ላስታ ወረዳ ዐ/ሕግ ጽ/ቤት

ላስታ ወረዳ ዐ/ሕግ ጽ/ቤት Lasta Woreda pbuh / law office has four working process and the crime process of human rights work process and documents and guard registration process

27/10/2020

የላስታ ወረዳ ዐ/ህግ ሰራተኞች
በቢሮ ችግር ምክኒያት ስራ ለመስራት መቸገራቸውን ገለፁ!!!

የላስታ ወረዳ ዐ/ህግ ጽ/ቤት ሰራተኞች በ06/02/2012 ዓ.ም ስራ ለመገምገም በተሠበሠቡበት ወቅት በቢሮ ጥበት ምክኒያት የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት መቸገራቸውን በምሬት ገፀዋል፡፡
የተቋሙ ሠራተኞች እንደሚሉት የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ከ10 ያላነሱ ክፍሎች ያሉት ቢሮ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን አሁን በሁለት ክፍሎች ሁሉም ሰራተኛ ሠራተኛ ተቀምጦ ስራ እያከናወነ መሆኑ ተገልፆል፡፡
የቢሮ ጥበት ባስከተለው ችግር ሳቢያ፤
 ሂደቶችን በቢሮ ነጥሎ ማሰራት አልተቻለም
 ከኮቪድ 19 አንጻር መምሪያውን መሠረት አድረጎ ስራን ማከናወን አልተቻለም
 ባለጉዳይ በአግባቡ ማስተናገድም ሆነ ሰነዶችን በአግባቡ ማስቀመጥ አልተቻለም
 አንዳንድ ሚስጥራቸው ተጠብቆ መስተናገድ ያለባቸውን ባለጉዳዮች ማስተናገድ አልተቻለም
 ሰራተኛው በአግባቡ ተሠማርቶ ሥራውን ሠርቶ ውጤት ማምጣት ተቸግሯል
 ያለው ቢሮ በፋይል በመጨናነቁ መደርደሪጠዎች ተጣመው እየወደቁ በሠራተኛ ላያ ጉዳት እያደረሱ ነው ወዘተ የሚሉ አቤቱታዎችን አንሰተዋል፡፡
ከመድረኩ በተሠጠ ምላሽም ችግሩን ለመፍታት ለላስታ ወረዳ አስ/ም/ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ በደብዳቤ፤ በካቢኔ ስብሰባ ኢንፎርማል በሆኑ ውይይቶች በመጠየቅም ሆነ ቢሮውን በአካል የሚመለከተው አካል እነዳየው ቢደረግም እስካሁን ችግሩ እንዳልተፈታ ተገልፆል፡፡ በተጨማሪም አሁንም ችግሩ እንደቀረፍ በተለመደው አግባብ ካስተዳደር ምክር ቤቱ ጋር እንደሚሰራ እና እስከዚው ድረስ ሰራተኛው በትዕግስት ስራውን እንዳከናውን የሚል ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

07/10/2020

ANRS Justice Bereau an organization that works towards enhancing justice, good governance and democratic system of the amhara region.

07/10/2020

የወንደሙን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ!!!

ANRS Justice Bereau an organization that works towards enhancing justice, good governance and democratic system of the amhara region.

07/10/2020

የወንደሙን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ!!

በላስታ ወረዳ 025/ድብኮ/ቀበሌ ኗሪ የሆነው ግለሰብ ለአቅም ሄዋን ያልደረሰች የ 10 ዓመት ታዳጊ ሴት ልጅ በመድፈር በእስራት ተቀጣ፡፡ የወንድሙን ልጅ አብረው ለእረኝነት በተሰማሩበት ቆጋ ወንዝ እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ ነሐሴ 20/2012 ዓ.ም አስገድዶ የደፈራት በመሆኑ የላስታ ወረዳ ዐ/ሕግ ከፖሊስ ተጣርቶ የደረሰውን መዝገብ መርምሮ በወንጀል ህግ አንቀፅ 627-1 ክስ መስርቶ የተከራከረ ሲሆን የላስታ ወረዳ ፍ/ቤት በ 22/01/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎል፡፡

03/10/2020
02/10/2020

የላስታ ወረዳ አቃቤ ህግ ጽ/ቤት በላስታ ወረዳ ላሊበላ ከተማ መቀመጫውን ያደረገ ጽ/ቤት ሲሆን በዚህም በስሩ በዋናነት የወንጀል የስራ ሂደት የፍታብሄር የስራ ሂደት፤ የሰነዶች የስራ ሂደት ሃላፊውን ጨምሮ የያዘ ሲሆን በአዲሱ አደረጃጀትም የሰብአዊ መብት የስራ ሂደትን የሚይዝ ይሆናል ፡፡
በዚህ ፔጅ የእያንዳንዱ የስራ ሂደቶች ዝርዝር ስራወች ፤ተገልጋዮች ሊያሟሏቸው ስለሚገቡ ጉዳዮች ፤ማህረሰቡ ሊገነዘባቸው yሚገቡ ህጎች፤በተቋሙ የተሰሩ አስተማሪ የሆኑ እና የተመረጡ ስራወች ይለቀቁበታል ፡፡

02/10/2020

ፍትሐዊ የሆነ ስራ በመስራት የሕዝብን ጥቅም እናስጠብቃለን።

Public figure

29/09/2020

ላስታ ወረዳ ዐ/ሕግ ፅ/ቤት በውስጡ አራት የስራ ሂደት ያሉት ሲሆን የፍታብሔር የስራ ሂደት፤የወንጀል የስራ ሂደት የሰብአዊ መብት የስራ ሂደት እና የሰነዶች እና ጠበቆች ምዝገባ ዋና የስራ ሂደት ይይዛል፡፡

Address

Lalibela

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ላስታ ወረዳ ዐ/ሕግ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share