ምዕራብ ኦሞ ዞን ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ

ምዕራብ ኦሞ ዞን ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ምዕራብ ኦሞ ዞን ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ, Public & Government Service, Mizan Teferi.

13/03/2026

የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አዋጅ

👉 የፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማቀዴ፣ የተለያዩ
ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግልቶችን ዜጎች ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ
እና በፍትሕ አስተዲደር ቀልጣፊፋና ውጤታማ አሠራር እንዲኖር ለማስቻል የሲቪል ምዝገባ እና የቤተሰብ ምዝገባ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ በመሆኑ ፤

👉 ዜጎች ወሳኝ ኩነቶችን በአግባቡና በወቅቱ እንዲያስመዘግቡ የሚያስችል ተደራሽ፣ ሁሉን አቀፍ እና አስገዳጅ የሆነ የሲቪል ምዝገባ እና የቤተሰብ
ምዝገባ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤

👉 የብሔራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ለማስጠበቅ እና በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ለዜጎች የሚሰጡ አገልግልቶችን ቀልጣፋ ለማድረግ የሲቪል ምዝገባ
እና የቤተሰብ ምዝገባ አገሌግልት መስጠት አስፈሊጊ በመሆኑ የሲቪሌ እና ቤተሰብ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 1370/2017 ተደንግጓል ።

15/04/2024

የሕጻናትን እና የሴቶችን መብት ለመጠበቅ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ሚና

እንደ ልደት፣ ሞት፣ ጋብቻ እና ፍቺ ያሉ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባን በተሟላ ሁኔታ የሚሰራ የሲቪል ምዝገባ እና የወሳኝ ስታስቲክስ (CRVS) ስርዓት ዋና አካል ነው። የእነዚህ ወሳኝ ኩነቶች ትክክለኛ እና የተሟላ ምዝገባ የሕጻናትን እና የሴቶችን መብትና መብት ለመጠበቅ ወሳኝ ነው። ይህን የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የህጻናት እና የሴቶች መብት ጥበቃን የሚደግፍባቸውን ቁልፍ መንገዶች ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርቧል ።

1. የልደት ምዝገባ፡-
- የልደት ምዝገባ የሕፃን ማንነት፣ ዕድሜ እና ዜግነት ህጋዊ ማረጋገጫ ይሰጣል፣ ይህም እንደ ጤና አጠባበቅ፣ ትምህርት፣ ማህበራዊ ጥበቃ እና ዜግነት ያሉ መሰረታዊ መብቶችን እና አገልግሎቶችን ለማግኘት አስፈላጊ ነው።
- የልደት ምዝገባ አለመኖር ህጋዊ የመታወቂያ ሰነድ የሌላቸው ህጻናት የበለጠ ተጋላጭ በመሆናቸው የልጅ ጋብቻ፣ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ ህገወጥ ዝውውር እና ሌሎች የብዝበዛ አደጋዎችን ይጨምራል።
- ዓለም አቀፋዊ የወሊድ ምዝገባን ማረጋገጥ በተለይም የተገለሉ እና ለመድረስ አስቸጋሪ ለሆኑ ህዝቦች የልጆችን መብት ለማስጠበቅ ወሳኝ እርምጃ ነው።

2. የሞት ምዝገባ፡-
- የሞት መንስኤን ጨምሮ ትክክለኛ የሞት ምዝገባ መከላከል የሚቻለውን የእናቶች እና ህጻናትን ሞት ለመለየት እና መፍትሄ ለመስጠት የሚረዳ ሲሆን ይህም የተሻሻሉ የጤና ውጤቶችን እና ፖሊሲዎችን ያመጣል.
-የሞት ምዝገባ መረጃ የእናቶችና ህጻናትን ሞት ለመቀነስ የታለሙ ፕሮግራሞችን እና ጣልቃገብነቶችን አፈፃፀም እና ውጤታማነት ለመከታተል ያስችላል።

3. የጋብቻ እና የፍቺ ምዝገባ፡-
- የጋብቻ እና የፍቺ ምዝገባ እንደ ልጅ ጋብቻ፣ የግዳጅ ጋብቻ እና የቤት ውስጥ ጥቃትን የመሳሰሉ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ህጋዊ ሰነዶችን በማቅረብ ለእነዚህ ክስተቶች እውቅና ለመስጠት ይረዳል።
- የጋብቻ እና የፍቺ ምዝገባ መረጃ ከሴቶች መብት፣ ከቤተሰብ ምጣኔ እና ከሥርዓተ-ፆታ ጥቃት ጋር የተያያዙ ፖሊሲዎችን እና ፕሮግራሞችን ማሳወቅ ይችላል።

4. ከሌሎች ስርዓቶች ጋር ትስስር;
- የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ማህበራዊ ጥበቃ እና ጤና አጠባበቅ ካሉ ሌሎች ስርዓቶች ጋር ማቀናጀት አስፈላጊ አገልግሎቶችን እና መብቶችን በማመቻቸት የህጻናት እና የሴቶች መብቶች ጥበቃን ሊያሳድግ ይችላል።
- ለምሳሌ የወሊድ ምዝገባን ከማህበራዊ ጥበቃ መርሃ ግብሮች ጋር ማገናኘት ህጻናት በተለይም ከተገለሉ ማህበረሰቦች የመጡ ጥቅማጥቅሞችን እና ድጋፎችን እንዲያገኙ ያስችላል።

በአጠቃላይ ፡-
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ሥርዓትን ማጠናከር የህጻናትና ሴቶችን መብትና ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ እርምጃ ነው። ህጋዊ ማንነትን በማቅረብ፣ አስፈላጊ አገልግሎቶችን በማመቻቸት እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ መረጃ በማመንጨት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የህጻናትና የሴቶችን መብት በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። መንግስታት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና አለምአቀፍ አጋሮች ማንኛውም ልጅ ወይም ሴት ወደ ኋላ እንዳይቀር ሁሉን አቀፍ እና ሁሉን አቀፍ የCRVS ስርዓቶችን ማሳደግ ቅድሚያ መስጠት አለባቸው።

28/06/2022
15/06/2022

ክፍል 3
የተከሰቱ ኩነቶችን ማስመዝገብ በደስታ ሆነ በሐዘንም ጊዜም ይጠቅማል፡፡
የሞት ኩነት ምዝገባ በህይወት ለሚኖረው የትዳር ጓደኛ የማግባት ፈቃድ ለማስገኘት የሚጠቅም ስለሆነ መምህርት ናሴዴ ኦሎቻካጊ እንደገና ጋብቻ ለመመስረት ስለፈለገች ከእርሷ ጋር ከሚያስተምራት መምህር ኡዱሉ ባርዱላ ጋር ለመጋባት ሁለቱም ተስማምቶ የሟቹን የሞት ኩነት ሰርተፍኬት በመያዝ ጋብቻቸዉን እሷ ሁለት ምስክር ይዛ ስትቀርብ እርሱም ሁለት ምስክር፤የነዋሪነት መታወቂያ እና ሁለት ጉርድ ፎቶ በመያዝ በኪብሽ 01 ቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ በክብር መዝገብ ሹም ፊት ቃልኪዳን በመግባት ህጋዊ ጋብቻቸዉን ፈጽሟሉ፡፡ ስለዚህ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ፡-
ዜጐች በሕገ-መንግስቱ እና በሌሎች ሕጐች የተረጋገጡላቸው መብቶች በአግባቡ እንዲጠቀሙ፣
በሀገሪቱ የሚዘጋጁ ፖሊሲዎች እና ዕቅዶች በተሟላ መረጃ እንዲደገፉ ለማስቻል፣
ዜጎች በመንግስት የሚሰጡ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በፍትሃዊነትና በተሟላ ሁኔታ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና
በፍትህ አካላት ማስረጃ አቀራረብና ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮች እንዲቀረፉ በማድረግ የፍትህ ሥርዓቱን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ ነዉ፡፡
ስለዚህ ከላይበተጠቀሰዉ ምስሌ ጠቃሚ ትምህርረት የተሰጠ ስለሆነ እርሰዎ ከትዳር አጋርዎ ጋር በቀበሌ ጽ/ቤት የተከሰቱ ኩነቶችን በማስመዝገብ ተጠቃሚ ይሁኑ!ለጓደኛዎ ያጋሩ! አስተያየትዎን ይስጡ! ለጓደኛዎ ይጋብዙ !
ማሳሰቢያ፡-ከወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የሚገኙ ግለሰባዊ መረጃዎች ምስጢራዊነታቸው የተጠበቀ ሲሆን መረጃዎች በህግ ከተፈቀደላቸው አካላት ውጪ መረጃውን ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት የተከለከለ ስለሆነ ለማስተማሪያነት የተዘጋጀ ምሳሌያዊ ጽሑፍ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
ምንጭ፡-የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ ትምህርትና ስልጠና ክፍል

15/06/2022

ክፍል 2
የተከሰቱ ኩነቶችን ማስመዝገብ በደስታ ሆነ በሐዘንም ጊዜም ይጠቅማል፡፡

መምህርት ናሴዴ ኦሎቻጊ እርሱን ስትጠብቅ በ2000 ዓ/ም በድጋሚ ለ7 ዓመት በመከላከያነት ለማገልግል የዉል ፈቃዱን ካደሰ በኋላ ቤተሰብ ለመጠየቅ ፈቃድ ጠይቆ ወደ እጮኛዉ አገር ሱርማ ወረዳ በመምጣት ጋብቻዉን በአገር ባህል ከፈጸሙ በኋላ ወደ መከላከያ ስመለስ በተጋቡበት በ9 ወሩ ወንድ ልጅ ተወለደ፡፡በፈቃድ ከመካከያ እየተመላለሰ ሚስቱንና ልጁን እየጠየቀ ሳለ በመከላከያዉ በተከታታይ ባስመዘገባቸዉ ዉጤት መከላከያዉ ፻አለቃነት ማዕረግ ስሰጥ ቆይቶ የመጀመሪያ ልጁ በተወለደዉ 6 ዓመቱ ላይ ሌላ ሴት ልጅ ተወለደች፡፡ የወሣኝ ኩነት ምዝገባ እና የብሔራዊ መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 760/2004 እና በቅርቡ የተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 1049/2010 የወሳኝ ኩነቶች /የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻ፤ የፍቺና ጉዲፈቻ/ ምዝገባ መረጃ ዜጐች መንግስት በሚዘረጋው የህግ፣ የአስተዳደርና የማህበራዊ አገልግሎት አቅርቦት ፍትሀዊ ለማድረግና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ መሆኑን በሚዲያ የሰማዉ ፻አለቃ ከንፈሼ ቦሮዳ ፈቃድ በመጠየቅ በእረፍት ሠዓቱ ከሚስቱ ጋር የተፈጸመዉን ባህላዊ ጋብቻን በወቅቱ የነበሩ ሽማግሌዎችን በመያዝ በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱርማ ወረዳ ኪብሽ 01 ቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት በክብር መዝገብ ሹም ፊት የጋብቻዉንና የልጆቹንም የልደት ኩነት ምዝገባን ጨምሮ ካስመዘገበ በኋላ የእረፍት ሰዓቱን ጨርሶ ወደ መከላከያ ስመለስ በመከላከያዉ በተከታታይ ባስመዘገባቸዉ ዉጤት መከላከያዉ የጀነራልነት ማዕረግ ከሰጠ በኋላ ሚስቱና ልጆቹ ባሉበት ተዘዋዉሮ አካባቢዉን እያገለገለ ባለበት ጊዜ በደረሰዉ ድንገተኛ በሽታ ታሞ በሆስፒታል ስታከም ቆይቶ እንደማናቸዉም ሰዎች በልደት አማካይነት ወደ ዓለም ህብረተሰብ እንደሚቀላቀሉና በአንጻሩ በሞት አማካይነት ከዚህ ዓለም እንደሚለዩ በሞት ተለየ ፡፡የመከላከያ ሚንስቴሩም የሟችን መብት ለማስከበር ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ከሚሰጠዉ ጥቅም አንጻር ቤተሰብ መረጃ እንዲያቀርብ ሲጠየቅ መምህርት ናሴዴ ኦሎቻካጊ የጋብቻ ሰርተፍኬትእና የልጆቹን ልደት ሰርተፍኬት ይዛ ስትቀርብ የመከላከያዉ ሚንስቴሩም ለሟች ቤተሰብ ስለመሞቱ ህጋዊ መረጃ በመስጠት ፤ውርስ የሚገባቸው የመውረስ ጥያቄን በማስተናገድእና ሌሎችንም ጥቅሞች እንዲከበር አድርጓል፡፡(ክፍል 3 ይቀጥላል)
ማሳሰቢያ፡-ከወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የሚገኙ ግለሰባዊ መረጃዎች ምስጢራዊነታቸው የተጠበቀ ሲሆን መረጃዎች በህግ ከተፈቀደላቸው አካላት ውጪ መረጃውን ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት የተከለከለ ስለሆነ ለማስተማሪያነት የተዘጋጀ ጽሑፍ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
ምንጭ፡-የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ ትምህርትና ስልጠና ክፍል

14/06/2022

የተከሰቱ ኩነቶችን ማስመዝገብ በደስታ ሆነ በሐዘንም ጊዜም ይጠቅማል፡፡
ወሳኝ ኩነት ሲባል በአንድ ሰው ላይ ከልደት እስከ ሞት የሚከሰት ተፈጥሮአዊ እና ማህበረሰባዊ የአቋም ለውጥ ጠቋሚ ክስተት እንደመሆኑ መጠን የተከሰቱ ኩነቶችን ማስመዝገብ በደስታ ሆነ በሐዘንም ጊዜም ይጠቅማል፡፡ከዚህ በታች ያለዉ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የሚሰጠዉን ጥቅም የሚያሳይ ምሳሌ ነዉ፡፡ከዚህ ምሳሌ ምን ይማራሉ?
ክፍል 1
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ተጠቃሚ የሆኑት ከንፈሼ ቦሮዳ እና ናሴዴ ኦሎቻካጊ አንዱ አካላት ናቸዉ፡፡ ከንፈሼ ቦሮዳ የኮንታ ዞን ተወላጅ በ1973 ዓ/ም በጨታ ቀበሌ ተወልዶ በ1980 ዓ/ም ጨታ 1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ስማር ቆይቶ በ1991 ዓ/ም ጭርሶ ሳለ በ1992 ዓ/ም በወረዳ ላይ መምህራንን ለማሰልጠን በወጣዉ ማስታወቂያ ተወዳድሮ በማለፍ ቦንጋ መምህራን ማሰልጠኛ ለመሰልጠን ስመጣ በምዕራብ ኦሞ ዞን በሱርማ ወረዳ ኪብሽ ቀበሌ ተወላጅ የሆነች ናሴዴ ኦሎቻጊ በ1973 ዓ/ም ተወልዳ በ1980 ዓ/ም በኪብሽ ከ1ኛክፍል እስከ 6ኛክፍል ተምራ ከ7ኛ እስከ12ኛ ክፍል ሚዘን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስትማር ቆይታ በ1991 ዓ/ም አጠናቃ ሳለች በወረዳዉ በወጣዉ የመምህራን ስልጠና ማስታወቂያ ተወዳድራ በማለፍ ቦንጋ መምህራን ተቋም ስትሰለጥን ከእጩ መምር ከንፈሼ ቦሮዳ ጋር ከተቋሙ ተመርቀዉ ሲወጡ እንደምጋቡ ከተስማሙ በኋላ ስልጠናዉን በ1992 ዓ/ም በመጨረስ ተመርቀዉ ወደ መጡበት ወረዳ ማህበረሱን በመምህርነት ሙያ ለማገልገል በገቡት ቃል መሠረት እያገለገለ ሳሉ መ/ር ከንፈሼ ቦሮዳ በ1993 ዓ/ም በኮንታ ወረዳ የአገር መከላከያ ሠራዊትነት ማስታወቂያ ስወጣ በአገር መከላከያ ሠራዊትነት ሙያ ማገልገል የአገርን ደህንነት መጠበቅነዉ በማለት በመወሰነዉ ዉሳኔ መሠረት ተመዝግቦ ከሄደ በኋላ ለእጮኛዉ መሄዱንና ስመለስ እንደሚጋቡ በደብዳቤ ሲያሳዉቅ እጮኛዉ መምህርት ናሴዴ ኦሎቻጊ በኪብሽ 1ኛ ደረጃ ስታስተምር የነበረችዉ በሐሳቡ ተስማማች፡፡(ክፍል 2 ይቀጥላል)
ምንጭ፡-የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ ትምህርትና ስልጠና ክፍል

መዛግብቶችን መጠበቅ ስልጣን ከተሰጠዉ አካል የሚጠበቅ ኃላፊነት ነዉ፡፡              የክብር መዝገቦች አሰረጨጨት ለክልል የሚያገለግሉ የክብር መዝገቦች አግባብ ካለዉ የፌደራል አካል ጋ...
06/06/2022

መዛግብቶችን መጠበቅ ስልጣን ከተሰጠዉ አካል የሚጠበቅ ኃላፊነት ነዉ፡፡
የክብር መዝገቦች አሰረጨጨት ለክልል የሚያገለግሉ የክብር መዝገቦች አግባብ ካለዉ የፌደራል አካል ጋር በመተባበር የክልሉ አካል አዘጋጅተዉ ለሁሉም የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤቶች ያሰራጫል፡፡የመዝገቦችም አያያዙና አቀማመጡ ኩነቶች በግለሰቦች ላይ መከሰታቸውን ወይም መድረሳቸውን በትክክል የሚያረጋግጡ ሕጋዊ የመንግሥት ቋሚ ሰነዶች ስለሆነ ለሥራ ቅልጥፍናና ለአያያዝ በሚያመች ሁኔታ መዘጋጀትና ማስረጃነታቸው ለረጅም ዘመናት በሚያገለግል አኳኋን በከፍተኛ ጥንቃቄ መያዝ ይጠበቃል።የክብር መዝገቦች አያያዝ ትክክለኛነትና ለሥራ ያላቸው አመቺነት የሚለካው መዝገቦቹ ለሥራ በሚፈለጉበት ጊዜ በሚቀርቡበት ፍጥነት ልክና ደህንነታችውን በመጠበቅ ባላቸው አመቺነት ነው።
መልካም ተሞክሮ
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉት ከ6ቱ ዞን ዳዉሮ፤ኮንታ፤ሸካ፤ካፋ፤ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞን መካከል አንዱ ሸካ ዞን ሲሆን በሸካ ዞኑ ከሚገኙ 3 ወረዳና 2 ከተማ አስተዳደር ዉስጥ የኪ ወረዳ አንዱ ነዉ፡፡ በወረዳዉ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባን ከሚያካሂዱት 22 ቀበሌያት ዉስጥ 7 ቀበሌያት በተከታታይ የሚመዘግቡ፤10 ቀበሌያት የሚያንጠበጥቡእና 5 ቀበሌ በጸጥታ ችግር ምክንያት ምዝገባዉን ያቋረጡ ናቸዉ፡፡በ2014 በጀት ዓመት የምዝገባዉ አፈጻጸም ሽፋን ከፍተኛ 2 ቀበሌ ፤መካከለኛ 10 ቀበለያት እና ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገቡ10 ቀበሌያት ናቸዉ፡፡እስከ አሁን በወረደዉ ቀበሌያት ከተሠራጨዉ ስርተፍኬትና ክብር መዝገብ ዉስጥ የክብር መዝገብ ልደት 64፤ሞት 58፤ጋብቻ 64፤ፍቺ 58 ሲሆን ቀሪ በወረዳዉ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በንብረትነት ልደት 10፤ሞት 10፤ጋብቻ 10፤ፍቺ 10እና ሰርተፍከቶችንም ጭምር በመረጃነት ተይዟል፡፡ወረዳዉ ቀበሌያትን በቼክ ሊስት ስደገፍ ከወረዳ ወደ ቀበሌ የመጡ/የተላኩ/የወሳኝ ኩነቶች ክብር መዛግብትና ሰርተፍኬት የተሠራ፤ያልተሠራ፤የተበላሸ፤ቀሪ፤የወደመእና ከምዝገባዉ የተገኘዉ ገንዘብ ለወረዳዉ መንግስት ገቢ የተደረገዉንና ገቢ ያልተደረገዉን የመለየት ስራ ይሠራል፡፡
ስለዚህ የሕዝብ የክብር መዝገቦች የመንግስት ንብረት የሆኑና ወሳኝ ኩነቶች በትክክል መከሰታቸውን የሚያረጋግጡ የህግና የአስተዳደር ሕጋዊ ሰነዶች ስለሆኑ የወሳኝ ኩነት ክስተቶችን በሕዝብ የክብር መዝገቦች ውስጥ እንዲመዘግብ ሥልጣን የተሰጠው መዝጋቢ ዋነኛ ተግባር ሲሆን ኩነቱን እንዲያስመዘግብ በሕግ ኃላፊነት የተሰጠው አስመዝጋቢ በሚሰጠው መረጃ ላይ በመመሥረት የራሱን ተጨማሪ ማጣሪያ ካደረገ በኋላ ኩነቱንና ከኩነቱ ጋር ተዛማጅ የሆኑ የሥነ-ሕዝብ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን ለዚህ ተግባር በተዘጋጁ የሕዝብ የክብር መዝገቦችና የወሳኝ ኩነት ስታቲስቲክስ ሪፖርት ቅጾች ውስጥ የተመዘገበዉን መዝገብ በጥንቃቄ በመጠበቅ በመረጃነት መያዝ የመዝጋቢዉ አካልእና መዛግብቶችን እንዲጠብቅ ስልጣን ከተሰጠዉ አካል የሚጠበቅ ኃላፊነት ነዉ፡፡
ዘገበዉ፡-የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ ትምህርትና ስልጠና ክፍል

17/04/2022

ኩነቶቹ ለምን ወሳኝ ኩነት ተባሉ?
***
ወሳኝ ኩነት ሲባል በአንድ ሰው ላይ ከልደት እስከ ሞት የሚከሰት ተፈጥሮአዊ እና ማህበረሰባዊ የአቋም ለውጥ ጠቋሚ ክስተት ማለት ነው ፡፡ እነዚህም:-1)ተፈጥሯዊኩነቶች፡-በሕይወት መወለድና ሞት ሲሆኑ፣
2)ማህበረሰባዊ ኩነቶች፡-ጋብቻ፣ፍቺ፣ጉዲፈቻ፣
ልጅነትን መቀበል/አባትነትን በፍ/ቤት ማወቅ፣ ናቸዉ። ኩነቶቹ ወሳኝ የተባሉበት ዋነ ዋና ምክንያቶች :-
1/ በየሀገሮች ህገ-መንግስት እና በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች የታወቁ መሰረታዊ የሰብአዊ ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መብቶችን ለመጠበቅ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ እና ግብዓት በመሆናቸው
2/ ግለሰቦችን ከመንግስት ጋር በማገናኘት የማንነት መነሻ ህጋዊ መረጃዎች በመሆናቸው እና
3/ የአንድን ሀገር ህዝብ ብዛትና ዕድገት የሚወስኑ ፣ ለህብረተሰቡ አልፎም ለግለሰቦች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚዘጋጁ ፖሊሲዎች እና ፕሮግራሞችን በመቅረጽ ፣ ዕቅዶችን በማዘጋጀት፣ አፈጻጸማቸውን በመከታተልና በመገምገም ወሳኝ የስነ-ህዝብ እና ጤና መረጃዎች በመሆናቸው ነው፡፡
የወሳኝ ኩነቶችም ዝገባ መርሆች፦
ሀ/ የማይቋረጥ/continuity/፡-
ለ/ ቋሚነት/permanence/፡
ሐ/ አስገዳጅነት/compulsoriness
መ/ ሁሉን አቀፍ /universality/:-
ሠ. ምስጥራዊነት (confidentiality) ናቸዉ።
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ባህሪያት፦
ሀ.ተከታታይነት/continuity/
ለ. ወጥ እና ተነጻጻሪ/consistency & comparability/-
ሐ.የተሟላ/completeness/
መ.ትክክለኛነት/correctness/
ሠ.በህግ ፊት በራሱ በቂ የሆነ ማስረጃ (authenticity)
ረ.አዋጭነት/cost-effective/
ሰ.ተቋማዊ ዘርፈ-ብዙነት ያለው /multi-Sectoral/
ሸ.ሙያዊ ዘርፈ -ብዙነት ያለው /multi-desciplinary/ ናቸዉ።
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አስፈላጊነት፦
1/ ዜጐች በሕገ- መንግስቱ እና በሌሎች ሕጐች የተረጋገጠላቸውን መብቶች በአግባቡ እንዲጠቀሙ ለማስቻል፡
2/ ዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በተሟላ ሁኔታ እንዲያገኙ ለማድረግ፡
3/ በሀገሪቱ የሚዘጋጁ የተለያዩ ፖሊሲዎች እና እቅዶች በተሟላ መረጃ እንዲደገፍ ለማስቻል
4/ በፍትህ አካላት ማስረጃ አቀራረብ እና ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ነዉ።
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጠቀሜታ፦
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አስፈላጊነት መሰረታዊ መነሻ ግለሰቦች በዜግነታቸው በሀገራቸው ኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ሙሉ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን አልፎም በተለያየ ጊዜያት በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉትን የስብዓዊ፣ የማህበራዊና ፖለቲካዊ መብቶች ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሕጋዊ፣ ግለሰባዊና መንግስታዊ መረጃዎችን ማስገኘት ነው፡፡
የምዝገባ ሥርዓቱ የሚያስገኛቸው ህጋዊ፣አስተዳደራዊና ስታስቲክሳዊ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ይገኙበታል።
>

16/03/2022

የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ለህግ፣አስተዳደርና ስታስቲክ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል።
++++++++++++++++++++++++++++
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ለግለሰቦች እና ለመንግስት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ይሰጣል፡፡ እነዚህን ጠቀሜታዎች በጥቅሉ በሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
ሀ. ህጋዊ ጠቀሜታ
ከወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት የሚገኙ መረጃዎች ከህግ አንፃር ለግለሰብ፣ ለማህበረሰብ ለመንግስት በጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን ከእነዚህም ዋና ዋናዎቹ፡-
መረጃዎቹ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለመገልገል እንዲሁም ህጋዊ ማንነት ለማግኘትና ትክክለኛ ዕድሜን ለማወቅ፣ ያለዕድሜ ጋብቻ፣ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ፣ ህገወጥ የህጻናት ዝውውር፣ እንዲሁም ዕድሜን መሰረት ያላደረገ የህጻናት እስርን ለመከላከል፣ የወራሽነት መብትን ለማረጋገጥ ፓስፖርት ለማውጣት፣ የብድር አገልግሎት ለማግኘት፣ የመምረጥና የመመረጥ መብትን በማስከበር ረገድ ግለሰቦች ማንነታቸውን ለመግለጽና የኩነቶችን መከሰት ለሚፈልጉት የመብትና የአገልግሎት ጥያቄ በመረጃነት በማቅረብ ይጠቀሙባቸዋል፡፡
ለ.አስተዳደራዊ ጠቀሜታ
ወሳኝ ኩነቶች በአስተዳደር ዘርፍ መንግስት የሚያወጣቸውን ጥቅል ዕቅዶችና ፕሮግራሞችን መሠረት በማድረግ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ወቅታዊ፣ ቀጣይና ቋሚ ክትትልን የሚያስችል የአሠራር ሥርዓትን ለመዘርጋት ጥቅም ላይ የሚውሉ መረጃዎችን በማፍለቅ ተግባር ላይ የሚዉልበት ነው። ለህዝብ ጤና አጠባበቅ ፕሮግራሞች፣ የትምህርት ፕሮግራሞችን በፍትሃዊነት ለማዳረስ፣ ለህዝብ ማህበራዊ ደህንነት አደጋ ለመከላከልና ወንጀልን ለመቀነስ የአንድን አካባቢ ትክክለኛ የህዝብ ብዛት መረጃ ለማወቅ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
ሐ. ስታትስቲካዊ ጠቀሜታ
ስታትስቲካዊ መረጃዎች ዕቅዶችን ለማቀድ፣ ስትራቴጂዎችን፣ ፕሮግራሞችንና ፖሊሲዎችን ለመንደፍ፣ ጥናትና ምርምር ለማካሄድ፣ የህዝብ ቁጥር ለውጥን እና የጤና ልማት ውጤት አመልካች መረጃዎችን ለማመንጨት፣ የሞት ምክንያት፣ የበሽታ ወረርሽኝ ወይም ያልተለመዱ አዳዲስ በሽታዎች መከሰትና የጤና ሥርጭትን ለመረዳት የሚያስችል መረጃ ለማመንጨት ይጠቅማል፡፡

08/03/2022
16/02/2022

የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ታርካዊ አጀማመር
በአለም ደረጃ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አጀማመር መሠረቱ የሃይማኖት ተቋማት ቢሆንም ተቋማቱ ይመዘግቡ የነበረዉ ኩነቱን ሳይሆን ስርዓቱን ነበር ።ለምሳሌ ልደቱን ሳይሆን ክርስትናዉን፣ሞቱን ሳይሆን ቀብሩን እንዲሁም ጋብቻዉን ሳይሆን ሰርጉን ነበር ።ይህም ከ15ኛዉክፍለዘመንጀምሮበስፔን፣በእንግሊዝ(በ1538 )፣በፈረንሳይ( በ1539)፣እንዲሁም በ17ኛዉ ክፍለዘመንበሌሎችሀገሮችበስዊድን( በ1608)፣ካናዳ(በ1610 )።ይሁን እንጂ ዘመናዊ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የመንግሥት ሥራ ሆኖ በመንግስት ህግ የተካተተዉ እ.አ .አ በ1804 በንጉሠናፖሊዮን አማካይነት በወጣዉ የፈንሳይ ሲቪል ህግ ነዉ።
በአፈርካ ደረጃ
በአፈርካ የአመሠራረትና ዕድገት ታርክ በአማዛኙ ከቀኝ ግዛት መስፋፋት ጋር የተያያዘ ሲሆን አንዳንድ የአፈርካ አገራት በዘመናት የሚቆጠር የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ታርክ አላቸዉ( ሞሪሺየስ1667፣ጋና በ1888)።በመጀመሪያ ደረጃ የምዝገባዉ ስራ አፈርካዊያንን እንዲያካትት አልተደረገም።ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነዉ በደቡብ አፈርካ እስከ ቅርብ ጊዜ የነበረዉ ሲሆን የወሳኝ ኩነቱ ምዝገባ ጥቁሮችን እንዲካተቱ የተደረገዉ እ.አ .አ 1986ነዉ።
ማናቸዉም ቅኝ ገዥዎች በሀገራቸዉ የተከተሉት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስርዓት በአፈርካዊያኑ ቅኝ ገዥዎቻቸዉ እንዲታወቅም ሆነ እንዲተገበር አላደረጉም።በቀኝ ገዥዎች ፍላጎትና ቅኝት ላይ የተመሠረተ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አሠራር ከነፃነት በኋላ ቅርቱን ይዞ ለሀገርቱ ህጎች በሚጠቅምና ሀገራዊ ገጽታ እንዲኖረዉ አድርጎ ለማስኬድ በየሀገሩ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም የምዝገባ ስርዓቱ በሚፈለገዉ ደረጃ ተሟልቶ ሊገኝ አልቻለም።በዚህም ሂደት በአፈርካና በሌሎች አህጉሪት በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሀገሮች በማገዝ ሰፊ ዓለም አቀፍ ንቅናቄ የነበረዉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኩል ነበር።የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስርዓትንለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊ ችግር አድርጋና በከፍተኛ የመንግስትና ፖለቲካ አካላት መነጋገር የተጀመረዉ እ.አ.አ ከ2009 ጀምሮ ነዉ።በዚሁም ጥረት የመጀመሪያዉ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የአፈርካ የሚንስትሮች ጉባኤ እ.አ.አበ2010 በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ በቅቷል።
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ በኢትዮጵያ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ በኢትዮጵያ በ1952 የፍትሃብሔር ህግ ልደት፣ሞትና ጋብቻ ማስመዝገብ ግዴታ መሆኑ ቢታወጅም በዚሁ ልክ አንቀስ3361 ምዝገባዉ በመንግስት እስክታዘዝ ድረስ እንደማይጀመር ተደንግጓል።ከኩነቶቹ ምዝገባ የሚገኙት ሜስረጃዎች እንደ አንድ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማግኘትና ከምዝገባዉ የሚገኘዉ ስታትስቲክስም ለመንግስት ብሎም ለሌሎች አካላት ግድ ይል ስለነበር አገራችን ምትክ የመረጃ የመሰብሰብና አሰጣጥ ዘዴን ስትጠቀም ቆይታለች።የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ መረጃን ግለሰቦች ሲፈልጉ በማያቀርቡት ጥያቄ መሠረት የሚሠጥ እንጂ ሁሉን አቀፍና አስገዳጅ አለመሆኑና የምዝገባመሠረታዊባህሪያትንያሟላአልነበረም።መንግስትም ከምዝገባዉ የሚገኘዉን ጠቀሜታ ከግምት ዉስጥ በማስገባት አግባባዊዉን የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ እና ብሔራዊየመታወቂያአዋጅቁጥር760/2004( ማሻሻያ አዋጅ 1049/2009) በሀገር አቀፍ ደረጃ አቋቁሟል።ወሳኝ ኩነቶች በአንድ ሰዉ ላይ ከልደት እስከ ሞት የሚከሰት ተፈጥሮኣዊና ማህበረሰባዊ የአቋም ለዉጥ ክስተት ሲሆን በአገራችን በኢትዮጵያ ትኩረት የተሰጠዉተፈጥሮኣዊኩነቶችበሕይወትመወለድናሞትሲሆኑማህበረሰባዊኩነቶችጋብቻ፣ባልናሚስትበህግመለያየት(ፍቺ)፥ጉዲፈቻ፣ልጅነትንና አባትነትን በፍ/ቤትመቀበልናቸዉ።

12/02/2022

የልደት ምገባ ሰርተፍኬት ጥቅም ከዚህ በታች የቀረበዉን ምሳሌዉን በማንበብ ተጠቃሚ ይሁኑ። ባቹማ ከተማ በደቡብ ምዕራብ ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን ባቹማ ከተማ አስተዳደር ከተማ ነዉ።አቶ ካፊ ሻሽጌ የባቹማ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ የአንድ ሚስት ባል እና የአንድ ወንድና የአንድት ሴት ልጆች አባት ናቸዉ።የወንዱ ልጁ ዕድሜ 8ዓመት ሲሆን የሴቷ ዕድሜ 6ዓመት ነዉ።በ2014 ትምህርት ዘመን ልጆቻቸውን በባቹማ አንደኛ ደረጃ ት/ ቤት 1ኛ ክፍል ለማስመዝገብ ከልጆቻቸው ጋር ሲሄዱ የት/ቤቱ ዘበኛዉ ርቀታችሁን የማትጠብቁ ማክስ ሳታደርጉ የትነዉ? ብሎ ሲጠይቃቸዉ አቶ ካፊ አንድ ቤተሰብ ነን ማክስ በክሳችን ይዘናል፣ልጆቼን 1ኛ ክፍል ለማስመዝገብ ነዉ የመጣነዉ ሲሉ ዘበኛዉም ማክስ ተጠቀሙ፣ድንገት በሌላ ሰዉ ላይ ያለዉ ኮቭድ ወደ እናንተ ሊተላለፍ ይችላል ሲል እነርሱም በክሳቸዉ የያዙትን አፋቸዉ ላይ ካደረጉ በኋላ ዘበኛዉም በዕድሜ ትልቁን ልጅ በእጅ በጭንቅላትህ አርገህ ጆሮህን ያዝ ስለዉ ልጁም መያዝ ሲያቅተዉ ልጁን ዜሮ ክፍል ተመዝገብ አለ።ሴቷን በተመሳሳይ ጆሮይሽን ያዥ ስላት በጭንቅላቷ አድርጋ ስትይዝ አንደኛ ክፍል ተመዝገቢ ብሎ ትህዛዝ ከሰጠ በኋላ ግቢ እንዲገቡ አደረገ።በት/ቤቱ ርዕሰ መምህር ቢሮ ደረሰዉ ልጆቼ ለትምህርት የደረሱ ናቸዉ ሁለቱን ልጆቼን 1ኛክፍል እንዲማሩ መዝግብ የልጆችም ወላጅ አባት እኔ ነኝ ሲሉ የት/ቤቱ ር/መ/ር የልደት ምዝገባ ሰርተፍኬት የት አለ? ሲል ጠየቃቸዉ። የልጆቹ ወለጅ አባት እኔ ነኝ ሲሉ የት/ቤቱ ር/መ/ሩ መልሶ አባት ስለመሆነዎ እና የልጆችን ዕድሜ በትክክል ለማወቅ፣ነገስራላይለመቀጠር፣ጡሬታለመዉጣት፣የወላጅንማንነትለማወቅወይምለመለየት፣ያለዕድሜየሚፈፀመዉንግብረስጋግንኝነትናጋብቻንለማስቀረት፣የጉልበትብዝበዛንለመከላከል፣ህገወጥየልጆችንዝውውርወዘተለመከላከል የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ወሳኝ ስለሆነና የምናስተምራቸዉ ልጆችየነገ መሪስለሚሆኑ እና ዓላመቹንና ራዕያችሁን ለማሳካት እንዲቻል በቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት ከክብር መዝገብ ሹም ዘንድ ከወላጅ እናት ጋር የነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ ለአንድተማሪ 30ብር ለሁለት ተማሪ 60ብር ብቻ በመከፈል ለልጆቹ የሚሰጠዉን የልደት ሰርተፍኬት ኮፒ በማድረግ ከዋናዉ ጋር አምጡ ሲላቸዉ አቶ ከፊ እየተናደዱ ስራዬን ትቼ መምህሩ አጉል አደረገኝ ካሉ በኋላ ከባለቤታቸዉ ጋር በመመካከር የነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ በእጃቸዉ ብር አልነበረም ከባንክ ቤት 60ብር ወጪ በማድረግ በቀበሌ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ የልጆቻቸዉን ዕድሜ በክብር መዝገብ ላይ በማስመዝገብ የልደት ሰርተፍኬቱን ኮፒ በማድረግ ወደ ት/ቤት ሲመለሱ ር/መምህሩ በትክክለኛ ዕድሜ ወንዱን ልጅ በ8ዓመቱን 1ኛክፍል፣ሴቷን ልጅ በ6 ዓመቷ ዜሮ ክፍል እንዲመዘገቡ ካደረገ በኋላ ወንዱ ልጅ በ8ዓመት 2ኛክፍል መሆን ያለበትን 1ኛክፍል እንዲሆን ያደረገዉ ቀደም ሲል በወሳኝ ኩነት ባለመመዝገቡ ምክንያት እንደሆነ እና ትክክለኛ የ1ኛ ክፍል መመዝገቢያ ዕድሜ 7ዓመት መሆኑንሲያስረዳ መምህሩን በማመስገን ለልጆቻቸዉበተሰጠዉልደትሰርተፍኬትት/ቤትለመማርበመመዝገባቸዉልጆቹምወላጅአባታቸዉንናእናታቸዉንበመምህሩ ፊት አመስግነዉ ሲወጡ ወላጆችም የልጆቻቸዉን ሰርተፍኬት በእጃቸዉ ይዞ ወደቤታቸዉ ሲመለሱ መንገድ ላይ የተገናኘዉ የከተማዉ ነዋሪ አቶ ሸዋጌለች አራት ልጆችን ለማስመዝገብ ሲሄዱ የነበሩት መረጃዉን ከአቶ ካፊሰምቶበመረዳትእስከት/ቤቱድረስሳይለፉከመንገድተመልሰዉየአራቱንልጆችየልደትሰርተፍኬትበማዉጣትትዉ አራቱምልጆችደግሞወላጅአባታቸዉንናእናታቸዉንአመስግኗል።

Address

Mizan Teferi

Telephone

+251925905789

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ምዕራብ ኦሞ ዞን ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share