ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu

ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu Private

በአርሲ እየተካሄደ ያለውን ፀረ ኦርቶዶክስ ዘመቻን በፅኑ እቃወማለሁ ።መንግስት የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ እና አጥፊዎችን የመቅጣት ሀላፊነቱን መወጣት ይገባል ❗️❗️
03/03/2026

በአርሲ እየተካሄደ ያለውን ፀረ ኦርቶዶክስ ዘመቻን በፅኑ እቃወማለሁ ።
መንግስት የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ እና አጥፊዎችን የመቅጣት ሀላፊነቱን መወጣት ይገባል ❗️❗️

ከዛሬ አመሻሽ ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውል የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ ተደረገአዳስ አበባ ታኅሣሥ 29/2017 (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ ታህሳስ 29/2017...
07/01/2025

ከዛሬ አመሻሽ ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውል የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ ተደረገ

አዳስ አበባ ታኅሣሥ 29/2017 (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ ታህሳስ 29/2017 ዓ.ም አመሻሽ ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውል የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል።

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የነዳጅ ምርቶችን ችርቻሮ ዋጋ መሸጫ ዋጋ ይፋ የሆነው በየወሩ እየተከለሰ በስራ ላይ እንዲውል በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ውሳኔ በተሰጠው ኃላፊነት ሠረረት ነው።

በዚህም ከዛሬ ታኅሣሥ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት አንድ ሊትር የነዳጅ ምርት ችርቻሮ ዋጋ በብር ሲገበያይ እንደነዳጁ አይነት በሚከተለው መልኩ እንዲሆን መወሰኑን ገልጿል።

አንድ ሊትር ቤንዚን በብር 101.47፣ ናፍጣ በብር 98.98፣ ኬሮሲን በብር 98.98፣ የአውሮፕላን ነዳጅ በብር 109.56፣ የከባድ ጥቁር ናፍጣ በብር 105.97 እንዲሁም የቀላል ጥቁር ናፍጣ በብር 108.30 እንዲሸጥ ተወስኗል።

የነዳጅ ማደያዎችም ህጉን አክብረው ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ ሚኒስት መስሪያ ቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ስትራቴጂ ተግባራዊ ሆነ፡፡=============አዲስ አበባ፡ መስከረም 28/2017 ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ...
08/10/2024

የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ስትራቴጂ ተግባራዊ ሆነ፡፡
=============
አዲስ አበባ፡ መስከረም 28/2017 ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ የችርቻሮ የመሸጫ ዋጋ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ የህዝቡን አቅምና የአገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ የዋጋ ማስተካከያ ስትራቴጂ አተገባበር ላይ የሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ አህመድ ቱሳ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አቶ አህመድ ቱሳ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በመንግስት ተነድፎ ተግባራዊ የሚደረገው የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ስትራቴጂ ሁለት መነሻ ምክንያቶች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡

አንደኛው የአለም የነዳጅ ዋጋ በተለያዩ ምክንያቶች ከፍና ዝቅ የሚልበት ሁኔታ መፈጠሩ ሲሆን ሁለተኛው ምክንያት በቅርቡ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በተለይም የውጭ ምንዛሬ ተመን ለውጥ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

እንደ አቶ አህመድ ቱሳ ገለፃ የአለም የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ መጥቶ በቅርቡ በባርሜል እስከ 72 የአሜሪካን ዶላር ደርሶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በመካከኛዉ ምስራቅ ሀገሮች ከተከሰተዉ አለመረጋጋት እና ተያያዥ ምክንያቶች መነሻ እስከ 80 ዶላር ከፍ ማለቱን ገልፀው ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ የነዳጅ ዋጋው ሊጨምር እንደሚችልም አንስተዋል፡፡

አቶ አህመድ አያይዘዉ እንደተናገሩት ዛሬ ላይ የአዲስ አበባ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ቤንዚን በሊትር 82.60 ብር ሲሆን ናፍጣ በሊትር 83.74 መሆኑን ገልፀው አሁን ባለው የውጭ ምንዛሬ ተመን መነሻ ነዳጅ ከውጭ ተገዝቶና ተጓጉዞ በኢትዮጵያ ገበያ ለመሸጥ ዋጋው እስከ 120 ብር በሊትር ሊደርስ እንደሚችል ገልፀዋል፡፡
አዲሱ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ስትራቴጂ በተጠቀሱት ምክንያቶች መነሻ ተጠቃሚው ህብረተሰብ ላይ የሚደርሰውን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ ጥቅል ድጎማ እንዲደረግበትና አብዛኛውን ሸክም በተለይም ነጭ ናፍጣና ኬሮሲን ላይ 80 በመቶ የሚሆነውን ጭማሪ ልዩነት መንግስት የሚደጉም ሲሆን ዝቅተኛውንና 20 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ በስትራቴጂው መሰረት ተጠቃሚው ህብረተሰብ እንዲከፍል የሚያደርግ ነው ብለዋል አቶ አህመድ፡፡

አቶ አህመድ አያይዛዉም በቤንዚንና በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ የ75 በመቶ በመንግስት ጥቅል ድጎማ የሚደረግ ሲሆን ዝቅተኛውንና 25 በመቶ የሚሆነውን ተጠቃሚው እንዲሸፍን የሚያደርግ ስትራቴጂ ነው ብለዋል፡፡

የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አገር አቋራጭ እና የከተማ አውቶቦሶች እስካሁን የሚጠቀሙት ደጎማ እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ስትራቴጂም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አቶ አህመድ ገልፀዋል፡፡

ይህ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ስትራቴጂ ዓለማቀፍ የገበያ ዋጋ ሁኔታ እና በነዳጅ አምራች ሀገሮች ያለዉ ያለመረጋጋት በዚሁ ከቀጠለ የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ግንባታ ስትራቴጂው ለአንድ ዓመት ሊቆይ እንደሚችልና ለድጎማው መንግስትን እስከ 300 ቢሊዮን ብር እንደሚያስወጣ ተነስቷል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ
Email: [email protected]
[email protected]
Facebook:-https://www.facebook.com Ethiopian-Ministry-of-Trade-and-Regional-Integration
For trade license: www.etrade.gov.et
Website: www.motri.gov.et
Telegram channel: https://t.me/motri_gov_et
https://t.me/etrade_gov_et
https://www.youtube.com/Ethiopian Ministry of Trade& Regional Integrat

መንታ እህቷን እና ወላጆቿን በናዳው ያጣችው ህጻንይህች ከታች የምትመለከቷት ህጻን በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በተከሰተው የመሬት ናዳ በሚከሰትበት ዕለት በጠዋት ጎረበት ካሉ ህጻናት ጋር ...
09/08/2024

መንታ እህቷን እና ወላጆቿን በናዳው ያጣችው ህጻን

ይህች ከታች የምትመለከቷት ህጻን በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በተከሰተው የመሬት ናዳ በሚከሰትበት ዕለት በጠዋት ጎረበት ካሉ ህጻናት ጋር እየተጫወተች እያለች ከባድ ዝናብ ይዘንብና እዛው በሚጫወቱበት ቤት ተጠልላ እያለች ነው ናዳው የተከሰተው።

የመሬት ናዳው ከቀኑ 5:00 የተከሰተ ሲሆን የህጻኗ መንታ እህትና ሁለቱንም ወላጆቿን በናዳው አጥታ ብቻዋን ቀርታለች።

እግዚአብሔር ለምድራችን ይራራልን!!

Via Amanuel

ዎላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ እስከ አሁን ከ11 ሰዎች ሕይወት በላይ አልፏል።አደጋው አሁንም ልቀጥል እንደሚችል ይገመታል።  ስለዚህ የሚመለከተው...
05/08/2024

ዎላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ እስከ አሁን ከ11 ሰዎች ሕይወት በላይ አልፏል።

አደጋው አሁንም ልቀጥል እንደሚችል ይገመታል። ስለዚህ የሚመለከተው አካል አሁንም አፋጣኝ የሆነ የጥንቃቄ እርምጃ ይውሰድ ።
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን ታወጀ ************በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን፣ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ሕይወታቸው ላለ...
26/07/2024

ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን ታወጀ
************

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን፣ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ሕይወታቸው ላለፉ ዜጎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን አውጇል።

የአድስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ጠዋት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በጎፋ ዞን፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬቶ ቀበሌ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖቻችን የሚሆን የመጀመሪያ ዙር ከ...
25/07/2024

የአድስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ዛሬ ጠዋት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በጎፋ ዞን፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬቶ ቀበሌ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖቻችን የሚሆን የመጀመሪያ ዙር ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ የብር እና ቁሳቁስ የሰብአዊ ድጋፍ ወደቦታው መላካቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።

ወገኖቻችን በደረሰባቸው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳድር እና ህዝቡ ሁሌም ከጎናቸው መሆኑን አረጋግጠዋል ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ

Har'a ganama naannoo kibba Itoophiyaa, godina Goofaa, aanaa Gizee Goofaa ganda Keetootti lammiilee keenya balaa sigiga lafaa mudateen miidhamaniif kan ta'u marsaa jalqabaatiin meeshaalee fi birrii miiliyoona 45 ol ta'u deeggarsa namoomaaf gara bakka sanaatti ergineerra.

Balaa lammiilee keenyarra gaheen gadda guddaa natti dhagahame ibsaa bulchiinsi magaalaa Finfinnee fi uummatni isaa yeroo hunda isin cinaa ta'uu isiniif mirkaneessuun barbaada.

Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ...- 16 የቤተሰብ አባላቱን ያጣ አባት- አምስት የባለቤታቸው ቤተሰብ አባላትን የቀበሩ- 8 ልጆቿን ያጣች እናት -ሙሉ ቤ...
24/07/2024

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ...
- 16 የቤተሰብ አባላቱን ያጣ አባት
- አምስት የባለቤታቸው ቤተሰብ አባላትን የቀበሩ
- 8 ልጆቿን ያጣች እናት
-ሙሉ ቤተሰቦቹ አልቀውበት ብቻውን የቀረ ህፃን የሚገኙበት ሲሆን አሁን ድረስ ከ 40 በላይ ሰዎች አስክሬናቸው በጭቃ ተይዞ መውጣት እንዳልተቻለ እየተነገረ ይገኛል።

ወገኖቻችንን ለመርዳት ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጋር በመተባበር ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማሰባሰቢያ በአጭር የመልዕክት ቁጥር በማዘጋጀቱ ወደ 8091 በመላክ ለወገኖቻችን የአቅማችን እንረባረብ Xossoo Mara🙏

Address

Wolaita
S**o
LULSEGED

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category