Bayra koysha woreda Health office

Bayra koysha woreda Health office Health for all

30/05/2025
በባይራ ኮይሻ ወረዳ ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ፣ በቅሎ ሰኞ፣ የካቲት 14/2017 ዓ ም በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ የመጀመሪያ ዙር...
21/02/2025

በባይራ ኮይሻ ወረዳ ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ፣

በቅሎ ሰኞ፣ የካቲት 14/2017 ዓ ም በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ የመጀመሪያ ዙር የልጅነት ልምሻ(ፖሊዮ) ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል።

ክትባቱን የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝማቹ ዳዊት ከጤና ጽ/ቤት አመራሮችና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመሆን መልዕክት አስተላልፎ አስጀምሯል።

በወረዳው በሁሉም ቀበሌ ክትባቱ ከየካቲት 14—17/2017 ለተከታታይ አራት ቀናት የሚሰጥ ስሆን ወላጆች ልጆቻቸውን በማስከተብና በሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች ለሚደረገው አሰሳ ተገቢውን መረጃ በመስጠት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት ተላልፈዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የጤና ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ክትባቱ በሁሉም ቦታ ተደራሽ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንዲሰሩና ዘመቻው የተፈቀደው ቀን እስኪያልቅ ድረስ ወላጆች ከፍተኛ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለንባይራ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት ተቋማት ጥረት (EPAQ) 1ኛ ዑደት አፈፃፀም...
23/11/2024

እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን

ባይራ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት ተቋማት ጥረት (EPAQ) 1ኛ ዑደት አፈፃፀም በ2016 ዓ ም በክልል ደረጃ 1ኛ በመሆን ተሸላሚ ሆኗል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት ተቋማት ጥምረት ለጥራት (EPAQ) 1ኛ ዑደት አፈጻፀም ግምገማ መድረክ የባይራ ኮይሻ ወረዳ በ91 ወረዳዎች መካከል 1ኛ በመሆን የዋንጫ፣ የመዳሊያና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆኗል።

በሰው ህይወት ላይ አስከፊ ጉዳት ማድረስ የሚችለውን የወባ በሽታ ወረርሽን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለአጠቃላይ ህብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ድርሻ አለው ተብሏል፣በቅሎ ሰኞ፣ ጥቅምት 06/2017 ...
16/10/2024

በሰው ህይወት ላይ አስከፊ ጉዳት ማድረስ የሚችለውን የወባ በሽታ ወረርሽን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለአጠቃላይ ህብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ድርሻ አለው ተብሏል፣

በቅሎ ሰኞ፣ ጥቅምት 06/2017 ዓ ም በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ የወባ ወረርሽን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተግባራት ለማከናወን ወረዳዊ የኦሬኝተሽን መድረክ ተካሄደ።

እየጨመረ የመጣውና በሰው ህይወት ላይ አስከፊ ጉዳት ማድረስ የሚችለውን የወባ ወረርሽን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አጠቃላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ድርሻውን መወጣት ያስፈልጋል በማለት የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተወካይና የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳንሳ ተናገሩ።

የሚንሰራው ማንኛውም ተግባር ከህዝብ ጤና ተከትሎ የሚመጣ በመሆኑ ህብረተሰቡ በጤና ስራ ዙሪያ ያለውን የግንዛቤ ክፍተት ለማረም የወረዳ አመራሮች ከጤና ባለሙያዎች ጋር ጠንካራ ስራ ማከናወን ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዳንኤል ወረርሽኙን ለመግታት ከራሳችን የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት አለብን ብሏል።

የወባ ወረርሽን እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በሁሉም ጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች ላይ ለህዝብ የሚሰጠው አገልግሎት ከመቸውም ጊዜ በላይ ቀልጣፋ መሆን ያስፈልጋል በማለት የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር መደረግ አስፈላጊ መሆኑን አስቀምጧል።

የወባ ወረርሽን ለመከላከል የወረዳ አመራር ከጤና ባለሙያዎችና ከህዝብ ጋር ታች ላይ በሽታውን መከላከል በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ የወረዳ ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ አለማየሁ ኃ/ሚካኤል ተናገሩ።

የጤና ባለሙያዎች ለህዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ በማድረግና የበሽታ ስርጭትን ለመግታት በቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ላይ በልዩ ትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብሏል።

ቤት ለቤት የሚደረገው አሰሳና ክትትል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመግለፅ የወባ አስተላላፊ ቢንቢ እንዳይወለድ ውሃ ማፋሰስና የአልጋ አጎበር አጠቃቀም ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አንስቷል።

የወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ባንጫ በበኩላቸው ህብረተሰቡ ከመቸውም ጊዜ በላይ የራሱንና የአከባቢውን ንፅህና በሚገባ በመጠበቅ አስከፊውን የወባ በሽታ ለመከላከል ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል ብሏል።

በወረዳችን እየጨመረ የመጣውን ይህንን በሽታ ስርጭት ለመግታት ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ትምህርት ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል በማለት በተለይ የአልጋ አጎበር አጠቃቀምና በሌሎች ቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ላይ መዘናጋት አያስፈልግም ብሏል።

በሁሉም አከባቢ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ፈጣን ህክምና አገልግሎት መስጠት በሁሉም ቀበሌ ያሉ ጤና ኬላዎች ዝግጁ ሆኖ የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት አለባቸው ያሉት አቶ አበራ ከዚህ በተቃራኒው ለአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በመሆን ምክንያታዊ የሚሆኑ አካላትና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ብሏል።

በመድረኩ አጠቃላይ የወረዳ አመራሮች፣ የወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ባለሙያዎች፣ የጤና ጣቢያዎች ተወካዮችና ሌሎች አካላት የተሳተፉ ስሆን ቀጣን ተግባራት ዙሪያ ስምሪት ተሰጥቷል።

የወባ በሽታን መከላከልና ቁጥጥር በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል የወባ በሽታን ጫና ለመቀነስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ ...
13/10/2024

የወባ በሽታን መከላከልና ቁጥጥር በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል

የወባ በሽታን ጫና ለመቀነስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል

በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የወባ በሽታ ጫናን ለመቀነስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከዞን አመራሮች እና ከከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያምን ጨምሮ የክልል አመራሮች የዞን አስተዳዳሪዎችና የመንግስት ተጠሪዎች እንዲሁም ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

በመድረኩ ባለፉት 3 ወራት በክልሉ የወባ በሽታ ጫናን ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።

10/10/2024


*****************************************************
#መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ 40 ሚሊዮን የሚጠጉ የዓለም ሕዝቦች ከኤች አይቪ ኤድስ ጋር ይኖራሉ። ከእነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ከሰሐራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ላይ ደግሞ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል። ከነዚህ መካከል ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ህፃናት ከኤች አይ ቪ ኤድስ ጋር እንደሚኖሩና
በቫይረሱ ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ከሚሞትባቸው አህጉራት ውስጥም አፍሪካ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል፡፡

#ኤች አይ ቪ ኤድስ ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት፣ የደም ንክኪ፣ ስለታማ ነገሮችን በመጋራት እንዲሁም በእርግዝና ወቅት ከእናት ወደ ልጅ እንደሚተላለፍ ይታወቃል። በርካቶችም ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ ነው የሚባል ባይሆንም፤ አሁንም ግንዛቤው የሌላቸው ሰዎች እንዳሉና በይቫረሱ የሚያዙ ሰዎች ብዙ እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ለቫይረሱ መጋለጣቸውንም ቸል በማለት በወቅቱ ተመርምረው መድሃኒት ባለመጀመራቸው ለሞት ሊዳርጉ እንደሚችሉ ሐኪሞች ያስገነዝባሉ፡፡

#የበሽታው ስርጭት በአካባቢ (በጂኦግራፊ) ሲከፋፈል ግን አዲስ አበባ ከጋምቤላ ቀጥሎ እንደ ሀገር በሁለተኛ ደረጃ የምትገኝ ናት፡፡ ይህም በከተማ ከፍተኛ ስርጭት መኖሩን ይጠቁማል፡፡ በዚያው ልክ በሽታው በሴቶች፣ ህፃናት፣ አዛውንቶች፣ ወጣቶችና ላይ የስርጭት ደረጃው ይለያያል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ያለው ሁኔታም የበለጠ መትጋት እና በሽታውን መከላከል ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ የሚሳይ ነው፡፡

#የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ችግሩ ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊም ጭምር ነው፡፡ ይህም እንደ ሀገር ጉዳቱ ከፍተኛ ሲሆን ዘርፈ ብዙ ችግሮችንም ያስከትላል፡፡ በተለይም ደግሞ አምራቹን የማህረሰብ ክፍል ወይንም ወጣቶች በበሽታው በሰፊው የመጠቃት ዕድል ያላቸው በመሆኑ በአንድ ሀገር የምጣኔ ሀብት ዕድገት ወይንም ምርታማነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡ ይህ በመሆኑም በሽታውን ለመከላከል ብሎም ለመቆጣጠር አስቻይ ምህዳር መፍጠር ይገባል፡፡

#በሽታውን ለመከላከል ከሁሉም በቀደመ መልኩ የባህሪ ለውጥ ላይ መሥራት ተገቢ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ በተደጋጋሚ መረጃዎችን በማሰራጨት እና በማንኛውም የተግባቦት ስልት በመጠቀም ግንዛቤ በመፍጠር ላይ ለውጥ መምጣት አለበት። ይህን ለማድረግ ደግሞ ከማንኛው በላይ መገናኛ ብዙሃን በኃላፊነት ሊሠሩ ይገባል ፡፡ በአጠቃላይ ግን በሽታውን ለመከላከል እና ስርጭት ለመግታት ስልታዊ መዋቅር ስትራቴጂካል ስትራክቸር መፈጠር ያስፈልጋል፡፡

#በየሥራ ባህሪ ለበሽታው የመጋለጥ ሁኔታዎች እንደሚለያዩ ይታመናል ፤ ፆታዊ ጥቃቶች በብዛት ለበሽታው መስፋፋት ቀዳሚውን ሚና እንደሚወስዱ ይጠቆማል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በሴተኛ አዳሪነት የሚተዳደሩት ሴቶች ለበሽታው በመጋለጥ ቀዳሚውን ድርሻ የሚይዙ ሲሆን 19 በመቶ የሚሆኑት ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንደሚገኝ ይገመታል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ለበሽታው የሚጋለጡት ደግሞ በሽታው ወደ ሌሎች የመተላለፍ ዕድሉንም ያሰፋዋል፡፡

#የረዥም ወይንም ሀገር አቋራጭ አሽከርካሪዎች 4 ነጥብ 6 በመቶ በቫይረሱ ተጠቂ ናቸው፡፡ የትዳር አጋራቸው የሞቱባቸው 11 በመቶ ብሎም ፍቺ የፈፀሙ ደግሞ እስከ 2 ነጥብ 9 ስርጭቱ በመቶ የሚገኝባቸው ወይንም የመያዝ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ከዚህም በዘለለ ሜጋ ፕሮጀክት አካባቢ የሚሠሩ ዜጎች ለበሽታው የመጋለጥ ዕድል 1 ነጥብ 3 በመቶ ነው፡፡ ጥንቃቄ

Address

S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bayra koysha woreda Health office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share