የወላይታ ሶዶ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት -wolaita sodo city peace and security office

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • የወላይታ ሶዶ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት -wolaita sodo city peace and security office

የወላይታ ሶዶ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት -wolaita sodo city peace and security office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የወላይታ ሶዶ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት -wolaita sodo city peace and security office, Government Official, Sodo.
(1)

19/02/2026
04/02/2024

ሰላም የአሸናፊዎች ምርጫ ነው፡፡ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው ፡፡ በሰላም እጦት ምክንያት ለበርካታ አስርት አመታት የኢትዮጵያ ህዝብ የተጎዳና የተጎሳቆለ ህዝብ ነው፡፡ በባለፉት የአገዛዝ ዘመናት እጆቻችን ወደ ጦርነት እንጅ ወደ ልማት ባለመዘርጋታቸው ጥንት ከነበርንበት የስልጣኔ ማማ ተንከባለን ወርደን የድህነት ቅርቃር ውስጥ መግባታችንን ልንክደው የማንችለው የገሀዱ አለም እውነታ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣውን ሰላምን ብቻ ባለመከተላችን ነው፡፡

ሰላም ብቸኛ አማራጭ ነው፡፡ ጦርነት አንድም ጊዜ መፍትሄ ሆኖ አያውቅም፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ የእርስበርስ ውጊያዎች ተካሂደዋል፡፡ በእነዚህ የእረስበርስ ጦርነት ውስጥ ምንም አይነት አወንታዊ ውጤት ተመዝግቦበት አያውቅም፡፡ በእርስበርስ ጦርነት የሚፈታ የፖለቲካ ችግርም የለም፡፡ የሚያኮሩን ታሪኮች ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር ብቻ ያደረግናቸው ጦርነት እንጅ እርስበርስ ያደረገናቸው ውጊያዎች አይደሉም፡፡

ሰላም ከሌለ ለዘመናት የተገነቡ የስልጣኔ አሻራዎች በሰዓታት ወይም ከዚያም ባነሰ ጊዜ ውስጥ ዶግ አመድ ሲሆኑ በአገር ልጆች አለመግባባት ሰማይ በባሩድ ጭስ ሲታጠን፣ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች ሲጋዩ፣መሰረተ ልማት ሲወድም፣በሰላም ወጥቶ መግባት አደጋ ላይ ሲወድቅ፣ዜጎች ሰላማዊ ህይወትን ፍለጋ ድንበርና ባህርን ለማቋረጥ ሲሰቃዩ ሰላም በዋጋ ሊተመን የማይችል ውድ ሀብትና ሁላችንም በጋራ ልንቆምለት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

የአገራችን የርሀብና እርዛት እንዲሁም ኋላ ቀርነት ተምሳሌት ሊፋቅ የሚችለው የሰላም አየር እየተነፈስን፤የኢትዮጵያን ከፍታ እያሰብን በጋራ በልማት ጎዳና መትመም ስንችል ነው፡፡ ሁሌም ቀውስ መለያው በሆነው የአፍሪካ ቀንድ መገኘታን በሰላማችን ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ቀላል ባይሆንም ለሰላም መደፍረስ መንስኤ የሆኑ ውስጣዊ ችግሮችን በመፍታት ላይ በትኩረት በመስራት ከአገራችን አልፎ የአፍሪካ የሰላም ዘብ መሆን እንችላለን፡፡

ዛሬ የሰፈነው ሰላም ነገም በአስተማማኝ ደረጃ ሊቀጥል የሚችለው ሁሉም ለሰላም ተግቶ ሲሰራና ሰላምን የሚያፈርሱ ነገሮችን ያለ ምህረት ሲታገል ብቻ ነው፡፡እውቁ ማህተመ ጋንዲ በአንድ ወቅት እንዳሉት ‹‹ስለ ሰላም ማውራት በቂ አይደለም፡፡ አንድ ሰው በሰላም ማመን አለበት፡፡ ማመን ብቻ ደግሞ በቂ አይደለም ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ግድ ይላል፡፡›› ሲሉ ሁላችንም ስለ ሰላም ዘብ መቆምና ተግባራዊ ማድርግን እንዳለብን መክረዋል፡፡

ትናንት በአስተማማኝ ሰላም ላይ የነበሩ ሀገሮች ዛሬ ሰላማቸው ደፍርሶ ዜጎቻቸው ሰርቶ መኖርን ይቅርና በህይወት ለመቆየት እንኳ ፈተና ሆኖባቸዋል፡፡ለዚህም ሶሪያ፣ሊቢያና የመንን እንደምሳሌነት መመልከት ይቻላል፡፡

በሀገራችን ሰላምና ሰላማዊ ሁኔታ ጠብቀን ማስቀጠል ከቻልን ወቅታዊ ችግሮቻችን ብቻ ሳይሆን ተብትቦ ከያዘን ድህናትና ኋላቀርነትም ለዘለቄታው መላቀቅ እንችላለን፡፡ ሰላም ከሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ የሀገራችንን ራእይ እውን ማድረግ እንደምንችል መገመት አያዳግትም፡፡ስለ ሰላም እንዘምር ስለተግባራዊነቱ ሁላችንም እንቀሳቀስ!

መልካም የእረፍት ቀን እንዲሆንላችሁ ተመኘን!!

04/02/2024
31/01/2024
በዲሽታ ጊና ምድር  (ጂንካ ) ማዕከል  ጉዞአችን ከዕዳ  ወደ ምንዳ ይሆናል ።
03/12/2023

በዲሽታ ጊና ምድር (ጂንካ ) ማዕከል ጉዞአችን ከዕዳ ወደ ምንዳ ይሆናል ።

Address

Sodo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የወላይታ ሶዶ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት -wolaita sodo city peace and security office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share