Mizan Aman city Admin Prosperity Party /የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ

  • Home
  • Ethiopia
  • Mizan Teferi
  • Mizan Aman city Admin Prosperity Party /የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ

Mizan Aman city Admin Prosperity Party /የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ Media

የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ ሰለሞን ሌዊ (ኢንጅነር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።በዙህ መሰረት1. አቶ አምና ታደሰ : የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፕላን ጽ/ቤት ኃላፊ2. አቶ ሰለሞን ወ...
17/10/2025

የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ ሰለሞን ሌዊ (ኢንጅነር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።
በዙህ መሰረት

1. አቶ አምና ታደሰ : የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፕላን ጽ/ቤት ኃላፊ
2. አቶ ሰለሞን ወንጌል : የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ
3. አቶ ደጀኔ በቀለ : የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ
4. አቶ ዘሪሁን መንግስቱ : የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ
5. ወ/ሮ ምርታለም ደሳለኝ : የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ
6. አቶ ዘውዴ ሽዱ : የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ም/ኃላፊ
7. አቶ ኤልያስ ታምሩ ፦ የህብረት ቀበሌ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ
8. ወ/ሪት ገነት ናካ፦ የአማን ቀበሌ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ
9. ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ ፦ የዕድገት ቀበሌ ብልጽግና ፓርቲ ኃለፊ

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር በአጠቃላይ 15 አመራሮችን ከኃላፊነት የማንሳት ፣ የማሸጋሸግና በአዲስ መልክ የማደራጀት ስራ ተሰርቷል ሲሉ የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት...
16/10/2025

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር በአጠቃላይ 15 አመራሮችን ከኃላፊነት የማንሳት ፣ የማሸጋሸግና በአዲስ መልክ የማደራጀት ስራ ተሰርቷል ሲሉ የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ጊስካር ገለፁ።

የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ጊስካር ከተማዊ የአመራር ምዘናና ግምገማን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሃላፊው በመግለጫቸው በብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሠረት ከዞን እስከ ታችኛው መዋቅር የሚገኙ አመራሮች የግምገማና የምዘና መድረክ በጥብቅ ዲስፕሊን ሲመራ መቆየቱን ገልጸዋል።

ግምገማው የ2017 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ የ2018 የፓርቲና የመንግስት ድርብና ድርብርብ ተልዕኮዎችን ማስፈጸምና መፈጸም የሚችሉ አመራሮችን ለመፍጠር ከወትሮው በተለየ መልኩ የከተማውን ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበ ጥልቀት ያለው ሰነድ በማዘጋጀት ችግሮችንና ጥንካሬዎችን በሚዛኑ በማሳየት የአመራር ግምገማና ምዘና መካሄዱን ተናግረዋል።

ግምገማውን መነሻ በማድረግ ተልዕኮዎችን በቁርጠኝነት መፈጸምና ማስፈጸም የሚችል የአመራር ስምሪት በአዲስ መልክ ማዋቅር መቻሉን አቶ ተስፋዬ አክለው ገልጸዋል።

በዚህም በአጠቃላይ በከተማ አስተዳደሩ በሁሉም መዋቅር በተካሄደ የአመራር ምዘናና ግምገማ መሰረት በማድረግ ወንድ 6 ሴት የለም በድምሩ 6 አመራሮች ከኃላፊነተቻው የተነሱ ሲሆን በሽግሽግ ወንድ 2 ሴት 1 በድምሩ 3፣ በአዲስ መልክ ወደ አመራርነት የተቀላቀሉ ወንድ 4 ሴት 2 ድምር 6 በአጠቃላይ 15 አመራር ከኃላፊነት የማንሳት ፣ የማሸጋሸግና በአዲስ መልክ ወደ መንግስትና ፓርቲ መዋቅር የመቀላቀል ስራዎች መሰራቱን አቶ ተስፋዬ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

የአመራር ስምሪቱ የአመራርን ውጤታማነት ፣ ስነ ምግባርን እና ዝግጁነትን መሠረት በማድረግ በጥልቀት የተገመመገመ መሆኑ ተመላክቷል።

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የደመራ እና የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።ሚዛን አማን መስከረም 15/2...
26/09/2025

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የደመራ እና የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሚዛን አማን መስከረም 15/2018 ዓ/ም የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ ኢ/ር ሰለሞን ሌዊ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የከተማችን ነዋሪዎች የፍቅር፣ የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍ እና የመከባበር እሴቶቻችን ማሳያ ለሆነው የደመራና የመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

ከንቲባው በመልዕክታቸው፣ መስቀል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ ያለምንም ልዩነት እስከ መስቀል እና ሞት ድረስ ራሱን አሳልፎ የሰጠበት ተወዳዳሪ የማይገኝለት ፍቅር መገለጫ ነው ብለዋል።

እኛም በመስቀሉ ላይ የተገለጠው የክርስቶስ የቤዛነት፣ የፍቅር እና እውነት መጠን፣ እርስ በእርስ በመዋደድና በፍቅር፣ በአንድነት በመኖር እንደ ደመራ አሰባሳቢ ጥበብን እየገበየን፣ በዓመት አንዴ ደመራን ስናከብር ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ በተግባር እውነተኛ የመስቀሉ ወዳጆች መሆናችን በፍቅራችን እየገለጽን በአሉን ማክበርና መኖር ይገባናል ሲሉም አክለዋል።

ከንቲባው በመልዕክታቸው የደመራና መስቀል በዓል በመላ ሀገሪቱ የሚከበር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በህዝቦች መካከል የአብሮነት የመኖር እሴቶችን የሚያጎለብት እንዲሁም የአንድነትና የመቻቻል መንፈስን የሚያጠናክርበት በመሆኑ በዓሉ ለሰላምና ለአንድነት መጽናት ከመቼውም ጊዜ በላይ የምንተጋበትና ትስስራችንን የበለጠ የምናፀናበት በዓል እንዲሆንም መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ ብለዋል ፡፡

መስቀሉ ጥላቻ የተወገደበትና ፍቅርና አንድነት የሰፈነበት በመሆኑ ምዕመኑ በዓሉን ሰላሙንና አብሮነቱን በሚያጠናከር መልኩ ማክበር እንዳለበት ተናግረዋል።

የደመራና የመስቀል በዓል ሲከበር ከመስቀሉ አብነት የተገኘውን ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት በማጠናከር ሊሆን ይገባል ሲሉም ከንቲባው በመልዕክታቸው ጠቁመዋል።

የ2018 ዓ/ም የደመራና መስቀል በአልን ስናከብር እንደ ደመራ ችቦ ተሰናስለን የከተማችንን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የምናስቀጥልበት ሊሆን ይገባል።

ሁላችንም ለከተማችን እና ለሀገራችን ሰላም እና ልማት ደመራውን እንደምር ያሉት ከንቲባው፣ በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የጤና እና የብልጽግና እንዲሆን ተመኝተዋል።

በድጋሚ እንኳን ለደመራና ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ

የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ

እንኳን 2018 ዓ.ም የደመራ እና የመሰቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! አቶ ተስፋዬ ጊስካርየሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ...
26/09/2025

እንኳን 2018 ዓ.ም የደመራ እና የመሰቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! አቶ ተስፋዬ ጊስካር

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ጊስካር የደመራና የመስቀል በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሃላፊው በመልዕክታቸው የመስቀል በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ክብር የሚሰጠውና በታላቅ ድምቀት የሚከበር ልዩ በዓል ነው ብለዋል።

የደመራና መስቀል በአል በዩኒስኮ የተመዘገበ ታላቅ በአል መሆኑን የገለፁት አቶ ተስፋዬ በመስከረም ወር አጋማሽ በየዓመቱ የሚከበር ታላቅ ሃይማኖታዊ በአል ነው ብለዋል።

መሰቀል ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ሁሉ ያለምንም ልዩነት እስከ መሰቀልና ሞት ድረስ እራሱን አሳልፎ የሰጠበት ተወዳዳሪ የማይገኝለት ፍቅር መገለጫ ነው ሲሉም በመልዕክታቸው አስቀምጠዋል፡፡

እኛም በመስቀሉ ላይ የተገለጠው የክርስቶስ የቤዛነት፣ የፍቅር እና እውነት መጠን ፣ እርስ በእርስ በመዋደድ በመትጋት ከማይረቡ ጉዳዮች፣ እርስ በእርሳችን ከሚጋጩና ከሚያጠራጥሩን ሃሳቦችና ድርጊቶች ርቀን በፍቅር፣ በአንድነት በመኖር እንደ ደመራ አሰባሳቢ ጥበብን እየገበየን ፣ በዓመት አንዴ ደመራን ስናከብር ብቻ ሳይሆን በእለት እለት ህይወታችን ውስጥ በተግባር እውነተኛ የመስቀሉ ወዳጆች መሆናችን በፍቅራችን እየገለፅን መኖር ይገባናል ብለዋል፡፡

ስለሆነም የመስቀል በዓል ከሃይማኖታዊ ስረዓት በተጨማሪ በሀገራችን እሴት በመሆን ከማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል በዩኒስኮ የተመዘገበ በዓል ሲሆን የህዝቦችን አንድነት፣አብሮነት እና ቤተሰባዊ ፍቅርን የሚያጠናክር በመላው ሀገራችን ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት የሚከበር ትልቅ በዓል ነው።

በዓሉን ስናከብር የሀገራችንን የመደጋገፍ እሴት በጠበቀ መልኩ በመተሳሰብ አብሮ በመብላትና በመረዳዳት ሊሆን እንደሚገባም በመልዕክታቸው አካተዋል።

በድጋሚ እንኳን 2018 ዓ.ም የደመራ እና የመሰቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን እያልኩ በዓሉ የፍቅር ፣ የሰላም፣ የጤና እና የብልጽግና እንዲሆን እመኛለሁ።


አቶ ተስፋዬ ጊስካር
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ
መስከረም 16/2018 ዓ.ም

17/09/2025
የሚዛን አማን ከተማ ህዝብ በታላቁ ኢትዮጵያ  ህዳሴ ግድብ ገቢ አሰባሰብ ያሳየውን ህዝባዊ ተሳትፎ ግድቡ መጠናቀቁን ተከትሎ በነገው እለት በሚደረገው ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ ሊደግመው ይገባል። ኢ...
16/09/2025

የሚዛን አማን ከተማ ህዝብ በታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ገቢ አሰባሰብ ያሳየውን ህዝባዊ ተሳትፎ ግድቡ መጠናቀቁን ተከትሎ በነገው እለት በሚደረገው ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ ሊደግመው ይገባል። ኢ/ር ሰለሞን ሌዊ

ሚዛን አማን መስከረም 06/2018 ዓ/ም የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ተከትሎ እንደ ሃገር የድጋፍ ሰልፎች እየተደረጉ መሆኑን የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ ገልጸዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብዝሃ ዋና ከተማ በሆነችው የሚዛን አማን ከተማ በነገው እለት መስከረም 07/2018 ዓ/ም ከ200 ሺህ በላይ የከተማችን ነዋሪዎች የሚሳተፉበት ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ከንቲባው አክለው ገልጸዋል።

የድጋፍ ሰልፉን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ የሚዛን አማን ከተማ ህዝብ እንደ ሌሎች የሃገራችን ህዝቦች በግድቡ ግንባታ ወቅት ሀብት በማሰባሰብ ሰፊ ህዝባዊ ተሳትፎ ሲያደርግ እንደነበር ተናግረዋል።

ግድቡ ተጠናቆ በመመረቁ ለመላው የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ከንቲባው በነገው ህለት የሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ ሁሉም የከተማችን ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ደስታውን በአደባባይ የሚገልጽበት ነው ብለዋል።

በነገው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ለሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የገለጹት ከንቲባው ሰልፉ በሚዛን ዋናው አደባባይ እስከ ከፋ በርና ሃይስኩል መንገድ ዝግ ስለሚሆን ለተወሰኑ ሰአታት አሽከርካሪዎች ሌሎች የመንገድ አማራጮችን ሊጠቀሙ ይገባል ብለዋል።

ሰልፉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላት ስምሪት የተሰጠ ቢሆንም ማህበረሰቡ በተለይ ወጣቶች ሰልፉን በማስተባበር፣ ተሽከርካሪ በተፈቀደለት መንገድ እንዲሄድ በማድረግና አጠቃላይ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የጸጥታ ስራዎችን በመስራት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ አመራሮች፣ ባለሃብቶች፣ ፐብሊክ ሰርቫንቱ፣ ነጋዴዎችና በአጠቃላይ የከተማችን ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ከንቲባው ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በሚዛን አማን ከተማ እየተሰራ ያለውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጎበኙ።መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ሲ...
13/09/2025

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በሚዛን አማን ከተማ እየተሰራ ያለውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጎበኙ።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ሲጠናቀቅ የመንግስት አገልግሎትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያቀላጥፍ መሆኑም ተጠቅሷል ፡፡

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ውስጥ ያለው ድርሻ የላቀ ነው፡፡

ማዕከሉ ይኸንኑ እውን ለማድረግ በክልሉ ሚዛን አማን ከተማ ላይ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰራ ይገኛል ።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ግንባታዉ የደረሰበትን ደረጃ ምልከታ ለማድረግ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በሚዛን አማን ከተማ ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በስፍራው ተገኝተው በሰጡት አስተያየት የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ማስጀመር ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

የማዕከሉ ግንባታ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የህዝብና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ያዘምናልም ብለዋል።

የጠቅላይ ሚነስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ኢኒሼቲቭ አካል የሆነው ይህ የሚዛን አማን ማዕከል የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ የንግድና ኢንቬስትመንት ፣ የገቢ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል ስለመሆኑም ገልጸዋል።

ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የህዝብ ቅሬታዎችን ለመፍታት፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል እና ተጠያቂነትን ለማስፈን ያግዛልም ብለዋል።

ማዕከሉ የተቀናጀ አገልግሎት ለተገልጋዩ መስጠት የሚያስችል ትልቅ ውጤታማ ስራ መሆኑንም ገልጸው፤ ማዕከሉን በማደራጀት ወደ ስራ ማስገባቱ በሀገሪቱ የታለመውን ድጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ማዕከሉ ቅሬታ ይቀርብባቸው የነበሩ አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል በማስገባት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በማዕከሉ የቴሌኮሙኒኬሽን ፣የባንክ አገልግሎት ፣የፋይዳ መታወቂና የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ አገልግሎት እንደሚሰጥም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ።

ማዕከሉ በቅርቡ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የክትትልና ድጋፍ ስራው ይጠናከራልም ብለዋል።

በክልሉ የተጀመረው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በሌሎችም እንዲስፋፋ ይደረጋልም ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝታቸው የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ህንጻ ግንባታና የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልል፣የዞን እና የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

‎‎በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር  የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማው ለሚገኙ ለአቅመ ደካሞችና ለተቸገሩ  ከ550 በላይ ወገኖች  የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ተከናወነ።‎‎...
11/09/2025


‎በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማው ለሚገኙ ለአቅመ ደካሞችና ለተቸገሩ ከ550 በላይ ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ተከናወነ።

‎ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት እና የከተማ አስተዳደሩ ሴቶች ህፃናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ለአቅመ ደካሞችና ለችግር ለተጋለጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት መረሃ ግብር አከናውነዋል።

በሚዛን እና በአማን በሁለት ቦታዎች የተካሄደው ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም ከ550 በላይ አረጋውያንና የጎዳና ተዳዳሪዎችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉም ተመላክቷል።

‎ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ የበዓል ወቅቶችን ከአቅመ ደካሞችና ለችግር የተጋለጡ ወገኖች ጋር ማሳለፍ በዓል ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

‎ለችግር የተጋለጡ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመርዳት ተግባሩን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የገለጹት ከንቲባው ሌሎችም የመረዳዳት ባህልን በማጠናከር ሰብአዊ ተግባርን እንዲያከናውኑ ጥሪ አሰተላለፈዋል፡፡

የሙፍቲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ፣ ኦኤም ማተሚያ ቤትና አቶ ጴጥሮስ ሽፈራው ማዕድ በማጋራቱ ላይ ላበረከቱት አስተዋጾ ከንቲባው አመስግነዋል።

በአማን በተካሄደው የምገባ ፕሮግራም የተገኙት የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ጊስካር ለአረጋውያንና አቅመ ደካሞች ማዕድ ከማጋራት ባሻገር ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰና የኢኮኖሚ አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

‎የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት ለማ በበዓላት ይህ ተግባር ሲደረግ የመጣ ቢሆን አሁንም በየወቅቱ ከበዓላት ውጪ ለማድረክ ተጠናክሮ እየተሰራ እንዳለ አብራርተዋል።

‎በዕለቱ በሚዛን ከ300 እና በአማን ከ250 በላይ ለሚሆኑ አረጋዊያንና በጎዳና ላይ የሚገኙ ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ከ200 ሺህ ብር በላይ በማውጣት በዓሉን አሰመልክቶ የምሳ ግብዣ ተደርጎላቸዋል ተብሏል።

‎በማዕድ ማጋራቱ በችግር ውስጥ ሆነው ለሚማሩ የሙፍቲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል 12 ደርዘን ደብተር ሁለት ፓኮ ስክሪፕት ፣ ኦኤም ማተሚያ ቤት ቲሸርቶችን እንዲሁም አቶ ጴጥሮስ ሽፈራው ውሃ በማቅረብ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ወ/ሮ ትዕግስት ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የሚዛን አማን ከተማ ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ፣ የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ጊስካር፣ ምክትል ከንቲባና የገቢዎች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ታገል ወንድሙን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደርና የቀበሌ ዓመራሮች፣ የወጣቶችና ሴቶች ክንፍ አመራሮችና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተሳትፈዋል።

አዲሱ ዓመት አብሮነት እና ወንድማማችነትን በማጎልበት ለተሻለ ለውጥ የምንተጋበት ዓመታችን ነው ፦ የቤንች- ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃብታሙ ካፍትን።‎ሚዛን- አማን፦ መስከረም 1/2018...
11/09/2025

አዲሱ ዓመት አብሮነት እና ወንድማማችነትን በማጎልበት ለተሻለ ለውጥ የምንተጋበት ዓመታችን ነው ፦ የቤንች- ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃብታሙ ካፍትን።

ሚዛን- አማን፦ መስከረም 1/2018 ዓ.ም (ቤ.ሸ.ቴ)
የሚዛን- አማን ከተማ እና አከባቢዋ የወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት ሕብረት በጋራ በሚዛን አደባባይ አዲሱን ዓመት በተለያዩ መርሓ-ግብር አክብረዋል።

‎በበዓሉ ላይ መላው ሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ታድመዋል።

‎በመርሓ- ግብሩ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላላፉት የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃፍታሙ ካፍትን አዲሱ ዓመት 2018 ሀገራችን በርካታ ድሎችን ያስመዘገችበት እና በልማት ማማ ላይ የሆነችበት ብሎም ስኬት የተጎናፀፈችበት ልዩ ዓመት መሆኑን ተናግረዋል።

‎የዘንድሮው የዘመን መለወጫ በዓል የሁላችን አሻራ ያረፈበት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በተመረቀበት ማግስት የተከበረ በመሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

‎የሚዛን- አማን ከተማ ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ በበኩላቸው ለ2018 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደገለፁት የሚዛን- አማን ከተማ፤ የአንድነትና የመቻቻል ማሳያ የሠላም እና ብዝኃነትን ተምሳሌት መሆኗን ጠቁመዋል።

‎ኢኒጅነር ሰለሞን በመልዕክታቸው ሕዝበ ክርስትያኑ በአሉን ተደስተዉ ሲያከብር የታመሙትን በመጠየቅ የተራቡትን በማብላት እና የታረዙትን በማልበስ ልሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።

‎በአዲስ ዓመት ወደ ራዕይ ተስፋ እና ብልፅግና ጉዞ የምንቀላቀልበት ዓመት እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

‎የሚዛን- አማን አስተዳደር አብያተ- ክርስቲያናት ካውንስል ሰብሳቢ አቶ ዳዊት ገሞ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን የደህንነት ወንጌል ከማሰራጨት ባሻገር ከመንግሥት ጋር ጎን ለጎን በመሆን በመልካም አሥተዳደር፣ በልማት እና በሠላም ላይ በጋራ እንደሚሠሩም ጠቁመዋል።


‎ #ቤንች ሸኮ ቲቪ

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ጊስካር የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ። አቶ ተስፋዬ ባስ...
10/09/2025

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ጊስካር የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ።

አቶ ተስፋዬ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ አዲሱ ዓመት ጅማሬ ልዩ የሚያደርገው በህዝባችን የላብ፣ እንባ እና ደም ጠብታ የተገነባውን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባስመረቅንበት ማግስት መሆኑ ነው ብለዋል።

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅፈት ቤት ኃላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ አዲሱን ዓመት በይቅርታ እና ፍጹም ምህረት በማድረግ መሻገር አለብን በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘመኑ የሠላም፣ የመልካም እሴት ግንባታ፣ የብልጽግና፣ የፍስሀ፣ የመቻቻል፣ የበጎነት እና የፍቅር እመኛለሁ።

አዲሱ ዓመት ስናከብር የፓርቲያችን የሰው ተኮር መርህ በሆነው ችግረኞችን በመርዳት፣ ለጎዳና ተዳዳሪዎችን ማዕድ በማጋራት፣ የታመሙትን በመጠየቅ፣ በተለያያ ምክንያት ማህበራዊ እክል የገጠማቸውን በመደገፍ ፣ በአንድም በሌላ ማህበራዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች በማሰብ በይቅርታ እና አንዳችን የአንዳችንን በደል በመተው ፍጹም ምህረት በማድረግ መሻገር አለብን።

በአዲሱ ዓመት መላው የከተማችን ነዋሪዎች ከመንግስት ጎን በመሆን የብልጽግና ጎዳናውን በማስቀጠል የአንበሳውን ድርሻ የሚጫወትበት ዓመት ይሆን ዘንድ በመመኘት ነው።

መላው የከተማችን ነዋሪዎች የነበርንበትን ችግር ወደ ኋላ በመተው በሁሉም የልማት እና የመልካም እንዲሁም የፍትህ ስርዓት በተስተካከለ መንገድ የሚራመድበት የክፍታ ዘመንና የከተማ ግብርናችን በተሻለ መንገድ ወደ ላቀ ምርት እና ምርታማነት የሚቀየርበት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሽግግር ውጤታማ የሚሆንበት እና የፓርቲያችን ኢኒሼቲቭ የሆነውን የሌማት ትሩፈት ተግባራት አጠናክረን የምንቀጥልበ ዘመን እንዲሆን ጥሪ አቀርባለሁ።

በሁሉም የልማት አውታሮች የጀመርናቸው ስራዎች ውጤታማ የሚሆንበት፤ በማናቸውም ወገን በኩል መፈፀም እና ማለቅ የነበረባቸው አዳሪ ፕሮጀክቶችን እና በተግባር መንጠባጠብ የነበሩ ያላለቁ የቤት ስራዎችን ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው የልማቱ ባለቤት እና ባለመብት ለሆነው ህዝባችን የምናስረክብበት

በመጨረሻም መጪው ዘመን ለመላው የከተማ ነዋሪዎቻችን እና የሀገራችን ህዝቦች ሳንካዎች የተወገዱለት፣ ውጥኑ የተሳካለት፣ ትልቅ ተስፋ፣ ለውጥ፣ የብልጽግና፣ የመቻቻል፣ የመተባበር ፣ የፍቅር፣ የልማት፣ የይቅርታ፣ የምህረት ፣ የእውቀት ሽግግር የሚታይበት እንዲሆንልን እመኛለሁ።

እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን አደረሰን!

መልካም አዲስ ዓመት


ጳጉሜ 5/2017 ዓ/ም
ሚዛን-አማን

የሚዛን አማን ከተማ ከንቲቫ ኢንጂነር ሰለሞን ሌዊ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ  የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ሰለሞን ለዊ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት...
10/09/2025

የሚዛን አማን ከተማ ከንቲቫ ኢንጂነር ሰለሞን ሌዊ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ሰለሞን ለዊ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ። የመልካም ምኞት መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

እንኳን ለ2018 ዓ/ም አዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን! መጪው አዲስ የተለየ ጅማሬ የሚያደርገው በህዝባችን የላብ፣ እንባ እና ደም ጠብታ የተገነባውን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባስመረቅንበት ማግስት መሆኑ ነው

ሀገራች ኢትዮጵያ በራሷ የዘመን አቆጣጠር የምትመራና 13ወር ፅጋ ባለቤት መሆኗ ልዩ ያደርጋታል።
ዘመን አልፎ ዘመን ሊተካ፣ አሮጌ ምዕራፍ ተዘግቶ አዲስ ምዕራፍ ሊገለጥ፣ መጪውን ዘመን ልንቀበለው በምንዘጋጅበት በዛሬው የዋዜማ ምሽት ላይ ሆነን መጪውን አዲስ ዓመት በአዲስ ተስፋ ማስተናገዱ አይቀርም።

በ2017 ዓ/ም ዓመት ስናስብ ትውስታችን በብዙ መልካምና እኩይ አጋጣሚዎች ተሞልቶ እናገኘዋለን። በአንድ በኩል ዓመቱ ዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት ተከትሎ የሸቀጣች ዋጋ መጨመር እና በወባ ወረሽኝ የተፈተንበት።

በሌላ በኩል ደግሞ የወረስናቸውና ለዘመናት ሲንከባለሉ የወቆዩ የህዝባችንን መልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበሩትን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን በተወሰነ መልኩ ምላሽ እንዲያገኙ የተደረገበት። በተለይ ነባር የነበሩ መንገዶችን በገጠር ኮሪደር ፓኪጅ ህዝብን ባሣተፈ መልኩ የሰራንበት; አዳዲስ መንገድ ከፈታዎች; የነባር ጠጠር መንገድ ጥገናና ኮረት ማልበስ ሰራዎችን ተሰተዋል።

የጤና ሽፈንን ከማሣደግ አንፃር የዘመናት ጥያቄ የበረውን የአማን ጤና ጣቢያ ጥያቄ በአጭር ጊዜ መልስ የተሰጠበትና በከተማችን የመጀመሪያ የሆነውን የህዝብ መድሀኒት ቤት በመገንባና በግብዓት አደራጀቶ ወደ ስራ ማስገባት የተቻለበት የአዲስ ዓመት አዲስ ብስራት ለህዝባችን ያበሰርንበት ነው።

የከተማን ግብርን ከማዘን አንፃር የሌማት ትሩፋት ተግባራት ላይ ትኩረት በመስጠት እና የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ በመሰብ ዘመናዊ የዶሮ መርቢያ ፋርም ክላስተር በማስገባት ወጣቶችን በመደራጀት መስኩን እንቀላቀሉ የተደረገበትና በሀገራዊ ደረጃ የተበሰረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን በውጤታማነት የተገበርንበት ነው።

በማህበራ ኃላፊነታችንን ከመወጣት አንፃር ለአቅመ ደካማ ወገኖቻች ህዝብን በማሣተፍ ቤት ሰርቶ የማስረከብ እና የማህድ ማጋራት ስራዎቻችንን አጠናክረን የቀጠልንበት ሲሆን ወጣቶቻችን በበጋና የክረምት በጎፍቃድ በማሣተፍ የሀገር ፍቅራቸው እንዲጨምር እና ማህበራ ኃላፊነታቸው እንዲወጡ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር በርካቶች እንዲሣተፉበት ተደርጓል።

በከተማችን የትምህርት ጥራትን እና ሽፈን ከማረጋገጥ አንፃር የትምህርት ለትውልድን መርሀ ግብር ህዝባዊ በመድረግ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ስራዎች መስራት ተችሏል። እነዚህንና ሌሎች በርካታ ስራዎችን የሰራንበት ዓመት ነበረ።

በአዲሱ ዓመት አዲስ ዕይታ፣ አዲስ ዓለም፣ አዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ መንገድ፣ አዲስ ሀብት፣ አዲስ ቴክኖሎጂ፣ አዲስ፣ አሠራር፣ አዲስ ዘይቤ ይፈጥራሉ። አዲስ ነገር በማድረግ፣ ዘመኑ ብቻ ሳይሆን ቀኑም አዲስ እንዲሆን ያደርጋሉ።

እነዚህ ግን ማሳያዎች እንጂ ፍጻሜዎች አይደሉም። አገልግሎት አሰጣጥን ከሌቦች በማጽዳት፣ የፍትሕ ሥርዓቱን ውጤታማ በማድረግ፣ የኑሮ ውድነትን ጫና በመቀነስ፣ የአምራች ዘርፉን ድርሻ በማሳደግ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር፣ ግብርናን ይበልጥ በማዘመን፣ መልካም አስተዳደርን በማስፈን እና ወዘተ. እነዚህ ሁሉ፣ ዘመን የሚቀይሩ ልጆችን ከተማችን ትፈልጋለት።

በሚመጣው አዲስ ዓመት አምና ያልነበረ ለውጥ፣ ሥራና ተአምር ከፈጠርን ዓመቱ አዲስ ዓመት ይሆናል፤ የተለየ አዳዲስና ዘመናዊ አሠራሮች፣ አዳዲስ መፍትሔዎች፣ አዳዲስ መንገዶች፣ አዳዲስ ዕይታዎች፣ አዳዲስ ዐሻራዎች፣ አዳዲስ የአገልግሎት አሰጣጥ መንገዶች፣ አዳዲስ ፕሮጀክቶች፣ አዳዲስ መሠረተ ልማቶች፣ አዳዲስ የዕውቀት ብልጭታዎች፣ አዳዲስ የግብርና ዘይቤዎች በማምጣት ዘመኑን አዲስ እንድናደርገው ጥሪዬን አቀርባለሁ።
በድጋሚ ዘመኑን በአዲስ ሥራ አዲስ አድርገነው አዲስ ዓመት እንዲሆንልን እመኛለሁ።

🌻በአዲስ ተስፋ 🌼አዲስ አሰተሳሰብ 🌻 አዲስ ዘይቤ🌼 በህዝባዊነት መሠረት የጋራ ቤታችን የሆነችውን ከተማችን ወደ ታላቅነት ለማሻገር በትኩረት እንሰራለን።

መልካም አዲስ ዓመት
ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም
ኢንጂነር ሰለሞን ሌዊ
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

Address

Mizan Aman
Mizan Teferi

Telephone

+251995000968

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mizan Aman city Admin Prosperity Party /የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Mizan Aman city Admin Prosperity Party /የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ:

Share