Tilahun Yeshiwas

30/11/2024
እኔ የማውቀው የእህልን ዘር  ነው
12/08/2024

እኔ የማውቀው የእህልን ዘር ነው

"ጥዋት ስትነሳ ምታስበው ነገር . . . ለዛሬ ብለህ ያዘጋጀኸው . . . ሁሉንም ለማድረግ አቅደህ ከቤትህ ስትወጣ ሌሎችም እንዳንተው የራሳቸው እቅድ ያላቸው አሉና ላንተ ጥቅም ስትል በነሱ ...
02/02/2023

"ጥዋት ስትነሳ ምታስበው ነገር . . . ለዛሬ ብለህ ያዘጋጀኸው . . . ሁሉንም ለማድረግ አቅደህ ከቤትህ ስትወጣ ሌሎችም እንዳንተው የራሳቸው እቅድ ያላቸው አሉና ላንተ ጥቅም ስትል በነሱ መንገድ ላለመግባት ሞክር፡፡ ይህን ካደረክ የሁለታቹም ከመንገድ ፍፃሜው መልካም ይሆናል፡፡

💞 💞

🌹❣🌹❣🌹🌹❣

 #ለጥንቃቄ⤵ አዲስ የታተሙ የብር ኖቶች አይነት እና የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች~~~~❶ ተከታታይ ቁጥሮች፦የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይ...
14/10/2020

#ለጥንቃቄ⤵
አዲስ የታተሙ የብር ኖቶች አይነት እና የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች
~~~~
❶ ተከታታይ ቁጥሮች፦
የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይለወጣሉ፡፡
❷ ማየት ለተሳናቸው እውቅና ምልክት፦
የብሩን ዋጋ የሚገልጽ ማየት የተሳናቸው በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ ምልክት፡፡
❸ ጎርባጣ_መስመሮች (PEAK)፦
የባንክ ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የኖቱ ዋጋ ይታያል፡፡
❹ ደማቅ አንፀባራቂ ምልክት፦
ገንዘቡ ወደላይ ወይም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ (SPARK) የደህንነት መጠበቂያ ምልክት፡፡
❺ የደህንነት መጠበቂያ ክር፦
የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮከብ አዲስ የደህንንት መጠበቂያ ክር፡፡ በክሩ ውሰጥ NBE፣ ኢብባ እና የገንዘቦቹ አይነት ተጽፎ ይገኛል፡፡
❻ የውሃ ምልክት፦
ገንዘቡ ወደብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላዩ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ የውሃ መልክ ያለው ምልከት ይታያል፡፡
❼ ትይዩምልክት፦
የብር ኖቶች ከብርሃን አቅጣጫ ሲታዩ ኳስ መሳይ ምልክት ከገንዘቡ በስተኋላው ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍጹም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ፡፡
❽ ፈሎረሰንስ ምልክት፦
አንበሳው ምስል ራስ ላይ አልትራቫዮሌት ጨረር ሲበራበት ወደቢጫነት የሚለወጥ ፈሎረሰንት ምልክት፡፡
👉ያስተውሉ፦
አዲስ የታተሙት የብር ዓይነቶች በአካላቸው ላይ የሚገኙ የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ያሉባቸው ናቸው፡፡
እነዚህን ያላሟሉ ወይም ተመሳስለው የተዘጋጁ ገንዘቦቸን የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ግለሰቦች ካጋጠሙዎት ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ/ የጸጥታ አካል ያሳወቁ፡፡

በተራበው ጎኔ፣ በተጎዳው ኪሴእኔም ሰው ነኝና፣የከንፈር ወዳጄን ተጠምታብኝ ነበሴየጥምቀት ለት ሎሚ፣ኪሴን በሚጎዳ በሚነርት ዋጋይሁን ብየ ገዛሁ፣ደረቷን ልመታ የዛችን ውብ ሸጋ።ሎሚውን በእጄ ያ...
22/01/2020

በተራበው ጎኔ፣ በተጎዳው ኪሴ
እኔም ሰው ነኝና፣
የከንፈር ወዳጄን ተጠምታብኝ ነበሴ
የጥምቀት ለት ሎሚ፣
ኪሴን በሚጎዳ በሚነርት ዋጋ
ይሁን ብየ ገዛሁ፣
ደረቷን ልመታ የዛችን ውብ ሸጋ።

ሎሚውን በእጄ ያዝኩ
ኮረዳዋን ፈለግኩ
ባ'ይኖቼ አማተርኩ

ከኋላዋ አየኋት...
ፀጉሯ ሹሩባ ነው፣ ፊቷ አይታይም
ኋላዋ ካማረ...
ፊቷ ምንም ይሁን እኔን አይጨንቀኝም

ዳሌዋ... ቢዮንሴን ያስንቃል
በንቅልፍ የቧዘዘን አጣድፎ ያነቃል
ስንት የወጣባትን፣
የኛን ሳተላይት ከቻይና ያመጥቃል (አንጥሮ😂)

ወገቧ... አካበድክ ባትሉኝ
ከቀጭኗ እግሬ ሚወፍር አይመስለኝ

ወይኔ ሹሩባዋ
ለመግለፅም እንኳን አንደበትን ያስራል
በቆሙበት መሬት አፍዞ ያስቀራል።

ወደራሴ መጣሁ...
ልወርውር አልወርውር?
ልወርውር አልወርውር?

ወረወርኩ...
ድምም... እዛው ዳሌዋ ላይ
አሟት ዩን ደስ ብሏት ዞር ብላ ብታይ
የኔ ልብ ደንግጣ ልትበር ወደ ሰማይ

እየሮጠች መጣች፣
እያነፈነፈች ትንፋሿ እስከሚያጥራት
ክፉ አስባ ይሆን ልሩጥ ልጠብቃት?

ደረሰች...
ፊቴ ከመድረሷ፣
አንድ ጊዜ በጥፊ አወላመመችኝ
ወደላይ ወደታች፣
መላ ሰውነቴን በደምብ ቃኘችኝ
ወደግራ ጆሮየ በጣም ተጠጋችኝ

ጊዜው የድንጋይ ነው ሎሚ አታባክን
ኪስህን አሟጠህ፣
በገዛኸው ሎሚ ፈፅሞ አትጨክን
አሁን ሳናቅማማ ቶሎ እንሽጠው
ይሄ ውድ ሎሚ፣
ላ'ዲሱ ጎጇችን ትልቅ መሰረት ነው
ብላ አቀፈችኝ
እሰየው ዘንድሮ ለኔም ተሳካልኝ።

Welcome to Christmas
07/01/2020

Welcome to Christmas

05/11/2019

እስኪ እኛ አገርም ያለውን አጠፋልን ትራምብየ ካንተ ምን ይሳንሀል

ቆይ ግን ይህን ዘፈን ሪምክስ የማረግ ዘፋኝ ይጥፋ በአሁኑ ስአት የአስፈልገን ነበር ጀሮአችን በእነ እጅህን ትቆሪጣለህ አሊቆርጢም የሚል ዘፈን  ደነቆረ እኮ ኡኡኡኡኡ
04/11/2019

ቆይ ግን ይህን ዘፈን ሪምክስ የማረግ ዘፋኝ ይጥፋ በአሁኑ ስአት የአስፈልገን ነበር ጀሮአችን በእነ እጅህን ትቆሪጣለህ አሊቆርጢም የሚል ዘፈን ደነቆረ እኮ ኡኡኡኡኡ

.አንድ መምህር የመቶ ብር ኖት ወደ ላይ ከፍ አድርጎ በመያዝ ለተማሪዎቹ ‹‹ማን ነው ይህን የሚፈልግ›› አላቸው።ሁሉም እጃቸው በማውጣት ‹‹ቲቸር እኔ... እኔ ...›› ማለት ጀመሩ።መምህሩ ...
03/11/2019

.
አንድ መምህር የመቶ ብር ኖት ወደ ላይ ከፍ አድርጎ በመያዝ ለተማሪዎቹ ‹‹ማን ነው ይህን የሚፈልግ›› አላቸው።ሁሉም እጃቸው በማውጣት ‹‹ቲቸር እኔ... እኔ ...›› ማለት ጀመሩ።
መምህሩ ብሯን በእጁ ጭምድድ ካደረጋት በኋላ ዳግም ወደላይ ከፍ አድርጎ ‹‹አሁንስ ማነው መውሰድ የሚፈልግ?›› አላቸው።ሁሉም ተማሪዎች አሁንም እጃቸውን በማውጣት ልክ እንደመጀመሪያው‹‹እኔ... እኔ›› እያሉ ጩኸታቸውን ቀጠሉ።መምህሩ ብሯን መሬት ላይ ከጣላት በኋላ በጫማው እየረጋገጠ አቆሸሻት። ከዚያ ወደ ላይ ከፍ በማድረግ ‹‹አሁንስ ማነው መውሰድ የሚፈልግ?›› አላቸው።ተማሪዎቹ ብሯን በዋዛ ሊያሳልፏት ስላልፈለጉ ልክ እንደመጀመሪያዎቹ ጊዜያት እጆቻቸውን በማውለብለብ ቲቸር‹‹እኔ... እኔ...›› ማለታቸውን ቀጠሉ።መምህሩ ብሯን ወደ ኪሱ በመመለስ ‹‹የዛሬው ትምህርታችሁ እዚህ ላይ ያበቃል። ቀዳደህ ካልጣልካት በስተቀር በማሸት፣በማቆሸሽና በመረጋገጥ የዚህችን ወረቀት ዋጋ መቀነስ እንደማይቻለው ሁሉ እናንተንም ሰዎች ሊያንቋሽሿችሁ፣ሊያሳንሷችሁ፣ ሊያዋርዷችሁ፣ ሊያፌዙባችሁ፣ … ጥረት ቢያደርጉም ትክክለኛ ዋጋችሁን ሊቀንሱ እንደማይችሉ እወቁ።/መምህሩ ትንሽ ፋታ ከወሰደ በኋላ... /ይህን ካወቃችሁ ከውድቀት በኋላም መነሳት ትችላላችሁ። ሁሉም ትክክለኛ ዋጋችሁን እንዲያውቅ ማድረግ ትችላላችሁ። ነገር ግን ትክክለኛ ዋጋችሁን የረሳችሁ እና በራስ መተማመናችሁን ያጣችሁ ቀን ሁሉንም ነገር ማጣታችሁን እወቁ!››
የማንቂያ ደወል፤ የትምህርት ቤቱ ደወል ተደወለ፡፡ መምህሩም ከክፍል ወጣ፡፡

አሁን ላይ ያለው አንዳንድ የሰዎች አስተሳሰብ ያው መጠየቃቸው አይቀርም ብየ ነው
31/10/2019

አሁን ላይ ያለው አንዳንድ የሰዎች አስተሳሰብ ያው መጠየቃቸው አይቀርም ብየ ነው

Address

Tilahunyeshiwas1@gmail. Com
Senbete

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tilahun Yeshiwas posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share