13/06/2025
ከሰኔ3-6/10/2017 ዓ.ም ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል በ41 ት/ት ቤቶችና 6ኛ ክፍል በ46 ት/ት ቤቶች ክልል አቀፍ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሰላም ተጠናቀቀ።
በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፓሊስና ሰላም አሰከባሪዎች በሁሉም ቀበሌ ፈተናው የሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች ፈተናው ምንም የፀጥታ ችግር ሳይፈጠር በስላም መጠናቀቁን የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ገለፁ።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ኃላፊ ም/ኮ/ር መሐመድ አሊ በበኩላቸው ፓሊስ በሁሉም ፈተና የሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች ላይ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ ተገብቶ በሰላም መጠናቀቁን ገለፁ::