Gizaw Gagiabe T.

Gizaw Gagiabe T. Head of southe west Ethiopian people region industry and innovation bureau

20/06/2026

የትጉ ስኬት ማማ

የህብረት ሥራ ፋይዳ እና የተግዳሮቶች መሻገሪያ ስልት
​የህብረት ሥራ ማህበራት የአንድን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ሕይወት ለመቀየር ያላቸው ፋይዳ በምርምርና በጥናት የተረጋገጠ የልማት ምሰሶ ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተካሄዱ ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ በተለይም የቁጠባና ብድር የህብረት ሥራ ማህበራት (SACCOs) የፋይናንስ ተደራሽነትን በማስፋት፣ የተበታተነ የህዝብ ሀብትን በማሰባሰብና ፍሰቱን ወደ አምራች ዘርፎች በመምራት ረገድ ወደር የሌለው ሚና አላቸው። ይህ ሥርዓት ግለሰባዊ ጥረትን ወደ የጋራ ጉልበት በመቀየር የገበያ ክፍተቶችን የሚደፍን ከመሆኑም በላይ፣ አባላት በራስ የመተማመንና የቁጠባ ባህላቸውን አሳድገው የኢኮኖሚ ባለቤት እንዲሆኑ ያስችላል። የምርምር ውጤቶች በተደጋጋሚ የሚያረጋግጡት እውነት ቢኖር፣ ጠንካራ የህብረት ሥራ መዋቅር ባለበት ማህበረሰብ ውስጥ የድህነት ቅነሳና ፍትሐዊ የሀብት ስርጭት በተጨባጭ እንደሚረጋገጥ ነው።

​ይሁን እንጂ ይህንን ታላቅ ፋይዳ ወደ መሬት አውርዶ ስኬታማ ማድረግ ግልጽ ራዕይና የሰለጠነ አመራርን ይጠይቃል። በዘርፉ የተደረጉ በርካታ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ አብዛኛዎቹ የህብረት ሥራ ማህበራት ከሚገጥሟቸው ዋና ዋና ተግዳሮቶች መካከል አንዱና ዋነኛው የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ውስንነትና የቢሮክራሲ መጓተት ነው። ባህላዊ አሰራርን ሙጥኝ ብሎ መቆየት የማህበራትን ተወዳዳሪነት ከመቀነሱም በላይ የአባላትን እምነትና ተሳትፎ ያሻክራል። ነገር ግን ይህንን ስጋት አስቀድሞ በመረዳት የአሰራር ዘይቤን ማዘመን፣ ዲጂታል መሠረተ-ልማትን መዘርጋትና አባላትን ያማከለ ቀልጣፋ የሞባይል ባንኪንግና የኮር ባንኪንግ አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ ማህበራቱን ወደ ላቀ የዕድገት ምዕራፍ እንደሚያሸጋግራቸው የምርምር ውጤቶች ይሞግታሉ።

​በትጉ ማህበር ውስጥ የታየው የተግባር እውነት
​ይህንን ሳይንሳዊና ጥናታዊ እውነት በተግባር በመተርጎም ረገድ የትጉ ማህበር (Tigu SACCOS Ltd) ጉዞ እጅግ አርአያነት ያለውና ተስፋ ሰጪ ነው። ማህበሩ የህብረት ሥራን ጥልቅ ፋይዳ እንዲሁ በፅንሰ-ሀሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን፣ የአባላቱን የዕለት ተዕለት ሕይወት በሚቀይር መልኩ በመስመር ላይ እያዋለው ይገኛል። የተበታተነውን የህብረተሰብ ቁጠባ በማሰባሰብና ለስራ ፈጣሪዎች ምቹ የብድር አቅርቦት በመፍጠር ረገድ ማህበሩ እያሳየ ያለው መነቃቃት፣ በጥናት ደረጃ የሚነገረውን የህብረት ሥራ ሚና በተግባር ያረጋገጠ ነው። ትጉ ማህበር የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ አቅም ለመገንባትና የኢኮኖሚ ጥግግት ለመፍጠር የያዘው ቁርጠኝነት፣ የህብረት ሥራ ማህበራት እንዴት የለውጥ ሞተር መሆን እንደሚችሉ ፍጹም ማሳያ ሆኗል።

​ይህ ስኬት ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን፣ ተግዳሮቶችን አስቀድሞ በመመልከትና መፍትሔ በመቅረጽ የተገኘ ነው። ማህበሩ የዘመኑን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አስፈላጊነት በጥልቀት በመረዳት፣ በባህላዊ አሰራር ላይ የሚነሱትን ጥናታዊ ስጋቶች ቀልብሷል። የአባላትን መረጃ ጥራት ከማሻሻል ጀምሮ የሞባይል ባንኪንግ እና የኮር ባንኪንግ መተግበሪያዎችን ወደ ስራ ለማስገባት ያደረገው ዝግጅት፣ ማህበሩ የቴክኖሎጂን ፋይዳ ምን ያህል በአግባቡ እንደተረዳ ያሳያል። ይህ ዓይነቱ ስትራቴጂካዊ እርምጃ የአሰራር ግልጽነትን የሚያረጋግጥ፣ የአባላትን አመኔታ የሚያጎለብትና ማህበሩን በፋይናንስ ዘርፉ ተወዳዳሪና ቀዳሚ የሚያደርግ የጥናትና ምርምር ምክረ-ሀሳቦችን ያካተተ ተግባር ነው።

​የማንኛውም ተቋም ስኬትና ውድቀት የሚወሰነው በዋናነት መሪው በሚከተለው መርህና አቅጣጫ ነው። የትጉ አመራር ይህንን የህብረት ሥራ ጥልቅ ፋይዳና ሳይንሳዊ ሚና ጠንቅቀው የተረዱ፣ ሰፊ የትምህርትና የልምድ ዝግጅት ያላቸው መሪ በመሆናቸው ማህበሩን በዕውቀት ላይ በተመሰረተ መንገድ እየመሩት ይገኛሉ። ይህንን የላቀ የጋራ ራዕይና የጥናት ውጤት ተገንዝበው ሌት ተቀን የሚተጉ የቦርድ አባላት፣ የሥራ አመራር ኮሚቴዎችና መላው ሠራተኞች መኖራቸው ደግሞ ለተቋሙ ልዩ ጥንካሬና ግስጋሴ ሆኗል። አመራሩና ሠራተኞቹ በአንድ ልብ፣ በአንድ ራዕይና በተመሳሳይ የባለቤትነት ስሜት መጓዛቸው ተቋማዊ ትስስሩን ፍጹም ጠንካራና የማይበገረ ያደርገዋል።

​ይህንን ሳይንሳዊ እውነትና ዘመናዊ አሰራር ተረድቶ ሌት ተቀን የሚተጋ አመራርና ሠራተኛ ባለበት ሁኔታ፣ የትጉ ማህበር ቀጣይ ጉዞ ወደ ላቀና ይበልጥ አስደማሚ ወደሆነ የስኬት ማማ መሸጋገሩ የማይቀሬ ሀቅ ነው። የጋራ ራዕይ፣ ዕውቀት-መር መሪነትና የሠራተኞች የነቃ ተሳትፎ በተቀናጁበት በዚህ መድረክ ላይ፣ ማህበሩ አባላቱን ወደ ተሻለ ብልጽግና እንደሚያሸጋግር ሙሉ እምነት አለ።

ማህበሩ የጀመራቸውን ዘመናዊ የዲጂታል አሰራሮች
አጠናክሮ በመቀጠል፣ ለቀጣይ ትውልድ የሚተርፍ ጠንካራ የፋይናንስ ተቋም ሆኖ ይቀጥላል።

ጉዟችን የዕድገት፣ ውጤታችን ደግሞ የላቀ ብልጽግና ይሆናል!

19/06/2026

ትጉ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር አሰራሩን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማዘመን ላይ ይገኛል

​ሚዛን አማን - ሰኔ 2018 ዓ.ም

​በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ ሚዛን አማን ከተማ የሚገኘው "ትጉ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር" አጠቃላይ የአሰራር ስርዓቱን በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አማራጮች በማደራጀት ላይ ይገኛል። ማህበሩ የፋይናንስ አገልግሎቱን ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ተደራሽ ለማድረግ በኮር ባንኪንግ (Core Banking) ቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረጉ ሥሰራ መቆየቱ ይታወሳል።

​የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግዛው ጋግያብ እንደገለጹት፤ ማህበሩ የደንበኞችን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ በዘመናዊ አፕሊኬሽን (Application) ጭምር በመታገዝ ሁሉም የፋይናንስ ስራዎች በቴክኖሎጂ እንዲመሩ ታቅዶ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነው። አቶ ግዛው አክለውም፣ “የቴክኖሎጂ ሽግግሩ ትጉ ማህበርን የአገልግሎት አሰጣጥ ከባህላዊ አሰራር ወደ ዲጂታል ስነ-ምህዳር ያሸጋገረ ነው፤ የዛሬው የቴክኖሎጂ ስኬትም የዚሁ ስትራቴጂያዊ እቅዳችን ውጤት በመሆኑ ደስታችን ወደር የለውም” ብለዋል።

​ይህ የቴክኖሎጂ ለውጥ አባላት በአካል ሳይመላለሱ፣ ባሉበት ቦታ ሆነው የቁጠባ እና የብድር አገልግሎቶችን በስልካቸው እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ ለአባላቱ ብሎም ለአካባብው የፋይናንስ ዘርፍ እድገትም አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑ ተገልጿል። ማህበሩ በቀጣይም የቴክኖሎጂ አቅሙን በማጠናከር እና የሳይበር ደህንነትን በመጠበቅ፣ የህብረተሰቡን አመኔታ በላቀ ደረጃ ለማቆየት እንደሚሰራ አስታውቋል።

ትጉ የትውልዱ ተስፋ!

19/06/2026
15/06/2026
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! 🇪🇹​የብልፅግና ጉዟችንን ለማስቀጠል፣ ለነገዋ የተሟላች ኢትዮጵያ ዛሬም በጋራ እንቁም!​መንገዳችን፦ መደመር!​ምልክታችን፦ የስንዴ ነዶ (ምርታማነትና አንድነት...
12/02/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! 🇪🇹
​የብልፅግና ጉዟችንን ለማስቀጠል፣ ለነገዋ የተሟላች ኢትዮጵያ ዛሬም በጋራ እንቁም!
​መንገዳችን፦ መደመር!
​ምልክታችን፦ የስንዴ ነዶ (ምርታማነትና አንድነት)!
​መዳረሻችን፦ የብልፅግና ተምሳሌታዊት ሀገር!
​የጋራ ብልፅግናችንን እውን ለማድረግ፣ የግንቦት 24 ምርጫ ምርጫዎ ብልፅግና ይሁን!
​ #ብልፅግናንይምረጡ #ምርጫ2018 #መደመር #የስንዴነዶ

🌿 ጎደሬ፦ የቤንች ምድር "የመጠባበቂያ ባንክ" እና የጥንካሬ ምስጢር!በለምለሟ የቤንች ሸኮ ምድር፣ ከቤት ጓሮ እስከ ሰፊው ማሳ የአረንጓዴው ንጉስ ጎደሬ ነው። ለቤንች ህዝብ ጎደሬ ዝም ብሎ ...
11/02/2026

🌿 ጎደሬ፦ የቤንች ምድር "የመጠባበቂያ ባንክ" እና የጥንካሬ ምስጢር!

በለምለሟ የቤንች ሸኮ ምድር፣ ከቤት ጓሮ እስከ ሰፊው ማሳ የአረንጓዴው ንጉስ ጎደሬ ነው። ለቤንች ህዝብ ጎደሬ ዝም ብሎ ምግብ አይደለም፤ የህልውና ዋስትና እና የታሪክ መገለጫ እንጂ!
ለምን ጎደሬ ለቤንች ህዝብ ልዩ ነው?
* 🛡️ አስተማማኝ ጋሻ፦ ድርቅም ይሁን ከባድ ዝናብ ጎደሬን አይበግረውም። አፈር ውስጥ ተደብቆ መከራን የሚያልፍ፣ ረሃብ ሲመጣ ደግሞ ቤተሰብን የሚታደግ "የመጠባበቂያ ባንክ" ነው።
* 💰 የኢኮኖሚ ምሶሶ፦ ልጆችን ለማስተማርና የኑሮ መሰረትን ለማደላደል ገበሬው የሚታመንበት የገቢ ምንጭ ነው።
* 💪 የጥንካሬ ምንጭ፦ ለከባድ ስራ ብርታት የሚሰጥ፣ በማዕድናት የበለፀገ የጤና ቁልፍ ነው።
ሳይንስ ስለ ጎደሬ ምን ይላል? 🔬
* አስፋው (2016)፦ ጎደሬ የቤንች ህዝብ የማንነት መገለጫና ባህላዊ ሃብት መሆኑን አረጋግጠዋል።
* ታደሰ (2018)፦ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም "የጽናት ተምሳሌት" ሰብል መሆኑን መስክረዋል።
* CSA ሪፖርት፦ በአካባቢው ኢኮኖሚ ውስጥ አንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝ ያሳያል።
* ወንድሙ (2020)፦ በውስጡ የያዘው ንጥረ-ነገር ለብርቱ ማህበረሰብ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ገልጠዋል።
ባጠቃላይ፣ ጎደሬ የቤንች ህዝብ ትላንት፣ ዛሬና ነገ ነው! 💚🌱
#ጎደሬ #ቤንች

ኢትዮጵያ ደግሳለች !የምድራችን ረዥሙ ወንዝ ዓባይ በኢትዮጲያውያን ያበረ ክንድ  ለጋስነቱ ለእናቱ ሆኗል።እናም ኢትዮጲያ ደስታ ላይ ናት ።ኢትዮጲያ የቁጭት እና ትካዜ ገጿን በመጨረሻው ሳቅ ተ...
24/08/2025

ኢትዮጵያ ደግሳለች !

የምድራችን ረዥሙ ወንዝ ዓባይ በኢትዮጲያውያን ያበረ ክንድ ለጋስነቱ ለእናቱ ሆኗል።

እናም ኢትዮጲያ ደስታ ላይ ናት ።ኢትዮጲያ የቁጭት እና ትካዜ ገጿን በመጨረሻው ሳቅ ተክታለች ።

የግጭት እና ጦርነት ፣ የረሃብና የተስፋ ቢስነት ሽንቁሯን ለማስፋት ለሚደክሙ ድግሱ መርዶ ቢሆናቸው እንጂ ድንኳን ሰባሪ ይሉት አይነት ወዳጅ መስሎ ለመታየትም ብርታቱ የላቸውም ።

''ብነካው ተነኩ አንቀጠቀጣቸው'' ያለችው የድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ትንቢት በድግሱ ዋዜማም አለቀቃቸውም ።

ሆኖም ለወዳጅም ለጠላትም ኢትዮጲያ ደግሳለች ። ይህ ድግስ የሰላም እና የልማት ነው ።

ለጥቁር ህዝቦች የነጻነት ፀሀይን ፈንጥቃ ፤ ቀኝ ገዥዎችን ወደ ምስራቅ ተመልከቱ ያስባለችው ኢትዮጲያ ፣ ዛሬም ግዙፉን በራስ የመቆም የሚዳስሰው የመቻል ቅርስን ሀቁን እና እውነቱን እንዲውጥ የሚያስችለውን ህዳሴ ግድብን ልትመርቅ ነው ።

አሸናፊነትን ፣ ጀምሮ መጨረስን ፣ በትውልድ ቅብብል የሀገር የዘመናት ህልምን ማሳካትን ፣ ሀገር በጸና የጋራ ሀብቷ በጥረት እና ትግል መጽናቱን ለድግሷ ታዳሚዎች አቅርባለች ።

እናም እጅ ለእጅ ተያይዘው ምድር እስክታረግድ የስኬትን ከፍታ የዘመናት ተረት ተረትን በመቀየር የሚጋሩት ነው ። በጉባ በረሃ ከ14 አመት በፊት መጀመሩ ሲበሰር የደስታ ሲቃ ያለቀሱ ዛሬ የሀሴት ዳንኪራን የሚረግጡበት ከፍታቸው ነው ።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ''ቀደምት ኢትዮጲያውያን ወደ ነበሩበት የአለም የስልጣኔ ጠርዝ ለመድረስ የህዳሴ መንገድ ጀምረዋል'' ያሉትን በአታካች ድርድር የድርሻቸውን የተወጡትን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን የኋልዮች ላስታወሰ የቁርጠኝነት ሀውልት ሆኖ ፤ ''ተስፋ ሳይሆን ሪቫን እንቆርጣለን ''ባሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፍጻሜው ሲበሰር ባለ ድልም ፣ ባለ እድልም የሆነው ትውልድ በኢትዮጲያ ድግስ መፈንጠዙ የሚጠበቅ ነው ።

የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጠናቀቅ ብስራትን የኔ ግድብ ነው ።

IT’S my dam ! የጋራ አቋማችንን ሲያዩ ያልነቁ ፣ ዛሬም 'ድር ቢያብር አንበሳ ያስር' ብሂላችን ትርጉሙ በገቢር ጉባ ላይ ቢገለጥ ለተምታታባቸው የኢትዮጲያ ብሄራዊ ፕሮጀክት ድል ፣ የቅዥት ምናብ ውስጥ እያመላለሳቸው ይመስላል ።

የምናብ አድማሳቸው ወሰን የፈረንጆቹ 1929 እና 1959 የሚል የቀኝ ግዛት ውል ላይ ቢጸናም የኢትዮጲያን የተጨበጠ ህልም ግን በወል ሀብታቸው ፤ የወል ታሪክ እያስከተባቸው ይገኛል።

ሰሞነኛው የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን ጨምሮ ያካለለው የዲፕሎማቶቻቸው ሩጫ በባከነ ሰአትም ቢሆን በቀኝ ግዛት ውሎች ትዝታን አድምጡልን ካልሆነ በቀር ፤ አባይ ሰም እና ወርቅ ለሆነባቸው ኢትዮጲያውያን 'እንዘጭ እንቦጭ 'እስከመቼ እንዲሉ ቢያደርጋቸው እንጂ ከድግሱ ደፋ ቀና ሸብረክ አያደርጋቸውም ።

በርግጥ የደስታውን ጣሪያ በፕሮፓጋንዳ ጥላ ውስጥ ሸፍኖ አንዳች ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ መላላጥ እና መጋጋጥ መሆኑን እርቃኑን የሚታይ ክሹፍ ዲፕሎማሲ ነው ።

እናማ ይህ ድግስ የወንዝ ተገድቦ ሀይል ማመንጨት ብቻም አይደለም ።ይህን ደስታ ከመዳፋችን ፈልቅቆ ለማውጣት ለሚጥሩ የሚነግራቸውም ጠንካራ መልእክት አለው ።

የአድዋ ድላችንን - ለመደሰት 7 አመት ቅድመ - አያቶቻችን ጠብቀዋል ።

እዚህ ጋር 'የትርክት እዳና በረከት ' በተሰኘውን የሙአዝ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መጽሃፍን እንግለጥ -

''መጀመሪያው የአድዋ ድል በአል የተከበረው ጦርነቱ በተካሄደ በሰባተኛው አመት በ1895 ዓ.ም ነው ። በአሉም ሲከበር የትእቢትና የጥጋብ እንዳይሆን ጥንቃቄ ተደርጓል ። እግዚአብሄርን ለማመስገን መሆኑም ተገልጧል ።በዚህ ክብረ በአል ላይ ያልተሳፈ የኢትዮጲያ የህዝብ አይነት አልነበረም ። ''

ስለዚህም ድላችንን በደስታ እንዳንዋሃድበት ፣ ግጭት እና ጦርነት ያከሰመ መልካችንን እንዳናፈካ የአሸናፊነት ወኔያችን ከጅግጅጋ ሞያሌ ፣ ከጋምቤላ መቀሌ ከጎንደር እስከ ባሌ በአንድ ድምጽ እንዳይስተጋባ አለም ቢቀያየርም ቅሉ በታሪካዊ ጠላትነት የቆሙ እዛው በተውናቸው የቀኝ ግዛት መንደር ናቸው ።

ሆኖም ኢትዮጲያውያን የህዳሴ ግድብ ለልጆቻቸው የአሸናፊነት ልእልና የሚያወርሱበት ጥሪታቸው ነውና ስኬታቸውን ይደሰቱበታል ፤ ይፈነጥዙበታል ፤ ይደልቁበታል ፤ ይንቀባረሩበታልም ።

የቅርብ አመታት የጋራ ደስታችን በአትሌቶቻችን ወርቆች ፣ ከ31 አመት በኋላ በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ፣ እንዳሻን አፍሪካ ዋንጫ የሄድንበት የታሪክ እጥፋቶች በጋራ ስቀናል ።

ደግሞ ወርሃ ሰኔ በ16ተኛው ቀን 2010 ዓ.ም የፖለቲካ ለውጥ እንዲሁ የኢትዮጲያን ድግስ በጋራ ተቀምጠን ፈገግ ማለታችንን አንረሳም ።

እናማ አሁንም እንደ አደይ አበባ ቀለማት የኢትዮጲያ የተስፋ ፍንጣቂዎች ስፍራቸውን ይዘዋል ።

ምክንያቱም ለዳግማዊ አድዋ ኢትዮጲያ ደግሳለች ።

አልጀዚራ ከ14 አመት በፊት Struggle over the nile የተሰኘ ተከታታይ ሶስት ዘጋቢ ፊልም የአባይ ጂኦ ፖለቲካ ታሪካዊ እሰጣ ገባዎችን ወደ ኋላም ወደፊትም ሊዳስስ ሞክሮ ነበር ።

ይህም የጋራ ክሮቻችንን ማጽኛ የመሰረተ ድንጋይ ከተቀመጠ ሁለት ወራቶች በኋላ እንደማለት ነው ። በጊዜው ለናይል ኢኒሼቲቭ ድርድሮች ለጋራ ራእይ ፣ የጋራ ወንዛችንን እንጠቀም ላሉት አስር የወንዙ የበይ ተመልካች ሀገራት ይሰጣቸው የነበረው ምላሽ ፊት ከመንሳት አለመተናነሱን ያስመለክተናል ።

በወቅቱ የኬኒያ የውሃ ዘርፍ የስራ ሀላፊ ጆን ኒዮሮ አባይን በጋራ በስምምነት ከመጠቀም ውጭ ምንም አማራጭ እንደሌለ ተናግሯል ። ኢትዮጵያ እንደጀመረችው ግድብ ሁሉ ሌሎች የተፋሰሱ ሀገራትም አይደግሙትም ማለት አይቻልም ብለው ነበር ።

ፍትሃዊነት ያኔም በመዝገበ ቃላቷ ላይ የሌለ የምትመስለው ሀገር ዛሬም እዛው ነች ።የናይል ኢኒሼቲቭ ግን ወደ ኮሚሽን አድጓል ። ጥርስ ወደ ማውጣትም እየተንደረደረ ይገኛል ።

ወንዙን በታንኳ ለመሸራሸር በምስል ለማህደራቸው ማስጌጫ ያደረጉት በርካታ የተፋሰሱ አባል ሀገራት ግን የራእይ መጋራት ከጉባ የህዳሴ ግድብ ምረቃት ድግስ ጠንካራ መልእክት እንደሚሰድላቸው አይጠረጠርም ።

ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ''የማይደርቅ የማይነጥፍ ፣ ለዘመን የጸና ።'' እንዳለችው ሁሉ ባለግርማ ሞገሱ አባይ ፣ ኢትዮጲያን ግርማ አልብሶ ለህዳሴውም ተደግሷል ።

ጠሪ አክባሪ ነው እንግዶቿም ይጠበቃሉ ።

"sile hulumi negeri igizī’ābiḥērini āmesiginu..."
05/06/2025

"sile hulumi negeri igizī’ābiḥērini āmesiginu..."

Address

Mizan Teferi

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gizaw Gagiabe T. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share