Teshome Naka Gitab Attorney & Consultant at Law

Teshome Naka Gitab Attorney & Consultant at Law ለመብትዎ ቅድሚያ እንሰጣለን!!

በአማን መካነየሱስ ማ/ምዕመናን ሻሎም መዘምራን መዝሙር ተባረኩበት
06/09/2026

በአማን መካነየሱስ ማ/ምዕመናን ሻሎም መዘምራን መዝሙር ተባረኩበት

The Ethiopian Evangelical church maken eysus hebert mezumer

04/08/2026

በይዞታ ላይ የሚፈጠር ሁከት በፍርድ ስለማስወገድ
=====================
በሕጋዊ ይዞታው ላይ ሁከት የተፈጠረበት ወይም ከሕግ ውጭ ንብረቱ የተወሰደበት ሰው ጉዳዩን ለፍርድ ቤት በማቅረብ በይዞታው ላይ የተፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ወይም የተነጠቀው ንብረቱ እንዲመለስ በመጠየቅ የክስ አቤቱታ ሊያቀርብ ይችላል።
በፍ/ብሔር ሕግ ቁ.1149 ላይ ስለ ሁከት ማስወገጃ ክስ እንደሚከተለው ተመልክቷል፦

➡️1. ይዞታው የተወሰደበት ወይም በይዞታው ላይ ሁከት የተነሳበት ሰው የተወሰደበት ነገር እንዲመለስለት ወይም የተነሳው ሁከት እንዲወገድለት እንዲሁም ስለደረሰበት ጉዳት ኪሳራ እንዲሰጠው ለመጠየቅ ይችላል።
➡️2. የያዘው ነገር ከተነጠቀበት ወይም በይዞታው ላይ ሁከት ከተነሳበት ቀን አንስቶ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ በፍርድ ካልጠየቀ እጅ ይዛወርልኝ የማለት ክስ መብቱ ይቀርበታል።
➡️3.ተከሳሹ የሰራውን አደራረግ የሚፈቅድ ለርሱ የሚናገለት መብት መኖሩን በፍጥነት እና በማይታበል ዓይነት ካላስረዳ በቀር ዳኞቹ የተወሰደው ነገር እንዲመለስ ወይም የተነሳው ሁከት እንዲወገድ ያዛሉ።”

ከተጠቀሰው ድንጋጌ ይዘት መረዳት እንደሚቻለው ሁከት ለማስወገድ በፍ/ብሔር ሕግ ቁ.1149 መሰረት የሚቀርብ የክስ ኣቤቱታ (possessory action) ይዞታን የመከላከል ግብ አለው። የይዞታ መብት የሕግ ጥበቃ ስለሚደረግለትም በሕግ ላይ የተደነገገውን ስርዓት በመከተል ሌላ ባለመብት ነኝ የሚል ወገን መብቱን ከሚያስከብር በስተቀር ሓይልን በመጠቀም ባለይዞታውን ማስለቀቅ በሕግ ተቀባይነት አይኖረውም።

የዳኝነት ተቋማትም የሓይል ጥቃት ሰለባ ሆነው የባለይዞታነት መብታቸውን ከሕግ ውጭ የሚያጡ ሰዎች የሚያቀርቡትን የሁከት ማስወገጃ ክስ የተፋጠነ ሁኔታ በማየት ውሳኔ ለመስጠት ካልቻሉ ሕገ ወጥነትን ለመከላከልም ሆነ ለማስወገድ ያላቸው ብቃት የተዳከመ ይሆናል። በተለይም ሁከት ከመፈጠሩ በፊት በባለይዞታው በኩል ሁከቱ ሊፈጠር መሆኑን ከሚያስረዳ ማሰረጃ ጋር ለፍ/ቤት የቀረበ የሁከት ይወገድልኝ ክስ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሓይል ተግባራት ተፈፅሞ የሕ/ሰቡ ሰላምና ደህንነት ከመረበሹ አስቀድሞ የዳኝነት ተቋሙ ተገቢውን የሕግ ማስከበር ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ይጠበቅበታል። የሁከት ድርጊቱ ከተፈፀመ በኃላ ሰሚቀርብ የሁከት ማስወገጃ ክስ የተከሳሹ የሓይል ተግርባር መፈፀም ያለመፈፀምና የከሳሹን ይዞታ መንጠቅ ያለመንጠቅ ተገቢውን ስነ-ስርዓት ተከትሎ መጣራትና በፍጥነት ውሳኔ ማግኘት ያለበት ጭብጥ ነው።

በመሆኑም በፍ/ብሔር ሕግ ቁ.1149 (3) አነጋገር ተከሳሹ የስራውን አደራረግ የሚፈቅድለት ለርሱ የሚናገርለት መብት (right) መኖሩን በፍጥነት እና በማይታበል ዓይነት (forthwith and conclusively) ማስረዳት የሚጠበቅበት መሆኑን ስለሚያሳይ የማስረዳት ሸክሙና የጊዜውን አጠቃቀም ፍርድ ቤቶች ከግንዛቤ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ይሆናል።

ከሁከት ማስወገጃ ክሶች አንፃር በፍርድ ቤቶች መካከል የአፈፃፀም ልዩነት ይታያል። የክሱን ይዘት የባለቤትነት መብት ማረጋገጫ አድርጎ መመልከት እንደሌሎች ጉዳዮች መደበኛውን ስነ-ስርዓት ተከትሎ መምራት እና የጉዳዮችን የተፋጠነ መፍትሄ ፈላጊነት ትኩረት ያለመስጠትና የማስረዳት ሸክሙን የትኛው ወገን መወጣት እንዳለበት የተለያዩ አቋሞችን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል።

02/08/2026
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Tewodros Abebe, Yemane Mergia, Miru Marasa, Aniley Belay,...
30/07/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Tewodros Abebe, Yemane Mergia, Miru Marasa, Aniley Belay, Zed Asnak, Samuel Assefa Ambo, Mengistu Mulugeta, Tadesse Tesfaye, Haile Gimiyo, Meaza Admasu, Tilahun Mengesha, Yonas Belay, Zemari Hyela Balmu, Esayas Yisahak Gahd, Yohannes Getabeh, Simegno Fikadu, Befikadu Tesfaye Wodajo, Aman Iyasu, Eliyas Teshome Beqele, Yakob Wolebo, Esral Asfa, Dagim Sazi, Mihiretu Tesfaye, Biruke Demissa, Bekele Tako, Mengesha Melaku, Dagne Taye, Samson Tadese, Tadele Kochito Mamo, Marduru Suri Stb, Ye Abat Nafikot, Gezahegn Gadissa, Bekele Ashagire, Ashe Ashe

27/07/2026

ዋስትና አሰጣት

24/07/2026

ወድ ተከታዮች ከዚሀ
ህ በፊት በቤንች ሸኮ ዞን ዐቃቤ ሕግ ሆኜ በማገለግልበት ወቅት ለሕዝብ የሕግ ንቃተ ሕግ ግንዛቤ የሚሠራጭበት ገፅ የነበረ ሲሆን አሁን ከዚህ በኋላ የሚተላለፈው መልዕክት በጠበቃ ተሾመ ናካ ወይም ተጋባዥ እንግዳ መሆኑን እያሳሰብኩ የበለጠ የሕግ ግንዛቤ ለማህበረሰቡ ለማድረስ ለጓደኞችዎ በማድረግ ተባብሩን።

ጓደኞቼ ፣የስራ ባልደረቦቼ የቤንች ሸኮ ዞን ፍትህ መምሪያ ጠቅላላ ሠራኞች በእውነት ላሳያችሁኝ ፍቅር ከልቤ አመሠግናችዋለሁ። እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ወንድማችሁ ተሾመ ነኝ።
22/07/2026

ጓደኞቼ ፣የስራ ባልደረቦቼ የቤንች ሸኮ ዞን ፍትህ መምሪያ ጠቅላላ ሠራኞች በእውነት ላሳያችሁኝ ፍቅር ከልቤ አመሠግናችዋለሁ። እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ወንድማችሁ ተሾመ ነኝ።

Address

Mizan Teferi

Opening Hours

Monday 02:00 - 12:00
Tuesday 02:00 - 12:00
Wednesday 02:00 - 12:00
Thursday 02:00 - 12:00
Friday 02:00 - 12:00
Saturday 02:00 - 12:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Teshome Naka Gitab Attorney & Consultant at Law posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share