የስልጢ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት-Selti Woreda Office of Agriculture

  • Home
  • Ethiopia
  • Kibet
  • የስልጢ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት-Selti Woreda Office of Agriculture

የስልጢ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት-Selti Woreda Office of Agriculture Official Page of Silti Woreda Office of Agriculture. "The new generation culture is Agriculture"

በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገራችን አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ ዝናብ ያገኛሉበሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገራችን አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባ...
03/06/2026

በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገራችን አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ ዝናብ ያገኛሉ

በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገራችን አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ እንዳስታወቀው እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ በመምጣት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ ምሥራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የዝናብ ስርጭት ይኖራቸዋል።

በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገራችን ክፍሎች ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር አኃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ።

በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜን እና በደቡብ ምዕራብ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በመደበኛ ሁኔታ ወቅታዊው የክረምት ዝናብ ቀደም ብሎ በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ አጋማሽ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ በሂደት እየተጠናከረ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ ሌሎች አካባቢዎችም እንደሚስፋፋ ተጠቁሟል።

በዚህም መሠረት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በምሥራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ዝናቡ በመጠንም ሆነ በስርጭት የተሻለ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ይህ የሚኖረው እርጥበት ለግብርና ሥራ የማሳ ዝግጅት ለማድረግ፣ የመኸር ሰብሎችን ለመዝራት እንዲሁም ለበልግ ሰብል ተጠቃሚ አካባቢዎች መልካም አጋጣሚን እንደሚፈጥር ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል።

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገራችን ተፋሰሶች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጸ ምድር የውኃ ፍሰት እንደሚኖርም ታውቋል።

በዚህም መሠረት በመካከለኛው እና ታችኛው አባይ፣ በላዩኛው እና መካከለኛው ባሮ አኮቦ፣ በላዩኛው ስምጥ ሸለቆ፣ በኦሞ ጊቤ፣ በአዋሽ እንዲሁም በገናሌ ዳዋ ተፋሰሶች ከመካከለኛ እስከ ከባድ የገጸ ምድር የውኃ ፍሰት እንደሚጠበቅ ተጠቅሷል።

በተመሳሳይ በላይኛው አባይ፣ በኦጋዴን፣ በመካከለኛው አዋሽ፣ በስምጥ ሸለቆ እና በኦሞ ጊቤ ተፋሰሶች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የገጸ ምድር የውኃ ፍሰት እንደሚኖራቸውም ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ ገልጿል።

ወቅታዊ የግብርና ተግባራትን በሙሉ አቅም ለማሳካት የማናጅመንት ግምገማ ተካሄደ!​ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (የስልጢ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት)​የስልጢ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት በወቅታዊ የግብ...
03/06/2026

ወቅታዊ የግብርና ተግባራትን በሙሉ አቅም ለማሳካት የማናጅመንት ግምገማ ተካሄደ!

​ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (የስልጢ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት)

​የስልጢ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት በወቅታዊ የግብርና ሥራዎች፣ በሀገራዊ ምርጫ ስራ ምክንያት ባልተሰሩ በተቋማዊ አፈጻጸሞች ዙሪያ ሰፊ የማናጅመንት ግምገማና የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጫ መድረክ አካሂዷል።
መድረኩ በዋናነት እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት ላይ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት፣ በቀጣይ መካካስ ያለባቸውን ሥራዎች በእውቀትና በትኩረት ለመምራት ያለመ ነው።

​በግምገማ መድረኩ ላይ በዝርዝር የተገመገሙና በቀጣይ በልዩ ትኩረት እንዲፈጸሙ አቅጣጫ የተሰጠባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡

​1. ባለሙያውንና አመራሩን ወደ መደበኛ ሥራ መመለስ

​የተቋሙን አመራርና ባለሙያ ካሉበት መዘናጋት በማውጣት፣ ሙሉ ትኩረታቸውንና አቅማቸውን ወደ መደበኛ የልማት ሥራዎች እንዲመልሱና ለሕዝብ አገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል።

​2. የወቅታዊ ሰብልና የልማት ፕሮጀክቶች ስምሪት

​የበልግ ቀሪ ተግባራት፡ የቀሩትን የበልግ የግብርና ሥራዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ሙሉ በሙሉ ማሳካት።
​የልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች ተከላ፡ የፍራፍሬ፣ የቡና፣ የቅመማ ቅመም እና የጃክ ፍሩት (Jackfruit) ፕሮጀክቶችን በሙሉ አቅም መተግበር።
​የቀበሌዎች ትኩረት፡ በተለይም በአሳኖ፣ አጎዴ፣ ጡጦ፣ ባቲ፣ አጅራ እና ሌሎችም ቀበሌዎች የፍራፍሬ፣ የቡናና የጃክ ፍሩት ተከላ ሥራዎችን በስፋትና በላቀ ደረጃ ማካሄድ።

​3. የተቋም አፈጻጸም፣ የአረንጓዴ አሻራና የአደጋ ስጋት ዝግጁነት
​ተቋማዊ ሥራዎች፡ እስካሁን የተሰሩ የተቋም ሥራዎችን ይበልጥ ማጠናከርና የታዩ ጉድለቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማረምና መተካት።

​የቅድመ ማስጠንቀቂያና አደጋ ስጋት፡ የክረምቱን መግባት ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያና የአደጋ ስጋት ሥራዎችን ከወዲሁ ማጠናቀቅ።

​የመሬት አስተዳደርና አረንጓዴ አሻራ፡ የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ሥራዎችን እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ዝግጅትን ከወዲሁ በትኩረት መምራት።

​4. ኮሪደር ልማትና የሌማት ትሩፋት

​የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ማፋጠን፣ በሰቆጣ መርሃ-ግብር ሥር ያሉ የእንስሳት ማድለብና ማሞከት እንዲሁም የመኖ ልማትና ተከላ ሥራዎችን በቁርጠኝነት መፈጸም።

​በማጠቃለያውም፣ ማናጅመንቱ በግምገማው መሠረት ለቀጣይ ሥራዎች ግልጽ ስምሪትና አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን፣ ሙሉ የወረዳው የግብርና መዋቅር ለተግባራዊነቱ ሌሊትና ቀን እንደሚሠራ ተገልጿል።

መድረኩን የስልጢ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ አብደላ መሀመድ የመሩት ሲሆን ሌሎች የግብርና አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

​ #የስልጢወረዳግብርና
#የሌማትትሩፋት
#አረንጓዴአሻራ
#ኮሪደርልማት

የቀበሌ የግብርና ባለሙያዎችን አቅም መገንባት ለምርታማነት ዕድገት!​በሀገር አቀፍ ደረጃ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ካሉ ቁልፍ ተግባራ...
03/06/2026

የቀበሌ የግብርና ባለሙያዎችን አቅም መገንባት ለምርታማነት ዕድገት!

​በሀገር አቀፍ ደረጃ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ካሉ ቁልፍ ተግባራት መካከል የባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ ቀዳሚው ነው።

​በዚሁ መሠረት የግብርና ሚኒስቴር ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በአገር አቀፍ ደረጃ ለ2 ሺህ 726 የቀበሌ የግብርና ባለሙያዎች በተለያዩ 8 የግብርና ኮሌጆች የደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

​የዚህ ታላቅ አገራዊ ንቅናቄ አካል በሆነውና በኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ እየተሰጠ በሚገኘው ስልጠና ላይ ከአማራ፣ ከአፋርና ከድሬዳዋ የተውጣጡ 1 ሺህ 151 ባለሙያዎች ከመጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የታገዘ ስልጠና እየወሰዱ ነው።

አሁናዊ የቅድመ በልግ የቦሎቄ ምርት አሰባሰብ በከፊልስልጢ ወረዳ የስልጢ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ግንቦት 26/2018 ዓ/ም
03/06/2026

አሁናዊ የቅድመ በልግ የቦሎቄ ምርት አሰባሰብ በከፊል
ስልጢ ወረዳ

የስልጢ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ግንቦት 26/2018 ዓ/ም

ከግንቦት 24 እሰከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም የሚኖረው የአየር ሁኔታ አዝማሚያ//////////////////በግንቦት የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽ...
31/05/2026

ከግንቦት 24 እሰከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም የሚኖረው የአየር ሁኔታ አዝማሚያ
//////////////////
በግንቦት የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በሚቀጥሉት ቀናቶች ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ ከባድ (ከ1-30 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛወ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በግንቦት የመጨረሻው አስር ቀናት ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ሀይል ጋር በተያያዘ በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜንና በደቡም ምዕራብ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ሊይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ ትንበያዎች ያመላክታሉ፡፡

ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም ለአቮካዶ ምርታማነት ዕድገት!*************************** ግንቦት 21/2018  ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም ሃገራችን ከአቮካዶ ምርት የም...
29/05/2026

ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም ለአቮካዶ ምርታማነት ዕድገት!
***************************
ግንቦት 21/2018

ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም ሃገራችን ከአቮካዶ ምርት የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

ይህ ፕሮግራም ከሌሎች ሀገራዊ እና ዓለማቀፋዊ የልማት ግቦች ጋር እንዲጣጣም ተደርጎ የተቀረፀ ሲሆን በዚህም የሀገራችንን ኢኮኖሚ ለማሳደግ፣ የህብረተሰባችንን ኑሮ ለማሻሻል እና የምግብና ስርዓተ-ምግብ ዋስትናን ለማሳደግ እንዲሁም ለአግሮ-ኢንዱስትሪ በቂ ጥሬ ዕቃ ለማቅረብ ትልቅ አቅም እንዲኖረው ተደርጎ የተቀረፀ ነው።

በዚህም ፕሮግራሙ እየተተገበረ በሚገኝባቸው ክልሎች ያለውን አፈፃፀም በመገምገም ውሳኔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ከክልል ከፍተኛ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት ተደርጓል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእርሻ እና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ደሳለኝ ተሻለ እንደተናገሩት፤ ይህ ፕሮግራም ሀገራችን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞችን ከጀመረችባቸው ዘርፎች አንደኛው ተደርጎ የሚወሰድና በግንባር ቀደምትነት ትኩረት ተሰጥቶት በመንግስት ከፍተኛ በጀት የሚሰራ ስራ ነው።

ብሔራዊ አቮካዶ ልማት ፕሮግራም ከአረንጓዴ አሻራ፣ ከሌማት ትሩፋት እንዲሁም ሌሎች ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች ጋር በማቆራኘት ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ተደርጎ መቀረፁን አንስተው፣ ሀገራችንም ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን የውጭ ምንዛሬ፣ የስራ እድል ፈጠራና መሰል ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀና ለ15 ዓመት የሚቆይ ፕሮግራም መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል።

የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ፕሮፌሰር አሊ መሃመድ የአቮካዶ እሴት ሰንሰለት አለም አቀፋዊ እና ሀገራዊ እይታ፣ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታና ዕድሎች እንዲሁም የሆርቲካልቸር ዘርፍ ለውጥ ላይ ትኩረት ያደረገ ጽሁፍ አቅርበዋል።

በምግብና ስርዓተ-ምግብ ራሳችንን ለመቻል፣ ለኢንዱስትሪዎች የጥሬ እቃ አቅርቦት እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ አቮካዶ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት አማካሪው ባቀረቡት ጽሁፍ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም አጠቃላይ እይታ፣ በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶች፣ ተግዳሮቶች እና የወደፊት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች እንዲሁም ገበያ ተኮር የሆነ ክላስተር ላይ የተመሰረተ አቮካዶ ምርትን በተመለከተ ጽሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

#ግብርናሚኒስቴር #ከማምረትበላይ #ኢትዮጵያ

የስጋ ዶሮ መኖ አዘገጃጀት Formulationየስጋ ዶሮ (Saso) የተመጣጠነ መኖ አዘገጃጀትዋና ዋና የሃይል (Energy)፣ የፕሮቲን (Protein) እና የማዕድን (Mineral) ምንጮችን ...
29/05/2026

የስጋ ዶሮ መኖ አዘገጃጀት Formulation

የስጋ ዶሮ (Saso) የተመጣጠነ መኖ አዘገጃጀት

ዋና ዋና የሃይል (Energy)፣ የፕሮቲን (Protein) እና የማዕድን (Mineral) ምንጮችን በአግባቡ ማቀናጀት ይጠይቃል።

የስጋ ዶሮ (Sasso meat) ማሳደግ ከፈለጉ መጪውን 30% ለመቀነስ እና ዶሮዎቹ በቂ ፕሮቲንና ጉልበት እንዲያገኙ በአካባቢዎ በሚገኙ ጥሬ እቃዎች መኖ ማዘጋጀት ይችላሉ።

ለስጋ ዶሮ በብዛት የሚውሉ ሁለት አይነት የመኖ ደረጃዎች አሉ።

1. የዕድገት መኖ (Starter Diet - ለዐ እስከ 8 ሳምንት ጫጩቶች)

የዶሮዋን ፈጣን እድገት ለማፋጠን ከፍተኛ የፕሮቲን መጠን (18-20%) ያስፈልጋቸዋል።

ለ 100 ኪሎ ግራም (1 ኩንታል) የሚሆን የመኖ መጠን

የተፈጨ በቆሎ (Maize): 50 ኪ.ግ
የአኩሪ አተር ዱቄት ፡ 17.5 ኪ.ግ
የአሳ ዱቄት (Fish Meal): 12 ኪ.ግ
የበቆሎ ብሬን (Maize Bran): 10 ኪ.ግ
የሱፍ ፍሬ ዱቄት : 4.5 ኪ ግ
የኖራ ድንጋይ (Limestone): 4 .ኪግ
የአጥንት ዱቄት (Bone Meal): 1.5 ኪ.ግ
ጨው (Salt): 300 ግራም
ቫይታሚን ፕሪሚክስ (Premix): 200 ግራም
ቶክሲን ባይንደር (Toxin Binder): 100 ግራም

2. የማጠናቀቂያ መኖ (Finisher Diet - ለ9ኛ ሳምንት እና ከዚያ በላይ)

ለስጋ መድረሻ የሚሆን የጡንቻ እድገት ለማረጋገጥ መካከለኛ ፕሮቲን (16-18%) ያለው መኖ ይሰጣል፡፡

ለ 100 ኪሎ ግራም (1 ኩንታል) የሚሆን የመኖ መጠን

የተፈጨ በቆሎ (Maize): 60 ኪ.ግ

የአኩሪ አተር ዱቄት ፡- 14 ኪግ

የአሳ ዱቄት (Fish Meal): 10 ኪ.ግ

የበቆሎ ብሬን (Maize Bran): 7 ኪ.ግ

የሱፍ ፍሬ ዱቄት 5 ኪ.ግ

የኖራ ድንጋይ (Limestone): 2.5 ኪግ

የአጥንት ዱቄት (Bone Meal): 1.2 ኪ.ግ

ጨው (Salt): 200 ግራም

ቫይታሚን ፕሪሚክስ (Premix): 100 ግራም

ቶክሲን ባይንደር (Toxin Binder): 50१८

አዘገጃጀት እና ጥንቃቄ

እህልቹ በደንብ መታሸት እና መፍጨት አለባቸው (ከ3.2 ሚ.ሜ ያልበለጠ መጠን)።

ዶሮዎች ጤናማ ሆነው ስጋ እንዲሰጡ በንፅህና አዘውትረው የተመጣጠነ ምግብ ማቀላቀል ይመረጣል።

እነስተኛ ወይም ትልቅ መጠን ያላቸውን የስጋ ዶሮዎች መኖ በምንቀይርበት ጊዜ የሚፈለገውን የካሎሪ እና የፕሮቲን መጠን በትክክል ለማወቅና ለማስተካከል የተዘጋጁ መመሪያዎችን መጠቀም ይመረጣል፡፡

ከተጠቀሰው ባሻገር የስጋ ዶሮዎች 2 ወር እድሜ እና ከዛ በላይ ከሞላቸው ንፅህናውን የጠበቀ የወጥቤት ትርፍራፊን በተወሰነ መልኩ ተጨማሪ በመስጠት የመኖ አማራጭን መጠቀም ይቻላል።

እንደዚህ አይነት መመሪያዎችን ለማግኘትና ለመረዳት በስራው ላይ የቆዮ ባለሙያዎችንም በተጨማሪ ያማክሩ፡፡የስጋ ዶሮ መኖ አዘገጃጀት Formulation

የስጋ ዶሮ (Saso) የተመጣጠነ መኖ አዘገጃጀት

ዋና ዋና የሃይል (Energy)፣ የፕሮቲን (Protein) እና የማዕድን (Mineral) ምንጮችን በአግባቡ ማቀናጀት ይጠይቃል።

የስጋ ዶሮ (Sasso meat) ማሳደግ ከፈለጉ መጪውን 30% ለመቀነስ እና ዶሮዎቹ በቂ ፕሮቲንና ጉልበት እንዲያገኙ በአካባቢዎ በሚገኙ ጥሬ እቃዎች መኖ ማዘጋጀት ይችላሉ።

ለስጋ ዶሮ በብዛት የሚውሉ ሁለት አይነት የመኖ ደረጃዎች አሉ።

1. የዕድገት መኖ (Starter Diet - ለዐ እስከ 8 ሳምንት ጫጩቶች)

የዶሮዋን ፈጣን እድገት ለማፋጠን ከፍተኛ የፕሮቲን መጠን (18-20%) ያስፈልጋቸዋል።

ለ 100 ኪሎ ግራም (1 ኩንታል) የሚሆን የመኖ መጠን

የተፈጨ በቆሎ (Maize): 50 ኪ.ግ
የአኩሪ አተር ዱቄት ፡ 17.5 ኪ.ግ
የአሳ ዱቄት (Fish Meal): 12 ኪ.ግ
የበቆሎ ብሬን (Maize Bran): 10 ኪ.ግ
የሱፍ ፍሬ ዱቄት : 4.5 ኪ ግ
የኖራ ድንጋይ (Limestone): 4 .ኪግ
የአጥንት ዱቄት (Bone Meal): 1.5 ኪ.ግ
ጨው (Salt): 300 ግራም
ቫይታሚን ፕሪሚክስ (Premix): 200 ግራም
ቶክሲን ባይንደር (Toxin Binder): 100 ግራም

2. የማጠናቀቂያ መኖ (Finisher Diet - ለ9ኛ ሳምንት እና ከዚያ በላይ)

ለስጋ መድረሻ የሚሆን የጡንቻ እድገት ለማረጋገጥ መካከለኛ ፕሮቲን (16-18%) ያለው መኖ ይሰጣል፡፡

ለ 100 ኪሎ ግራም (1 ኩንታል) የሚሆን የመኖ መጠን

የተፈጨ በቆሎ (Maize): 60 ኪ.ግ

የአኩሪ አተር ዱቄት ፡- 14 ኪግ

የአሳ ዱቄት (Fish Meal): 10 ኪ.ግ

የበቆሎ ብሬን (Maize Bran): 7 ኪ.ግ

የሱፍ ፍሬ ዱቄት 5 ኪ.ግ

የኖራ ድንጋይ (Limestone): 2.5 ኪግ

የአጥንት ዱቄት (Bone Meal): 1.2 ኪ.ግ

ጨው (Salt): 200 ግራም

ቫይታሚን ፕሪሚክስ (Premix): 100 ግራም

ቶክሲን ባይንደር (Toxin Binder): 50१८

አዘገጃጀት እና ጥንቃቄ

እህልቹ በደንብ መታሸት እና መፍጨት አለባቸው (ከ3.2 ሚ.ሜ ያልበለጠ መጠን)።

ዶሮዎች ጤናማ ሆነው ስጋ እንዲሰጡ በንፅህና አዘውትረው የተመጣጠነ ምግብ ማቀላቀል ይመረጣል።

እነስተኛ ወይም ትልቅ መጠን ያላቸውን የስጋ ዶሮዎች መኖ በምንቀይርበት ጊዜ የሚፈለገውን የካሎሪ እና የፕሮቲን መጠን በትክክል ለማወቅና ለማስተካከል የተዘጋጁ መመሪያዎችን መጠቀም ይመረጣል፡፡

ከተጠቀሰው ባሻገር የስጋ ዶሮዎች 2 ወር እድሜ እና ከዛ በላይ ከሞላቸው ንፅህናውን የጠበቀ የወጥቤት ትርፍራፊን በተወሰነ መልኩ ተጨማሪ በመስጠት የመኖ አማራጭን መጠቀም ይቻላል።

እንደዚህ አይነት መመሪያዎችን ለማግኘትና ለመረዳት በስራው ላይ የቆዮ ባለሙያዎችንም በተጨማሪ ያማክሩ፡፡

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን #ከማምረትበላይ ---------------በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለ...
26/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን

#ከማምረትበላይ

---------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

▶️tiktok
https://www.tiktok.com/

▶️instagram https://www.instagram.com/siltiworedaofficeagriculture

▶️facebook https://www.facebook.com/SiltiWoredaOfficeofAgriculture

▶️X https://x.com/AgriOfficeSilti

▶️ቴሌግራም https://t.me/SiltiWoA

▶️threads https://www.threads.com/

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉአዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2018(ኢዜአ)፦ በሚቀጥሉት አስር ...
22/05/2026

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2018(ኢዜአ)፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ አካባቢዎች ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ብርካታ ቦታዎችን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ ስፍራዎች ላይ ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች አንጻራዊ ጥንካሬ ይኖራቸዋል።

ከእርጥበት አዘል የአየር ሁኔታው ጋር ተያይዞም የተሻለ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖር ገልጿል።

በዚህም በደቡብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ በምስራቅ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖር አመልክቷል።

በሚቀጥሉት ቀናት ከሚኖሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት፤ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ብዙ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብሏል።

አልፎ አልፎ በውኃ አካላትና በአካባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት፤ በጥቂት የደቡብ፣ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች መጠቆማቸውን ገልጿል።

ይህም ለግብርና ሥራ በቂ እርጥበት እንዲኖር በማድረግ ለሰብሎች፣ ለግጦሽ ሳርና ለመጠጥ ውኃ አቅርቦት አዎንታዊ ተፅዕኖ እንዳለው አስታውቋል።

በተጨማሪም ለመኸር ሰብሎች የማሳ ዝግጅትና ዘር፣ ፍሬ በማፍራትና በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎችና ለአረንጓዴ ዕፅዋት ልምላሜ የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁሟል።

በተፋሰሶች ላይ ያለውን የእርጥበት ሁኔታ በተመለከተም ባሮ አኮቦ፣ መካከለኛና ታችኛው አባይ፣ በአብዛኛው ኦሞ ጊቤ፣ በላይኛውና መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ የገጸ ምድር ውኃ ፍሰት ይኖራቸዋል ብሏል።

በላይኛው ገናሌ ዳዋ፣ ኦጋዴን፣ ታችኛው ተከዜ እንዲሁም በላይኛውና መካከለኛው ዋቤ ሸበሌ ደግሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የገጸ ምድር ውኃ ፍሰት እንደሚያገኙ ይጠበቃል ብሏል።

በተጨማሪም ደረቅ የገጸ ምድር ውኃ ፍሰት የሚኖራቸው በአብዛኛው አፋር ደናኪል፣ አይሻ፣ መካከለኛና ታችኛው አዋሽ እንዲሁም በታችኛው ገናሌ ዳዋ መሆኑን የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ ሲል ገልጿል።

በሌላ በኩል በበልግ ወቅት የሚኖረው የሙቀት መጠን መጨመርና በሌሊት ደግሞ የሚታየው ወበቅ አንዱ የዚህ ወቅት ክስተት መሆኑን ጠቁሟል።

ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ኃይል ጋር ተያይዞም በተለይም በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በቤንሻንጉል-ጉሙዝና በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት ከ32 እስከ 41 ዲግሪ ሴልሺየስ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል።

በምስሉ ላይ የሚታየው ክስተት በበቆሎ ተክል ላይ የሚከሰት "Crazy Top" (የበቆሎ እብድ ራስ በሽታ) ወይም በከፊል "Tassel Ear" (የወንድ አብቦ ወደ እሸትነት መቀየር) በመባል የ...
21/05/2026

በምስሉ ላይ የሚታየው ክስተት በበቆሎ ተክል ላይ የሚከሰት "Crazy Top" (የበቆሎ እብድ ራስ በሽታ) ወይም በከፊል "Tassel Ear" (የወንድ አብቦ ወደ እሸትነት መቀየር) በመባል የሚታወቅ የዕድገት መዛባት/በሽታ ነው።

​ የበቆሎ ተክል የወንድ አበባ (Tassel) ማውጣት በሚገባው የላይኛው ክፍል ላይ፣ ያልተለመደ የሴት እሸት (Ear) ወይም ከፊል እሸትና ከፊል አበባ የሆነ ቅርጽ ይዟል።

​ይህ ለምን እንደሚከሰት፣ መንስኤዎቹን እና የመከላከያ መንገዶችን ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

​1. ዋና ዋና መንስኤዎች
​የፈንገስ በሽታ (Crazy Top Downy Mildew): ይህ በሽታ Sclerophthora macrospora በሚባል የፈንገስ ዝርያ የሚመጣ ሲሆን፣ አፈሩ በውሃ በሚጥለቀለቅበት ጊዜ (በተለይ በቆሎው በበቀለ በመጀመሪያዎቹ ከ4 እስከ 5 ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ) ፈንገሱ ወደ ተክሉ ውስጥ ይገባል። ይህም የተክሉን የሆርሞን ስርዓት በማዛባት የወንድ አበባው ወደ እሸትነት እንዲቀየር ያደርጋል።
​የሆርሞን መዛባት (የአካባቢ ተጽዕኖ): ተክሉ ገና በወጣትነት ዕድገት ደረጃ ላይ እያለ ከፍተኛ የውሃ መብዛት (የመሬት መታፈን)፣ ድንገተኛ የቅዝቃዜ ወይም የሙቀት መለዋወጥ እና የሜካኒካል ጉዳት ከደረሰበት የሆርሞን መዛባት ይፈጠራል። ይህም የወንድ እና የሴት መራቢያ ክፍሎችን መለያየት ያዛባዋል።

​2. የመከላከያ እና የቁጥጥር ዘዴዎች
​ይህ በሽታ አንዴ ከተከሰተ በኋላ ወደ ኋላ መመለስ ወይም ማከም ስለማይቻል፣ ዋናው ትኩረት መሆን ያለበት አስቀድሞ መከላከል ላይ ነው።

​ሀ. የውሃ ፍሳሽ ማስተካከል (Drainage Management)
​በማሳ ውስጥ ውሃ እንዳይተኛ እና መሬቱ እንዳይታፈን ለማድረግ ጥሩ የውሃ ማፍሰሻ ቦዮችን ማዘጋጀት። ይህ በሽታው እንዳይከሰት የሚያደርግ ትልቁ መፍትሔ ነው።

​ለ. የሰብል መለዋወጥ (Crop Rotation)
​ፈንገሱ በአፈር ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል፣ በበሽታው በተጠቃ ማሳ ላይ በሚቀጥለው የምርት ዘመን በቆሎ ከመዝራት ይልቅ በፈንገሱ የማይጠቁ እንደ ጥራጥሬ (ባቄላ፣ አተር) ወይም ሌሎች ሰብሎችን ማፈራረቅ።

​ሐ. ተከላካይ የሆኑ ዝርያዎችን መጠቀም
​በአካባቢው ለሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች በማማከር ለ"Downy Mildew" ወይም ለፈንገስ በሽታዎች የተሻለ የመቋቋም አቅም ያላቸውን የተሻሻሉ የበቆሎ ዝርያዎችን መርጦ መዝራት።

​መ. ማሳን በፅዳት መያዝ
​በሽታው የታየባቸውን ተክሎች ነቅሎ ማቃጠል ወይም ማሳው ውስጥ እንዳይቀበሩ ማድረግ ፈንገሱ በቀጣይ ዓመት ወደ ሌላ ተክል እንዳይደገም ይረዳል።

​ሠ. የዘር አያያዝ (Seed Treatment)
​ዘር ከመዘራቱ በፊት በፈንገስ ማጥፊያ (Fungicide) መታከሙን ማረጋገጥ ወይም የታከመ ዘር መጠቀም ከመሬት የሚነሱ የፈንገስ በሽታዎችን ለመቀነስ ይረዳል።

Address

Silti
Kibet

Telephone

+468820030

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የስልጢ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት-Selti Woreda Office of Agriculture posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የስልጢ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት-Selti Woreda Office of Agriculture:

Share