Shone town administration manicipality office

Shone town administration manicipality office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Shone town administration manicipality office, Government Organization, Sodo.

29/04/2020

✴ በህይወት ሰልፍ ውስጥ ሳለህ ልብ ልትላቸው የሚገቡ እነኚህን ነጥቦች በአጽንኦት አንብባቸው።

🌀ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!" ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፤ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፤
ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም።

🌀የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም! ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፤ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል፤ ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና።

🌀መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል! ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘አውሮፕላን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ፣ ደግሞስ እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ? እርሱን ተወውና በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው።
🌀ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን!"
►በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ!
►ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣
►በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣
►ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣
►ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣ ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም።
ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል።

✅በጊዜ ስራ እንጂ ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!" ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም። አንተንም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፤
በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን።

✅መክሊትህን ፈልግ!"
ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁና። አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለም እየኖረች ያለችው። በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት። አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ ፈልገውና አውጣው። ቁፋሮ ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ ነው? ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው? ድንጋይ ቅርፅ (ኮብልስቶን) እየሰሩ መኖር ነው? ምንድነው? እባክህ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው፣ "ምን ይሻለኛል?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ። በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው።

✅መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን እንዳልሆነ አስተውል!" ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀየር ብቃት አለው። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል። መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው፤ መጥፎነት ከአንተ ይራቅ፤ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም።

✅ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን አባባል አስታውስ፤
የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል፤ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ፤ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል። ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ፤ ራስህን አትሸውድ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ፤ ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።

✅ለራስህ ስትል መልካም ሁን፣ በጎውንም አስብ!" ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም።
🌀በማንም ላይ አትፍረድ!"

ፍርድ የፈጣሪ ነው። ፍጥረት ሁሉ እንከን አለበት። የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል።
*ለውጥ ከራስ ይጀመራል! እናም አሁኑኑ መለወጥ ጀምር።
መልካም ግዜ ይሁንልን ሼር
ምርጥ መጣጥፎች

27/04/2020



የኮሮና ቫይረስ ዓለማቀፍ ወረርሽኝ መንሰራፋትን ተከትሎ በርካታ የዓለም አገራት፤ ተቋማትና ግለሰቦች ኢትዮጵያ ላይ የተለየ ትኩረት ሲያደርጉ እያየን ነው፡፡ የዓለም ባንክ ከብዙዎቹ አፍሪካ አገራት ቀድሞ ለወረርሽኙ መከላከያ የሚውል ድጋፍ የቸረው ለኢትዮጵያ ነው፡፡ አፍሪካውያንን ወክለው ለዓለም ሃብታም አገራት የድጋፍ በጀት ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተደረገው ጠ/ሚ አብይ አህመድ /ዶ/ር/ ናቸው፡፡ ቻይናዊው ቱጃር ጃክ ማ ወረርሽኙን ለመከላከል ይችሉ ዘንድ አፍሪካውያንን ለመደገፍ ሲነሳ የድጋፉ ማዕከል አድርጎ የመረጠው ኢትዮጵያን ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅትም የአፍሪካ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር እንቅስቃሴው መቀመጫ ኢትዮጵያ እንድትሆን መርጧታል፡፡

በቅርቡ እንግሊዝ የድጋፍ ትጥቋን ወደ ኢትዮጵያ ጭና ልካለች፡፡ ቻይናም የድጋፍ ቁሳቁስና ገንዘቧን ብቻ ሳይሆን ሙያተኞቿንም ወደዚሁ ሰዳለች፡፡ ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕ/ት ትራምፕ ሰሞኑን ከጠ/ሚ አብይ አህመድ /ዶ/ር/ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ‹‹ኢትዮጵያ የቬንትሌተር እጥረት ስላለባት በዚህ ረገድ ድጋፍ እንደምናደርግላት ተማክረናል›› ማለታቸውን መስማታችን ነው፡፡ ይህንን ዜና አስገራሚ ያደረገው ትርምፕ ባገራቸው ወረርሽኙ ሲስፋፋ ለደቡብ ኮሪያ የቬንትሌተር ድጋፍ ጥያቄ ያቀረቡ መሆናቸው ነው፡፡

እንዲህ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በተከታታይ እያስተዋልን ነው፡፡ ሁሉም ለጋሾች በዚህ አደገኛ ጊዜ የራሳቸው ችግር እያለባቸው ኢትዮጵያን ማሰባቸውና ሊረዱ መነሳታቸው ያስመሰግናል፡፡ ነገር ግን እንዲህ ያለው የድጋፍ ርብርብ የተለመደ አይደለምና ጥያቄም ያጭራል፡፡ መቼም በዚህች ውድድሩና ፉክክሩ እንደ ሲባጎ በከረረባትና በሰጥቶ መቀበል የተመሰረተ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት በገነነባት ዓለም፤ ድጋፍ አድራጊው ሁሉ እኛ ላይ መረባረቡ ለፅድቅ ነው ብሎ ማሰብ ይቸግራል፡፡ ከዚህች አገር የተፈለገ አንድ የተለየ ጉዳይ ሳይኖር እንዳልቀረ አይታያችሁም? ያ ፍላጎታቸው ምን ይሆን?

በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ፤ ጤናችሁ ይለምልም ።
Kassa_Ayalew_Kassa

Address

S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shone town administration manicipality office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share