የካዎ ኮይሻ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት/kawo koisha woreda prosperity party office

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • የካዎ ኮይሻ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት/kawo koisha woreda prosperity party office

የካዎ ኮይሻ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት/kawo koisha woreda prosperity party office Wolaita ethiopia

"በዞኑ በሁሉም ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የታቀደውን ዕቅድ፥ በጊዜና በጥራት እንዲከናወን የአመራሩ ቁርጠኝነት ይጠይቃል "ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ላሾ ቄራ፣ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም የወላ...
25/10/2025

"በዞኑ በሁሉም ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የታቀደውን ዕቅድ፥ በጊዜና በጥራት እንዲከናወን የአመራሩ ቁርጠኝነት ይጠይቃል "ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ

ላሾ ቄራ፣ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም የወላይታ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የዞን ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ገምግሟል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪና የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በግምገማው ማጠቃለያ እንደገለጹት በሁሉም ሴክተር የታቀደውን ዕቅድ፥ በጊዜና በጥራት እንዲከናወን የአመራሩ ቁርጠኝነት ይጠይቃል ብለዋል።

በአስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች የሚከናወኑና የተከናወኑ አስተዳደራዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት እንቅስቃሴዎችን በትኩረት የማስፈፀም አቅም ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል ።

በሩብ ዓመት አፈጻጸም የታዩ ጉድለቶችን በመለየት በቀጣዩ ዕቅድ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉና እንዲያስፈጽሙ አቅጣጫ ተቀምጧል ።

የዞኑን ህዝብ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ የልማት ፖሊሲዎች መሰረት እቅዶች፤ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች ተዘጋጅተው በአገባቡ እንዲተገበሩ የቅርብ ክትትል እንድደረግ አጽንኦት ተሰጥተዋል ።

በየዘርፉ አፈጻጸማቸውን በመገምገም በዞኑ የሚኖሩ ሁሉም ህብረተሰብ የልማቱ እኩል ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የበኩሉን አስተዋኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የጠቆመው ፡፡

በአስተዳደራዊ፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ የተሠሩና እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ከውትሮ በላቀ ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው አስፈጻሚ አካላት እንዲመሩና እንዲያስፈጽሙ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

በትምህርት ፣ በጤና፣ በገቢ፣ በግብርና በፋይናንስ በሴቶችና ሕጻናት፣ በፍትህ ተቋማት እንዲሁም በሌሎች ሴክተር በ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ጠንካራ ጎኖችን በማቀጠል ክፍተት ያለባቸውን አፈጻጸም የመለየት ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥተዋል ።

የዞኑ ፕላንና ልማት መምሪያ የተዘጋጀ የዞን ሴክተር መ/ቤቶች የ2018 በጀት ኣመት የ1ኛ ሩብ ኣመት አፈጻጸም ሪፖርት በማጠቃለል ለዞኑ አስፈጻሚ አካላት አቅርበዋል ።

በመድረኩ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፣ ም/አስተዳዳሪ አቶ ተስፋሁን ታዲዮስ፣ የዞኑ ካቢኔን ጨምሮ የዞን አመራሮች ተሳትፈዋል።

ተልዕኮዎችን መሸከም የሚችል ጠንካራ አደረጃጀት ለመፍጠር የጋራ ርብርብ ማድረግ ይገባል- ወ/ሮ እቴነሽ በየነላሾ ቄራ፣ ጥቅምት 15/02/2018 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴ...
25/10/2025

ተልዕኮዎችን መሸከም የሚችል ጠንካራ አደረጃጀት ለመፍጠር የጋራ ርብርብ ማድረግ ይገባል- ወ/ሮ እቴነሽ በየነ

ላሾ ቄራ፣ ጥቅምት 15/02/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የ 2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

ክንፉ በ 2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት በዝርዝር የገመገመ ሲሆን በጥንካሬ የተለዩትን ለማስቀጠልና ድክመት የታየባቸውን የቀጣይ ዕቅድ አካል በማድረግ እንደሚሰራ ተገልጿል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እቴነሽ በየነ የበጀት ዓመቱን በየደረጃው በሚገኙ የክንፉ መዋቅሮች ተገቢውን ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ መገባቱን ገልፀዋል።

ተልዕኮዎችን መሸከም የሚችል ጠንካራ አደረጃጀት ለመፍጠር የጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ኃላፊዋ ጠቅሰው አባላቱም በሚያከናዉኗቸዉ ተግባራት ግንባር ቀደም መሆን እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

በሩብ ዓመቱ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራን በቅንጅት መምራት መቻሉ በጥንካሬ የሚጠቀስ ተግባር መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ ስራ የህዝብ ለሕዝብ ትስስርን በሚያጠናክር እና እህትማማችነትን በሚያጎለብት መንገድ በማከናወን የበርካታ አቅመ ደካማ እናቶችን እንባ ያበሰ ስራ መሠራቱም ተመልክቷል።

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ጨምሮ በፓርቲ መሪነት የተከናወኑ የንቅናቄ ስራዎች ጅምር ዉጤት የተገኘባቸው እንደነበሩ የተገለፀ ሲሆን ከመዋቅር መዋቅር የሚስተዋለው የአፈፃፀም ወጥነት ችግር ሊታረም እንደሚገባ አፅንኦት ተሰጥቶታል።

በቀጣይም በሶስተኛው ዙር የ 90 ቀናት ዕቅድ ጠንካራ አፈፃፀም ለማስመዝገብ መረባረብ፣ የፋይዳ ንቅናቄ እና ኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን ማጠናከር፣ የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም የሚያጎለብቱ ተግባራት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ከስምምነት በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል።

በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ሴቶች ክንፍ እንዲሁም የ 12ቱም ዞኖችና 3ቱ ሪጂዮ ፖሊሲ ከተሞች ሴቶች ክንፍ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች በተጠናከረ መንገድ ሊቀጥል ይገባል- አቶ ገ/መስቀል ጫላላሾ ቄራ፣ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ...
25/10/2025

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች በተጠናከረ መንገድ ሊቀጥል ይገባል- አቶ ገ/መስቀል ጫላ

ላሾ ቄራ፣ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባና በሶስተኛው ዙር የ 90 ቀናት ዕቅድ አተገባበር ላይ ትኩረት ያደረገ ዉይይት አካሂደዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ማንኛውም ዜጋ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) መያዝ እንደሚጠበቅበት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በክልሉ ዛሬ ቅዳሜና ነገ ዕሁድ ልዩ ንቅናቄ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ጫላ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባና የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በተጀመረው አግባብ ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዲጂታል ኢትዮጵያን በመገንባት ረገድ የፋይዳ መታወቂያ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የገለፁት ኃላፊው በተያዘው ቅዳሜና ዕሁድ በሚካሄደው ንቅናቄ ሕብረተሰቡ በነቂስ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ምዝገባው በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ እንደሚገኝ ኃላፊዉ ገልፀዉ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናም በተጀመረው አግባብ ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተመሳሳይ መልኩ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የመሸጋገር ሀገር አቀፍ ንቅናቄ፣ ኑሮ ዉድነትን በማቃለል ረገድ የሰንበት ገበያዎችን ማጠናከርና የኮንትሮባንድ ንግድን መከላከል በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

በከተማና ገጠር የተጀመረውን የኮሪደር ልማት፣ የገቢ ስራዎች፣ በክረምቱ በስኬት የተከናወነውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በበጋውም አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲሁም የሌማት ትሩፋት ስራዎች ግለታቸዉን ጠብቀዉ እንዲሄደ ማድረግ እንደሚገባ ተመላክቷል።

የክልሉ አስፈፃሚ አካላትን መልሶ የማደራጀት ስራዎችን የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ባስቀመጠው አቅጣጫና ህግና መመሪያዎችን በተከተለ መንገድ እስከ ታችኛው መዋቅር ተፈፃሚ ማድረግ ይገባል ተበሰሏል።

በዉይይቱ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የታቀዱ ተግባራትን አመራሩ ለመፈጸምና ለማስፈጸም መትጋት ይገባል፦ ዶ/ር አማረ አቦታላሾ ቄራ፤ጥቅምት 15/2018 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2...
25/10/2025

የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የታቀዱ ተግባራትን አመራሩ ለመፈጸምና ለማስፈጸም መትጋት ይገባል፦ ዶ/ር አማረ አቦታ

ላሾ ቄራ፤ጥቅምት 15/2018 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

ቀጣይ አቅጣጫን ያስቀመጡት የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማረ አቦታ ለተግባር ውጤታማነት አደረጃጀቶችን በማጠናከር አባላትን በተገቢው ሁኔታ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

አያይዘውም የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶችም መጠቀም እንደሚገባም ያመለከቱት ኃላፊው፥ የተጀመሩ ስራዎች ለማጎልበት ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የፓርቲ አባላት መረጃን የማጣራት ስራ መሰራት እንዳለበት ያሳሰቡት ኃላፊው፥ ጠንካራ አባልን ማፍራት ለጠንካራ ፓርቲ እጅግ ወሳኝ እንደሆነም አስገንዝበዋል።

የፓርቲውን ሀብት ለማሰባሰብ የታቀደውን ግብ ለማሳለጥ፤ ያለውን አባልና ደጋፊውን እንዲሁም ሰፊውን የህዝብን አቅም መጠቀም እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

የደረሱ ሰብሎችን ለማንሳት ቴክኖሎጂ መጠቀምና ህዝቡን የማስተባበር ስራ መሰራት ይገባል ያሉት ኃላፊው፥ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተጀመሩ ስራዎችም መጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል።

የሌማት ትሩፋት በየመንደሩ ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመረው ልዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበት ያሳሰቡት ኃላፊው፥ የቡና ግብይት ሂደት በቅንጅት መምራት ይገባልም ብለዋል።

ሁሉም ህብረተሰብ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ባለቤት እንዲሆኑ፤ እንዲመዘገቡ የማድረግ ስራ በንቅናቄ መምራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

ማህበራዊ ሚዲያውን መግራትና በአግባቡ ማስተዳደር ያስፈልጋል ያሉት ኃላፊው፥ ሀሰተኛና የተዛቡ መረጃዎችን ማረምና መታገል ያስፈልጋልም ብለዋል።

የወላይታ ዞን ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፍን ቶማስ የፖለቲካ ጤናማነት ለተግባር ስኬታማነት ወሳኝ በመሆኑ ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

የህዝቡ መሠረታዊ ጥያቄዎችን በመለየት ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ታቅዶ መሰራት አለበት ያሉት አቶ መስፍን፥ በተለይም ለወጣቱ የስራ ዕድልን ለመፍጠር ቀዳሚ አጀንዳ ተደርጎ መምራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ሚዲያ በአግባቡ በመጠቀም ፓርቲያችን አንግቦ የተነሳውን ራዕይን ለማስረጽ እና ገዢ ትርክትን ለመገንባት ያስፈልጋል ያሉት አቶ መስፍን፥ ጥላቻን በጥላቻን ሳይሆን በበጎ ሀሳብና በሀሳብ የበላይነት ማሸነፍ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የወላይታ ዞን የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል በበኩላቸው አመራሩ ሁሉንም ተግባራትን አቀናጅቶ ውጤት በሚያመጣ መልኩ መፈጸም ያስፈልጋል ብለዋል።

ለተቋም ግንባታ ልዩ ትኩረት በመስጠት መምራት እንዳለበት ያሳሰቡት ወ/ሮ ሰላማዊት፥ የብልፅግና ህብረትና ቤተሰብ ለማጠናከር የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ተናግረዋል።

ያለውን አባልን በየማህበራዊ መሠረት የማጥራትና አዲሱን የማፍራት ስራ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ መሆን እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

"ኢኮኖሚ ለሀገር እድገት ወሳኝ እንደሆነ ሁሉ ለዘላቂ ሰላምም የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል"  ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ   ላሾ ቄራ፤ ጥቅምት 15/2018በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዲላ ከተማ በተካ...
25/10/2025

"ኢኮኖሚ ለሀገር እድገት ወሳኝ እንደሆነ ሁሉ ለዘላቂ ሰላምም የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል" ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ

ላሾ ቄራ፤ ጥቅምት 15/2018

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዲላ ከተማ በተካሄደው ሶስተኛው ምዕራፍ የመጀመርያ ዙር የስለኢትዮጵያ መድረክ ላይ የመወያያ ሀሳብ ያቀረቡ ፓናሊስቶች እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በርካታ ጸጋዎች ያላት ሀገር በመሆኗ ይህንን በአግባቡ ለመጠቀም ሰላማችንን ማጽናት ይገባል።

በመድረኩ "ሰላም እና ልማት ያላቸው ትስስር" በሚል የውይይት መነሻ ፅሑፍ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) አቅርበዋል

እሳቸው እንዳሉት፤ ሰላም ተንቀሳቅሶ ለመስራት፣ ለመነገድና ምርት ለማምረት ወሳኝ ናቸው። ሰላምና ልማት እርስ በእርስ የተሳሰሩና የማይነጣጠሉም ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

ኢኮኖሚ ለሀገር እድገት ወሳኝ እንደሆነ ሁሉ ለዘላቂ ሰላምም የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል። ለአብነት ዝቅተኛ ኢኮኖሚ ባለበት ሥፍራ ግጭት፣ ድህነትና የሰላም እጦት ይበራከታል። በአንፃሩ ደግሞ ጠንካራ ኢኮኖሚ አንድነት እና መተባበርን ያጠናክራል ብለዋል።

እድገት ጠንካራ ኢኮኖሚ ልማትን የሚፈልግ መሆኑን አንስተው ልማት በልፋት፣ በድካምና በሥራ ይገኛል ብለዋል። ሰላምም እንደዚሁ ድካምና ሥራ እንደሚፈልግ ጠቁመው፤ ይህ ደግሞ ዴሞክራሲን ያሰፍናል ነው ያሉት።

ሰላም ካለ ማምረት ይቻላል፣ተንቀሳቅሶ መስራት ይቻላል። በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ትስስሩ ይጠናከራል ሲሉም ጠቁመዋል።

የክልሉ መንግስት ከየትኛውም ጉዳይ በላይ ለሰላም ልዩ ትኩረት በመስጠት ክልሉን የሰላም የመቻቻል እና የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረ እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

“ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶቻችን እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና ለሰላም ያላቸው ሚና“ በሚል ርዕሰጉዳይ የመወያያ ሀሳብ ያቀረቡት ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል መኮንን እንደገለጹት፤ ከችግሮቻችን ለመውጣት ሁለት መሰረታዊ በሮች አሉ። እነሱም ነባር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶቻችንና ማህበራዊ እሴቶቻችን ናቸው።

ወደ ውስጥ መመልከት ከቻልን መፍትሄው በእጃችን ነው ያለው ያሉት አቶ ዳንኤል፣ ይህም የህዝብ ለህዝብ ትስስሮችን ተቋማዊ ማድረግ ነው ብለዋል።

የመደመር እሳቤ ህዝብ ለህዝብ እንተሳሰር የሚል መሆኑን ጠቅሰው፤ የአገርን ሰላም ለማጽናት የባህላዊ እሴቶቻችን ወሳኝ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና ማህበረ እሴቶቻችንን ለሰላም ግንባታ ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

ሌላው እኛና እነሱ የሚሉ ትርክቶች አደገኞች መሆናቸውን ጠቁመው፣ የጋራ ቁስሎች፣ የጋራ ህመሞች አሉብን።

በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሁኔታዎች ክትትል ዳይሬክተር ጀነራል ዘሩባቤል ጌታቸው (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት ነባሩ የአንድ ዋልታ መር የአለም ሥርዓት ቀርቶ ባለብዙ ዋልታ መር ሥርዓት እየተገነባ ነው።

ባለብዙ ዋልታ መር ሥርዓት ፉክክርና ውጥረት ያለበት ነው ያሉት ዶክተር ዘሩባቤል፤ ቀጣናችን ስትራቴጂካዊ ከሚባሉ ቀጣናዎች አንዱ እንደመሆኑ ሶስቱ የአፍሪካ፣ የአውሮፓና የእስያ አህጉራትን የሚያስተሳስር ነው ብለዋል።

“የአፍሪካ ቀንድ የህዝብ ቁጥር እድገት ያለበት ነው። የማህበራዊ አገልግሎት ማዳረስ ፈተና ሆኗል። ቀጣናችንን ቆመን የምናይበት ሰዓት አይደለም። አገራችንም የቀጣናው መልህቅ ነች” ብለዋል።

ዶክተር ዘሩባቤል እንደተናገሩት፣ በቀጣናው የሚከሰት አለመረጋጋት ኢትዮጵያን ችግር ውስጥ ይከታል። የቀጣናው ሰላም ለኢትዮጵያ አስፈላጊ ነው።

የቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር ሲታሰብ ኢትዮጵያ ያላማከለ መሆን አይችልም። ኢትዮጵያን ከባህር አርቆ ማቆየት የማይቀጥልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ጥያቄ ፍትህና

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል ላሾ ቄራ፤ጥቅምት 15/2018 የወላይታ ዞን ብ...
25/10/2025

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል

ላሾ ቄራ፤ጥቅምት 15/2018 የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ግምገማና ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች የውይይት መድረክ አካሂዷል።

የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ታደለ ሜጋ የወጣቱን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

አያይዘውም በዞኑ ባለፉት ወራት በወጣቶች ክንፍ መሪነት ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወኑን ጠቅሰው ቀጣይ ጉድለት ያሉባቸው ጉዳዮችን ለይተን ለመሰራት ቁርጠኛ መሆን አለብን ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ የወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በወላይታ ዞን ገበያን ለማረጋጋት የተጀመረውን 'የሰንበት ገበያ' ተጠናክሮ ቀጥሏል ላሾ ቄራ፥ጥቅምት 15/2018 በወላይታ ዞን ገበያን ለማረጋጋት የተጀመረውን 'የሰንበት ገበያ' በሁሉም አከባ...
25/10/2025

በወላይታ ዞን ገበያን ለማረጋጋት የተጀመረውን 'የሰንበት ገበያ' ተጠናክሮ ቀጥሏል

ላሾ ቄራ፥ጥቅምት 15/2018 በወላይታ ዞን ገበያን ለማረጋጋት የተጀመረውን 'የሰንበት ገበያ' በሁሉም አከባቢዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ገበያው በዋናነት በዝቅተኛ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን ሳያባክኑ ያለምንም የደላላ ቀጥታ ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምቱና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው፡፡

የቅዳሜና እሁድ ገበያው በየጊዜው እየታየ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠርና በምርት አቅርቦትና ስርጭት የሚፈጠረውን ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረት ለመቀነስ ያስችላል።

የሰንበት ገበያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ኑሮ ውድነትና ገበያ ለማረጋጋት ሁነኛ መፍትሔ እንዳለው ታውቆ ገበያውን ለማጠናከር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

የቅዳሜና እሁድ ገበያው በዝቅተኛ ነሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ማህብረሰብ ትልቅ እፎይታን የሚሰጥ በመሆኑ ሸማቹና አምራቹን የማገናኘት ስራም እየሰራ ይገኛል።

ለዚህም የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በአይነትና በጥራት ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ መሆኑን ታውቋል።

ለሸማቹ ማህበረሰብ የዋጋ ዝርዝር ግልፅ በሆነ በቦታ ላይ ተለጥፎ በመስራቱ ህብረተሰብ ሳይቸገር ምርቱን እየገዛ ይገኛል።

የምርት አቅርቦት እና ስርጭት ላይ ጣልቃ የሚገቡ ህገወጥ ደላሎችን መከላከል እንደሚገባም ተመላክቷል።

በካዎ ኮይሻ ወረዳ የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በተጠናከረ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው ላሾ ቄራ፥ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ የሚገኙ ሁሉም የህብረተሰብ ...
25/10/2025

በካዎ ኮይሻ ወረዳ የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በተጠናከረ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው

ላሾ ቄራ፥ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ የሚገኙ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እየተመዘገበ ይገኛል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ 🆔 በብሔራዊ ደረጃ የሚያገለግል ህጋዊ እና መሠረታዊ የመታወቂያ ዓይነት ሲሆን፣ የአይን፣ የፊት እና የጣት አሻራን ከግል መረጃ ጋር በማቀናጀት በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ማናቸውም ነዋሪዎች ያለመከልከል የሚያገኙት መለያ ነው።

ዕድሜው ከ5 ዓመት ጀምሮ ያለ ማንኛውም ሰው አሻራ በመስጠት፣ ከዛ በታች ለሆኑ ህፃናት በወላጅ ምስክር ብቻ ያለ ባዮሜትሪክስ መመዝገብ ይቻላል።

ይህም ለልደት እና ተያያዥ ሲቪል ምዝገባ ሲስተሞች ፋይዳ እንደ ልዩ ቁጥር ሆኖ እንዲያገለግል ይረዳል።

የካዎ ኮይሻ ወረዳ ሳምንታዊና ወቅታዊ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።ላሾ ቄራ፥ ጥቅምት 15/2018 ዓ/ም በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ሳምንታዊና ወ...
25/10/2025

የካዎ ኮይሻ ወረዳ ሳምንታዊና ወቅታዊ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።

ላሾ ቄራ፥ ጥቅምት 15/2018 ዓ/ም በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ሳምንታዊና ወቅታዊ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል።

መድረኩ የመሩት የካዎ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አበባየሁ ዮሐንስ እንደተናገሩት አመራሩ የተሰጠውን ተልዕኮ ተቀብሎ ወቅቱን የጠበቀ ሥራ በመሥራት ውጤት ለማስመዝገብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ተግባራት ለቅሞ መሰራታቸዉን በመለየት ከፍተኛ ዉጤት ለማስመዝገብ ትኩረት መሰጠት እንደሚገባ ገልጸዋል።

አቶ አበባየሁ አክለውም እያንዳንዱ አመራር ሁሉንም ተግባራት በቀኝ እጅ በመያዝ እና ትኩረት በመስጠት በተመደበበት ቀበሌ ወርዶ ችግር ፈች ድጋፍ በማድረግ የተጣለበትን አደራ በሚገባ መወጣት እንዳለበት አመላክቷል።

ሁሉም አመራርና ባለሙያ በስራ ገበታው በመገኘት ሥራውን እንዲሰራ በየተቋሙ፣ በየቀበሌው ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ ሂደትን በየሥራ መስኩ በማጠናከር የግብርና ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ ጨምሮ ሌሎችም ወደ ሥራ ገበታው ህዝብን በታማኝነት በማገልገል ተግባሩን ሊመራ ይገባል ብለዋል።

አመራር በልዩ ትኩረት መከታተል ያለበት ተግባራት የልማት ትሩፋቶች፣ የእንስሳት ዝሪያ ዘመናዊ ማድረግ ሲንክሮናይዜሽን ፣ወልማ፣ ህንጻ ግንባታ፣ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ፓርቲ መዋጮ፣ እና ዲቻ መዋጮን እንዲሁም ሌሎች በንቅናቄ የሚመሩ ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ልሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የካዎ ኮይሻ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሳበቦ በበኩላቸው አመራሩ ከመንግስትና ከፓርቲ የሚወርደውን ተልዕኮ በቁርጠኝነት በመምራት በተመደቡበት ቀበሌ ወርደው በመደገፍ ወቅቱን የሚመጥን አካሄድ በመከተል ሊተገብረው እንደሚገባ ገልፀዋል።

አቶ ሀብታሙ አክለውም ሁሉም አመራር የተሰጠውን ተልዕኮ ቆጥሮ ሁሉንም በአንድ ዓይን አይቶ ተግባርን ቆንጥጦ በመምራት የአመራር ዲስፕሊን በሚጠይቀው ልክ በቁርጠኝነት መሰራት እንዳለበት በአፅንኦት አሳስበዋል።

ሳምንታዊ አፈጻጸም ግብረ መልስ እንዳየነው የአመራር ስምሪትና ድጋፍ ከውጤት አንጻር የተፈለገው ውጤት ባለመታየቱ፣ ክፍተት ያሳዩ እና በተግባር ላይ እንደ ድክመት የታዩ ጉዳዮችን ለቀጣይ እንዳይደገሙ ፈጥነን በማረምና በመሙላት አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ተናግሯል።

አጠቃላይ ተግባራት በጥንካሬ እና በጉድለት ተለይቶ በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮች ተጠናክሮ እንዲቀጥልና በጉድለት የተገመገሙ ተግባራት በአስቸኳይ እንዲስተካከል አፅንኦት ሰጥቷል።

ከፓርቲና መንግስት የሚወርደውን ተልዕኮ አመራሩ በብቃት በመምራት በተመደበበት ቀበሌ ወርደው በመደገፍ ሁሉንም ተግባራት በሚያሳካ አካሄድ በመከተል ሊተገብረው እንደሚገባ በአፅንኦት አሳስበዋል።

በዞኑ በፓርቲ መሪነት በሁሉም ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ ናቸው፦ ዶ/ር አማረ አቦታ ላሾ ቄራ፤ጥቅምት 15/2018 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1...
25/10/2025

በዞኑ በፓርቲ መሪነት በሁሉም ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ ናቸው፦ ዶ/ር አማረ አቦታ

ላሾ ቄራ፤ጥቅምት 15/2018 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማረ አቦታ ባለፉት በክረምት ወራት በፓርቲ መሪነት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ናቸው ብለዋል።

በፓርቲ መሪነት ተግባራትን ለማሳካት በተደረገው ጥረት የተሻለ ስራ መሰራቱን የገለጹት ኃላፊው፥ የፓርቲውን ዕሳቤዎችን ለማስረጽ የተሰራው የፖለቲካ ስራዎች እጅግ የተሻለ እንደሆነም ገልፀዋል።

የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ህዝባዊ እንዲሆንና በአደባባይ በድምቀት እንዲከበር የተሰራው የፖለቲካ ስራ ውጤታማ መሆኑንም አንስተዋል።

የግብርና ዘርፍ በተለይም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር የተጀመረው ስራ የተሻለ መሆኑን በመጠቀስ፥ ምርታማነትን ለማሳደግ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሻሻል እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

የጤና እና የትምህርት ስራዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መጠናከር እንዳለበትም ጠቅሰዋል።

ህብረተሰቡ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የኢትዮ ኮደርስ ባለቤትና ተጠቃሚ እንዲሆን የተጀመረው ስራ መጠናከር እንዳለበትም አሳስበዋል።

ከደመወዝ ጭማሬ ጋር ተያይዞ የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር እና የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የተሰራው የሰንበት ገበያ ውጤት እያመጣ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።

የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ብዙ ስራ ይጠይቃል ያሉት ኃላፊው፥ ለዚህም ህዝቡን በማሳተፍና በየአካባቢው ያለውን ሀብት በመጠቀም ለመመለስ አመራሩ መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል።

የፓርቲ አደረጃጀቶችን ይበልጥ ለማጠናከር በንቅናቄ መምራት እንዳለበት ያሳሰቡት ኃላፊው፥ የብልፅግና ህብረትና ቤተሰብ ውይይት ቤቶችን ለመገንባትና ለመጠገን ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞን እውን ለማድረግ የተጀማመሩ ስራዎች አጠናክረን ማስቀጠል ይጠብቅብናል ሲሉም አሳስበዋል።

ቀጣይ በጥንካሬ የተከናወኑ ተግባራትን በማጎልበት እና ጉድለቶችን ለማረም አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ፈጠራና ፍጥነትን መጨመር እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በአፈጻጸም ግምገማ መድረኩ የወላይታ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማረ አቦታን ጨምሮ የዞን ማዕከል ፓርቲ አመራሮች እና የወረዳና ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ናቸው።

የወላይታ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነውላሾ ቄራ፥ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም የወላይታ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የ2018 በ...
25/10/2025

የወላይታ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነው

ላሾ ቄራ፥ ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም የወላይታ ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የዞን ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አፈጻጸም እየገመገመ ይገኛል።

በመድረኩ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማን ጨምሮ የዞን አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በዞኑ ፕላንና ልማት መምሪያ በኩል በአስፈፃሚ መ/ቤቶች የሚከናወኑና የተከናወኑ አስተዳደራዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት እንቅስቃሴዎች በሰነድ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ነውላሾ ቄራ፤ጥቅምት 15/2018 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ...
25/10/2025

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ነው

ላሾ ቄራ፤ጥቅምት 15/2018 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ይገኛል።

ቅ/ጽ/ቤቱ የበጀት ዓመቱ ባለፉት ሶስት ወራት በፓርቲ መሪነት የተከናወኑ የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸምን በመገምገም ላይ ይገኛል።

ባለፉት ሶስት ወራት በጥንካሬ የተከናወኑትን በማጎልበትና በጉድለት የተለዩ ጉዳዮችን በመገምገም እና ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎም ይጠበቃል።

በአፈጻጸም ግምገማ መድረኩ የወላይታ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማረ አቦታን ጨምሮ የዞን ማዕከል ፓርቲ አመራሮች እና የወረዳና ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ናቸው።

Address

S**o

Telephone

+251960554469

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የካዎ ኮይሻ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት/kawo koisha woreda prosperity party office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share