Kindo Koysha Woreda Government communication Affairs Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • Kindo Koysha Woreda Government communication Affairs Office

Kindo Koysha Woreda Government communication Affairs Office Government Organization

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ በዓል በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰን!፦ ዕጩ ዶ/ር ደገፉ ዳልኬየኪንዶ ኮይሻ ወሰዳ ዋና አስተዳዳሪ ዕጩ ዶ/ር ደገፉ ዳልኬ የገ...
06/01/2026

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ በዓል በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰን!፦ ዕጩ ዶ/ር ደገፉ ዳልኬ

የኪንዶ ኮይሻ ወሰዳ ዋና አስተዳዳሪ ዕጩ ዶ/ር ደገፉ ዳልኬ የገና በዓልን በማስመልከት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪዉ ገና በዓል በክርስቲና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ትርጉም ያለውና ተከታዮች መንፈሳዊ ፣ ማህበራዊ እና ሰብዓዊ ውጤቶችን ያገኙበት በዓል በመሆኑ ይህንን በዓል ትርጉም ባለው ሁኔታ ያከብሩታል ብለዋል።

ገና በዓል የፍቅርና የሠላም መልእክት ለዓለም የተላለፈበትና ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ህዝብ ፍቅሩን ያሳየበት ፣ምህረትን ፣ይቅርታንና ሠላምን ለዓለም ህዝብ ያወጀበት በዓል በመሆኑ ትርጉም ተሰጥቶት እንደሚከበርም አብራርተዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው ልጆች እና በአምላክ መካከል የነበረውን ጥል አስወግዶ በምህረት፣ በይቅርታ እና በታላቅ ፍቅር ወደ ምድር መምጣቱ የሰላም እና ፍቅር ምሳሌ መሆኑ የሚያንፀባርቅ በዓል ነዉ ስሉም ገልፀዋል፡፡

እኛም በዓሉን ስናከብር ያለው ለሌለው እያካፈልን ፣ የታመሙትን በመጠየቅ፣ የተቸገሩትን በመርዳት የአብሮነት እሴቶችን በማስቀጠል ሊሆን ይገባል ስሉም ዋና አስተዳዳሪዉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የወረዳችን ነዋሪዎች የአከባቢያችንን ሰላም ከፀጥታ መዋቅራችንና ከአመራሮች ጋር በጋራ በመሆን አስፈላጊውን መረጃ በመለዋወጥ በዓሉን ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አሳስበዋል።

በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት ፤ የመቻቻል እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ብለዋል።

!!

በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በ16ኛው ወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፕዮና እግር ኳስ ውድድር  ሻምፕዮን የሆነው የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ እግር ኳስ ብድን ዋንጫውን ይዘው ስመለሱ ደማቅ አቀባበል ተደር...
28/04/2025

በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በ16ኛው ወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፕዮና እግር ኳስ ውድድር ሻምፕዮን የሆነው የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ እግር ኳስ ብድን ዋንጫውን ይዘው ስመለሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጓል ።

ኪንዶ ኮይሻ ፦ሚያዝያ 2017 ዓ.ም በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በ16ኛው ወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፕዮና እግር ኳስ ውድድር ሻምፕዮን የሆነው የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ እግር ኳስ ብድን ዋንጫውን ይዘው ስመለሱ የአከባቢው ማህበረሰብ፣የፀጥታ አካላት እንድሁም የሞተር እና ብያጃጅ አሽከርካሪዎች መንገድ ላይ ወተው ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

በዚህም ስፖርተኞች የወረዳው ስም በማስጠራት የዋንጫና ሌሎች ወርቅና ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆናቸው የአከባቢው ማህበረሰብ በመደሰት በነቂስ ወጥተው ስፖርተኞችን እያሞገሰ በማረታታት ዋንጫውን ይዘው በመዞር ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል ።

የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትዕዛዙ ጌታሁን ጨምረው የወረዳው አስተባባሪዎች በ16ኛው ወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፕዮና ውድድር በ15 ቀን ቆይታቸው የስፖርት ጨዋነትን በማሳየት ጠንካራ ሠራተኛ እና ተወዳዳሪ በመሆን የወረዳውን ስም በማስጠራት የዋንጫ ተሸላሚ የሆነውን የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የእግር ኳስ ብድን፣እንድሁም ወርቅና የሜዳሊያ ተሸላሚ የሆኑ ወርልድ ተኳንዶ፣እና ፓራኦሎምክ ተወዳዳሪዎችን በወረዳው ስም አመስግነዋል ።

 #እንኳን ደስ አላችሁ  መላው የስፖርት አፊቃሪያን በሙሉኪንዶ ኮይሻ ፦ ሚያዝያ 19/2017 ዓ/ም በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ው...
27/04/2025

#እንኳን ደስ አላችሁ መላው የስፖርት አፊቃሪያን በሙሉ

ኪንዶ ኮይሻ ፦ ሚያዝያ 19/2017 ዓ/ም በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር ኪንዶ ኮሻ ድጉና ፋንጎ አቻውን 8 ለ 7 በሆነ መለያ ምት በማሸነፉ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋ ።

መላው የወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛልኪንዶ ኮይሻ፤ሚያዚያ 19/2017 16ኛው መላው የወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን ...
27/04/2025

መላው የወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል

ኪንዶ ኮይሻ፤ሚያዚያ 19/2017 16ኛው መላው የወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል።

ለተከታታይ 15 ቀናት የቆየው 16ኛው መላው የወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን እንደሚያገኝ ተገልጿል።

ዛሬ ከረፋዱ 6:00 ሰዓት ላይ የተጀመረው የከተሞች ጨዋታ አረካ ከተማ ከቦዲቲ ከተማ አቻው የእግርኳስ ፍጻሜ ውድድር እየተደረገ ነው።

የእግርኳስ ሻምፒዮና ዛሬ ድጉና ፋንጎ እና ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በሚያደርጉት ጨዋታ ፍጻሜውን ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ሚያዚያ 3/2017 ዓ.ም የተጀመረው መላው የወላይታ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮን ውድድር ከ1357 በላይ ስፖርተኞች በ11 ስፖርት አይነቶች መሳተፋቸውን ይታወሳል።

ዛሬ በሚደረገው የፍጻሜ ውድድር የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያምን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ስፖርት አፍቃሪያን ተገኝተዋል።

ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን በማሸነፍ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ አለፈበኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ወደ ፍጻሜ ማለፉን...
26/04/2025

ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን በማሸነፍ ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ አለፈ

በኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ወደ ፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል፡፡

ወላይታ ድቻ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገውን ሸገር ከተማን ባሸነፈበት ጨዋታ ዘላለም አባተ እና ብዙዓየሁ ሰይፈ የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡

ወላይታ ድቻ ድሉን ተከትሎ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታቸውን ከሚያደርጉት መቻልና ሲዳማ ቡና አሸናፊ ጋር በፍጻሜው ይፋለማል፡፡

በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚ የነበረው ወላይታ ድቻ በፍጻሜው በኢትዮጵያ ቡና ተሸንፎ ዋንጫውን ማጣቱ ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን የሚሆነው ክለብ በቀጣዩ ዓመት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ተሳታፊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ! ደስ አለን!

ፕሮጀክቶች እና ስኬቶቻችን ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን በጊዜና በተገቢ ደረጃ ለማጠናቀቅ የተሰጠው አቅጣጫ ብዙዎችን ለፍጻሜ እያበቃቸው ነው፡፡ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 98.66 ደርሷል፡፡ የ...
26/04/2025

ፕሮጀክቶች እና ስኬቶቻችን

ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን በጊዜና በተገቢ ደረጃ ለማጠናቀቅ የተሰጠው አቅጣጫ ብዙዎችን ለፍጻሜ እያበቃቸው ነው፡፡ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 98.66 ደርሷል፡፡ የኮይሻ፣ አይሻና አሰላ የኃይል ማመንጫዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሠረት እየተጓዙ መሆናቸው ተገምግሟል፡፡ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታም የኢትዮጵያን ነገ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የቅድመ ዝግጅት ምእራፉ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የኮሪደር ልማት በአዲስ አበባ በ8 ኮሪደሮች እና በመላው ኢትዮጵያ በ65 ከተሞች እየተከናወነ መሆኑ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡ ብዙዎቹ የመስኖ ግድቦች ወደ ፍጻሜያቸው እየደረሱ ናቸው፡፡ ከዘጠኙ የመስኖ ግድቦች ውስጥ ስድስቱ አፈጻጸማቸው ከ75 በላይ ደርሷል፡፡

የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ለወረዳና ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት አመራሮች፣ ለሶፍትዌር፣ ሳይንስና ፈጠራ እንዲሁም ኔትዎርክ ባለሙያዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው።ኪንዶ ኮይሻ...
24/04/2025

የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ለወረዳና ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት አመራሮች፣ ለሶፍትዌር፣ ሳይንስና ፈጠራ እንዲሁም ኔትዎርክ ባለሙያዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው።

ኪንዶ ኮይሻ፣ ሚያዝያ 16/2017 (ወዞመኮጉመ)

የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ አሉላ ሥልጠናውን በከፈቱበት ንግግራቸው መንግሥት ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ እንደሆነ በማመን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ያለ ቴክኖሎጂ የትኛውንም ተግባር ማከናወን በማንችልበት ጊዜ ይመጣል ሲሉ ተናግረው ዘመኑን የሚመጥን የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክሂሎት ልንታጠቅ ይገባናል ብለዋል አቶ አበራ።
የመምሪያው ኃላፊ አያይዘውም በቴክኖሎጂ ዕውቀት የበቁ አመራሮች እና ባለሙያዎች ማፍራት አስፈላጊ ነው ሲሉ በመግለጽ በሥልጠናው የተገኘውን ዕውቀትና ክሂሎት ለሌለው የማሠልጠን ኃላፊነት እንዳለባቸውም አቶ አበራ ገልጸዋል።

ባለሙያዎች እና አመራሩ ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ተናግረው የኢትዮ ኮዴርስ የዞናችን ዕቅድ ለማሳካት ሁሉም ርብርብ ሊያደርግ እና በባለቤትነት ሊመራ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል።

ሥልጠናው በኢትዮ ኮዴርስ፣ በሳይንስና ፈጠራ በሶፍትዌር እና ኔትዎርክ ሥራዎች ዙሪያ ያተኮረ ነው።
ለበለጠ መረጃ:-
በFace book:- https://www.facebook.com/wolaitazoncom
Telegram :-https://t.
me/+GBv6ogcPjnM3N2M0፤
https://t.me/+6iRg3Z_zlpjMGY0https://t.me/+uBR_aSLcGeQ0YTE0
በYouTube፡-https://youtu.be/DPl3adPnDjc
ይከታተሉን፡፡

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ   የአለም አቀፍ IT ክህሎት ባለቤት ይሁኑ!!ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን  #ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮግራም ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመ...
24/04/2025

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ

የአለም አቀፍ IT ክህሎት ባለቤት ይሁኑ!!

ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን #ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮግራም ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር አስጀምራለች።

ፕሮግራሙ ለ 3 ዓመታት ያህል የሚቆይ ሲሆን በፕሮግራሙ የተካተቱ ስልጠናዎች Programming Fundamentals, Data Science Fundamentals እና Android Developer Fundamentals ናቸው።

?

ስልጠናዎቹን Udacity በተሰኘው አለም አቀፍ እውቅና ባለው ኦላይን የትምህርት ፕላትፎርም ተዘጋጅተው ይቀርባሉ።

?

በዚህ ድረ-ገጽ አድራሻ ፡ https://ethiocoders.et/
ሰልጣኞች ያለ አንዳች ክፍያ በነጻ ኮምፒውተራችሁን ወይም ስማርት ስልካቸውን በመጠቀም መሰልጠን ትችላላችሁ። ስልጠናዎቹ 6-7 የሚሆኑ ሳምንታትን የሚፈጁ ሲሆን በማጠቃለያው ላይ አለም አቀፍ ሞያዊ ሰርተፊኬት ይሰጣል።

?

በዚህ ድረ-ገጽ አድራሻ ፡ https://ethiocoders.et/ )
በክልል በዞን በወረዳ በከተማ አስተዳድር ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ/መመሪያ/ጽ/ቤት
ይሄን መልዕከት Share በማድረግ መልዕክቱ ለሁሉም እንዲደርስ አድርጉ !!

Address

S**o

Telephone

+251910042504

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kindo Koysha Woreda Government communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share