Guraferda woreda communication

Guraferda woreda  communication ቢፍቱ ጉራፈርዳ

ነገ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ በጉራፈርዳ ወረደ ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ  ቦታዎችን ጨምሮ ሌሎች  ዝግጅቶች ተደርገዋል -የየምርጫ ጣቢያ ሀላፊ...
31/05/2026

ነገ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ በጉራፈርዳ ወረደ ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ቦታዎችን ጨምሮ ሌሎች ዝግጅቶች ተደርገዋል -የየምርጫ ጣቢያ ሀላፊዎች።

በሸኮ ምርጫ ክልል ውስጥ የሚገኘው የጉራፈርዳ ወረዳ 29 የሸኮ መደበኛ እና 22 የሸኮ ልዩ በድምሩ 51 የምርጫ ጣቢዎች አሉ።

በወረዳው ነገ ለሚካሄደው የድምፅ መስጫ ፅለት በየምርጫ ጣቢያዎች በቂ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ያነጋገርናቸው የምርጫ ጣቢያ ሀላፊዎች ገልፀውልናል።

ሚስጥራዊ የድምፅ መስጫ ቦታዎችን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲ ታዛቢዎች ቦታዎች መዘጋጀታቸውን የኩጀ ከተማ ቀበሌ የምርጫ ጣቢያ ሀላፊ ማናዬ ጌታሁን ገልፀዋል።

ሀላፊው አክለውም መራጮች በድምፅ አሰጣጣጥ ሂደት እንዳይደናገሩ ስለድምፅ አሰጣጡ ሂደት የሚገልፁ ፖስተሮች በሚታይ ቦታ መለጠፉን ተናግረዋል።

በሴጋ ምርጫ ጣቢያ መደበኛና የሸኮ ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን የነገሩን ደግሞ የጣበያው ሀላፊ ጅሬኛ ኒጉሳ ናቸው።

ሃላፊ ሆነው በሚመሩት የምርጫ ጣቢያው ለነገው ድምፅ መስጫ ቀን በጣቢያው አስፈለጊው ዝግጅቶች መጠናቁን ተናግረዋል።

የጮዲት ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ ሀላፊ አየነ በቀለ በበኩላቸው ለመራጮች መጠለያና ማረፊያ ቦታ ከማዘጋጀት ጀምሮ የሚስጥር ድምፅ መስጫ ቦታዎች ፣ የፖለቲካ ፓርቲ ታዘቢዎች ማረፊያዎችን በማዘጋጀት ለነገው ድምፅ አሰጣጥ ምቹ ሆኔታዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል።ቤንች ሸኮ ቴሌቭዥን ዘግቧል።

"በነገው እለት ለሚካሄደው ምርጫ ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል :-የጉራፈረዳ ወረዳና የቢፍቱ ከተማ  ነዋሪዎች በነገው እለት የሚካሄደውን 7ተኛው  አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫን ተከትሎ መራጮች...
31/05/2026

"በነገው እለት ለሚካሄደው ምርጫ ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል :-የጉራፈረዳ ወረዳና የቢፍቱ ከተማ ነዋሪዎች

በነገው እለት የሚካሄደውን 7ተኛው አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫን ተከትሎ መራጮች 12:00 ስአት ጀምሮ የምርጫ ድምጻቸውን ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የጉራፈረዳ ወረዳና የቢፍቱ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎች እንደገለፁት ካርድ ያወጣ ማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል ግንቦት 24 ወደ ምርጫ ጣቢያ መሄድ እና ለሀገር የሚበጀውን መምረጥ ሀገር አለኝ ከሚል ዜጋ የሚጠበቅ እንደሆነም ገልጸዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ነገ ከለሊቱ 12:00ሰዓት ጀምሮ የምታደርገው 7ተኛ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫም ያለምንም ችግር ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ እንፈልጋለንም በማለት ለዚህም ኀላፊነታችን እንወጣለን በማለት ተናግረዋል።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ:-1. 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 871 መራጮች ተመዝግበዋል፣2.በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ፤3. 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም4. 80 የ...
30/05/2026

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ:-

1. 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 871 መራጮች ተመዝግበዋል፣

2.በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ፤

3. 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም

4. 80 የግል እጩዎች በምርጫው ይወዳደራሉ።

5. ፓርቲዎች በተደለደለላቸው የአየር ሰዓት 19 የክርክር መድረኮችን በአምስት ቋንቋዎች አካሂደዋል፤

6. ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከ250 ሺህ በላይ ተወካዮቻቸውን የምርጫውን ሂደት እንዲከታተሉ ይልካሉ፤

7. ለታዛቢነት የአፍሪካ ሕብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ተወካዮቻቸውን ልከዋል፤

8. 59 አባላት ያሉት የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ እየተመራ ሥራውን ይሰራል፤

9. ኢጋድ 26 አባላት ያሉት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድንን ያሰማራል፤

10. በሀገር ውስጥ የተደራጁ 55 ሲቪክ ማኅበራት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ ገብተዋል፤ 55ቱ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች 1 ሺህ 562 የምርጫ ታዛቢዎችን አሰማርተዋል።

11. የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ለ33፣ በአፋር ለ32፣ በአማራ ለ130፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለ22፣ በማዕካላዊ ኢትዮጵያ ለ35፣ በድሬዳዋ ለ48፣ በጋምቤላ ለ14፣ በሐረሪ ለ3፣ በኦሮሚያ ለ179፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ለ56፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለ22 ክልሎች የምርጫ ቁሳቁስ ተሰራጭቷል።
FMC

42 የፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ ይወዳደራሉ - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድበ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚወዳደሩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ...
29/05/2026

42 የፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ ይወዳደራሉ - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚወዳደሩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እና 80 የግል እጩዎች በምርጫው ይወዳደራሉ።

ፓርቲዎች በተደለደለላቸው የአየር ሰዓት 19 የክርክር መድረኮች በአምስት ቋንቋዎች ማካሄዳቸውንም ሰብሳቢዋ አንስተዋል።

ተፎካካሪዎቹ ከ250 ሺህ በላይ ተወካዮቻቸውን የምርጫውን ሂደት እንዲከታተሉ እንደሚልኩም ገልጸዋል።

ኡሁሩ ኬንያታ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመታዘብ አዲስ አበባ ገቡ7ኛውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ለመታዘብ የተሰየመውን የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድንን በሊቀመንበርነት የሚመሩት...
29/05/2026

ኡሁሩ ኬንያታ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመታዘብ አዲስ አበባ ገቡ

7ኛውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ለመታዘብ የተሰየመውን የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድንን በሊቀመንበርነት የሚመሩት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር መለስ ዓለም አቀባበል አድርገውላቸዋል።።

ኢቢሲ

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የ7ኛው ጠቅ...
27/05/2026

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ እንዲከናወን መወሠኑ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ በዕለቱ ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ለመንግሥታዊ እና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል።

በዚህም መሠረት:-

👉ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ፣

👉ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ፤

የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።

👉የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

በጉራፈረዳ ወረዳ በኩጃ ቀበሌ  የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊ ወጣቶች የምረጡ ቅስቀሳ አካሄዱለድጋፍም የኩጃ ወጣት ባለሀብቶች 120 ሺህ ብር በላይ በማውጣት ለወጣቶች ቲሸርትና ኩፍያ በመግዛት የብል...
27/05/2026

በጉራፈረዳ ወረዳ በኩጃ ቀበሌ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊ ወጣቶች የምረጡ ቅስቀሳ አካሄዱ

ለድጋፍም የኩጃ ወጣት ባለሀብቶች 120 ሺህ ብር በላይ በማውጣት ለወጣቶች ቲሸርትና ኩፍያ በመግዛት የብልፅግና ፓርቲ አባል ወጣቶች የይምረጡ ቅስቀሳ እንዲያካሂዱ ተደርጓል።

ለድጋፉም የወረዳው አስተባባሪዎች ፣የቀበሌዎች ደጋፊ አመራሮች እና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች የተገኙ ሲሆን ግንቦት 24 /9/2018 ዓ/ም ለሚካሄደው ምርጫ ሰላማዊ እንድሆን ወጣቶች የድርሻቸውን እንድዋጡ መልክት ተላልፏል

ለክልል ምክር ቤት  መደበኛ የብልፅግና ፓርቲ ወክለው የሚወዳደሩ  እጩ ተወዳዳሪዎች በጉራፈረዳ ወረዳና በቢፍቱ ከተማ በመገኝት እራሳቸውን አስተዋወቁ።7ኛ ዙር ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ለክልል...
27/05/2026

ለክልል ምክር ቤት መደበኛ የብልፅግና ፓርቲ ወክለው የሚወዳደሩ እጩ ተወዳዳሪዎች በጉራፈረዳ ወረዳና በቢፍቱ ከተማ በመገኝት እራሳቸውን አስተዋወቁ።

7ኛ ዙር ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ለክልል ምክር ቤት መደበኛ የብልፅግና ፓርቲ ወክለው የሚወዳደሩ እጩ ተወዳዳሪዎች በጉራፈረዳ ወረዳና በቢፍቱ ከተማ በመገኝት ከወረዳውና ከቢፍቱ ከተማ አስተባባሪዎች ጋር አጭር ውይይት በማድሰግ እስከ እስከ ኩጃ ክላስተር በመንቀሳቀስ ለህዝቡ እራሳቸውን አስተዋዉቀዋል።።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤና ለክልል ምክር ቤት የሸኮ ልዩ እጩ ተወዳዳሪ አቶ ወንድሙ ኩርታ እንደገለፁት ምርጫው ሰላማዊና ፍትህዊ ሁኖ እንድጠናቀቅ ሁሉም ሀላፊነቱን መዋጣት አለበት በማለት ህዝቡ የወሰደውን ካርድ በመያዝ የሚበጀውን መንግስት መምረጥ እንዳለበት ተናግረዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና ለክልል ምክር ቤት የሸኮ ልዩ እጩ ተወዳዳሪ አቶ ደግፊ ኩድን ለምርጫው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በማቅረብ ምርጫው ሰላማዊና ፍህታዊ ሁኖ እንድጠናቀቅ አመራሩና አባላቱ ግንባር ቀደም ሁኖ መስራት አለበት በማለት ተናግረዋል።

ለክልል ምክር ቤት መደበኛ የብልፅግና ፓርቲ ወክለው የሚወዳደሩ እጩ ተወዳዳሪዎች አቶ አልማው ዘውዴ፣ወ/ሮ ተካዬ ኮቲ፣ወ/ሮ ካህኒ ገመዳ፣አቶ ዳዊት ተሰማ ፣ አቶ አለማየሁ አለሙ እና ወ/ሮ አብነት በቦታው በመገኝት እራሳቸውን ለህዝብ አስተዋዉቀዋል።

የጉራፈረዳ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኦይሳ አለሙ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አደሀ (አረፋ)  በዓል የእንኳን አደረሳችሁ  መልዕክት አ...
26/05/2026

የጉራፈረዳ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኦይሳ አለሙ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አደሀ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

በመልዕክታቸውም የዓረፋ በዓል ህዝበ ሙስሊሙ ለፈጣሪ በመታዘዝ እርስ በራስ በመደማመጥ በመረዳትና በመተሳሰብ፣ በጎነትን ቸርነትንና ተካፍሎ የመብላትን መንፈሳዊ ክዋኔዎችን በመፈፀም የሚከበር በዓል መሆኑን እና በማህበረሰቡ መካከል አብሮነትን፣ አንድነትን፣ ወንድማማችነትን፣ ይቅር ባይነትን የሚያጎልብትም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ታላቁን የአረፋ በዓል ሲያከብር የመረዳዳት፣ የመደጋገፍና ለተቸገሩ ወገኖች የመድረስን ልምድ ለማጠናከር አቅመ ደካሞችን በመጠየቅ፣ የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡

በድጋሚ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉም በዓል የጤና ፣የፍቅርና የመተሳሰብ እንድሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።

የጉራፈረዳ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ ኦይሳ አለሙ

የጉራፈረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታጋይ ኤሊያስ 1447 ኛውን የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉየጉራፈረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታጋይ ኤሊያስ...
26/05/2026

የጉራፈረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታጋይ ኤሊያስ 1447 ኛውን የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የጉራፈረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታጋይ ኤሊያስ ባስተላለፉት መልዕክት የኢድ አል /አረፋ በዓል በፍቅር፣ በአንድነትና በወንድማማችነት እንዲከበር ህዝበ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ አንድነቱንና ወንድማማችነቱን ማጠናከር አለበት ብለዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ታላቁን የአረፋ በዓል ሲያከብር አቅመ ደካሞችን በመጠየቅ፣ የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስ መሆን እንደሚኖርበትም አመልክተዋል።

ሀገር፣ ቤተሰብ፣ ልማትና እድገት የሚኖረው ሰላም ሲኖር በመሆኑ በወረዳው ያለውን ሰላም በዘላቂ በማፅናት ለሰላም ከፍ ያለ ዋጋ በመስጠት በሰዎች መካከል የትብብርና ወንድማማችነት መንፈስ ማስፈን እንደሚገባ ገልፀዋል።

የእስልምና እምነት አስተምህሮ ሰላምን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን የሚሰብክ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በዜጎች መካከል አብሮነትን፣ አንድነትን፣ ወንድማማችነትን፣ ይቅር ባይነትን የማጎልበት ድርሻው ላቅ ያለ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

እንደ ወረዳ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለማየት ፤ የሰላምና ልማት ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅብናል ብለዋል።

በዓሉ የሠላም፣ የአንድነት፣ የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የጉራፈረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
አቶ ታጋይ ኤሊያስ

Address

Biftu
Mizan Teferi

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guraferda woreda communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Guraferda woreda communication:

Share