ሸኮ ወረዳ ት/መ/ልማት ጽ/ቤት sheko werda transport and road development office

  • Home
  • Ethiopia
  • Mizan Teferi
  • ሸኮ ወረዳ ት/መ/ልማት ጽ/ቤት sheko werda transport and road development office

ሸኮ ወረዳ ት/መ/ልማት ጽ/ቤት sheko werda transport and road development office መንገድ ለሁሉም

25/12/2024
በትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ዳውሮ ዞን  ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡በወላይታ...
25/09/2024

በትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ዳውሮ ዞን ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወልዴ ቢሊሶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ከሟቾች በተጨማሪ በ29 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየየገለፅን ለወዳጅ ዘመድ መፅናናትን እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ከጉዳታቸው እንዲያገግሙ እንመኛለን።

የኮምቱ በዲ አጭር የህይወት ታሪክበረምበራስ ኮምቱ በዲ ከአባታቸው ከአቶ በዲ ጉርጫ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ኦቺ ጃሹ በ1945 ዓ/ም በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ጋይዚቃ ቀበሌ ተወለዱ።እድሜያ...
24/09/2024

የኮምቱ በዲ አጭር የህይወት ታሪክ
በረምበራስ ኮምቱ በዲ ከአባታቸው ከአቶ በዲ ጉርጫ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ኦቺ ጃሹ በ1945 ዓ/ም በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ጋይዚቃ ቀበሌ ተወለዱ።

እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ እውቀትን ፍለጋ ገና በለጋነት እድሜያቸው ት/ቤት የገቡት ኮምቱ በዲ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ሚዛን አሜሪካ ሚሽን ትምህርት ቤት ተምረዋል ።

7ኛ እና 8ኛ ክፍል ሚዛን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም 9ኛ ክፍል ጂማ ሚያዝያ 27 ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመከታተል አጠናቀዋል ።

በወቅቱ 9ኛ ክፍል አጠናቀው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በሚሰጣቸው የትምህርት እድል ተጠቃሚ በመሆን በአማራ ክልል ወሎ ጤና ማሰልጠኛ ተቋም በመግባት ትምህርታቸውን ተከታትለው በጤና ባለሙያነት ተመርቀዋል ።

የሸኮ፣የደቡብ ቤንች እና ማጂ ማህበረሰብን በጤና ሙያ ለረዥም አመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በሙያቸው አገልግለዋል ።

ኮምቱ በዲ የትምህርት ደረጃቸውን በማሻሻል ከጂማ ጤና ማሰልጠኛ ተቋም በፋርሚሲስት ዲፕሎማቸውን መስራት ችለዋል ።

ከጤና አገልግሎት ባሻገር ለሸኮና አካባቢው ማህበረሰብ ልማትና መልካምአስተዳደር ለማረጋገጥ ሸኮና አካባቢዋ የተሰኘ ፓርቲ በመመስረት ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በማድረግም ከፍተኛ ዋጋ ከፍለዋል ።

በረምበራስ ኮምቱ በዲ በነበራቸው የፖለቲካ አቋም እስከ መሰደድ የደረሱ ከአገር ለመውጣት እስከ ኬኒያ ጠረፍ ድረስ አቅንተው ሳይሳካላቸው እንደተመለሱ ታሪካቸው ያስረዳል ።

ጥቅምት 2ቀን 2015ዓ/ም የሸኮ ጎሳዎች መሪ በመሆን በባህላዊ ስርዓት የንግስና ሲመት የፈጸሙት በዲ እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ድረስ የሸኮን ጎሳዎች በእኩልነት እና በፍትሐዊነት ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል።

ከጎሳ መሪነት በተጨማሪም ኮምቱ በዲ በሸኮና አካባቢው ሰላም እንዲረጋገጥ ወጣቶችን በበምከርና በገሰጽ ስርዓት በማሲያዝ አሁን ሸኮ፣ቴፒ፣ጉራፈርዳና በአካባቢው ለተፈጠረው ሰላምና ጸጥታ ታላቅ ባለውለታ ነበሩ።

በልማት ረገድ ግምባር ቀደምና ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቁት ኮምቱ በዲ ለልማት የገንዘብና የሞራል ድጋፍም በማድረግ እንዲሁም የሸኮ ባህል፣ወግና ታሪክ ተጠብቆ ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፍ ያላሰለሰ ጥረት አድርገዋል ።

የሸኮ ብሄር ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ቲካሻ ቤንጊ ከ50 አመታት በኃላ እንዲከበር ጉልህ ሚናቸውን ተወጥተዋል ።

ኮምቱ በዲ ከትዳር አጋራቸው 5 ወንድና 4 ሴት በድምሩ 9 ልጆችን እንዲሁም 4 የልጅ ልጆችንም ማፍራት ችለዋል ።

ኮምቱ በዲ ፍጹም ሰብዓዊነት የሚሰማቸው የተቸገረን የሚያበሉ፣የተጠማን የሚያጠጡ፣የታረዙትን የሚያለብሱ፣የተጣለን የሚያስታርቁ፣የሌላውን ማህበረሰብ ባህል ወግና ታሪክ የሚያውቁና የሚያከብሩ ታላቅ አባት ነበረ።

ድንገት በገጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ጂማ ኦስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ/ም በተወለዱ በ72 አመታቸው ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል።
ኮምቱ በዲ
1945 _2017
ተፈጸመ

የ2017 በጀት ዓመት ኢተቃ ቀበሌ ሀ ብሎ የጀመሬ ሲሆን የአምናውን ታርክ ይደጊም ይሁን? ኢተቃሳ ደረጃውን ያስቀጥል ይሁን ? ለማንኛውም የ2017 በጀት ዓመት ወረዳው ከ350 ሚሊዮን ብር ፕ...
20/09/2024

የ2017 በጀት ዓመት ኢተቃ ቀበሌ ሀ ብሎ የጀመሬ ሲሆን የአምናውን ታርክ ይደጊም ይሁን? ኢተቃሳ ደረጃውን ያስቀጥል ይሁን ? ለማንኛውም የ2017 በጀት ዓመት ወረዳው ከ350 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ዉሰጥ በዚህ በጀት ዓመት 113 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን ኢተቃ ቀበሌ ማጩቃንና ጀምዶስ አስከትሎ ደረጃውን በአንድኝነት እየመራ ይገኛል ።አብዛኛው ሰው የአምናው ሻሚፒዮን ጀንጀቃ የታለ እያለ ነው ቀጣይስ ማን አመራር የትኛው ቀበሌ ደረጃውን ያሻሽል ይሁን የሚለዉን በጉጉት እየጠበቅን ነው

01/09/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! De File DeJene, Hiskel Demise, Sis Ayfhiab, Hamus Petros

ድጋፉ ቀጥለዋል ........አቶ  አገኘሁ ወርቁ የዞኑ ትራንስፖርት መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ ናቸው ።እኔም ሰለ ዳማ ድልድይ ግንባታ የድርሻዬን እወጣለሁ ብሎ 10000 አስገብተዋል ።ከልብ...
19/11/2023

ድጋፉ ቀጥለዋል ........

አቶ አገኘሁ ወርቁ የዞኑ ትራንስፖርት መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ ናቸው ።
እኔም ሰለ ዳማ ድልድይ ግንባታ የድርሻዬን እወጣለሁ ብሎ 10000 አስገብተዋል ።

ከልብ እናመሰግናለን

የወጋገን 0921261030301
የንግድ ባንክ አካውንት 1000444800376
የአቢሲኒያ 92345343

"አጥፍተናል ፤ የበደልነውን ህዝብና መንግስት ለመካስ ከነገ ጀምሮ በዲጂታል መነኃሪያ አገልግሎት ስራ እንጀምራለን"  ፦ አሽከርካሪዎች ፣ ባለንብረቶችና የቦርድ አመራሮች ጥቅምት 16/2016 ...
27/10/2023

"አጥፍተናል ፤ የበደልነውን ህዝብና መንግስት ለመካስ ከነገ ጀምሮ በዲጂታል መነኃሪያ አገልግሎት ስራ እንጀምራለን" ፦ አሽከርካሪዎች ፣ ባለንብረቶችና የቦርድ አመራሮች

ጥቅምት 16/2016 የዞኑን ሰላም ፣ አንድነትና አብሮነት ለማይፈልጉ አካላት መጠቀሚያ መሆን አይገባም ፦ አቶ ኮጁ ባደከች

በሚዛን አማን መነኃሪያ ዲጂታል የመነኃሪያ አገልግሎት ስራ ውስጥ አንገባም በማለት ላለፉት 3 ቀናት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ አድማ በማድረግ ስራ መስተጓጎሉ የሚታወስ ሲሆን የዞኑ የፀጥታ መዋቅርም ህግ ለማስከበር በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር ማድረጉ የሚታወስ ነው። እጥረቱን ለመቅረፍም በጊዜያዊነት የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ወደ ስምሪት በማስገባት ሲሰራም ተቆይቷል።

የቤንች ሸኮ ዞን ሠላምና ጸጥታ መምሪያ ፣ የዞኑ ፖሊስና የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ አመራሮች ዛሬ ከሰዓት በኀላ ከአሽከርካሪ ባለንብረቶች ፣ ከቦርድና ከማህበራት አመራሮች እንዲሁም ከአሽከርካሪዎች ጋር በፖሊስ መምሪያ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይድት አድርገዋል።

የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኮጁ ባደከች እንደተናገሩት ድርጊቱ አሳፋሪ ፣ ሰው ተኮር በሆነው የትራንስፖርት ዘርፍ ውስጥ መፈጸም የሌለበት ድርጊት መሆኑን ገልጸው ድርጊቱ ከወንጀልም በላይ ኢ ሞራላዊ ነው ብለዋል። የጸጥታ መዋቅሩ ችግሩን ለመቅረፍና ህግ ለማስከበር የተኬደበትን ርቀትም አድንቀው ድርጊቱ መደገም የሌለበት ነው ብለዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ ባለንብረቶች ፣ የማህበራት አመራሮች እና አሽከርካሪዎች "በተፈጠረው ችግር አፍረናል ፤ የዞኑ መንግስት የሰጠንን ዕድል ባለመጠቀማችን የተፈጠረ ነው ፤ ስሜታዊ በመሆን በዞኑና በከተማዋ ገጽታ እንዲሁም ህዝቡን በማንገላታታችን ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል።

"የበደልነውን ህዝብና መንግስት ለመካስ ከነገ ጀምሮ በመነኃሪያ በመገኘት በዲጂታል የመነኃሪያ አገልግሎት ወደ ስራ እንገባለን" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ እንደተናገሩት በአመፅ ፣ ህግን በመጣስና አድማ በመምጣት የሚሰጥ ምንም አይነት ምላሽ አይኖርም ብለዋል። በተቃራኒው በመነጋገር ፣ በመደማመጥና በጠረጴዛ ዙሪያ በርካታ ችግሮችን መፍታት እየተቻለ በአመፅ ህዝብን ማንገላታትና ገጽታን ማበላሸት ተገቢ አይደለም ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች መንግስትና ህዝቡን ይቅርታ መጠየቃቸው ተገቢና ተቀባይነት ያለው ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ለተፈጠረው ችግር ተገቢውን የገንዘብ ቅጣት የሚቀበሉ ሲሆን በጊዜ ቀጠሮ የሚገኙትን ደግሞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።

የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ወርቁ በበኩላቸው አመጽና አድማው በዞኑና በከተማዋ ገጽታ ላይ ጥላሸት ቀብቶ አልፏል ብለዋል። በመሆኑም በጠየቁት ይቅርታ መሰረት ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ የሚገባ ሲሆን የህዝብ ፍሰት መኖሩን እየወቁ ለማሳት አለመፈለግ በሚል የቅጣት ልክ እያንዳንዱ በአመፅ ውስጥ የተሳተፈ ተሽከርካሪ ባለቤት 2ሺ 500 ብር የሚቀጣ ሲሆን በጥቅሉ ከ785ሺ ብር በላይ ይቀጣሉ ብለዋል።

ይሁን እንጂ ከነገ ጀምሮ ወደ ስምሪት በማይገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍቸኛውን የቅጣት ጣሪያ ተቀጥተው ወደ መስመር እንደሚገቡ ኃላፊው ጠቁመዋል። በመሆኑም ህዝቡ ከነገ ማለዳ ጀምሮ በሚዛን መነኃሪያ በመገኘት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችልም አቶ አገኘሁ አስረድተዋል።

በሚዛን መነኃሪያ አገልግሎት በተፈጠረው የአገልግሎት መቋረጥ ህዝቡን ይቅርታ እንጠይቃለን ፦ አቶ አገኘሁ ወርቁሸኮ ፣ ጥቅምት 14/2016 በአሽከርካሪዎች የተደረገው የትራንስፖርት አድማ በየት...
26/10/2023

በሚዛን መነኃሪያ አገልግሎት በተፈጠረው የአገልግሎት መቋረጥ ህዝቡን ይቅርታ እንጠይቃለን ፦ አቶ አገኘሁ ወርቁ

ሸኮ ፣ ጥቅምት 14/2016 በአሽከርካሪዎች የተደረገው የትራንስፖርት አድማ በየትኛውም መስፈርት ህገ ወጥና መደገም የሌለበት መሆኑን ኃላፊው በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ወርቁ በመምሪያችን በላኩት መግለጫ በክልሉ በ4 ዋና ብዝሀ ከተሞች ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የወረደው የዲጂታል መነኃሪያ አገልግሎት ፍትሀዊ ፣ ፈጣን ፣ ህዝቡን ከትርፍ መጫንና ከታሪፍ ጭማሪ የሚታደግ ከመሆኑም በላይ ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎትን ተደራሽ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በክልሉ የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ አማካኝነት ለትራንስፖርት ማህበራት አመራሮች ፣ ለየዞንና ከተሞች የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ተቋማትና ለመነኃሪያ አስተዳደሮች በዲጂታል መነኃሪያ አገልግሎት ግልጽ ገለጻና ማብራሪያ የተሰጠበት ቢሆንም የአሽከርካሪ ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች ግንዛቤ አልተፈጠረልንም በማለት ያቀረቡትን ቅሬታ መነሻ በማድረግ ትላንት በሚዛን ሁለገብ አዳራሽ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።

ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ ዲጂታል የመነኃሪያ አገልግሎት ስራው በይፋ እንደሚጀመር የተገለፀ ቢሆንም ከህግና ከአሰራር ውጭ አድማ በማድረግ የዛሬውን የህዝብ ትራንስፖርት አገለግሎት ማስተጓጎላቸውን ገልጸዋል። ይህ ተግባር በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የሌለውና ህገ ወጥ መሆኑንም ኃላፊው ጠቁመዋል።

ዛሬ በቴፒ ፣ ቦንጋና ታርጫ መነኃሪያዎች ዲጂታል የመነኃሪያ አገልግሎቱን ወደ ስራ ለማስገባት እየሰሩ ባሉበት በሚዛን መነኃሪያ ህገ ወጥ በሆነ መልኩ ትራንፖርቱን ማስተጓጎል በህግም ተጠያቂ ያደርጋል ብለዋል።

በመሆኑም የዞኑ ነዋሪዎች በተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን ያሉት ኃላፊው ዛሬ ላይ በመነኃሪያ የነበሩ ተጓዦችን ችግርና መጉላላት ለመቀነስ ህዝቡንና ህጉን ያከበሩ ጥቂት ተሽከርካሪዎች ወደ ስራ የገቡ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በጭነት ተሽከርካሪዎች ጭምር የማስተናገድ ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው አጥፊዎች ላይ ህጋዊና አስተማሪ እርምጃ ወስደን አገልግሎቱን እስክናስተካክል ድረስ ህዝቡ ዛሬ ባሳየው ጨዋነት በትዕግስት እንዲጠባበቅ ኃላፊው ጠይቀዋል።
ምንጭ የዞኑ ኮምኒኬሽን

22/08/2023
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰዎች ህይወት፣አካልና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ትራፊክ ፖሊስ አስታወቀ።ጥር፣ 01 ቀን 201...
09/01/2023

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰዎች ህይወት፣አካልና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ትራፊክ ፖሊስ አስታወቀ።

ጥር፣ 01 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ ግንዛቤ መፍጠር ዲቪዥን ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር እስማኤል ሁሴን እንደገለፁት በክልል ከታህሳስ 24 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ሰባት ቀናት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች በሶስት ሰዎች ላይ ሞት ፤ በሰባት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳትና መጠኑ ያልታወቀ ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ነዉ የገለፁት።

እንደ ኢንስፒክተሩ ገለፃ መነሻውን ቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን መዳረሻውን ወደ ጋምቤላ ይጓዝ የነበረ ኮድ 4-00437 ጋ/ም የሆነ ፒካፒ ደብል ገቢና መኪና ሸኮ ወረዳ ግዝ መሬት ቀበሌ እንደደረሰ 300 ሜትር ገደል ውስጥ ገብቶ በመገልበጡ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል በሚዛን አማን አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል ።

ረዳት ኢንስፒክተሩ አክለውም በቤንች ሸኮ ዞን ሸይ ቤንች ወረዳ ሞተር ብስክሌት እግረኛ ገጭቶ በአንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት፣እንዲሁም ቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ ሞተር ብስክሌትና ዶልፍን ተጋጭቶ የሞተሩ አሽከርካሪ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በዚሁ ወረዳ ዶሊፊን ተሽከርካሪ ከሞተር ጋር ተጋጭቶ በ1 ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንና በዳውሮ ዞን ሎማ ወረዳ ተሽከርካሪ ላይ በመውደቅ በ1 ሰው ላይ የሞት አደጋ መከሰቱንና በሸካ ዞን ሞተር ከተሽርካሪ ጋር ተጋጭተው የሞተር አሽርካሪው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፤በካፋ ዞን ባጃጅ እግረኛን ገጭቶ በአንድ ሰው ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ጠቁመዋል፡፡

ባለፉት አንድ ሳምንት በክልሉ በደረሰው 6 አደጋዎች በሶስት ሰዎች ላይ ሞት፤በስድስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት፣በአንድ ሰዉ ላይ ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልፀው በንብረት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ለማወቅ ትራፊክ ፖሊስ መረጃ እያሰባሰበ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የአደጋዎቹ መንስኤዎቹ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣የተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር፣የአሽከርካሪው የጥንቃቄ ጉድለት ለአደጋው መከሰት መንስኤዎች መሆናቸውን ረዳት ኢንስፔክተር እስማኤል ሁሴን ተናግረዋል፡፡

Address

Sheko Werda
Mizan Teferi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሸኮ ወረዳ ት/መ/ልማት ጽ/ቤት sheko werda transport and road development office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category