ተ/ሃ/መ/ጠ ሆስፒታል THMG Hospital

ተ/ሃ/መ/ጠ ሆስፒታል THMG Hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ተ/ሃ/መ/ጠ ሆስፒታል THMG Hospital, Government Organization, Sek'ot'a.

The focus of public relations is to improve health digital technology, community participation and ownership, improve information-based decision-making systems, improve leadership and good governance,

15/11/2025

ሰሞኑን ጂንካ ላይ የታየው ወረርሽኝ የኢቦላ ዝርያ ግን ከኢቦላም የከፋ መሆኑ ተረጋገጠ

ወረርሹኙ ማርበርግ የተሰኘ ቫይረስ ( Marburg virus) የሚያስከትለው በሽታ መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና ሚንስተር አረጋግጧል።

የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል (CDC) ቫይረሱን “እምብዛም የማይከሰት ግን በጣም የከፋ በማለት ገልፆት ገዳይ ሊሆን ይችላል” ብሏል።

በሽታው ከ ‘ ግብጿ የፍራፍሬ ለሊት ወፍ’ ( Egyptian fruit bat) የሚመጣ ሲሆን በህመሙ ከሚያዙ ሰዎች ግማሽ ያህሉ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ጥናቶች ያሳያሉ።

በሽታዉ የሚተላለፈው በሰውነት ፈሳሽ ንክኪ ፤ ህክምናው ደግሞ እረፍትና ፈሳሽ አብዝቶ መውሰድ (የእገዛ ህክምና) መሆኑ ተዘግቧል።

ህብረተሰቡ የቫይረሱን መተላለፊያ መንገድ በመረዳት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል።
የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች እና ማዳረግ ስለሚገባን ጥንቃቄ ጤና ሚኒስቴር ያወጣውን መረጃ ከላይ ተያይዟል።

15/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንነት፣ መተላለፊያ መንገዶችና መከላከያ ዘዴዎች



Website: moh.gov.et
Facebook: facebook.com/EthiopiaFMoH
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

13/11/2025

ምንድን ነው?

‎ይህ በሽታ በቫይረስ የሚከሰት ከባድ የበሽታ ቡድን ነው ። በሽታው በመሰረቱ የደም መፍሰስን ወይም የደም መርጋትን በሰውነት ውስጥ የሚያመጣ ነው ። በርካታ የሰውነት አካላትን በማጥቃት እና በሰውነት ውስጥ ያሉ የደም ሥሮችን የሚጎዳ ፣ በተለያዩ ቫይረሶች የሚመጣ በሽታ ነው።

#‎የበሺታው_መንስኤ እና የቫይረስ ዓይነት

‎. Ebola and ,Rift Valley Fever (RVF) & Yellow Fever ተብሎ የሚከፈል ሲሆን እንደ #ኢቦላቫይረስ ፣ #ደንጉ እና #የለውፊቨር የተባሉ ቫይርሶች የበሺታው መንስኤ ሲሆኑ #በትንኝ ንክሻም የሚመጡ ናቸው ።

‎ በሽታው ስሙ እንደሚያመለክተው በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም እንዲፈስ በማድረግ ለሞት የሚዳርግ ህክምና አልባ አደገኛ በሺታ ነው።

‎በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም መድማት እና መፍስሥ ከተከሰተ የበሽታው ከባድ ደረጃ ምልክት ነው።

‎በሽታው እንዴት ይተላለፋል?

‎1· ከተያዙ እንስሳት ጋር በመነካካት፡ በእንስሳት (ለምሳሌ አይጥ) ፣ ሽንት፣ ምራቅ ፣ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች በሚነካኩበት ጊዜ።
‎2· በነፍሳት ንክሻ፡
‎3· ከሰው ወደ ሰው፡ ከተያዘ ሰው የሚገኘው ደም፣ ምራቅ፣ የሰውነት ፈሳሾች ወይም ሌሎች ክምችቶች በቀጥታ በሚነካኩበት ጊዜ። ይህ ለበሽታው ከባዱ እና ዋነኛው ዓይነት የመተላለፊያ መንገድ ነው።



‎ምልክቶቹ በድንገት ሊታዩ እና በፍጥነት ሊባባሱ ይችላሉ። አንድ ሰው በቫይረሱ በተጠቃ ከ 2-21 ቀናት ውስጥ ምልክቶቹ መታየት ይጀምራሉ

‎መጀመሪያ ላይ የሚታዩ ምልክቶች
‎ምልክቶቹን በሁለት ከፍሎ ማየት የሚቻል ሲሆን
‎የመጀመሪው ቀለል ያሉ ምልክቶች እና የመጨረሻው አደገኛ //አስጊ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚታዩ ናቸው


‎· ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት (ትኩሳት)
‎· ድካም እና የመዛል ስሜት
‎· የጡንቻ፣ የአጥንት ህመም እና ቁርጥማት
‎· ራስ ምታት
‎· የጉሮሮ ህመም

‎ (በሽታው እየተባባሰ ሲሄድ)፡

‎· በቆዳ ስር ደም መውጣት
‎. ከአፍ፣ አፍንጫ፣ ከዓይን ወይም ከጆሮ ደም መፍሰስ።
‎· የጭንቅላት አዕምሮ መናጋት ፣ መደንገጥ፣
‎. ራስን መሳት ኮማ ውስጥ መግባት)
‎· የኩላሊት እና የጉበት መጎዳት እና ስራ ማቆም
‎· ከፍተኛ ድካም እና ሾክ/Shock
‎· የበርካታ አካላት አለመሥራት

‎እንዴት መከላከል ይቻላል ?

‎በሽታው በትንኝ ንክሻ አማካኝነት የሚተላለፍ በመሆኑ ነፍሶን ከሞት መታደግ ስለሆነ በአግባቡ ይጠቀሙት ። ከታማሚ ሰው ጋር ያልዎትን ንክክ መከላከል እና
‎አፋጣኝ አስፈላጊ የህክምና እርዳታ ማግኘት አስፈላጉ ሆኖ ፣በሺታውን ሙሉበሙሉ ማዳን የሚችል ህክምና የለም ፣
‎መከላከል ብቸኛው ቁልፍ መንገድ ነው !

‎ የሚከተሉትን ማድረግ ያስፈልግዎታል !!

‎1. እጆችዎን በንፅህና ይታጠቡ፡ በሳሙና እና በንጹህ ውሃ ዘወትር ማጠብ አስፈላጊ ነው።
‎2. ከሌሎች ሰዎች (ክምችቶች) ራስዎን ይጠብቁ፡ ከሰዎች ደም፣ ምራቅ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች ንክኪዎች ራስዎን ይጠብቁ። ይህ ለቤተሰብ አባላት እና በተለይም ለህክምና ባለሙያዎች እጂግ አስፈላጊ ነው።
‎ብዙ የህክምና/ጤ ና ባለሙያዎች ህይወታቸውን የሚያጡበት ወረርሺኝ ነው።
‎3. ከእንስሳት ይራቁ፣ አይጦችን እና ሌሎች እንስሳት ከቤትዎ አርቀው ያቆዩ። የሚታወቁ የእንስሳት ክምችቶች ባሉበት ስፍራ ጥንቃቄ አይለይዎት
‎4.ከ ነፍሳት ይጠበቁ ፣ አጎበር መጠቀም፡ ነፍሳት እና ወረርሽኙ ወደተከሰተበት ቦታ ፈጽሞ አይሂዱ ፣ አ

12/11/2025

ወቅታዊ የጤና ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

Website: moh.gov.et
Facebook: facebook.com/EthiopiaFMoH
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

04/11/2025
09/10/2025

(ዘ-ሐበሻ ዜና ዳሰሳ) እ.ኤ.አ. በ1993 የተካሄደው የኤርትራ የነጻነት ሪፈረንደም፣ ህጋዊ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ሂደት ሳይሆን፣ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ወደብ አልባ ለማድረግ ለረጅም ጊዜ ስትከተለው የነበረው ስትራቴጂ ውጤት እንደነበር የሆርን ሪቪው ትንታኔ አመለከተ። ትንታኔው፣ በወቅቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ የነበሩት ግብፃዊው ቡጥሮስ ቡጥሮስ ጋሊ፣ የሀገራቸውን ስትራቴጂካዊ ግብ ለማሳካት ሂደቱን በማመቻቸት ቁልፍ ሚና እንደተጫወቱ ይከራከራል።

ትንታኔው እንደሚለው፣ የቡጥሮስ ቡጥሮስ ጋሊ ሙሉ የዲፕሎማቲክ ህይወት ከግብፅ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጋር የተቆራኘ ነበር። ዋና አላማቸውም የግብፅን የአባይ ወንዝ የበላይነት ማስጠበቅ፣ የቀይ ባህር ተጽዕኖን ማስፋት እና ኢትዮጵያን ማዳከም እንደነበር ይገልጻል። ጋሊ የተመድ ዋና ጸሐፊ ሆነው የተሾሙት፣ የግብፅ ተኪ ኃይሎች እንደሆኑ የተገለጹት ህወሓትና ሻዕቢያ አዲስ አበባ ላይ ስልጣን በያዙ በአመቱ መሆኑ፣ የካይሮን አጀንዳ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስፈጸም እንዳስቻላቸው ትንታኔው ያብራራል።

በተጨማሪም ትንታኔው ግብፅ ከ1950ዎቹ ጀምሮ የኤርትራን ተገንጣይ ቡድኖች (ጀብሃ እና ሻዕቢያ) በካይሮ ውስጥ በማደራጀት፣ የገንዘብ እና የሚዲያ ድጋፍ ስትሰጥ መቆየቷን ይጠቅሳል። ህወሓትም የተመሰረተው በግብፅ ድጋፍ እንደሆነ የሚከራከረው ጽሑፉ፣ የኤርትራን ነጻነት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል ለህወሓት ምስረታ ከግብፅ የስለላ ተቋም የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ እንደነበር ይገልጻል።

በጥር 1993 ቡጥሮስ ጋሊ አዲስ አበባን በጎበኙበት ወቅት፣ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሪፈረንደሙን በመቃወም ሰልፍ መውጣታቸውን ትንታኔው ያስታውሳል። ሰልፉ በኃይል የተበተነ ሲሆን፣ ጋሊ ለተፈጠረው ደም መፋሰስ ትኩረት ሳይሰጡ በማግስቱ ወደ አስመራ በማምራት ከሻዕቢያ ባለስልጣናት ጋር መገናኘታቸው፣ ለነጻነቱ ሂደት የነበራቸውን ድጋፍ ያሳየ ድርጊት ነበር ተብሏል።

ትንታኔው፣ በትጥቅ ትግል ስልጣን የያዘ የሽግግር መንግስት በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ፊት ሪፈረንደም እንዲያካሂድ መፈቀዱ በተመድ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ "ልዩ" ክስተት እንደነበር ይገልጻል። በወቅቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) ሊቀመንበርነት ከሰኔ 1993 ጀምሮ በግብፁ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ እጅ መግባትም፣ ካይሮ በአፍሪካ ተቋማት ላይ የነበራትን ተጽዕኖ ያሳያል ሲል ይከራከራል።

የሆርን ሪቪው ትንታኔ በማጠቃለያው፣ የ1993ቱ የኤርትራ ሪፈረንደም የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ እና ኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ ለማዳከም የተቀነባበረ በመሆኑ፣ ሂደቱ ዓለም አቀፍ ህግጋትን የጣሰ ነበር ይላል። በቡጥሮስ ጋሊ የተመራው የተመድ ሚናም የሂደቱን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ እንደከተተው ይገልጻል።

በዚህም ምክንያት፣ ትንታኔው ኢትዮጵያ የሪፈረንደሙን ህጋዊነትና ውጤቱን ላለመቀበል "የሞራል፣ የታሪክ፣ የህግ እና የዲፕሎማሲያዊ መሰረት" እንዳላት በመግለጽ ይቋጫል።

14/09/2025

የጥንቃቄ መልዕክት

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን የቴሌግራም ና ዋትሳፕ ተጠቃሚዎችን ያነጣጠረ የማጭበርበርና የአካዉንት ነጠቃ እንቅስቃሴዎች እየጨመሩ መጥተዋል።

ከሰሞኑም ከዚህ ቀደም ከነበረዉ በተለየ ሁኔታ የግለሰቦች የቴሊግራምና ዋትሳፕ አካዉንቶችን በመረጃ መንታፊዎች በከፍተኛ ደረጃ እየተነጠቀና ማጭበርበሮች እየተፈጸሙ መሆኑን በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የሳይበር አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ መስጫ ማዕከል/Ethio-CERRT/ ማረጋገጥ ችሏል።

እነዚህ የአካዉንት ነጠቃዎች የሚፈጸሙት ለጥቃት ኢላማ ላደረጉት አካል አጥፊ ተልዕኮ ያላቸዉን ሊንኮችን በመላክና ሊንኩን እንዲከፍቱ የሚያደርጉ ቴክኒኮችን በመጠቀም ነዉ። ከእነዚህ ቴክኒኮች መካከል በጣም ወሳኝ በሆነ ጉዳይ አስቸኳይ በዙም ወይም በሌሎች የኦንላይን ፕላትፎርሞች ስብሰባ ስለሚኖር በተላከዉ ሊንክ አማካኝነት እንዲሳተፉ በመደወልና በማግባባት ሲሆን ሊንኩን ከፍተዉ በሚገቡበት ወቅት አካዉንታቸዉን ይነጥቃሉ።

ከዚህ የአካዉንት ነጠቃ በኋላ የተነጠቀዉን የቴሊግራም ወይም ዋትሳፕ አካዉንት በመጠቀም ወደ ግለሰቡ ወዳጆች ለወሳኝ ጉዳይ ገንዘብ እንደሚያስፈልጋቸዉና እንዲያስገቡላቸዉ በጽሁፍ መልዕክት በመጠየቅ እያጭበረበሩ ይገኛሉ።

በመሆኑም የቴሌግራምና ዋትሳፕ ተጠቃሚዎች ከማታዉቁት አካል የሚላክላችሁን አጓጊ የሆኑና አስቸኳይነት ያላቸዉ ሊንኮች ሲላክልዎት እንዲሁም ሊንኩን እንዲከፍቱ ጥሪ ሲደርስዎት አካዉንትዎን ለመጥለፍ ሊሆን ስለሚችሉ ሊንኮችን ከመክፈት መቆጠብና ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ያሳዉቃል።

ከዚህ ባሻገር የቴሌግራምና የዋትሳፕ ተጠቃሚዎች ከወዳጅ ዘመድዎ ወይም የስራ ባልደረባዎ በእነዚህ አካዉንቶች የሚቀርብላችሁን የብድርና የድጋፍ ጥያቄዎች ምላሽ ከመስጠትዎ በፊት ወደ ጠያቂዉ ስልክ ደዉለዉ ሳያረጋግጡ ማንኛዉንም ገንዘብ እንዳይልኩ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ያሳስባል።

ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
• ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et
• ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/?_t=8qBKkyp092r&_r=1
• ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com//featured
• ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet
• ትዊተር (X) ፦ https://twitter.com/INSAEthio
• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት ነጻ የስልክ መስመር፡ 933

10/09/2025

የተፈራ ሃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ለአዲሱ አመት የዘመን መለወጫ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል

ሰቆጣ፣ ጳጉሜን 5፣2017 ዓ.ም (waghimra Communication) በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የተፈራ ሃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2018ዓ.ም የአዲስ አመት ዋዜማ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ታምሩ ቢምረው የዘመን መለወጫ ዋዜማውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ፣አዲሱ አመት የሰላም፣የፍቅር፣የአንድነት፣የመተሳሰብ፣የጤና እና የብልፅግና አመት እንዲሆን እንመኛለን ብለዋል።

ሆስፒታሉ በአለፉት ወራት የነበሩና የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመቅረፍ በአዲሱ አመት የተሻለ አገለግሎት ለመሰጠት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወኑ መሆናቸውን አቶ ታምሩ ቢምረው በመግለጫቸው ተናግረዋል።

በሆስፒታሉ በርካታ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ በየደረጃው ከሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር በመሆን የተለያዩ የመድረክ ውይይቶች መደረጋቸውን አውስተዋል።

በከፍተኛ ሁኔታ መስተጓጎል ከሚፈጠርባቸው የካርድ ክፍልና የጤና መድን የአገልግሎት አሰጣጥ ስራዎች ላይ ተጨማሪ የሰዉ ሀይል በመመደብ እና የካርድ ክፍል ሁሉም መስኮቶች አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መቻሉን አቶ ታምሩ ገልጸዋል።

አገልግሎት መስጠት አቁመዉ የነበሩ የኬሚስትሪ እና ኤክስሬይ ማሽኖችን በማስጠገን ወደ ስራ መገባቱንም አክለዋል።

በሆስፒታሉ የመድሀኒት እጥረትን ለመቅረፍ እና የነበሩ እዳዎችን በመክፈል 3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ከደሴ መድሀኒት አቅራቢ ድርጅት በዱቤ ግዥ መፈፀም መቻላቸውንም አቶ ታምሩ አብራርተዋል።

በሌላ በኩል በሆስፒታሉ ውስጥ የሚስተዋሉ ልዩልዩ የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች እጥረት፣ከፍተኛ የሀይጅን እና ሳኒቴሽን (IPC)ችግር ፣በመርዝ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እና የጨቅላ ህፃናት ሞት አሳሳቢነት እና የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ የግብአት ችግሮችን ለመፍታት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ሲሉ አቶ ታምሩ አሳስበዋል።

በብሄረሰብ አስተዳደሩ ብቸኛ የሆነው የተፈራ ሀይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል የተሻለ አገልገሎ መስጠት እንዲችል የሀይማኖት ተቋማት፣ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ባለሀፍቶች፣የአካባቢዉ ማህበረሰብ እና ወዳጆች በሙሉ አስፈላጊዉን ድጋፍ እንዲያደረጉ የሆስፒታሉ ስራ እስኪያጅ አቶ ታምሩ ቢምረዉ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

መልካም አዲስ አመት

#ሙሃባው ፈረደ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከዋግ-ኽምራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦችን ለመቃኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡
✔Facebookፌስቡክ:-https://www.facebook.com/waghimracom/
✔Telegram ቴሌግራም፡- https://t.me/waghimracomm
✔Twitterትዊተር:-https://twitter.com/waghimra_comm
✔You tube ዩቲዩብ፡-https:/www.youtub

09/09/2025

ጨቅላ ህፃናት ላይ የሚታዩ ህክምና የሚፈልጉ አደገኛ ምልክቶች
ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓም

⚫️የጨቅላ ህፃናት መታመም ለቤተሰብ ከባድ ነገር ነው። ጨቅላ ህፃናት ሲታመሙ እንደ ሌላ እድሜ ላይ እንዳለ ሰው ያመማቸውን ስለማይናገሩ ሁኔታውን የበለጠ ከባድ ያደርገዋል።

⚫️ስለዚህ የህፃኑን መታመም ቀድሞ ለይቶ ማወቅ የ የወላጅ ሃላፊነት ይሆናል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ምልክቶችን ልጅሽ ላይ ካስተዋልሽ ቶሎ ወደህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል።

⚪️ጡት በደንብ የማይጠባ ከሆነ፣ በሆነ ባልሆነው የሚነጫነጭ ከሆነ እንዲሁም እያባበልሽውም ካለማቋረጥ የሚያለቅስ ከሆነ❗️

⚪️በተደጋጋሚ የሚያስመልሰው ከሆነ እንዲሁም ምንም ነገር ባፉ አልወስድ ካለ❗️

⚪️ቆዳው እንዲሁም ነጭ የአይኑ ክፍል ቢጫ እንደሆነ ካስተዋልሽ❗️

⚪️ ከተወለደ በ 2 ቀናት ውስጥ ምንም ካካ ነገር ከሌለው፣ ሆዱ እየተነፋ የሚሄድ ከሆነ❗️

⚪️እትብቱ የተቆረጠበት ቦታ የሚደማ ከሆነ እንዲሁም ሌላ ፈሳሽ የሚወጣው ከሆነ❗️

⚪️ጡት ሲጠባ ከመጠን በላይ የሚያልባቸው ከሆነ:የሚያቆራርጥ ከሆነ፣ ከንፈሩ እንዲሁም እጆቹ የሚጠቁሩ ከሆነ❗️

⚪️የጭንቅላታቸው(ራሳቸው) መጠን ከቀን ወደ ቀን እያደገ(እያበጠ) መሆኑን ካስተዋሉ❗️

እነዚህን ምልክቶች ካስተዋልሽ ቶሎ ልጅሽን ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ይኖርብሻል።

ጤና ነክ እና ሌሎችም አስተማሪ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት እና ለማማከር በሚከተሉት አድራሻዎች ያገኙናል፡
የተኃመጠ ሆስፒታል ቻናል

ቴሌግራም https://t.me/thmgh

ፌስቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=10008448150433

Address

Sek'ot'a

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ተ/ሃ/መ/ጠ ሆስፒታል THMG Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share