የዋድላ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Kon
  • የዋድላ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

የዋድላ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የዋድላ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት, Government Organization, 22, Kon.

ዋድላየአሸድዬና የቡሄ በዓልን እንዲሁም የቅኔ ፌስትባል በሚያምር መልኩ አከበረ።
22/08/2025

ዋድላ
የአሸድዬና የቡሄ በዓልን እንዲሁም
የቅኔ ፌስትባል በሚያምር መልኩ አከበረ።

በዋድላ ወረዳ የአሸንዳየ በዓልን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ ።ነሃሴ 7 /2017 ዓ.ም (ዋድላ ወረዳ  ባህልናቱሪዝም ጽ/ቤት )በሰሜን ወሎ ዞን በ...
13/08/2025

በዋድላ ወረዳ የአሸንዳየ በዓልን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ ።

ነሃሴ 7 /2017 ዓ.ም (ዋድላ ወረዳ ባህልናቱሪዝም ጽ/ቤት )

በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ የ2017 ዓ.ም የአሸንዳየና የቡሄ በዓልን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ወጣቶችና ልጃገረዶች ባህሉን በጠበቀ መልኩ ለማክበር እየተዘጋጁ መሆኑን የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታወቀ ።

የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁን ወንድሜነው እንደገለፁት እንደዋድላ ወረዳ የአሸንዳየና የቡሄ በዓልን ሳይበረዝና ሳይከለስ ባህሉን ፣ወጉን ፣ ልምዱንና አለባበሱን በጠበቀ መልኩ በአደባባይና በፓናል ውይይት የቅኔ ውድድር ጭምር ለማክበር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል ። በተለይ ቅኔ ዋድላ ላይ የመጀመሪያ ምንጭ ሁኖ ታላቁ ፈላስፋ ዮሐንስ ገብላዊ የመሰረተው ስለሆነ በዓሉን በቅኔ ጭምር የምናከብረው ለሚቀጥለው ቅኔው በአለም ደረጃ የጥናትና ምርምር ማእከል አድርጐ ለማቆየት እንደ ወረዳ መንግስት እየሰራ ነው።

ሀላፊው አክለውም የአሸንዳየና ቡሄ ባህላዊ አጨዋወትን በትክክል የሚአሳዩ እንደወረዳ 40 ወጣቶችና 40 ልጃገረዶች ተመልምለው እስከ ነሀሴ 15 / 2017 ዓ.ም ድረስ በተግባር ልምምድ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል ።

አቶ ካሳሁን ወንድሜነው አያይዘውም የወረዳችን የአባቶቻችንና የእናቶቻችን ባህል አስጠብቆ ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍና ለማስቀጠል ወጣቶቹና ልጃገረዶቹ የዋድላን ባህል ሊገልጽ የሚችል አለባበስና የፀጉር አሰራር በመሰራት ቱባ ባህሉን አጉልቶ ለማሳየት በሚያስችል መልኩ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል ።

በዓሉ በሚከበርበት ወቅት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሌላ አካበቢን አለባበስና የፋሽን አለባበስን መልበስ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን ጠቁመው የአንድ አካባቢ ማህበረሰብ ባህል መገለጫ አንዱ አለባበስ መሆኑን አቶ ካሳሁን ያሉ ሲሆን መላው የባዓሉ ባለቤት በሙሉ ነሀሴ 16/2017 ዓ.ም የሚከበረውን የአሸንዳዬና ቡሄ በዓል የዋድላ ወረዳን ባህል ሊገልጽ የሚችል አለባበስ በመልበስ በዓሉን ማክበር ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

13/08/2025

በዋድላ ወረዳ የአሸንዳየ በዓልን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ ።

ነሃሴ 7 /2017 ዓ.ም (ዋድላ ወረዳ ባህልናቱሪዝም ጽ/ቤት )

በሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ የ2017 ዓ.ም የአሸንዳየና የቡሄ በዓልን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ወጣቶችና ልጃገረዶች ባህሉን በጠበቀ መልኩ ለማክበር እየተዘጋጁ መሆኑን የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታወቀ ።

የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁን ወንድሜነው እንደገለፁት እንደዋድላ ወረዳ የአሸንዳየና የቡሄ በዓልን ሳይበረዝና ሳይከለስ ባህሉን ፣ወጉን ፣ ልምዱንና አለባበሱን በጠበቀ መልኩ በአደባባይና በፓናል ውይይት የቅኔ ውድድር ጭምር ለማክበር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል ። በተለይ ቅኔ ዋድላ ላይ የመጀመሪያ ምንጭ ሁኖ ታላቁ ፈላስፋ ዮሐንስ ገብላዊ የመሰረተው ስለሆነ በዓሉን በቅኔ ጭምር የምናከብረው ለሚቀጥለው ቅኔው በአለም ደረጃ የጥናትና ምርምር ማእከል አድርጐ ለማቆየት እንደ ወረዳ መንግስት እየሰራ ነው።

ሀላፊው አክለውም የአሸንዳየና ቡሄ ባህላዊ አጨዋወትን በትክክል የሚአሳዩ እንደወረዳ 40 ወጣቶችና 40 ልጃገረዶች ተመልምለው እስከ ነሀሴ 15 / 2017 ዓ.ም ድረስ በተግባር ልምምድ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል ።

አቶ ካሳሁን ወንድሜነው አያይዘውም የወረዳችን የአባቶቻችንና የእናቶቻችን ባህል አስጠብቆ ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍና ለማስቀጠል ወጣቶቹና ልጃገረዶቹ የዋድላን ባህል ሊገልጽ የሚችል አለባበስና የፀጉር አሰራር በመሰራት ቱባ ባህሉን አጉልቶ ለማሳየት በሚያስችል መልኩ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል ።

በዓሉ በሚከበርበት ወቅት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሌላ አካበቢን አለባበስና የፋሽን አለባበስን መልበስ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን ጠቁመው የአንድ አካባቢ ማህበረሰብ ባህል መገለጫ አንዱ አለባበስ መሆኑን አቶ ካሳሁን ያሉ ሲሆን መላው የባዓሉ ባለቤት በሙሉ ነሀሴ 16/2017 ዓ.ም የሚከበረውን የአሸንዳዬና ቡሄ በዓል የዋድላ ወረዳን ባህል ሊገልጽ የሚችል አለባበስ በመልበስ በዓሉን ማክበር ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

ኪሮስ አፋፍ
24/06/2025

ኪሮስ አፋፍ

19/06/2025

የዘመኑ ድንቅ ሥራ ዳግማዊ ላሊበላ!
============+++======
የዳግማዊ ላሊበላ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ከጋሸና ወደ ላሊበላ በሚወስደው መንገድ ላይ በስተግራ በኩል በአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ከ2003 ዓ.ም እስከ 2010 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ውስጥ አባ ገብረ መስቀል በሚባሉ አባት ተጀምሮ በሌሎች አባቶች እና በአካባቢው ማኅበረሰብ እገዛ የተሠራ ከአለት ላይ ተፈልፍሎ የተሠራ ውብ አሻራ ነው።

ከዋድላ ወረዳ ባሕል እና ቱሪዝም ፅ/ቤት ና ስራውን ከሰሩት አባትና ወንድሞች ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ቤተ ክርስቲያኑ በውስጡ ብዙ ክፍሎች ያሉት፣ ሳቢ እና ማራኪ በኾነ መልኩ ተጠርቦ የተሠራ ነው፡፡ የቀደሙ አባቶች ሥራ በዚህ ትውልድ መሥራት እንደሚቻል የሚያሳይ ብዙ ፋይዳ ያለው የጥበብ ውጤት ነው።

የተሠራበት ቁስ እና የአሠራር ጥበቡ የተለየ እንዲኾን አድርጎታል፡፡ የፍልፍል አብያተ ክርስትያናቱ በወረቀት ላይ የተሳለ ዲዛይን በሌለበት እና በዘመናዊ ትምህርት የምህንድስና ሥራ ልምድ በሌላቸው በተፈጥሮ እና በልምድ ባገኙት ዕውቀት እና ጥበብ በእጅ መጥረቢያ ተጠርቦ የተሠራ መኾኑ አስደናቂ ያደርገዋል፡፡

አብያተ ክርስቲያናቱ ብዛታቸው አራት ናቸው። የተለያየ ቅርጽ እና መጠንም አላቸው፡፡ ኪነ ሕንጻዎቹ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲውሉ ታስበው ተፈልፍለው የታነጹ ናቸው፡፡

ቤተ ኤፍሬም መጀመሪያ የሚገኘው የፍልፍል ቤተ ክርስቲያኑ ክፍል ነው። አበባ መሰል የሦስት ማዕዘን ቀርጽ ይዞ ራሱን ችሎ የተፈለፈለ ነው፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን አሥራ ሁለት ምሰሶዎች ወይም አምዶች አሉት። በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት በ12ቱ ሐዋርያት ምሳሌነት የተሠሩ መኾናቸውም ይነገራል፡፡

የሁሉም ሐዋርያት ስሞች የመጀመሪያ ፊደላት በእያንዳንዱ አምዶች ላይ ተፈልፍለው ተቀርጸው ይታያሉ፡፡

ቤተ ኤፍሬም በአቅራቢያው የሚገኘውን የቅዱስ ላሊበላ ውቅር ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የቤተ ጊዮርጊስን አርዓያ በማድረግ የተሠራ እንደኾነ ይነገራል፡፡

ቤተ ኤፍሬም ዙሪያውን ጣራ የሌለው ቅኔ ማህሌት ያለው ከውስጥ ለመቅደስ ከተዘጋጀው ክፍል ውስጥ ከአለት የተቀረጸ መንበር ይገኛል። በስተጀርባ በኩል ካለው የዙሪያው የቅኔ ማህሌት ግድግዳ ላይ የኢትዮጵያ ካርታ በሰው አምሳል ተስሎ እጆቿን ዘርግታ ይታያል፡፡

ከጎኑም "ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሃ ሀበ እግዚአብሔር" (ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች) የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በግዕዝ ተጽፎ ይገኛል፡፡

ቤተ መቅደሱ ውስጥ ጠበብ ያሉ ሁለት ክፍሎች አሉት፡፡ ጣራው እና ግድግዳው ከአለቱ ላይ የተቀረጹ የተለያዩ ቅርጾች እና የግዕዝ ቃላት ተቀርጸው ይገኙበታል። ሲታዩ ማራኪ ናቸው፡፡

ቤተ ደቅስዮስ ሁለተኛው ቤተ መቅደስ ነው። ከቤተ ኤፍሬም ጋር ተያይዞ የተሠራ ነው፡፡ በውስጥ በኩል የመገናኛ በር አላቸው። የተለያየ መጠን ያላቸው አራት በሮች እና ሦስት መስኮቶችም አሉት፡፡

በሮቹ የቀስተ ደመና ቅርጽ ያላቸው እና አሰራራቸው ማራኪ ነው፡፡ መስኮቶቹ ደግሞ ከታች ሰፋ ብለው ከላይ እየጠበቡ የሚሄዱ ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጡ ግድግዳው ከወገብ በላይ እና የውስጥ ጣራው ከአለቱ ላይ በተፈለፈሉ የተለያዩ ጌጦች እና የግዕዝ ጽሑፎች ያጌጠ እና አሠራሩ አስደናቂ ነው፡፡

በዚህ ክፍል ውስጥ ቤተ መቅደስ፣ ቅድስት እና ቅኔ ማሕሌት ተብለው የተለዩ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች ይገኛሉ፡፡
ከግድግዳው ላይ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ትርጓሜ ያላቸው ቅርጾች አሉበት። ከእነዚህ መካከል መስቀል፣ ፈረስ ከነ ሰረገላው እና የተለያዩ ጽሑፎች

15/06/2025

🇲🇱በዋድላ ወረዳ ውስጥ ታሪካዊ ና ታሪክ ተሰርቶባቸዋል በርካታ የቱሪስት ፍሰት አለባቸው ለምርምር፣ለፍልስፍና፣ለአርኪዮሎጅ ጥናት ለማዕድን ፣ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነች ዋድላ ወረዳ አንዷ ነች። በውስጧም ብዙ ታሪካዊ ቦታዎችን የያዘች ነች። ከእነዚህም ውስጥ በትንሹ ቅጭብጭብ አድርገን እንደሚከተለው እናቀርባለን ።
1ኛ ፦ ወገዴት ና አካባቢዋ፦ ከወረዳው ምስራቅ ደቡባዊ ክፍል የምትገኘ ስትሆን ከወረዳው በ24 km ርቀት ተገኛለች።
🇲🇱 የስሟ ትርጉም ና ምንነት
✍ የወገዴት ቂርቆስ ታሪክ እና የቦታው ስያሜ በዘመነ መሳፍንት ጊዜ በዚሁ ቦ ታ ሌሎች እንግዶች መጥተው ስለቦታው ታሪክ ፣ምንነት ከቦታው ባልቤቶች ወይም ኗሪዎች ጋር ወሬ ወይም ወግ በሚያወሩበት ስዓት ስለቦታው ታሪክ የሚያወሩት ወይም የሚያወጉት እንግዶች ሰወች የቦታው ባለቤቶች ወይም ኗሪዎች ወጉ ትክክለኛ አለመሆኑን ወይም አልጥማቸው በሚልበት ጊዜ ይህ ወግ ወደየት እየሄድ ነው በማለት ሲመልሱ በዚያው የወገዴት ስያሜ ወግ-ዴት በማለ ት ወጥቶለታል ፅድቆለታል በማለት የዕድሜ ባለፀጋ ሰወች ይናገራሉ።
# የወገዴት ታሪክ ብዙነው ብቻ በአጭሩ ቀጭብጨብ አድርገን የሰማንውን ስንነግራችሁ በዚህ ቦታ አፄይኩኖ አምላክ የረገጠው ና ገድል የፈፀመበት መሆኑን አባቶች ይናገራሉ።ይኩኖአምላክ የአማረኛን ቋንቋ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን በይፋ ያወጀ ሰሎምናዊ ስርወ መንግስትን ያስቀጠለ የአማሮች አባት ነው ።
🇲🇱 ይኲኖአምላክ ከዛግዊ ዘመነ መንግስት በኋላ በስደት የቀጠለው የአክሱም መንግስት ዘር ነው።
1ኛ ፦ ማህበረም ወድም
2፦ አግብኦ ፅዮን
3፦ ፅንፈ አርኦድ
4፦ባሕር አርኦድ
5፦ተስፋ ኢየሱስ
6፦ነጋሽ ዛሬ
7 ፦አስፋሕ
8 ፦ያዕቆብ
9 ፦እድም አሠገድ
10ኛ፦ ይኩኖአምላክ ናቸው።
✍ ይኩኖ በስልጣን የቆየበት ጊዜ 15 አመት ማለትም 1253-1268 የኢትዮጲያ ንጉስ ሁኖ ከናዕኩቶለአብ ተቀብሎ አስተዳድሯል። ለማንኛውም ወደ ወገዴት ቂርቆስ ታሪክ እንመለስ ወገዴት በዘመኑ የዘመነ መንግስት መዳረሻ ቦታ እንደነበረች በአፈታሪክ አባቶች ይናገራሉ። በዚህ ቦታ አፄ ይኩኖ አምላክ እነ ይትባረክ ወገዴትን ከጥቦ እስከ አዘዞ አሁን ላይም የቅዱስ ቂርቆስ እናቱ እየሉጣ ፅላት እስከአለበት ድረስ ብዙ ታሪካዊ ስራ ተሠርቶበታል ጦርነት ተደርጓበታል የእያንዳንቸው ጦርነት የተደረገባቸው በዚሁ ቦታ ሲሆን ጥቦ ያለውን አጀማመር ሲናገሩ በጣም እየተፋፈመ መምጣቱ እና አይይ እንዴየ ከባድ መሆኑን ብለው ሲናገሩ እና ወደ ያዴ እንደተሸጋገሩ መቀጠሉን ሲያውቅ የተነገረው ነው።
🇨🇬ሲሉ አባቶች ተናግረዋል ከዚያም ታዞልና አለቆመም ወደፊት እንቀጥል ሲሉ አዘዞ ብለው አሁን ላይ ታቦቱ ወደሜዳ ወርዶ የሚያድርበት ጥምቀት ባህር የሚፈፀምበት ከዚሁ አዘዞ ቦታ በዚሁ ቦታ ተጋድሎ አድርገውበታል ብለው የዕድሜ አባቶች ተናግረዋል። ከዚያም አሁን ቤተክርስቲያኑ ካለበት ቦታ እንደአረፈ እና በስሙ በአፄው ስም 3 የዕድሜ ጠገብ ፅዶች መከነ መቃብር ያለበት በንጉሱ ዘመን አንስተው ያሉ አሁን ድረስ በስሙ ይጠሯቸዋል። ይህ ቦታ በውስጡ ብዙ የቱሪዝም መስህብ የያዘ ታላቅ የቅርስ ቦታ ነው ።እነዚህም መስህብ የምንላቸው አባቶች ሲነግሩን በዚሁ ቦታ የሚገኙ የዋሻ አይነቶች አሉ
🇲🇱 ጨለማ ዋሻ ይህ ዋሻ ወደላሊበላ የሚወስድ ነው ይላሉ።
🇲🇱 አመዴ ዋሻ
🇲🇱 ክፍሌ ዋሻ
🇲🇱ፃርቃኔ ዋሻ ይገኙበታል።
✍ ከወሻወቹ ደኖቹ ዕድሜ ጠገብ ፅዶች አዕዋፋት ብዙ ታሪክ

የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት "የደብረ ሳህል የዶጊት ሚካኤል ወሀመረ ብርሃን ቤተ-ዮሐንስ አቡነ ተክለ ሀይማኖት የአረንጓዴ መስህብ ሀብት ልማት ፕሮጀክት ትውውቅ አደረገ።ኮን፦ግንቦት ...
22/05/2025

የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት "የደብረ ሳህል የዶጊት ሚካኤል ወሀመረ ብርሃን ቤተ-ዮሐንስ አቡነ ተክለ ሀይማኖት የአረንጓዴ መስህብ ሀብት ልማት ፕሮጀክት ትውውቅ አደረገ።

ኮን፦ግንቦት 14/2017 ዓ.ም (ዋድላ ባህልና ቱሪዝም )

በሰሜን ወሎ ዞን የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት "የደብረ ሳህል የዶጊት ሚካኤል ወሀመረ ብርሃን ቤተ-ዮሐንስ አቡነ ተክለ ሀይማኖት የአረንጓዴ መስህብ ሀብት ልማት የፕሮጀክት ትውውቁን በዛሬው ዕለት የሀይማኖት አባቶች፣ የወረዳው አመራሮች እና የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት አካሂዷል።

ፕሮጀክቱ እውን የሚሆንበትን መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት በዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቱሪዝም አገልግሎት ባለሙያ ዲ/ን ጌታዬ ፍቅር ፕሮጀክቱ ሊሟሉለት የሚገቡ መሰረተ ልማቶች፣ ፕሮጀክቱን ለመተግበር ያሉ ምቹ ሁኔታዎች፣ ፕሮጀክቱን ለመተግበር ሊፈጠሩ የሚችሉ ስጋቶች በጥልቀት ያመላከቱ ሲሆን ፕሮጀክቱ አልቆ ወደስራ ሲገባ ማህበራዊ እሴትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስተሳስርና ለንግድና ለቱሪዝም መስህብነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አብራርተው ፕሮጀክቱ ከ30 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑም በትውውቁ ተመላክቷል።

ውይይቱን የዋድላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁን ወንድሜነው እና የዋድላ ወረዳ ቤተ-ክህነት ዋና ስራአስኪያጅ ሊቀ-ልሳናት እየበሩ ሀይሉ በጋራ በመሆን መርተውታል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ለአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ለሚመለከታቸው አካላት በእጅጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራት እንዳለበት ጠቁመው ፕሮጀክቱ ስራ ላይ ከዋለ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይጠበቃል ያሉት ተሳታፊዎቹ ይህንን ፕሮጀክት ዳር ለማድረስ የመጀመሪያው ስራ መሬቱን ከሶስተኛ ወገን ነጻ የማድረግ ስራ፣ አጠቃላይ የዲዛይን ስራ መስራትና ሌሎች የማስፈጸሚያ ስልቶችንና የሀብት ማፈላለግ ስራ በእጅጉ ይጠይቃል ብለው ወጭ የምንቆጥብበትን መንገድ በመፍጠር ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ።

፨እነሆ  ምን ቢቃጠሩ ደረሰ ቀኑ  ጥምቀት!!የሊቃውንት መፋለቂያ  የጥበብ ማማ በሆነችው በዋድላ ወረዳ  ከባለፋት አመታታ ባደገና ባህላዊና ሀይማኖታዊ  ትውፈቱን በጠበቀ መልኩ ለማክበር በ13...
16/01/2025

፨እነሆ ምን ቢቃጠሩ ደረሰ ቀኑ ጥምቀት!!የሊቃውንት መፋለቂያ የጥበብ ማማ በሆነችው በዋድላ ወረዳ ከባለፋት አመታታ ባደገና ባህላዊና ሀይማኖታዊ ትውፈቱን በጠበቀ መልኩ ለማክበር በ136 አብያተ ክርስቲያን የቅድመ ዝግጅት ስራው ተጨርሶል።
፨በተለይ የወረዳው ርዕሰ ከተማ በሆነችው በኮን ከተማና በጋሸና ከተማ የተዋቀረው የጥምቀተ ባህር ኮሚቴና የወጣት ተወካዮችን እንዲሁም የበአሉ ባለድርሻ አካላትጨምሮ በተሻለ መልኩ የከተራ በአሉን ጨምሮ የቅድመዝግጅት ስራወች እየተገመገሙ እየተመሩ ነቸው።
፨በመሆኑም ሁሉም የወረዳችን ኑሪወች የጥምቀት የከተራ በዓሉ በቀን10/5/2017 ማለትም ቅዳሜ ጥዋት ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው ወደ ታቦት ማደሪያቸው የሚወርዱና የከተራ በዓሉ የሚከበር መሆኑን አውቆ የቅድመ ዝግጅት ስራወችን ከሚመለከታቸው አስተባባሪ ኮሚቴወች ጋር በመቀናጀት ስራውን እንዲሰራ እያል በበዓሉ ወቅት ሁሉም የበዓሉ ታዳሚ በአሉን የሚመጥን የባህል አልባሳት ለብሶ ታቦታቱን እንዲያጅብ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

16/01/2025
24/12/2024

የምስራች

Address

22
Kon

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የዋድላ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share