Oromo Zone Civil Service Departement

Oromo Zone Civil Service Departement Tajaajila siivil sarviisii gahumsa qabu, iftoominaa fi madaalawaa ta’e mirkaneessuuf ni hojjanna.

Misooma humna namaa fi tajaajila mootummaa ammayyeessuun kaayyoo keenya.

02/06/2026


02/06/2026

  (Qacarrii Bara zeeroo kan muuxannoo hin barbaanne,eebbifamtoota haaraaf bahe. (የስራ ልምድ የሌላቸው ለአዲስ ሙሩቃን የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ
25/05/2026

(Qacarrii Bara zeeroo kan muuxannoo hin barbaanne,eebbifamtoota haaraaf bahe.
(የስራ ልምድ የሌላቸው ለአዲስ ሙሩቃን የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ

በክልሉ የመንግስት ሰራተኛው ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጠት የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ ይሰራልባህርዳር፤ ግንቦት 13/2018 **************************************...
22/05/2026

በክልሉ የመንግስት ሰራተኛው ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጠት የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ ይሰራል
ባህርዳር፤ ግንቦት 13/2018 ***********************************************************
የመንግስት ሰራተኛው ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጠት የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ የድርሻውን መወጣቱን እንደሚቀጥል የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ባንችአምላክ ገብረማርያም ገለጹ።

‎‎የመንግስት ሰራተኛውን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያወያይ መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

የቢሮ ኃላፊዋ በወቅቱ እንደገለፁት፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉና ለሀገር እድገት ዘላቂ መሰረት የጣሉ የልማት ፕሮጀክቶች መተግበራቸውን ገልፀዋል።

በየደረጃው እየተመዘገበ ላለው ውጤት የመንግስት ሰራተኛው ፈጣንና ፍትሐዊ አገልግሎት በመስጠት የልማት ስራዎች በመደገፍ የድርሻውን መወጣቱን መቀጠል ይገባዋል ነው ያሉት።

ኮሪደርን መሰረት ያደረገው የከተሞች ልማት፣ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የበጋ ስንዴና ሌሎች ኢንሼቲቮች በክልሉ ውጤት ከተመዘገበባቸው መስኮች መካከል ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

‎በትምህርትና በጤናው ዘርፎችም ይታዩ የነበሩ ችግሮችን ለማቃለል በተከናወኑ ተግባራት ጤናማ፣ ብቁና ሀገር ወዳድ ዜጋ ማፍራት እየተቻለ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

የተጀመሩ የልማት ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል የመንግስት ሰራተኛው የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል ሲሉ አስገንዝበዋል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ስንታየሁ ስንሻው እና አቶ ላመስግን አዳነ እንደገለጹት፤ የክልሉን የሀገር ልማትና ዕድገት በማፋጠን የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተለይም ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት ላይ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የገለጹት።

#ኢዜአ

20/05/2026

ለመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደር ሪፎርም መሳካት የመሪዎችን ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው።

​ባሕር ዳር: ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደር ሪፎርም በተመረጡ ስምንት ተቋማት የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራዊ እየተደረገ መኾኑን የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።

​የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኅላፊ ባንቺአምላክ ገብረ ማርያም ለሪፎርሙ ማስፈጸሚያ የሚኾን ፍኖተ ካርታ፣ አዋጆች፣ ስትራቴጂዎች እና ማኑዋሎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል።

በመጀመሪያው ዙር ገንዘብ ቢሮ፣ ገቢዎች፣ ሥራ እና ክህሎት፣ ትምህርት፣ ጤና፤ ግብርና፣ ፕላን እና ልማት ቢሮ እና የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮን ጨምሮ ስምንት ተቋማት ወደ ዝግጅት ምዕራፍ የገቡ ናቸው ነው ያሉት።

ተቋማቱ የራሳቸውን ዕቅድ እና ኮሚቴ አደራጅተው ተግባራትን እያከናወኑ መኾናቸውን ገልጸዋል።

​በሪፎርሙ የዝግጅት ምዕራፍ አተገባበር ላይ የገጠመውን የግንዛቤ ችግር ለመቅረፍ ከፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በሦሥት ዘርፎች የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ተሰጥቷል ብለዋል።

የተሰጣቸውን ሥልጠና ወደ ተግባር በመለወጥ በአንድ ማዕከል ተሰባስበው የየተቋማቸውን ሰነዶች እና የአገልግሎት መረጃዎች ያዘጋጃሉ ነው ያሉት።

በሁለተኛው ዙር ከሐምሌ 2018 ዓ.ም በኋላ ወደ አስር ተቋማት ወደ ሪፎርሙ እንደሚገቡም ጠቁመዋል።

ለሪፎርሙ ስኬት የመሪዎችን ቁርጠኝነት፣ የሠራተኞችን ዕውቀት፣ ጊዜ መስጠት እና ለተግባሩ ባለቤት መኾንን የሚጠይቅ ነውም ብለዋል።

ሠራተኞች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ተቋቁመው ሂደቱን በመልካም ሥነ ምግባር እና በትብብር ሊደግፉት እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

20/05/2026


  (Qacarrii Bara zeeroo kan muuxannoo hin barbaachifne. (የስራ ልምድ የሌላቸው ለአዲስ ሙሩቃን የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ።
19/05/2026

(Qacarrii Bara zeeroo kan muuxannoo hin barbaachifne.
(የስራ ልምድ የሌላቸው ለአዲስ ሙሩቃን የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ።

Address

Oromia Zone
Kemise

Telephone

+251920786504

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Oromo Zone Civil Service Departement posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share