መንዝ ጌራ ምድር ባህልና ቱሪዝም

መንዝ ጌራ ምድር ባህልና ቱሪዝም Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from መንዝ ጌራ ምድር ባህልና ቱሪዝም, Government Organization, Mehal Meda.

Menze Guassa Community Conservation Area
28/05/2025

Menze Guassa Community Conservation Area

26/07/2023

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ታላቅ መንፈሳዊ የበዓለ ንግስ ጥሪ
ለህዝበ ክርስቲያን በሙሉ እነሆ ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ/ም የአባታችን የፃድቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ በዓለ ንግስ በደማቅ ሁኔታ በየዓመቱ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ከላይ በተጠቀሰው ዕለት ተገኝታችሁ የበዐሉ ተሳታፊ እንድትሆኑ እያልን በአጭሩ የአባታችን የፃድቁ አቡነ ዕጨጌ ዮሐንስ በፍርኩታ በጽርሐ አርያም ቅ/ኪዳነ ምህረት ገዳም የአደረጉት ተአምራትና አሁንም የተቸገሩ ምዕመናን ለአባታችን እና ለቅ/ ኪዳነ ምህረት በመንገር ችግራችው እየተፈታላቸው ይገኛሉ ነገር ግን የፃድቁን ታሪክ የምታውቁት ብዙዎች ብትሆኑም የማታውቁት ካላችሁ አባታችን ፃድቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ እስራኤላዊ ሲሆኑ የተወለዱትም የያዕቆብ ልጆች ዕብራውያን ለእግዚአብሔር መስዋዕት ይሰውበት ከነበረው ፍልጥ /ሲሳራ/ ከተባለው ቦታ የፅድቅ ሥራን ይሠሩ ከነበሩ ቤተሰቦች ከአባታቸው ከዲላሶር እና ከእናታቸው ከእምነ ጽዮን ህዳር 28 ቀን ነው ፡፡ከዚያም 22 ዓመት ከቤተሰቦቻቸው ጋር 15 ዓመት ኤስድሮስ ከሚባል ሰውጋር የኖሩ ሲሆን ለገዳማተ ኢየሩሳሌም ውስጥ 13 ዓመት በጾም በጸሎት እና በአብዝሆ ስግደት እየኖሩ ሳለ እመቤታችን ተገልጻላቸው ንሳእ ህብስተ ሰገም ይኩን ለከ እስከ ለዓለም ምግብከ ዘለዓለማዊ ስንቅ እንዲሆንህ እንካ ብላ የገብስ እንጀራ ሰጥታቸው በበረከት እስከ እለተ ሞታቸው እህል ሳያስፈልጋቸው ስንቅ ሳያስፈልጋቸው ኖረዋል ፡፡ህብስቱን እንደተቀበሉም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የእመቤታችን የአስራት ሀገር ወደሆነችው ኢትዮጵያ ከጎንደር በበላሳ በኩል ከገቡ በኋላ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ
 50 ዓመት በደብረ ሊባኖስ ገዳም
 50ዓመት በሺ ፈጅ ዮሀንስ /ቡልጋ/
 50ዓመት በአፋር ዉስጥ አዘሎ በሚባል ቦታ
 50ዓመት በይፋት ዉስጥ ጠገሮ በሚባልቦታ
 50ዓመት በፍርኩታ ጽርሐ አርያም ቅ/ኪዳነ ምህረት ገዳም
 50ዓመት በጎንደር በለሳ ጉንዶ ተክለሃይማኖት
 50ዓመት በሰማይ
 50ዓመት በዳመና
 50ዓመት ከኡደተ አጽናፍ ዓለም በድምሩ 500 ዓመት እየጸለዩ በበረከት ና በጸጋ የኖሩ አባት ናቸዉ ፡፡በተለይ በሌሎችም ከጸለዩባቸው ገዳማት ሁሉ ለየት የሚያደርገው በፍርኩታ ቅ/ኪዳነ ምህረት በአት አጽንተው ፈጣሪያቸውን እያገለገሉ ሳሉ ከዕለታት በአንዱ ቀን በእግዚአብሔር ቸርነት እንደ መስታወት የሚንያጸበርቅ የመጾር መስቀል ከሰማይ ወርዶላቸዋል ፡፡በመስቀሉም ልዩ ልዩ ህሙማን ሲፈወሱበት ርኩሳን መንፈስ ያደረባቸው ሲላቀቁበት ኖረዋል ፡፡
ጻዲቁ አባታችን በጠቅላላ 500 ዓመታትን ኖረዉ በጎንደር በለሳ ሃምሌ 29 ቀን አርፈዉ ቅዱስ አጽማቸዉ በበለሳ 157 ዓመት ከኖረ ቡሃላ በፈቃደ እግዚአብሄር ከጎንደር በለሳ ፈልሶ ወደ መንዝ ሲመጣ ትኩስ እሬሳ ሆኖ ደማቸዉ በነጠፈበት በበለሳ ዉስጥ 1 ጸበል በፍርኩታ ኪዳነምህረት ገዳም 1 ጸበል ፈልቆበት ይገኛል ፡፡
ስለዚህ የፃድቁ አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ታሪክ እጅግ ባጣም ብዙ ቢሆንም በአጭሩ አጽመ ቅዱሳናቸው በዚችው ሲጸልዩባት እና ህሙማንን ሲፈውሱባት ከነበረችው በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ በአልፋ ምድር ቀበሌ በፍርኩታ ጽርሐ አርያም ቅ/ኪዳነ ምህረት ገዳም ዉስጥ ይገኛል፡፡ በስማቸዉም ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶላቸው እና ጽላት ተቀርጾላቸዋልም፡፡ አጽመ ቅዱሳናቸው ካረፈበት ቦታ እምነት አፈራቸውን በመዝገን እና በመቀባት ዛሬም እንደጥንቱ ከልዩ ልዩ ደወያት የተፈወሱ ህዝበ ክርስቲያን ምስክርነታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በስማቸው የፈለቀው ጸበል ብዙ ገቢረ ታአምር እየሠራ ይገኛል ፡፡
ስለዚህ የጻድቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ በዓለ እረፍታቸው ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ/ም በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ በአልፋ ምድር ቀበሌ በፍርኩታ ቅድስት ኪዳነምህረት ገዳም በደማቅ ሁኔታ ስለሚከበር ህዝበ ክርስቲያን በሙሉ በዚህ በተቀደሰ ቦታ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም ተጠርታችኋል ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ክቡር ሞቱ ለፃድቅ በቅድመ እግዚአብሔር መዝ፣ 115 ፣5

የደብሩ ሰበካ ጉባኤ

ታላቅ የኪነ-ጥበብ ምሽት  ለመንዝ ጌራ ምድር ወረዳና ለመሀል ሜዳ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ እነሆ በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ስር  ተደራጅተው የመንዝ ህዝብ ታሪክ፣ ወግና ...
13/07/2023

ታላቅ የኪነ-ጥበብ ምሽት
ለመንዝ ጌራ ምድር ወረዳና ለመሀል ሜዳ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ እነሆ በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ስር ተደራጅተው የመንዝ ህዝብ ታሪክ፣ ወግና ባህልን እያስተዋወቀ ያለው የፊታውራሪ የኪነ-ጥበብ ቡድን በዕለተ አርብ ማለትም 07/11/2015 ዓ.ም አመሻሹ 10:00 ላይ አስተማሪና አዝናኝ የሆኑ ታላቅ የስነ-ፅሁፍ ድግስ ከልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ጋር ይዞላችሁ ቀርቧል።
ስለሆነም እርስዎ ከፍቅረኛዎ፣ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በዕለተ አርብ ማለትም 07/11/2015 ዓ.ም አመሻሹ 10:00 ላይ በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ግቢ በሚገኘው ICT አዳራሽ በመገኘት ፕሮግራሙን አንዲከታተሉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

መግቢያ ዋጋ 10 ብር ብቻ

ለበለጠ መረጃ --0955934078
-0966276387 ይደውሉ

መቅረት ክልክል ነው።

ኑ ! ሁላችንም በሰዓቱ በመገኘት የኪነ ጥበብ ቡድኑን እንደግፍ፣እናጠናክር፡፡

የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት
መሀል ሜዳ

በመንዝ ጌራምድር ወረዳ 010/ገይ ቀበሌ/እንደጉሎ አካባቢ የሚገኘው ውብና አስደናቂ የአርኪዮሎጂ ስፍራ ኑ ሁላችንም ውብና ማራኪ የሆነውን አካባቢያችንን በጋራ እንጎብኝ
05/07/2023

በመንዝ ጌራምድር ወረዳ 010/ገይ ቀበሌ/እንደጉሎ አካባቢ የሚገኘው ውብና አስደናቂ የአርኪዮሎጂ ስፍራ ኑ ሁላችንም ውብና ማራኪ የሆነውን አካባቢያችንን በጋራ እንጎብኝ

በመንዝ ጌራምድር ወረዳ 010/ገይ ቀበሌ/እንደጉሎ አካባቢ የሚገኘው ውብና አስደናቂ የአርኪዮሎጂ ስፍራ ኑ ሁላችንም ውብና ማራኪ የሆነውን አካባቢያችንን በጋራ እንጎብኝ
03/07/2023

በመንዝ ጌራምድር ወረዳ 010/ገይ ቀበሌ/እንደጉሎ አካባቢ የሚገኘው ውብና አስደናቂ የአርኪዮሎጂ ስፍራ ኑ ሁላችንም ውብና ማራኪ የሆነውን አካባቢያችንን በጋራ እንጎብኝ

13/04/2023

ቀን 05/08/2015 ዓ.ም
የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ለመላው የወረዳችን ህዝብና ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያኖች በሙሉ እንኳን ለ2015 ዓ.ም ለጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሠላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሠላም፡የጤና:የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱንይገልፃል።
የወረዳችን ህዝብ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን ሲያከብር ወጉን ፣ባህሉንና ታሪኩን ባማከለና በጠበቀ መልኩ ሲሆን ጠንካራ እንግዳ ተቀባይ፣ሰውን የሚወድና የሚያከብር እንዲሁም ፈጣሪውን የሚፈራ ቃሉን ጠባቂ እና ጀግና ህዝብ ያለበት ወረዳም ነው፡፡በተጨማሪም ወረዳችን የበርካታ ጥንታዊና ታሪካዊ የሆኑ የተፈጥሮና ሠው ሠራሽ እንዲሁም ሀይማኖታዊና ባህላዊ ቱውፊቶች ያሉበትም ነው፡፡ በተለይ በዓለም ደረጃ በመታወቅ ላይ ያለውና የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ህዝብ ግርማ ሞገስ የሆነው የመንዝ ጓሳ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራም መገኛም ነው፡፡በዚህ አጋጣሚ ወደ ወረዳችን መጥታችሁ ጥንታዊና ታሪካዊ የሆኑትን እንዲሁም ሀይማኖታዊና ባህላዊ ቱውፊቶቻችንን በመጎብኘት የህሊና እርካታ እንድታገኙ በአክብሮት እየጋበዝን ሁላችንም የጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል /ፋሲካን/ ስናከብር የመቻቻል፣የመከባበር፡የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችንን የበለጠ በማጠናከር በዓሉን በተለያየ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን በማስታወስ ና በመደገፍ በአብሮነት መንፈስና ፈጣሪ በሚወደውና ባህላችንን በጠበቀና ባከበረ መንገድ ልናከብረው ይገባል። በተጨማሪም አሁን ላይ እንደሀገርም ሆነ እንደክልል የገጠመንን የሰላም ችግር ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት እና በሰከነ መልኩ በመወያየት ለሰላማችን ትልቅ ትኩረት በመስጠት ችግሩን ልንፈታ ይገባናል፡፡ምክንያቱ የሰላም ዋጋ በገንዘብ የሚገመት ስላልሆነ፡፡ አባቶቻችን ለሰላም ትልቅ ዋጋ ከፍለው ትልቅ ሀገር አስረክበውናል፡፡አሁን ላይ ግን ሰላምን ከገነዘብ ውሀን ከምግብ የሚቆጥረው የለም እንዲሉ አበው ለሰላም ትልቅ ዋጋ እየሰጠን አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንደ ሀገር ሰላም እንዲሰፍንና በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲገነባ ሁላችንም ለሰላማችን የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ስላልቻልን ነው፡፡ስለዚህ የሰላም ዕጦት የሚያስከትለውን ሁለንተናዊ ችግር ለመቀነስ የመቻቻል፣የመከባበር፡የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችንን በተግባር ልናሳይ ይገባናል እንላለን ፡፡
በድጋሚ በዓሉ የሠላም፡የጤና:የደስታና የፍቅር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱንይገልፃል። !

የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት

20/02/2023

ቀን 10/06/2015 ዓም
ታላቅ የጉዞ ፕሮግራም
ለመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እና ለመሀል ሜዳ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች በሙሉ፡-
አነሆ የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት በዘንድሮው ዓመት ለ127ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ የነፃነትና የድል በዓልን ዝክረ-አድዋ በሚል መሪቃል በ23/06/2015 ዓ.ም በወረዳ ደረጃ ባማረና በደመቀ መልኩ በወረዳችን ውስጥ በ019/አናዝጥድ ቀበሌ/ በሚገኘው ጥንታዊና ታሪካዊ በሆነው ስፍራ እንዲሁም በግራኝ መሀመድ ወረራ ጊዜ በወረዳችን ውስጥ ሳይቃጠል በቀረው ብቸኛውና ታሪካዊው በሆነው እንዲሁም በግራኝ መሀመድ ወረራ ጊዜ የአፄ ልብነድንግል ልጅ አቤቶ ያዕቆብ በተቀመጠበትና ባደገበት በገሜ ጊዮርጊስ ለማክበር ዝግጅታችንን አጠናቀናል፡፡
በመሆኑም የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እና የመሀል ሜዳ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች የሆናችሁ በሙሉ ይህንን ጥንታዊና ታሪካዊ ስፍራን በመጎብኘትና በማየት ወረዳችንና ከተማችን ያላትን ታሪክ እንዲሁም ለሀገረ መንግስት ግንባታ ያበረከተችውን አስተዋፅኦ መጀመሪያ ራሳችን አውቀን ለአለም ህዝቦች በማስተዋወቅ ሁላችንም የዜግነት ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንን እያስተላለፍን አካባቢን ለመጎብኘትና ታሪክን ለማወቅ ፍላጎት ያላችሁ የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እና የመሀል ሜዳ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች እስከ 17/06/2015 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን ፡፡

አዲስ እሳቤ ለቱሪዝም!!
ማሳሰቢያ
 የጉዞ ቀን በ22/06/2015 ከቀኑ 8፡00 ሲሆን መመለሻ በ23/06/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ይ ነው፡፡
 ጉዞው ከ1፡00 -1፡30 የእግር ጉዞ ስላለው ተጓዞች ሙሉ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው ለጉዞ የሚሆን ስንቅ መያዝና አለባበስን ይጨምራል፡፡
 ለደርሶ መልስ ትራንስፖርት ክፍያ የሚሆን 150 .00 /አን መቶ ሀምሳ ብር ብቻ/ መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር -2 ድረስ በመምጣት መመዝገብና መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116850600/0924141150/0988150676 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት
መ/ሜዳ

የመንዝ ጓሳ የመንግስት ሰራተኞች የሃገርህን እወቅ ክበብ አባላት በ መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ሾላ ቀበሌ ላምበር ማርያም እና ደበረ ንግስት ሐና ቅድስት ማርያም ገዳም ጉዞ አደረጉ፡፡  በመንዝ ...
24/01/2023

የመንዝ ጓሳ የመንግስት ሰራተኞች የሃገርህን እወቅ ክበብ አባላት በ መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ሾላ ቀበሌ ላምበር ማርያም እና ደበረ ንግስት ሐና ቅድስት ማርያም ገዳም ጉዞ አደረጉ፡፡
በመንዝ ጌረ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም አስተባበሪነትና አዲስ እሳቤ ለቱሪዝም! የሚለውን መፈክር ለማሳካት የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ማስፋፋትናማጠናከር ስለሚገባ በየደረጃው የሀገርህን ዕወቅ ክበባትን ማደራጀት ፣መደገፍና ማጠናከር ዋነኛ ስራችን ሊሆን ይገባል፡፡ በመሆኑም የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ በወረዳ ደረጃ በት/ቤቶችና በሴክተር መ/ቤቶች ውስጥ ልዩልዩ የሀገርህን ዕወቅ በማቋቋም እያደራጀና እየደገፈ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ጥር 14/2015 ዓ.ም ሃገርህን ማወቅ ከአከባቢ ይጀምራል" በሚሉ መሪ ቃሎች መነሻውን ከመሐልሜዳ ከተማ ወደ መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ሾላ ቀበሌ በማድረግ የወረዳ አመራሮች ፣ የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የቤተ ክህነት አባቶች የመንዝ ጓሳ የመንግስት ሰራተኞች ሃገርህን እወቅ ክበብ አባላት በጉዞው ተሳትፈዋል፡፡
በጉዞው በ1555ዓ.ም የተመሰረተችው ላምበር ማርያም እና በ479ዓ.ም በአባ መጣዕ (አባ ሊቃኖስ) የተመሰረተችው ደበረ ንግስት ሐና ገዳም ተጎብኝተዋል፡፡
ላምበር ማርያም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በመንዝ ጌራ ምድር ሾላ ቀበሌ ከመሐል ሜዳ ከተማ 30 ኪ.ሜ እርቀት ላይ የምትገኝ ጥንታዊ ቤተክርስቲን ነች፡፡
በእድሜ ጠገብ በሆኑት ታላቅ አባት አቶ አሰፋ ደባይ በፃፉት ትንሽ መፅሐፍ ይቺ ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው በ 1555 ዓ.ም በአፄ ገላውዲዎስ ዘመነ መንግስት ነው አይቴ እና ገኒ የተባሉ ባል እና ሚስት ከጎንደር ክፍለ ሃገር መጥተው አራት ልጆች ወልደው በዚህ ቦታ በሞት ተለይተዋል በማለት በመጠኑም ቢሆን ይዘረዝራል፡፡
ቤተክርስቲያኑን ለማደስ ግንቦት 16 /1999 ዓ.ም ከመቅደሱ ውስጥ በተደረገ ቁፋሮ አንድ ቅዱስ ዓፅም ተገኝቷል የዚህ ቅዱስ ዓፅም የተቀበረበት ወቅት በውል ያልታወቀ ሲሆን ፂም እና ፀጉራቸው ያልረገፈ ከ3 ቦታ ሐረግ የተገነዙ ናቸው፡፡በተጨማሪም በዙረያው መርካታ ቅዱሳን አፅምም ያለመሆኑን አባቶች አስረድተውናል፡፡
የአካባቢው ህዝብም ሁኔታውን በማየት እነዚህን ጨርቅ እና ሰሌን እንደዚሁም ሐረግ ለበረከት እያሉ እየቆራረጡ ወስደውታል፡፡ ዓፅሙ ግን በሚገባ ክብሩ ሳይሸረሸር እና ሳይቀንስ በሳጥን ውስጥ ቆመው እና ሳቅ ብለው ይገኛሉ።ወደ ስፍረው ጉዞ ያደረጉት የክበቡ አባላት ባዩት ነገር መደነቃቸው እና በቀጣይ መንዝ ውስጥ ብዙ ያልተነገረላቸው ታሪካዊ ፣ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ስላሉ ይህን አይነት የጉዞ ተግባርን አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም በወረዳችንና ከወረዳችን ውጭ ያላችሁ ህዝቦች የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ በርካታ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ የመስህብ ሀብቶች ያሉበት በተገቢው ቢለሙና ቢተዋወቁ አካባቢን ከመጥቀም አልፈው ሀገርንም ጭምር ሊጠቅሙ ስለሚችሉ አቅም ያላችሁ ሁሉ በምክር፣በገንዘብ ፣መጉልበት በአጠቃላይ በምትችሉት ሁሉ ተጋግዘን ይህን ታሪኩ ያልተነገረለትንና ያልተዘመረለትን አካባቢያችንን በጋራ ልነለማ ይገባናል የሚል መልዕክትን እያስተላለፍን በተለይ አጋርና ባለደርሻ አካላቶች ለዚህ በጎ ተግባር በተግባር በግንባር ቀደምነት እንድትሳተፉ አንላለን፡፡

24/01/2023
የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ለመላው የወረዳችን ህዝብና ለኢትዮጵያኖች እንዲሁም ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2015 ዓ.ም የጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክ...
06/01/2023

የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ለመላው የወረዳችን ህዝብና ለኢትዮጵያኖች እንዲሁም ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2015 ዓ.ም የጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሰን አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሠላም፡የጤና :የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
የወረዳችን ህዝብ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን ሲያከብር ወጉን ፣ባህሉንና ታሪኩን ባማከለና በጠበቀ መልኩ ሲሆን ጠንካራ እንግዳ ተቀባይ፣ሰውን የሚወድና የሚያከብር እንዲሁም ፈጣሪውን የሚፈራ ቃሉን ጠባቂ እና ጀግና ህዝብ ያለበት ወረዳም ነው፡፡ በተጨማሪም ወረዳችን የበርካታ ጥንታዊና ታሪካዊ የሆኑ የተፈጥሮና ሠው ሠራሽ እንዲሁም ሀይማኖታዊና ባህላዊ ቱውፊቶች ያሉበትም ነው፡፡ በተለይ በዓለም ደረጃ በመታወቅ ላይ ያለው የመንዝ ህዝብ ግርማ ሞገስ የሆነው የመንዝ ጓሳ የማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራም መገኛም ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ወደ ወረዳችን መጥታችሁ ጥንታዊና ታሪካዊ የሆኑትን እንዲሁም ሀይማኖታዊና ባህላዊ ቱውፊቶቻችንን በመጎብኘ ት የህሊና እርካታ እንድታገኙ በአክብሮት እየጋበዝን የጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል /ገናን/ ስናከብር የመቻቻል፣የመከባበር፡የመረዳዳትና መደጋገፍ ባህላችንን የበለጠ በማጠናከር በዓሉን በተለያየ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን በማስታወስ ና በመደገፍ በአብሮነት መንፈስና ፈጣሪ በሚወደው መንገድ ልናከብረው ይገባል።
በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት!

የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት

06/01/2023

Address

Mehal Meda

Telephone

+251116850600

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መንዝ ጌራ ምድር ባህልና ቱሪዝም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to መንዝ ጌራ ምድር ባህልና ቱሪዝም:

Share