West Omo Zone Plan and Development Department

West Omo Zone Plan and Development Department plan department Governmental sectors

በምዕራብ ኦሞ ዞን በ2018ዓም ከ208 ሺህ በላይ ሄ/ር መሬት በዘር መሸፈን መቻሉ ተገለፀ።ጀሙ:-ሐምሌ 2 ቀን 2018ዓምበምዕራብ ኦሞ ዞን የዞኑ የአስተዳደር ም/ቤት የተቋማት 2018 በጀት...
09/07/2026

በምዕራብ ኦሞ ዞን በ2018ዓም ከ208 ሺህ በላይ ሄ/ር መሬት በዘር መሸፈን መቻሉ ተገለፀ።
ጀሙ:-ሐምሌ 2 ቀን 2018ዓም
በምዕራብ ኦሞ ዞን የዞኑ የአስተዳደር ም/ቤት የተቋማት 2018 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2019 እቅድ የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የተቋማት የማጠቃለያ ሪፖርት ያቀረቡት የዞኑ ኘላን ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘርይሁን ወርቁ የግብርና አካባቢ ጥበቃ አፈጻጸም ሲያቀረቡ በዞኑ በ2018ዓም ከ208ሺህ በላይ ሄ/ር መሬት በዘር መሸፈን መቻሉን ገልጸዋል ።

በምርት ዘመን በመኸር ፣ በበጋ መስኖና በበልግ ከ6ሚሊዮን 165 ሺህ በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየተሠራ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

የፕላን መምሪያ ሃላፊ ቀሪ ተቋማት ሪፖርት በዝርዝር ለተሳታፊዎች እየቀረበ ይገኛል።

የምዕራብ ኦሞ ዞንየ2018 በጀት ዓመት  የ9 ወር ዕቅድ አፋፃፀም ተገምግሟል። በዞኑ በባለፉት 9 ወራት የተመዘገቡት ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል ጉድለቶችን ለይቶ መስራት እንደሚገባ የምዕራብ ...
23/04/2026

የምዕራብ ኦሞ ዞንየ2018 በጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፋፃፀም ተገምግሟል። በዞኑ በባለፉት 9 ወራት የተመዘገቡት ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል ጉድለቶችን ለይቶ መስራት እንደሚገባ የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ ተናገሩ ።
በባለፉት 9 ወራት የተሠሩ ስራዎች ቀርቦ ተገምግሟል።
‎‎በመድረኩ ማጠቃለያ የተገኙት የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ እንደተናገሩት በባለፈው
9 ወራት በዞኑ የተመዘገቡት የልማትና የመልካም አስተዳደር ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል ጉድለቶችን ለይቶ መስራት በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል ።
በዚህ መሠረት አመራሩና ባለሙያዎች ጊዜ የሚዋጀውን ሥራ መስራት የተቋማትን አፈጻጸም ከፍ ማድረግ ሲሉ ገልጸዋል ።
የተቋማት የ9 ወራት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የዞኑ ፕላንና ልማትና መምሪያ ሀላፊ አቶ ዘሪሁን ወርቁ በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊ እንዲሁም በአስተዳደር ዘርፍ የተደራጀው 2018ዓ/ም የ9 ወራት የሥራ አፈፃፀም አቅርቧል ።
በቀርበው የ2018ዓ/ም የ9 ወራት የሥራ አፈፃፀም በግብርና ዘርፍ በመኸር 1.4 ሚልዮን በኩንታል፣ በበጋ መስኖ ከ127ሽህ በላይ ምርት እንዲሁም በቡናና በቅባት እህሎች ምርት ተሰብሰቡ ለማዕከላዊ ገበያ መቅረብ መቻሉን ተገልጧል ።
በውሃና ማዕድን ተቋም አንፃር በባለፉት 9 ወራት 303.4 ኪ/ግ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማስገባት መቻሉን ተመላክቷል።
ከገቢ መምሪያ አኳያ 1ቢልዮን 23ሚልዮን 503ሽህ 110ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 705 ሚልዮን 68ሺ 553 ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 69 ከመቶ ስለመከናወኑ በቀረበው ሪፖርት ተብራርቷል ።
በትምህርት ዘርፍ ከ66ሚልዮን ብር ሀብት በመሰብሰብ ለሥራ ማዋል ዋቻሉ ተገልጿል ።
በጤና ወቅቱ የወባ ወረርሽን የሚከሰትበት ወቅት በመሆኑን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ከውይይቱ ተነስቷል ።
በባለፉት ወራት 9 ወራት በሠላምና ፀጥታ በመኤኒት ሻሻ ወረዳ በተከናወነው ወንጀለኞችን ለህግ አጋልጦ በመስጠት ከ90 በላይ ወንጀለኞች የተያያዘ ሲሆኑ 38
በነብሰ ግድያ የተጠረጠሩ መሆናቸው ለዞኑ ሞዴል ተሞክሮ የምቀመሩ ስለመሆናቸው ቀርቦል።
በዞኑ በፍትህ መምሪያ 870 የወንጀል መዝገቦች ቀርቦ ወሳኔ ማግኘታቸውን ተመላክቷል።
🙏ዘወትር :- ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን🙏

25/03/2026

የምዕራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ የ2017 የሶሽዮ-ኢኮኖሚ መረጃ ማጥራት፣ በአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት እና የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ከክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ባለሙያዎችን በመጋበዝ ለዞን...
23/03/2026

የምዕራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ የ2017 የሶሽዮ-ኢኮኖሚ መረጃ ማጥራት፣ በአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት እና የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ከክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ባለሙያዎችን በመጋበዝ ለዞን መምሪያ ኃላፊዎች፣ለልማት ዕቅድ ባለሙያዎች፣ለወረዳ ፕላን ጽ/ቤት ማኔጅመንት አካላት እና የወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

13/03/2026

ምዕራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ
የምህራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ በዞኑ ከሚገኙ መምሪዎች አንዱ ሲሆን በሰባት(7) የወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች የተዋቀረና በሶስት(3) የከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ሲሆን በዞኑ በድምሩ አስር(10) መዋቅሮች ሲኖሩት የፕላን ልማት ጽ/ቤት የተዋቀረባቸው በሰባቱ(7) ወረዳዎች ሲሆን የከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች መዋቅር ሲስተካከል እንደሚዋቀሩ ያለዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዞኑ ያሉ የወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

በዞኑ ያሉ የከተማ አስተዳደሮች የፕላን ልማት ፅ/ቤት

1. መኤኒት ጎልዲያ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

2. ጋችት ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

3. መኤኒት ሻሻ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

4. ጎሪ ጌሻ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

5. ማጂ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

6. ሡሪ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

7. ቤሮ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

1. ባቹማ ከተማ አስተዳደር

2. ጀሙ ከተማ አስተዳደር

3. ማጂ ቱም ከተማ አስተዳደር ናቸው፡፡



አቶ ዘሪሁን ወርቁ

የምህራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ

Background Of West Omo Zone

Location and Area

ምዕራብ ኦሞ ዞን በደ/ምዕራብ ኢትዮጲያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ከሚገኙ ዞኖች በሚያዝያ 23/2011 ዓ.ም በአድስ መልክ መመስረቱ ይታወቃል፡፡ ዞኑ በሀገሪቱ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 671 ኪ/ሜትርና ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ቦንጋ 200 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ዞኑ በሰሜንና በሰሜን ምስራቅ ከከፋ ዞን፣ በሰሜን ምዕራብ ከቤንች ሸኮ ዞን፣ በደቡብ ምሥራቅ ከደቡብ ኦሞ ዞን፣ በደቡብ ምዕራብ ከጋምቤላ ክልልና በደቡብ ከደቡብ ሱዳን ሪፖብሊክ ጋር ይዋሰናል።

ዞኑ 3 ክፍለ ከተማዎችና በ7 ወረዳዎች በ114 ቀበሌ አስተዳደር የተከፋፈለ ሲሆን የቆዳ ስፋቱ 1,458,400 ሄ/ር እንደሚሆንና በ1ስኩዌር ኪሎ ሜትር በአማካይ 20.6 ህዝብ እንደሚኖር ይገመታል።

ዞኑ የሚገኝበት በስተምስራቅ /Latitude/ 6.6384755 እና በስተ ምዕራብ /Longitude/ 35.7817109 ይገኛል፡፡

Population size and distribution

የ1999 ዓ.ም የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤትን መሰረት በማድረግና በዞኑ ካሉ ወረዳዎች የህዝብ ቁጥር መረጃ በመሰብሰብ በተገኘው መረጃ በ2017 ዓ.ም የዞኑ ህዝብ ብዛት ወ 163,542 ሴ 174,236 ድ 337,778 በዞን ማዕከል ፣ በከተማ አስተዳደርና በ7ቱ ወረዳዎች የሚገኙ አራቱ /4/ ነባር ብሄረሰቦች ማለትም የመኤኒት፣የዲዚ፣የሱርማና ዚልማሞ ብሔረሰቦችንና በሰፈራ ጣቢያዎች ተካቶ ያሉ የአማራ፤ የከምባታና የሲዳማ ብሔረሰቦችን ያካተተና በተጨማሪም በዞኑ ዉስጥ ባሉ ወረዳ ከተማዎች በንግድና በመንግስታዊ ስራ የተሰማሩ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ብሔረሰቦች ይገኛሉ፡፡

በዞኑ ዉስጥ በዋናነት የመኤኒት፣ የዲዚ፣የሱርማና የዚልማሞ ብሔረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን ከነባሩ ህዝብ ጋር በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ ሌሎች ብሄር ብሔረሰቦች በአንድነት ተሳስበዉና ተፈቃቅደዉ ተከባብረዉ የሚኖሩበት ዞን ነዉ ፡፡ አብዛኛዉ ህዝብ የሚተዳደረዉ በከፊል አርብቶ አደርነት፤ በግብርና እና በማዕድን ምርት የሚተዳደር ህዝብን ጨምሮ የያዘ ነዉ፡፡

የህዝብ አሰፋፈሩ በመኖሪያ አካባቢ በገጠር 294,179 (87.09%) እና በከተማ 43,599 (12.9

Address

Jemu
Mizan Teferi
NONE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when West Omo Zone Plan and Development Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share