03/01/2026
"በሁሉም መዋቅር ትርጉም ያለው የወጣቶች ተሳትፎ እንድረጋገጥ የወጣቶች ማህበር ሚና ወሳኝ ጉዳይ ነው"ብለዋል ወጣት ምህረት ዳና
ወላይታ ሶዶ፤ታህሳስ 25/2018 ዓም የወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የስድስት ወር አፈጻጸምና በቀጣይ ያለው ሥራ አቅጣጫ ዙሪያ ግምገማ አካሂዷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ፌደሬሽን ም/ፕረዚዳንትና የወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር ፕረዚዳንት ወጣት ምህረት ዳና በግምገማው መድረኩ እንደገለጹት በሁሉም መዋቅር የወጣቶች ማህበር ከመቼውም ጊዜ በላይ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሠራ አስረድተዋል ።
የወጣቶች ማህበር በመተዳደሪያ ደንቡና መመሪያና መሠረት በሁሉም መዋቅር በንቃት እንዲሳተፉና ከአቻ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ሥራ እንዲሠሩ ፕረዝዳንቱ አጽንኦት ስጥተዋል።
ማህበሩ በበጀት ዓመት ግማሽ ዓመት አፈጻጸም ላይ የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችና የታዩ ክፍተቶችን በመለየት በቀሪ ዕቅድ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ከስምምነት መድረሱን ፕረዚዳንቱ ጠቁመዋል ።
የወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር ም/ፕረዚዳንት ወጣት አረጋኸኝ ብርሃኑ እንደገለጹት በየመዋቅሩ ያሉ የማህበሩ ሰብሳቢዎች የተሰጠውን ኃላፊነት በአገባቡ በመወጣት ውጤታማ ሥራ እንዲሠሩ አሳስበዋል ።
የማህበሩ አሠራሩና ደንቡ በሚፈቅደው መንገድ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ያስታወሱት ም/ፕሬዝዳንቱ በየደረጃው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ተናግረዋል ።
በግምገማው መድረክ የክልሉ ወጣቶች ፌደሬሽን ም/ፕረዚዳንት ፣የዞኑ፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የወጣቶች ማህበር ፕረዚዳንቶች ተሳትፈዋል ።