ትውልድ የሰብዓዊነት ድልድይ የመሆን ወሳኝ ታሪካዊ ሚና እንዳለቸው ገልጸው የክንፉ አመራሮች በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ብለዋል።

ሥልጠናው በዞኑ ያሉ የክንፉ አመራሮችና አባላት የቀይ መስቀልን ዓለም አቀፍ መርሆዎች እንዲረዱና በሰብዓዊ አገልግሎት ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ እንደነበረ ያስታወቁ ኃላፊው የውይይት ተሳታፊ የክንፉ አመራሮችም የቀይ መስቀል መሰረታዊ መርሆች በጥልቀት አተገባበር ላይ፣ በአደጋ ወቅት የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥ ተግባራዊ ክህሎቶች ላይ፣ በጎ ፈቃደኞች በአካባቢያቸው ለሰብዓዊነት አርአያ የመሆን ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የወጣቶቹ ክንፍ አመራሮች እና አባላት በበኩላቸው፣ የሰለጠኑበትን ዕውቀትና የሰለጠኑበትን መንፈስ ይዘው በአካባቢው የሰብዓዊነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትልቅ አስተዋፅዖ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል የወጣቱን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማረጋገጥ ወሳኝ ነው፣ ሻምበል ስለሞን ላቤናሁምቦ፦ ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረ...
29/10/2025

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል የወጣቱን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማረጋገጥ ወሳኝ ነው፣ ሻምበል ስለሞን ላቤና

ሁምቦ፦ ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የፐብሊክ ግንባር ህብረት ይፋዊ ምስረታ አካሄደ።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሁምቦ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖሊቲካ እና ሕዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ኃላፊ ሻምበል ሰለሞን ላቤና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል የወጣቱን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ገለጹ።

አክለውም ወጣቶች በሀገር ዕድገት ብልጽግና የድርሻውን ሚና እንዲወጡ አደረጃጀቶችን በማጠናከር በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና በአካባቢ ሰላም የማስፈን ስራና በበጎ ፍቃድ ተግባራት ላይ ራሳቸው ግንባር ቀደም ተዋናይ ሆነው ሊሳተፉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ወጣቶች ስራን ከመጠበቅ መንፈስ ተላቅቀው ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑና መንግሥት ያመቻቸውን ስራ ዕድል ተጠቃሚ በመሆን ከራስ አልፎ ለህብረተሰቡ ጭምር አምራች ዜጋ መሆን እንዲችሉ የግንዛቤ ሥራውን በሁሉም አከባቢ በአደረጃጀት ሊሠራ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ወጣቶችን የሚያደራጀው የፓርቲው አባል እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ዕድገትና ብልጽግና ዕቅዶችን በመተግበር ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይና የለውጡ ባለቤት እንዲሆኑ ነው።

የሁምቦ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ንጉሴ ኢልካ ወጣቱን በሁሉም ዘርፎች ተሳታፊና ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዉ በበጀት ዓመት በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የነበሩ የተግባር ዉስንነቶችን ለቅሞ በማረም የተያዙ እቅዶችን በጥንካሬ ማስቀጠል እንደሚገባ አብራርተዋል።

የወጣቶች ክንፍ "የተግባር ሩጫን በማፍጠን፣ የጥራትና የውጤታማነት ጉድለቶችን በመሙላት" በቀሪው የበጀት ዓመት የታሰበውን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማምጣት ወጣቱ ትውልድ ድርሻውን በበለጠ እንዲወጣ ተግቶ የሚሰራ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

የአባላትን መዋጮ በተመለከተ፣ በወጣቶች ስብዕና ግንባታ እና በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ የወረዳው ወጣቶች ክንፍ ከባለድርሻ ተቋማትና ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ እንዲሁም የወጣት አደረጃጀቶችን የበለጠ የማጠናከር ስራ እንደሚሰራ ተናግሯል።

ማህበራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶች በበጋ ወራት ለሚከናወኑ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸው ተመላክቷል።

የሁምቦ ወረዳ ወጣቶች ፌደሬሽን ፕረዝዳንት ወጣት አበባየሁ ተመስገን በበኩላቸው እንደገለጹት የወጣቶችን ተጠቃምነትን ለማረጋገጥ በሁለንተናዊ መልኩ ወጣቱ ክፍል የሀገርም ባለቤት በመሆኑ ትጉህና ታታር፤ ፈተናውን ታግለው በማለፍ ለሀገርና ማህበረሰቡ ኢኮኖምያዊ፣ ማህበራዊና ፖለትካዊ ዘርፎች ለውጦችን ማምጣት እንዳለባቸው አንስተዋል።

ወጣቶች ክንፍ ከሌሎች አቻ አደረጃጀቶች ጋር ተናቦ እና ተቀናጅተው የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እና ፖለቲካዊ ተሳትፎን ለማረጋገጥ የሚያደረገው ውጤታማ ተግባርን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ገልጸዋል።

አክለውም በቀጣይ የወጣቶች አደረጃጀቶችን በማጠናከር ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን የሚያጎሉ ተግባራትን በማከናወን ብሎም በስብዕና ግንባታ ዘርፍ በክንፉ አስተባባሪነት ይሠራል ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ተግባራትን ለማከናወንና ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት ለመፍጠር በየጊዜው እየተገመገመ መመራቱ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የሁምቦ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የፐብሊክ ሰርቭስ ብልጽግና ህብረት አመራሮች ምርጫ በማካሄድ ተጠናቋል።

Address

Humbo
S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Humbo Woreda Prosperity Party Office Youths Wing = የወጣቶች ክንፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share