የሸኮ ወረዳ ፍ/ቤት /sheko werda primary court/

የሸኮ ወረዳ ፍ/ቤት /sheko werda primary court/ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሸኮ ወረዳ ፍ/ቤት /sheko werda primary court/, Post office, sheko, Mizan Teferi.

06/04/2024
14/09/2023

የከተማ መሬትና ቤት ይዞታ ስመ-ንብረት ዝውውር እንዴት ይፈፀማል
በስመ ንብረት ዝውውር ወቅት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች የከተማ ቦታን
በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 33 ንዑስ አንቀፅ 2
አንፃር ሲታይ
1.1. የከተማ ቤትና ይዞታ ስመ-ንብረት ዝውውር ስለመፈጸም የሚከተሉት
ማስረጃዎች/ሰነዶች ሲሟሉ የስመ ንብረት ዝውውር የሚፈጸም ይሆናል፤
1) ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት/ካርታ፣
2) ጸድቆ የተሰጠ የግንባታ ፕላን፣ የስራ ዝርዝር ግምት ወይም የጸደቀ የነባር
ግንባታ ፕላን፣
3) ጸድቆ በተሰጠው የግንባታ ፕላን መሰረት ስለመገንባቱ እና ግንባታው ያለበት
ደረጃ የተረጋገጠበት ማስረጃ/50% እና በላይ/፤
4) ውዝፍ የሊዝ/ኪራይ ዕዳ የሌለበት ስለመሆኑ የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ
ወይም ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳውን ገዥው ለመክፈል በፊርማ ያረጋገጠበት
የስምምነት ደብዳቤ ፣
5) በንብረቱ ላይ የባንክ እዳ/የፍ/ቤት ዕግድ የሌለበት ስለመሆኑ ማረጋገጫ
ሲቀርብ፣
6) የቤትና ይዞታ ስም ዝውውር ጥያቄው የቀረበው በህግ ባለመብት/በውርስ/
በፍርድ አፈጻጸም ወይም በውክልና ከሆነ ይህንኑ የሚገልጽ ማስረጃ፤
7) በግለሰቦች ግዥና ሽያጭ ወይም ስጦታ ስምምነት ከሆነ በዉልና ማስረጃ
በአካል ቀርቦ በእማኞች የተፈረመ የስምምነት የውል ማስረጃ ሲቀርብ፣
1.2. በሽያጭ/በስጦታ የሚተላለፍ ቤትና ይዞታ ስም-ዝውውር መሟላት
ያለባቸው መስፈርቶች፣
1) ግንባታው በዋስትና ያልተያዘ እንዲሁም እዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ
ወይም እዳው በሚመለከተው አካል በደብዳቤ መነሳቱ ሲረጋገጥ፣
2) የቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋገጥና በፍትህ
ወይም በመሪ ማዘጋጃ ቤት ፊት ቀርቦ ሲጸድቅ፣
3) ግንባታው ጸድቆ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት 50 በመቶና በላይ የተሰራ
መሆኑ በባለሙያ ተረጋግጦ ሲቀርብ፣
4) በይዞታው ላይ ውዝፍ የቦታ ኪራይ የሌለበት ስለመሆኑ ወይም ውዝፍ የቦታ
ኪራይ ክፍያ አጠናቆ የከፈለ ስለመሆኑ የቀረበ ክፍያ ደረሰኝ ማረጃ ሲቀርብ፣
5) የአገልግሎትና የገቢዎች ክፍያ በቤቱ ግምት መሰረት ስለመከፈሉ ሲረጋገጥ፣
# ዝውውሩ የሚፈፀመው # በሊዝ በተገኘ ይዞታና ግንባታ ላይ ከሆነ
1) የሊዝ ይዞታ ባለቤትነት ኦሪጅናል ካርታና ውል ሲቀርብ፣
2) በሊዝ ውል መሰረት ክፍያው የተጠናቀቀና ሌሎች ግዴታዎቹን የተወጣ
መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም የሊዝ እዳው ያልተጠናቀቀ ከሆነ ስም የሚዞርለት ወገን
እዳውን ለመክፈል እና ነባሩን የሊዝ ውል ግዴታዎች የተቀበለ ስለመሆኑ
ከከተማው በጽሁፍና በፊርማ አረጋግጦ ሲያቀርብ፣
3) በሊዝ የተገዛን የመሬት ይዞታ ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ በቅድሚያ በገባው
የሊዝ ውል መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የሚፈለገውን የግንባታ ደረጃ
ያሟላ መሆኑ ወይም የግንባታ ፈቃድ የጊዜ ገደብ ያላለፈ ወይም የግንባታ
ማራዘሚያ የተፈቀደለት መሆኑ ሲረጋጥ፣
4) የከተማ ቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋጥና
በዉልና ማስረጃ ቀርቦ ሲጸድቅ ይሆናል፡፡
1.3. በውርስ የተገኘ ይዞታና ቤት የባለቤትነት ስመ-ንብረት ዝውውር
አፈፃፀም፣
(ሀ) በውርስ የተላለፈ # ነባር_ይዞታ ዝውውር ለመፈፀም መሟላት ያለባቸው፡-
1) የሚዛወረው የመሬት ይዞታ ወይም ቤት ህጋ የባለቤትነት ማስረጃ/ካርታ
ሲኖረው፣
2) ወራሾች የውርስ ባለመብትነትን የሚያረጋግጥ የፍርድ ቤት ውሳኔ ማስረጃ
ሲያቀርቡ፣
3) ወራሾች በውርስ ያገኙትን ይዞታ ወይም ቤት በየግላቸው የባለቤትነት ማስረጃ
ለመያዝ ሲፈልጉ ለእያንዳንዳቸው ድርሻ መጠን በፍ/ቤት የፀደቀ ማስረጃ
ሲያቀርቡ ወይም የሁሉም ወራሾች የጋራ ስምምነት በውል አፅዳቂ አካል ጸድቆሲቀ

Address

Sheko
Mizan Teferi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሸኮ ወረዳ ፍ/ቤት /sheko werda primary court/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category