የቦርከና ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት

የቦርከና ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ይህ ገፅ በግብርና ታክስ ዙረያ መረጃ የሚሰጥበትና የግንዛቤ ፈጠራ ስራ የሚሰራበት ሲሆን ህብረሰተሰቡ በዚህ ዙሪያ ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማድረግ ለከተማችን ልማት የምንተጋገዝበት ይሆናል።

15/07/2026

የታክስ/ግብር ውሳኔ ቅሬታ አቀራረብ

09/07/2026

የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1142/2018 በአጭሩ

***********************************

የታክስ አስተዳደራችንን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም የግብር ስወራን ለመከላከል የገቢዎች ሚኒስቴር አዲስ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1142/2018 (Directive No. 1142/2026) አውጥቷል።

በመመሪያው የተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

•ዲጂታል ደረሰኝ (Electronic Invoice)፦ በየቀኑ የሚደረጉ ግብይቶች በሚኒስቴሩ እውቅና ባገኘ ሶፍትዌር አማካኝነት ዲጂታል ሆነው ይመዘገባሉ። እያንዳንዱ ደረሰኝ ልዩ የደረሰኝ ምዝገባ ቁጥር (IRN) እና ፈጣን መላሽ ኮድ (QR Code) ይኖረዋል።

•የኢኮሜርስ (e-Commerce) እና የዲጂታል ገበያ ቦታዎች፦ በኦንላይን መድረኮች ላይ የሚከናወኑ ግብይቶችም በተናጠል በሻጩ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ደረሰኝ እንዲቆርጡ ሥርዓት ተዘርግቶላቸዋል።

•ከቀጥታ ግንኙነት ውጭ (Offline Mode) መሥራት፦ የኢንተርኔት ግንኙነት በሚቋረጥበት ወቅት ግብይት እንዳይስተጓጎል ለተወሰነ ጊዜ ከመስመር ውጭ ሽያጭን መመዝገብና ግንኙነቱ ሲመለስ በቀጥታ ወደ ማዕከላዊ ሲስተሙ መላክ የሚያስችል አማራጭ ተካቷል።

• ጠንካራ የደህንነት ሥርዓት፦ ጥቅም ላይ የሚውሉ የሽያጭ መመዝገቢያ ሶፍትዌሮች ሁሉ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የደህንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ለአቅራቢዎችና ለአገልግሎት ሰጪዎች የተቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎች፦

•የዕውቅና ምስክር ወረቀት ለማግኘት አልሚዎችና አቅራቢዎች እንደየዘርፋቸው ተስማሚ የባለሙያ ብዛትና በየሁለት ዓመቱ የሚታደስ የመልካም አፈጻጸም ዋስትና (Performance Guarantee) በባንክ ወይም በመድን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፦

•የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት አቅራቢዎች፦ 30,000 የአሜሪካን ዶላር ዋስትና እና ቢያንስ 4 ባለሙያዎች

•የሶፍትዌር አገልግሎት አቅራቢዎች ፦ 50,000 የአሜሪካን ዶላር ዋስትና እና ቢያንስ 6 ባለሙያዎች

•የኢኮሜርስ ኦፕሬተሮች፦ 25,000 የአሜሪካን ዶላር ዋስትና

•ለራሱ ብቻ የሚጠቀም ታክስ ከፋይ፦ 15,000 የአሜሪካን ዶላር ዋስትና

የዋስትና መጠኑና የባለሙያዎቹ ብዛት እንደ ታክስ ከፋዮች ብዛትና ዓመታዊ ጥቅል የሽያጭ መጠን ሊጨምር ይችላል። ይህ መመሪያ በታክስ ሕጉ መሠረት የሂሳብ መዝገብ በሚይዙ ሁሉም ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

09/07/2026

የፌደራል የታክስ አስተዳደርን ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ይዟቸው የመጡ አዳዲስ ለውጦች

የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008ን ለማሻሻል የወጣው ማሻሻያ አዋጅ በርካታ መሠረታዊ ለውጦችንና አዳዲስ አሰራሮችን ይዞ ቀርቧል። ዋና ዋናዎቹ ለውጦች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. አዳዲስ ትርጓሜዎችና የተቋም ስም ለውጥ

👉🏽 መስማማት (Settlement)፡ የታክስ አለመግባባቶችን በውይይትና በስምምነት ለመፍታት የሚያስችል አዲስ አሰራር በትርጓሜ ደረጃ ተካቷል።
👉🏽 የታክስ ማጭበርበር፡ ታክስን ለመሰወር የሚደረጉ እንደ ሐሰተኛ ደረሰኝ ማቅረብና ገቢን መደበቅ ያሉ ተግባራት በዝርዝር ተተርጉመዋል።

2. የታክስ አለመግባባቶችን በመስማማት የመፍታት ሥርዓት

ይህ አዋጁ ይዞት የመጣው ትልቁ ለውጥ ሲሆን፣ ክርክሮችን በፍርድ ቤት ወይም በይግባኝ ኮሚሽን ከመጨረስ ይልቅ በባለሥልጣኑና በታክስ ከፋዩ መካከል በሚደረግ ስምምነት እንዲቋጩ የሚያስችል ነው።
👉🏽 የአስማሚ ሚና፡ የታክስ ባለሥልጣኑ ነጻና ገለልተኛ "አስማሚ" በመመደብ ሂደቱን ያመቻቻል።
👉🏽 ሂደቱ፡ መስማማት የሚቻለው በታክስ ውሳኔ ላይ ቅሬታ ከቀረበ በኋላ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት ለይግባኝ የተቀመጡ የጊዜ ገደቦች ታግደው ይቆያሉ።
👉🏽 ውጤቱ፡ የሚደረሰው ስምምነት በጽሁፍ ሆኖ በሁለቱም ወገኖች ከተፈረመ አስገዳጅና ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

3. በአዲስ ማስረጃ አቀራረብ ላይ የተጣለ ገደብ

👉🏽 ታክስ ከፋዮች የታክስ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በቅሬታ ወይም በይግባኝ ወቅት አዲስ ማስረጃ የማቅረብ መብታቸው ተገድቧል።
👉🏽 አዲስ ማስረጃ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው ማስረጃው የታወቀው ከውሳኔ በኋላ ከሆነ ወይም አቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልቀረበ ብቻ ነው።
👉🏽 በዚህ መልክ የሚቀርብ አዲስ ማስረጃ በታክስ ዕዳው ላይ 20% ቅጣት እንዲከፈል ያደርጋል።

4. የታክስ ስሌት ማሻሻያና የይርጋ ጊዜ

👉🏽 የማጭበርበር ድርጊት፡ ባለሥልጣኑ የታክስ ማጭበርበር መኖሩን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካገኘ፣ የታክስ ስሌቱን የማሻሻያ ጊዜ (ይርጋ) እስከ 10 ዓመት እንዲራዘም ተደርጓል።
👉🏽 መደበኛው የታክስ ስሌት ማሻሻያ ጊዜ ግን በነበረበት 5 ዓመት ቀጥሏል።

5. በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የታክስ ክሊራንስ

👉🏽 የታክስ ዕዳ ያለባቸው ነገር ግን በክርክር ላይ ያሉ ወይም የክፍያ ስምምነት የፈጸሙ ታክስ ከፋዮች የንግድ ፈቃድ ለማደስ፣ በጨረታ ለመሳተፍና ብድር ለማግኘት የሚያስችላቸው "በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የታክስ የምስክር ወረቀት" ማግኘት የሚችሉበት አሰራር ተዘርግቷል።

6. የታክስ ከፋዮች ምደባ

👉🏽 የታክስ ከፋዮች ምዝገባ ኢትዮጵያ በተቀበለችው የዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ምደባ ደረጃ (ISIC) መሠረት እንዲከናወንና ታክስ ከፋዮች በተለያዩ ምድቦች እንዲመደቡ ተደንግጓል።

7. የቅጣት ማስተካከያዎች

👉🏽 ደረሰኝ አለመስጠት፡ የታክስ ደረሰኝ ሳይሰጥ ሲቀር የሚጣለው አስተዳደራዊ ቅጣት በእያንዳንዱ ደረሰኝ ብዛት ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እንዲሆን ተሻሽሏል።
👉🏽 የድርጅት ኃላፊዎች ተጠያቂነት፡ አንድ ድርጅት የታክስ ወንጀል ሲፈጽም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ወይም የፋይናንስ ኃላፊ ወንጀሉ መፈጸሙን ካወቁ ወይም ካዘዙ ተጠያቂ ይሆናሉ።

02/07/2026

የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ
*********************************

አንድ ግብር ከፋይ የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ በሚያከናውንበት ጊዜ ለግብይቱ የሽያጭ ደረሰኝ የመቁረጥ ግዴታ አለበት፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ግብር ከፋዩ ከንግድ ሥራው እንቅስቃሴ ውጪ በሚገኙ ሌሎች ገቢዎች ላይ ወይም ማንኛውም በጥሬ ገንዘብ፣ በቼክ ወይም በባንክ በታክስ ከፋዩ ስም ለተከፈለ ክፍያ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ መቁረጥ አለበት፡፡

በሌላ በኩል፣ ግብይቱ በዱቤ የተፈጸመ በሚሆንበት ጊዜ አሠራሩ የተለየ ጥንቃቄን ይሻል። ግብር ከፋዩ አስቀድሞ የዱቤ ዕቃ ወይም አገልግሎት ሽያጭ ሲያከናውን የዱቤ ደረሰኝ መስጠት ያለበት ሆኖ በስምምነታቸው መሰረት ለተሸጠው ዕቃ ወይም አገልግሎት ክፍያ በሚፈጸምበት ወቅት ሻጩ ለተቀበለው ገንዘብ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ (CRV) መቁረጥ ይኖርበታል። በዚህ ጊዜ ቀደም ሲል በዱቤ ደረሰኙ ላይ የተጠቀሰውን ቁጥር የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ላይ ማወራረስ ይኖርበታል።

ከላይ የተገለፁት ቢኖሩም፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ከዕቃ ወይም ከአገልግሎት ግብይት ገዢ የቅድሚያ ክፍያ (Advance Payment) የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ መስጠት ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ለቅድሚያ ክፍያ (Advance Payment) የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ (CRV) ፈፅሞ አይፈቀድም፡፡

በግምት የተወሰነ የታክስ ስሌት እንዴት ሊታረም ይችላል?********************************•የግምት የታክስ ውሳኔ ላይ ስህተት አለበት የሚል ታክስ ከፋይ የግምት ታክስ ስሌት ...
24/06/2026

በግምት የተወሰነ የታክስ ስሌት እንዴት ሊታረም ይችላል?
********************************

•የግምት የታክስ ውሳኔ ላይ ስህተት አለበት የሚል ታክስ ከፋይ የግምት ታክስ ስሌት ማስታወቂያ በተሰጠው ከ5 ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የታክስ ስሌቱን ላከናወነው ወይም ውሳኔውን ለሰጠው የስራ ሂደት ጥያቄውን በጽሑፍ በማቅረብ ስህተቱ እንዲታረምለት ሊጠይቅ ይችላል፤

•የግምት ታክስ ስሌቱን የሠራው ሥራ ሂደት የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ ከሰጠው በኋላ በታክስ ስሌትና አወሳሰን ሂደት የተፈጸመ ግልጽና የማያከራክር ስህተት የፈጸመውን ባለሙያ አስተያየት ጭምር በማያያዝ ስህተቱ እንዲታረም የውሳኔ ሀሳብ ለቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ያቀርባል፤

•የቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ስህተቱ እንዲታረም ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት በአግባቡ መመርመር ያለበት ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበለትን ባለሙያና የስራ ሂደት አስተባባሪን ጠርቶ ማነጋገርና ማወያየት ይችላል፤

•ስራ አስኪያጁ ታክስ ከፋዩ ጥያቄ ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጥያቄው ላይ ውሳኔ መስጠት አለበት፤

•የቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ሊታረም የሚችል ስህተት አለመኖሩን በመግለጽ ውሳኔ የሰጠ እንደሆነ ታክስ ከፋዩ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ካለው ውሳኔው በደረሰው በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለዋና መ/ቤቱ የሚመለከተው ዳይሬክቶሬት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ዳሬክቶሬቱም በ2 የሥራ ቀናት ውስጥ እንደ ጉዳዩ ሁኔታ ለሀገር ውስጥ ታክስ ከፋይ ወይም ለሕግ ማስከበር ም/ዋና ዳይክተር (ሚኒስትር ዴኤታ) ያስተላልፋል፤

•በቀረበው ቅሬታ ላይ የሀገር ውስጥ ታክስ ወይም የሕግ ማስከበር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ለጥያቄው በቀረበው በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ ሊሰጥበት ይገባል፤

•በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ታክስ ከፋይ ውሳኔው በደረሰው በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለዋና ዳይሬክተሩ በጽ/ቤቱ በኩል ሊያቀርብ ይችላል፤

•ጥያቄው በቀረበ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዋና ዳይሬክተሩ ጽ/ቤት በኩል ለታክስ ከፋዩ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፤

•ስህተቱ እንዲታረም ከተወሰነ፡- የታረመው ውሳኔ የመጀመሪያ ውሳኔ በሰጠው የስራ ክፍል በኩል የተስተካከለ የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ ይሰጣል፤

•ለታክስ ከፋዩ ተስተካክሎ የሚሰጠው የታክስ ስሌት ማስተወቂያ ቀደም ሲል የተሰጠው የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ የተሻረ መሆኑን የሚገልጽና ስህተቱ በታረመበት ጊዜ ያለውን ቀንና ቁጥር የያዘ መሆን አለበት፤

•ስህተትን ለማረም የሚወስደው ጊዜ በታክስ ውሳኔ ላይ በመደበኛ መንገድ ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜን ከመቆጠር የሚያስቀር አይሆንም፤

•ከላይ በተዘረዘሩት መሠረት የሚቀርብ ስህተት የማረም ጥያቄ ጉዳይ በቅሬታ ወይም ይግባኝ ወይም በፍ/ቤት ደረጃ ደርሶ የታየ ቢሆንም የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

የታክስ ማስታወቂያ ዘግይቶ ማቅረብ የሚያስከትለው ቅጣትI. በሕግ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የታክስ ማስታወቂያ ግዴታውን ያልተወጣ ታክስ ከፋይ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ የታክስ ጊዜ ወይም ከፊል ለሆ...
08/06/2026

የታክስ ማስታወቂያ ዘግይቶ ማቅረብ የሚያስከትለው ቅጣት
I. በሕግ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የታክስ ማስታወቂያ ግዴታውን ያልተወጣ ታክስ ከፋይ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ የታክስ ጊዜ ወይም ከፊል ለሆነው ጊዜ ያልተከፈለውን ታክስ 5% (አምስት በመቶ) 25% (ሃያ አምስት በመቶ) እስኪሞላ ድረስ ቅጣት ይከፍላል፡፡
II. ለመጀመሪያው የሒሣብ ጊዜ ወይም ከፊል ለሆነው ጊዜ የታክስ ማስታወቂያ ያላቀረበ ሰው በዚህ ተራ ቁጥር (|) ድንጋጌ መሠረት የሚከፍለው ቅጣት ከብር 50ሺ (ሃምሳ ሺ ብር) አይበልጥም፡፡
III. ለዚህ አፈጻጸም ያልተከፈለ ታክስ ነው የሚባለው በታክስ ማስታወቂያ ላይ መታየት በነበረበት እና ታክሱ መከፈል ባለበት ቀን በተከፈለው ታክስ መካከል ያለው ልዩነት ነው፡፡
IV. በማናቸውም ሁኔታ የሚጣለው ቅጣት ቀጥለው ከተመለከቱት ከዝቅተኛው ያነሰ አይሆንም፦
ሀ) ብር 10ሺ (አሥር ሺ ብር)፤
ለ) በታክስ ማስታወቂያ ላይ መመልከት ከነበረበት የታክስ መጠን 100% (መቶ በመቶ)፡፡
V. በዚህ የተመለከተው ቢኖርም ታክስ ከፋዩ በታክስ ጊዜው ሊከፍል የሚገባው ታክስ የሌለ እንደሆነ፣ የታክስ ማስታወቂያ ሳያቀርብ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ የታክስ ጊዜ ብር 10ሺ (አሥር ሺ ብር) ቅጣት ይከፍላል፡፡
VI. የታክስ ማስታወቂያን ዘግይቶ በማቅረብ የተጣለው ቅጣት ተፈጻሚ የሚሆነው የታክስ ማስታወቂያ ሊቀርብባቸው በሚገባ:-
ሀ) በፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት በሚኖርበት የታክስ ማስታወቂያ፣
ለ) በፌዴራል የገቢ ግብር አዋጁ መሠረት በከፋዩ ተቀንሶ የሚያዝን ታክስ በሚመለከት የሚቀርብ የታክስ ማስታወቂያ፣
ሐ) በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሠረት የሚቀርብ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቂያ፣
መ) ወደ ሀገር በገባ ዕቃ ላይ የሚከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ኤክሳይዝ ታክስ የሚያሳይ የጉምሩክ ዲክላራሲዮን፣
ሠ) በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ መሠረት የሚቀርብ የታክስ ማስታወቂያ፣
ረ) በተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ መሠረት የሚቀርብ የታክስ ማስታወቂያ እና፣
ሰ) በታክስ ከፋዩ መቅረብ የነበረበት ታክስ ማስታወቂያ ላይ ነው፡፡
VII. የቅጣቱ አወሳሰን:-
ሀ) ለገቢ ግብር አዋጅ በዓመት፣
ለ) ለተጨማሪ እሴት ታክስ እንደታክስ ከፋዩ የግብይት መጠን በየወሩ ወይም በየሶስት ወሩ፤
ሐ) የደረጃ ሀ የተርን ኦቨር ታክስ ከፋይ እንደታክስ ከፋዩ የግብይት መጠን ለእያንዳንዱ በወር ወይም በሶስት ወር፣
መ) ለኤክሳይዝ ታክስ በወር፣
ሠ) ለደረጃ ለ ለተርን ኦቨር ታክስ ከፋይ በየሶስት ወሩ፣
ረ) ከተከፋይ ሂሳብ ተቀንዶ የተከፈለን ሳይጨምር የሰንጠረዥ መ ገቢ የታክስ ማስታወቂያ ዘግይቶ ማቅረብ ስለሚያስከትለው ቅጣት በተቀመጠው መሠረት የሚሰላ ይሆናል፡፡
የተጣለው ቅጣት ተፈጻሚ የሚሆነው የዘገየው የታክስ ማስታወቂያ እንድ አንድ ጥፋት ተቆጥሮ አንድ ቅጣት ተግባራዊ በማድረግ ነው፡፡

1. የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ምንድ ነው?የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ማለት የጥሬ ገንዘብ መመዝገቢያ መሳሪያ ወይም የሽያጭ ነቁጣ መሳሪያ ሲሆን የመደበኛውን ማንዋል ደረሰኝ ሰርዓት ተክቶ የተ...
06/06/2026

1. የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ምንድ ነው?
የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ማለት የጥሬ ገንዘብ መመዝገቢያ መሳሪያ ወይም የሽያጭ ነቁጣ መሳሪያ ሲሆን የመደበኛውን ማንዋል ደረሰኝ ሰርዓት ተክቶ የተለያዩ ሽያጮች መረጃዎችን ሳይበላሹና ሳይጠፉ ሊይዝ የሚችል ቋሚ ማስታወሻ (Fiscal memory) የተገጠመለት ነው፡፡ መሳሪያው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ታሽጎ የሚዘጋጅና በሽቦ አልባ መሳሪያ (GPRS Terminal) አማካኝነት ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መረጃ ቋት ጋር መገናኘት የሚችል የቴክኖሎጂ ውጤት ነው፡፡
2. የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ መጠቀም ያለባቸው እነማን ናቸው?
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999 ማንኛውም የደረጃ "ሀ"" እና የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮች የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ የመጠቀም ግዴታ እንዳለባቸው ደንግጓል፡፡ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች በህግ ባይገደዱም በፍቃደኝነት መሳሪያው መጠቀም ይችላሉ፡፡
3. የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ጥቅሞች
የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ለግብር ከፋዩና ለታክስ ሰብሳቢው መ/ቤት በርካታ ጥቅሞች አሉት፡፡ ከጥቅሞቹ መካከል፡-
ዘመናዊ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ አንዲኖር ያደርጋል፤
ሽያጮችን ለመቆጣጠር ያስችላል፤
የዕቃ ክምችትን/ስቶክ/ለመቆጣጠር ያስችላል፤
በጥቂት የሰው ሀይል ስራ ለመስራት ያስችላል፤
ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓትን ለማስፈን ይረዳል፤
ከታክስ ሰብሳቢ መ/ቤት ጋር የሚፈጠሩ አላስፈላጊ ክርክሮችን ያስቀራል፤
መረጃ ላይ የተመሰረተ የግብር አሰባሰብ ስርዓት በማስፈን በግብር ከፋዮችና በግብር ሰብሳቢው መካከል መተማመን ይፈጥራል፡፡
4. ደረሰኝ ወይም የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ተጠቃሚ ግብር ከፋዮች ኃላፊነቶች ምንድ ናቸው?
አንድ ደረሰኝ ወይም የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ የመጠቀም ግዴታ ያለበት ግብር ከፋይ የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉበት፡-
ለእያንዳንዱ ሽያጭ ደረሰኝ መስጠት፤
እውቅና ያልተሰጠው ወይም በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ መሳሪያ ወይም የሽያጭ ነቁጣ ሶፍትዌር አለመጠቀም፤
መሳሪያው በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት መስጠት ያቆመ እንደሆነ ለቅ/ጽ/ቤቱ በማሳወቅ በባለስልጣኑ ፍቃድ የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ መጠቀም፤
በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ ለቅ/ጽ/ቤቱ በማሳወቅ በአገልግሎት ማእከል እንዲጠገን መውሰድ፤
የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያውን ከመረጃ ማስተላለፊያ ጋር በማያያዝ መጠቀም፤
የምርመራ መዝገብ ከማሽን ጎን ማስቀመጥ፤
የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ለቁጥጥር በሚመጡበት ወቅት መረጃ መስጠት፤
የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ የሚቀመጥበትን የንግድ ቦታ ትክክለኛ አድራሻ ለባለስልጣኑ ማሳወቅ፤
የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ያለአድራሻ አለማስቀመጥ፤
የአድራሻ ወይም የስም ለውጥ ሲደረግ ወይም የንግድ ሥራውን የሚያቋርጥ ሲሆን ከሦስት ቀናት አስቀድሞ ለባለስልጣኑ ማሳወቅ፤
በንግድ ድርጅቱ መሟላት ያለባቸውን 3ቱን ማስታወቂያዎች ግልጽ በሆነና በሚታይ ቦታ ላይ መለጠፍ፤
የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ ደረሰኝ እንዳይቆረጥበት ወዲያውኑ ለፖሊስ ጣቢያ እና ግብር ለሚከፍሉበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማሳወቅ፤
እንደስራ ዘርፋችሁ ባህሪ ዜድ ሪፖርት ማውጣትና መረጃዎችን ሳይበላሹና ሳይጠፉ በአግባቡ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
4.1. የማሳወቂያ መንገዶች፡-
ማሽኑ በሚበላሽበት ጊዜ ግብር ከፋዩ ከሚከተሉት ሦስት መንገዶችን አንዱን ተጠቅሞ ማሳወቅ አለበት፡-

የቅ/ጽ/ቤቱን ስልክ በመጠቅም/በመደወል/፤ ወይም
በአካል ቅ/ጽ/ቤቱ ጋር በመሄድ ማሳወቅ አለበት፡፡
ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ታትመው የሚወጡ ሰነዶች በሙሉ ቅጂ ወይም ጆርናል

ደረሰኞች መያዝ የሚገባቸው መረጃዎችደረሰኝ በእቃ ወይም በአገልግሎት ግብይት ላይ ተመስርቶ ከሻጩ አቅራቢው/ለገዥው የሚሰጥ እና ግብይት ስለመፈጸሙ፣ ገንዘብ ስለመሰብሰቡ፣ ዋጋው ስለመከፈሉ ወይ...
06/06/2026

ደረሰኞች መያዝ የሚገባቸው መረጃዎች

ደረሰኝ በእቃ ወይም በአገልግሎት ግብይት ላይ ተመስርቶ ከሻጩ አቅራቢው/ለገዥው የሚሰጥ እና ግብይት ስለመፈጸሙ፣ ገንዘብ ስለመሰብሰቡ፣ ዋጋው ስለመከፈሉ ወይም ለወደፊቱ ለመክፈል ውል መግባቱን የሚያሳይ ሰነድ ነው፡፡

በህጉ መሰረት የሽያጭ ደረሰኝ ቢያንስ የሚከተሉትን መሰረታዊ መረጃዎች ሊይዝ ይገባል፡-

1. የአቅራቢው ሙሉ ስም፣ አድራሻ እና የተመዘገበ የንግድ ስም የታተመበት፤

2. የአቅራቢው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቁጥር እና ለታክስ የተመዘገበበት ቀን የታተመበት፤

3. የደረሰኙ ተከታታይ ቁጥር የታተመበት፤

4. የገዥው ሙሉ ስም፣ አድራሻ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤

5. የተገዛው፣ የተሸጠው ዕቃ ወይም የተሰጠው አገልግሎት አይነት እና መጠን፤

6. ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ላይ የሚፈለገውን የተጨማሪ እሴት ታክስ/የተርን ኦቨር ታክስ መጠን፤

7. በፊደል እና በቁጥር የተጻፈ ጠቅላላ የሽያጭ ወይም ግብይት ዋጋ፤

8. ደረሰኙ የተሰጠበት ቀን፤

9. ደረሰኙን ያዘጋጀው ወይም ገንዘቡን የተቀበለው ሰራተኛ ስም እና ፊርማ፤

10. የደረሰኝ አታሚው ድርጅት ስም፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የታተመበት ቀን እና የአታሚው የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ቁጥር፤

11. ደረሰኙ እንዲታተም በገቢዎች ሚኒስቴር የተፈቀደበትን ደብዳቤ ቁጥር እና ቀን ናቸው፡፡

06/06/2026

የህጋዊ ደረሰኝጠቀሜታ
• በደረሰኝ አያያዝና አሰጣጥ ላይ የሚደረገው ቁጥጥር በአገራችን ካለው የአመራረት፣ የክፍፍል የስርጭትና ግብይት ሁኔታ ጋር ለማጣጣም፣
• በመሠረቱ ደረሰኝ ሊሰጥ የሚገባው በአቅራቢ ቢሆንም በጊዜው በተለየ ሁኔታ ከገዢው በኩል የወጪ ሰነድን በማረጋገጥ ቁጥጥሩ ሊፈፀም እንደሚችል ለማሳወቅ፣
• የንግዱ ሕብረተሰብ በቁጥጥር ስርዓት እንዲገዛ ማድረግ፣
• ተጠያቂነትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮች እንዲታወቁ ለማድረግ፣
• ተግባራዊ የሚሆነውን ቁጥጥር ሥርዓት ለመምራትና ለማስፈፀም፣
• የደረሰኝን ሕትመት ስርዓት ሳያሟሉ የትም ታትመው ገበያ ላይ የሚውሉ ደረሰኞች ህትመትና አገልግሎት ለማቋረጥ፣
• በማንኛውም ግብይት የሚሰጠው ደረሰኝ ህትመትና ስርጭቱ በታወቀና ቁጥጥር በሚደረግበት ሁኔታ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለማድረግ፣
• በባህላዊ የማምረት ተግባር የሚተዳደሩ አቅራቢዎች የሚፈጽሙት ግብይት የሚሸፍን ስርዓት ታሳቢ ለማድረግ፣
• ደረሰኝ ህጋዊ አሰራርን የሚያመለክት እጅ በእጅ ወይም በዱቤ እቃ ወይም አገልግሎት ስለመሸጡ ለማረጋገጥ የሚረዳ ሰነድ መሆኑ፣
• ግብር ከፋዮች ለሚሰጡት የሽያጭ አገልግሎቶች ለተጠቃሚው ደረሰኝ መስጠታቸው ለሚከፍሉት ግብር ትክክለኛነት በመረጃ ምንጭነት ያገለግላል፣
• በግብር ሰብሳቢው አካልና በግብር ከፋዩ ዘንድ አለመግባባቶችን ይከላከላል፣
• ግብር ከፋዩ በግብር መክፈያ ወቅት አለአግባብ ግብር እንዳይጠይቅና ከአግባቡም በታች እንዳይከፍል ለማድረግ ይጠቅማል፣
• በሀገራችን የዕቃና የአገልግሎት ግብይት በአብዛኛው በጥሬ ገንዘብ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር ሥርዓትን መዘርጋት ከፍተኛ ጥቅም አለው፡፡

Address

Kombolcha

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቦርከና ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share