Modjo Customs Branch ሞጆ ጉምሩክ

Modjo Customs Branch ሞጆ ጉምሩክ MODJO CUSTOMS BRANCH(established in July 1/2005 EC as one branch) is one among the other 17 branches
(3)

28/05/2026
‹‹‹‹‹‹‹በጉምሩክ ሥነ-ስርዓት አፈጻጸም እና የጉምሩክ አስተላላፊዎች ሙያዊ ሥነ-ምግባር ዙሪያ  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተካሄደ›››››››          (ግንቦት 13/2018 ዓ.ም ሞጆ...
21/05/2026

‹‹‹‹‹‹‹በጉምሩክ ሥነ-ስርዓት አፈጻጸም እና የጉምሩክ አስተላላፊዎች ሙያዊ ሥነ-ምግባር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተካሄደ›››››››
(ግንቦት 13/2018 ዓ.ም ሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)

የሞጆ ጉ/ቅ/ጽ/ቤትበጉምሩክ ሥነ-ስርዓት አፈጻጸም እና በጉምሩክ አስተላላፊዎች ሙያዊ ሥነ-
ምግባር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ስለሚገጥሙ ተግዳሮቶች የጉምሩክ አስተላላፊዎች እና የባለድርሻ አካላት አመራሮች በተገኙበት በቀን 13/09/2018ዓ.ም ያከናወነ ሲሆን የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጌቱ አለሙ የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የደንበኞች ትምህርት ቡድን አስተባባሪ አቶ ጥላሁን አያሌው የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና ሰነዱ ላይ ዝርዝር ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በገላፃቸዉም የጉምሩክ ሥነ-ስርዓት አፈፃፀም ሂደቶችን፣የጉምሩክ እና የባለድርሻ አካላ የህግ ማዕቀፎችና አሰራሮች እንዲሁም የጉምሩክ አስተላላፊዎች ሚናና የስራ ላይ ስነ-ምግባር ተካተውበታል፡፡
በመጨረሻም የሞጆ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጌቱ አለሙ እና የሞጆ ሎጅስቲክስ ማዕከል ቺፍ ኦፕሬሺን ኦፊሰር (CO) አቶ ሳሙኤል ካሳሁን በጋራ በመሆን መድረኩን እየመሩ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ዉስጥ በሚገጥሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ከተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ በመስጠት የዕለቱ መርሃ-ግብር ተጠናቋል፡፡

20/05/2026

ጉምሩክ ኮሚሽን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን በመከላከል ከፍተኛ ሚናውን እየተወጣ ነው

ግንቦት 11/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ጉምሩክ ኮሚሽን ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን መከላከል እና የገቢ አሰባሰብን የሚያዛቡ የተጭበረበሩ ሰነዶችን መቆጣጠር የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በተቋም ግንባታ የፋና ወጊነት ሚና እየተወጣ መሆኑን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የፌደራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡

በዚህም ሀገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ ተቋማዊ ሪፎርም በማድረግ ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን መከላከል፣ የገቢ አሰባሰብን ማሳደግ የሚያስችል አደረጃጀት ፈጥሯል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ተቋሙ በአዋጅ ከተሰጠው ቁልፍ ተልዕኮዎች መካከል ከገቢና ወጭ እቃዎች ታክስን አስልቶ ገቢ መሰብሰብ ነው፡፡

ሀገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ በተደረገው የተቋም አደረጃጀት ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን መከላከል የሚያስችሉ ግልጽ የህግ ማዕቀፎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከሪፎርሙ በፊት በ2011 በጀት ዓመት የተሰበሰበው ገቢ 78 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር እንደነበር ገልጸው፤ በተያዘው በጀት ዓመት አስር ወራት ከታቀደው በላይ 600 ነጥብ 23 ቢሊየን ብር በላይ ጥቅል ገቢ ተሰብስቧል ብለዋል፡፡

ሪፎርሙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ ህጎችን በማሻሻልና አሰራርን በማዘመን የገቢ አሰባሰብ፣ የህገ ወጥና ኮንትሮባንድን መከላከል የሚያስችል አቅም መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑ ዕቃዎችን ከአደጋ በመከላከል ደህንነታቸው ተጠብቆ ከመዳረሻ ቦታቸው እንዲደርሱ የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ ቴክኖሎጂ ሥራ ላይ አውሏል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ በምትልካቸው እቃዎች በመንገድ ላይ ይደርስ የነበረውን መዘግየት፣ ቅሸባና ስርቆት እና መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ መቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በቴክኖሎጂ የታገዘ የተቀናጀ የድንበር ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት የካርጎ እንቅስቃሴዎችን ማዕከል ላይ ሆኖ መቆጣጠር የሚቻልበት ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ የተገልጋይ መንገደኞችን እንቅስቃሴ በመቆጣጠር ህገ ወጥ እንቅስቃሴን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ መዋሉን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑ ሪፎርሙ በፈጠራቸው መልካም ዕድሎች ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት በኢትዮጵያ የተቋማት ግንባታ ፋና ወጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በርካታ ቴክኖሎጂዎች ሥራ ላይ መዋላቸውን ገልጸው፤ የማንዋል አሰራርን በማስወገድ ለአምራቾች፣ አስመጭዎችና ላኪዎች የተሳለጠ አገልግሎት እየሰጡ ነው ብለዋል፡፡

የኦን ላይን አገልግሎቶችን በመስጠት የተገልጋዮችን ጊዜና ጉልበት ይቀንሳል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ቴክኖሎጂዎች ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ መከላከል እና የገቢ አሰባሰብን የሚያዛቡ የተጭበርበሩ ሰነዶችን መቆጣጠር እንዳስቻሉ ገልጸዋል፡፡

ይህም የማንዋል አሰራሮችን በማስቀረት እና ብልሹ አሰራርን በማስወገድ ኮሚሽኑ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ እንዳስቻለው የኢዜኣ ዘገባ ያመለክታል።

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላ

15/05/2026

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የ8 ዓመታት የገቢ አፈጻጸም ዕድገት

ግንቦት 07/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የ8 ዓመታት የገቢ አፈጻጸም ዕድገት ከ2011 እሰከ 2018 ዓም

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

Address

Modjo, Oromiya
Mojo

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Modjo Customs Branch ሞጆ ጉምሩክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Modjo Customs Branch ሞጆ ጉምሩክ:

Share