መርሳ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት/Mersa revenue office/

  • Home
  • Ethiopia
  • Mersa
  • መርሳ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት/Mersa revenue office/

መርሳ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት/Mersa revenue office/ Collecting tax fairly to answer different economic & social development of society

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ ) በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።‎በአሉ የሰላም ፣የአንድነት ፣የመከባበርና የስኬት  ይሁንላችሁ :...
26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ ) በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
‎በአሉ የሰላም ፣የአንድነት ፣የመከባበርና የስኬት ይሁንላችሁ ::

‎ የመርሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት

26/05/2026

የሚኒስትሮች ምክርቤት የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅን አሻሻለ
ምክር ቤቱ የተወያየው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ወጥቶ ሲሰራበት የቆየ ቢሆንም ባለፉት አመታት በሀገራችን በርካታ የኢኮኖሚ ለውጦች የተደረጉ በመሆኑ የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ከዘመናዊ ዓለም አቀፍ ልምዶች ጋር ለማጣጣም፤ የታክስ አለመግባባቶችን በፍትሐዊነት፣ በሰላማዊ መንገድና በቅልጥፍና ለመፍታትና የተጠያቂነትና ግልጸኝነት አሰራር ለማስፈንና የታክስ ሕጎችን በተጠናከረ መልኩ ለማስፈጸም እንዲያስችል ተደርጎ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

18/05/2026

ቀን10/09/2018
‎የመርሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የእቅዱን 77.2% ገቢ ሰበሰበ።
‎የመርሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የገቢ አወሳሰን አሰባሰብና ክትትል ዋና የስራ ሂደት የተገኘዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ በበጀት አመቱ ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ ብር 234,282,860 ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከ ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ብር 181,007,006 በመሰብሰብ የእቅዱን 77.2% መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ፦
‎* ቀጥታ ታክስ እቅድ ብር 83,911,319 ክንዉን ብር 68,638,861.3" አፈጻጸም 81.8%
‎* ቀጥታ ያልሆነ ታክስ እቅድ ብር 23,812,672 ክንውን ብር 29,928,038.3 አፈጻጸሞ 125.6%
‎* ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች እቅዶ 5,669,684 ክንዉን ብር 459,798.27 አፈጻጸም 8.1%
‎ * ጥቅል መደበኛ ገቢ እቅድ ብር 113,393,674 ክንዉን ብር 99,026,697.97 አፈጻጸም 87.3%
‎* የከተማ አገልግሎት ገቢ እቅድ ብር 120,889,186 ክንዉን ብር 81,980,308.08 አፈጻጸም 67.8 % የተሰበሰበ ሲሆን ይህ ከባለፈዉ ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመደበኛ ገቢ ብር 27,946,600 በከተማ አገልግሎት ገቢ ብር 35,607,267.78 በጥቅሉ ብር 63,553,868.33 ብልጫ የተሰበሰበ ሲሆን የመርሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ለዚህ ዉጤት መምጣት የተሻለ አስተዋፆ ላደረጉ የጽ/ቤቱ ሙያተኞች፥ ድጋፋ ላደደረጉ አመራሮች እና ከጎናችን ሁነዉ በቅንጅት ለሰሩ አጋርና ባለድርሻ አካላት ልባዊ ምስጋናዉን እያቀረበ በቀጣይ ቀሪ ጊዚያት የተለያየዪ የገቢ አማራጮች በመለየት የበጀት አመቱ እቅድ በውጤታማነት ይፈጸም ዘንድ ጥሪዉን ያቀርባል።
‎መረጃዉ፦ የግብር ትምህርትና ኮሚኒኬሽን የስራ ሂደት ነው::

14/05/2026

ለከተማችን የደረጃ ለ እና ሀ ግብር ከፋዬች በሙሉ፦
እንደሚታወቀዉ የደረጃ ለ የ3ኛዉ ሩብ አመት እና የደረጃ ሀ የ2ኛዉ ሩብ አመት ቅድመግብር ክፍያ የመክፍያ ጊዜ ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 30/2018ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም በተቀመጠዉ ጊዜ ገደብ መሰረት የሚጠበቅባችሁን የግብር ግዴታ እንድትወጡ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግብርን በወቅቱ ባለመክፈል ለሚመጣዉ አላስፈላጊ ቅጣት እና ወለድ ገቢ ጽ/ቤቱ ተጠያቂ እንደማይሆን ከወድሁ በጥብቅ ያሳስባል።

08/05/2026
20/04/2026
ቀን 08/08/2018 ዐ.ም የመርሳ ከተማ አስ/ር ገቢዎች ፅ/ቤት እስከ  መጋቢት 30/2018 ዓ.ም ከበጀት አመቱ እቅድ መካከል 69.98% ማሣካት ቻለ::🎤🎬 ገቢውን👉ከቀጥታ ታክስ=እቅድ 8...
16/04/2026

ቀን 08/08/2018 ዐ.ም
የመርሳ ከተማ አስ/ር ገቢዎች ፅ/ቤት እስከ መጋቢት 30/2018 ዓ.ም ከበጀት አመቱ እቅድ መካከል 69.98% ማሣካት ቻለ::
🎤🎬 ገቢውን
👉ከቀጥታ ታክስ=እቅድ 83,911,319 ክ ንውን 62,757,355.06 አፈፃፀም 74.79%
👉ቀጥታ ያልሆኑ ታክሶች እቅድ 23,812,672 ክንውን 26,406,053.80አፈፃፀም 110.89%
👉ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች እቅድ 5,669,684 ክንውን 428,357.80 አፈጻጸም 7.56%
👉መደበኛ ገቢ ድምር እቅድ 113,393,674 ክንውን 89,591,766.66አፈጻጸም 79.09%
👉አገልግሎት ገቢ እቅድ 120,889,186 ክንውን 74351092.66 አፈጻጸም 61.50% የሰበሰበ ሲሆን
👉ጠቅላላ ከበጀት አመቱ እቅድ 234,282,860 መካከል 163,942,859.32 ገቢ በመሠብሰብ አፈጻጸሙን 69.98% ማድረስ ተችሏል::በቀጣይም ላልተሰበሰቡ ገቢዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት የበጀት አመቱን እቅድ በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም አካላት በግንዛቤ ፈጠራና በቅስቀሳ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል:: በዚህም መሠረት የከተማችንን እድገትና ስኬት ለማጠናከር ያልተከፈለ ,,የ2018 በጀት አመት የ1ኛ እና 2ኛ ሩብ አመት 25% ንግድ ትርፍ ግብርና የኪራይ አከራይ ቅድመ ግብ እንድሁም አፈርና ጣራ የሊዝ የዘመንና /ውዝፍ /ክፍያ ያልከፈላችሁ ግለሰብና ድርጅት ግብር ከፋዮች ያለባችሁን እዳ በፍጥነት እንድትከፍሉ እያሳሰብን:
👉የተጀመሩ የኮሪደርና ሌሎች መሠረቶልማችን ፍጥነት በማጠናከር ጥራትና ደህንነት በጋራ በመጠበቅ ብልሹ አሰራርን በመታገል የአሰራር ግልጸኝነትን በማጎልበትና ፍትሀዊነትን በማስፈን ከተማችንን በጋራ እናልማ!!!
ግብርን በወቅቱ በመክፈል ሀገርን ማልማት የብልህ ዜጎች መገለጫ ነው!!!
የመርሳ ከተማ አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት!!!

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ:_እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
11/04/2026

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ:_
እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

07/04/2026

በመንግስት መሥሪያ ቤት ውስጥ መሥራት ትልቅ የኃላፊነት ቦታ ነው።
የመንግስት ሠራተኛ መሆን ማለት የግለሰብን ሳይሆን የሕዝብንና የአገርን ጉዳይ ማስተናገድ በመሆኑ፣ ሥራው ጥንቃቄንና ታማኝነትን ይጠይቃል።

አንድ የመንግስት ሠራተኛ ስኬታማና ውጤታማ እንዲሆን የሚከተሉትን 5 ዋና ዋና ነጥቦች እናንሳ
1. ሙያዊ ብቃትና ወቅታዊነት (Professionalism & Self-Improvement)
 ዓለምና አሠራሮች በየጊዜው እየተቀያየሩ ነው።
 በመንግስት መሥሪያ ቤት ውስጥ "ድሮም የምንሰራው እንዲህ ነው" በሚል መርህ ብቻ መጓዝ ለኋላ ቀርነት ይዳርጋል።
 የሥራ መመሪያዎችን፣ ደንቦችንና አዳዲስ አዋጆችን በደንብ ያንብቡ።
 ቴክኖሎጂን (ለምሳሌ፦ Excel, Digital tools) በመጠቀም ሥራዎን ያቀልሉ፣ ጥራትም ይጨምሩ።

2. ለተገልጋይ ቅድሚያ መስጠት (Customer Stewardship)
 ተገልጋዩ ሕዝብ የእርስዎ ደመወዝ ምንጭ መሆኑን አይዘንጉ።
 ተገልጋይን በፈገግታና በትህትና ያስተናግዱ።
 ጉዳዩ ዛሬ መፈጸም የሚችል ከሆነ "ነገ ና" ከሚል ቢሮክራሲ ይራቁ። የአንድን ሰው ጊዜ ማባከን የአገርን ምርታማነት መቀነስ መሆኑን ይረዱ።

3. ታማኝነትና የሥነ-ምግባር መርህ (Integrity)
 መንግስትና ሕዝብ እምነት ጥለውብዎት የመንግስትን ሃብት፣ መረጃና ሥልጣን ሰጥተውዎታል።
 ከሙስናና ካልተገቡ ጥቅማጥቅሞች ራስዎን ይጠብቁ።
 የመንግስት ንብረትን (መኪና፣ ወረቀት፣ ኮምፒውተር) እንደ ግል ንብረትዎ በጥንቃቄ ይያዙ።
 የመሥሪያ ቤቱን ሚስጥር ይጠብቁ።

4. በቡድን የመሥራት ባሕል (Teamwork)
 በመንግስት መሥሪያ ቤት ውስጥ ውጤት የሚመጣው በቅንጅት ነው።
 ከሥራ ባልደረቦችዎ ጋር መልካም ግንኙነት ይኑርዎት።
 መረጃን ከመደበቅ ይልቅ ለሥራው ስኬት ሲባል ያጋሩ።
 ክፍት የሆነ የሥራ አካባቢ እንዲኖር የድርሻዎን ይወጡ።

5. የጊዜ አጠቃቀም (Time Management)
 በመንግስት መሥሪያ ቤት ውስጥ የሚታየውን "ሰዓት ማክበር" ላይ ያለውን ክፍተት ይሰብሩ።
 ወደ ሥራ በሰዓቱ ይግቡ፣ በሰዓቱ ይውጡ።
 የሥራ ሰዓትን ለግል ወሬ ወይም ለማኅበራዊ ሚዲያ ከመጠቀም ይቆጠቡ።
 ዕቅድ ይኑርዎት፤ የዛሬን ሥራ ለነገ አያሳድሩ።

ማጠቃለያ፦
የመንግስት ሠራተኛነት የክብር ቦታ ነው። ዛሬ በቅንነትና በታማኝነት የሚሰሩት ሥራ ነገ የእርስዎና የልጆችዎ አገር በፅኑ መሠረት ላይ እንድትቆም ያደርጋል። ሥራዎን የሚወዱትና የሚኮሩበት ይሁን!

ካነበብነው
በደሴ ገላው

02/04/2026

Address

Mersa
Mersa
0333310282

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መርሳ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት/Mersa revenue office/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to መርሳ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት/Mersa revenue office/:

Share