14/06/2026
የጤና ሚኒስትሯ ዶ.ር መቅደስ ዳባና የአፍሪካና ኢንዲያ ቢልጌትስ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት አንኩር ቮራ የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎብኝተዋል።
ላሊበላ፦ሰኔ ፣7፣2018 (የላሊበላ ኮሙኒኬሽን) የጤና ሚኒስትሯ ዶ.ር መቅደስ ዳባ፣ የአፍሪካና ኢንዲያ የቢልጌትስ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት አንኩር ቮራ እና ሌሎች የፋውንዴሽኑ የስራ ሃላፊዎችን የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች ናቸው አቀባበል ያደረጉላቸው።
የጤና ሚኒስትሯ ዶ.ር መቅደስ ዳባና የቢልጌትስ ፋውንዴሽን የአፍሪካና ኢንዲያ ፕሬዝዳንት አንኩር ቮራና እና ሌሎች የፋውንዴሽኑ የስራ ሃላፊዎች የቅዱስ ላሊበላን ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎብኝተዋል።
የስራ ሃላፊዎቹ ቅዱስ ላሊበላ በ12 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከዓለት ላይ ያነፃቸውን ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ነው የተመለከቱት።