Kombolcha Customs Branch -ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ ቤት

Kombolcha Customs Branch -ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ ቤት በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

  158 #በአንድ ቀን፤ አንድ መልዕክት!
03/06/2026

158
#በአንድ ቀን፤ አንድ መልዕክት!

  157 #በአንድ ቀን፤ አንድ መልዕክት!
30/05/2026

157
#በአንድ ቀን፤ አንድ መልዕክት!

 #የጨረታ ማስታወቂያ
29/05/2026

#የጨረታ ማስታወቂያ

  156 #በአንድ ቀን፤ አንድ መልዕክት!
29/05/2026

156
#በአንድ ቀን፤ አንድ መልዕክት!

  155 #በአንድ ቀን፤ አንድ መልዕክት!
28/05/2026

155
#በአንድ ቀን፤ አንድ መልዕክት!

‎መሠረታዊ የታክስና ጉምሩክ ሕጎች ሥልጠናን ላጠናቀቁ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዕጩ ተመራቂዎች የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡‎                ‎(ግንቦት 17 ቀን 2018፤ ኮም...
25/05/2026

‎መሠረታዊ የታክስና ጉምሩክ ሕጎች ሥልጠናን ላጠናቀቁ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዕጩ ተመራቂዎች የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

‎(ግንቦት 17 ቀን 2018፤ ኮምቦልቻ ጉምሩክ)

‎የገቢዎች ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሲሰጡት የነበረው የመሠረታዊ የታክስ እና የጉምሩክ ሕጎች ተከታታይ ሥልጠና ማጠቃለያ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት በደሴ ከተማ “ጎልደን ጌት ሆቴል” በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

‎በመድረኩ ላይ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ፈቃዱ ቸኮል፣ የሁለቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ተመራቂ ተማሪዎች ተገኝተዋል።

‎በገቢዎች ሚኒስቴር የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተቋማዊ አቅምና ድጋፍ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ አብርሃ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም ከገለጹት አንኳር ነጥብ መካከል መጪው ትውልድ የታክስና ጉምሩክን አስፈላጊነት ተረድቶ የሀገርን ወጪ በሀገር ውስጥ ገቢ ለመሸፈን በሚደረገው ጥረት ላይ የተማሪዎችና የአዲሱ ትውልድ ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ይህንን ተግባር በቅንነትና በታማኝነት ማስቀጠል የሁላችንም ኃላፊነት እንደሆነ አሳስበዋል።

‎የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰማን ዳውድ ባስተላለፉት የአደራ መልዕክት፤ ሥልጠናው የመርሃ ግብር ማሟያ ብቻ አለመሆኑን ገልጸው፣ የተሰጠው የምስክር ወረቀት የታክስ ጉዳይ የሀገር ጉዳይ መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

‎አክለውም፣ “የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የሀገርን ክብርና ጥቅም ከሚያጠፉ አጭበርባሪዎችና ኮንትሮባንዲስቶች ተቋምንና ሕዝብን በመጠበቅ የመፍትሔ አካል መሆን ይገባችኋል” ሲሉ አሳስበዋል።

‎በገቢዎች ሚኒስቴር የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ፋዮች ትምህርት ቡድን አስተባባሪ አቶ መሐመድ ሰይድ፣ ለ13 ሳምንታት ሲሰጥ የነበረውን የ52 ሰዓታት ሥልጠና ሂደት በዝርዝር አብራርተዋል።

‎በሥልጠናው 79 የሕግና ቢዝነስ ተማሪዎች ስኬታማ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጸው፤ ዋናው ዓላማም በሥነ-ምግባር የታነጸ፣ ለሕግ ተገዥ የሆነና ኮንትሮባንድን የሚፀየፍ ትውልድ መፍጠር መሆኑን አስገንዝበዋል።

‎ይህም ተመራቂዎች በሙያቸው ሀገርን በታማኝነት እንዲያገለግሉ የሚያስችል መሠረት ይጥላል።

‎በገቢዎች ሚኒስቴር የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ድርሻየ አሰፋ በበኩላቸው ለተመራቂዎች “የእንኳን ደስ አላችሁ!” መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎አዲሱ ትውልድ በታክስ አሰባሰብ ላይ አዲስ ጉልበት እንደሚሆን በመግለጽ፣ ሥልጠናው በሀገር ውስጥና በውጭ ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት የጎላ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።

‎በተለይም ተማሪዎች የታክስ ስወራንና ማጭበርበርን የሚጸየፉ መሆን እንዳለባቸው እና በስነ ምግባራቸው አርአያ እንድሆኑና ለፈጸሙት ክፍያ ቢያንስ ደረሰኝ የመቀበል ልምድን ዋና ተግባራቸው እንድያደርጉ በጥብቅ አሳስበዋል።

‎የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ዶ/ር ፈቃዱ ቸኮል በበኩላቸው፤ ከተግባር ትምህርቱ ጎን ለጎን የተሰጠው ይህ ስልጠና ተማሪዎች ሕግና መመሪያን አውቀው ወደ ሥራ ዓለም እንዲቀላቀሉ የሚያስችላቸው መሆኑን ገልጸው፣ ለገቢዎችና ጉምሩክ አመራሮችና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።

‎ሥልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው የመመዘኛ ፈተናውን ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎችና ለሥራው መሳካት አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላት የምስክር ወረቀት ከአቶ ሰማን ዳውድ እና ከአቶ ዮሐንስ አብርሃ እጅ ተረክበዋል።

‎ተቋምን በልህቀት፤ ገቢን በስኬት!

  154 #በአንድ ቀን፤ አንድ መልዕክት!
25/05/2026

154
#በአንድ ቀን፤ አንድ መልዕክት!

ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ዕጩ ተመራቂዎች የተዘጋጀው የታክስና የጉምሩክ ህጎች ተከታታይ ስልጠና ማጠቃለያ የመመዘኛ ፈተና ተሰጠ።(ግንቦት 16 ቀን 2018፤ ኮምቦልቻ)በገቢዎች ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ጉ...
24/05/2026

ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ዕጩ ተመራቂዎች የተዘጋጀው የታክስና የጉምሩክ ህጎች ተከታታይ ስልጠና ማጠቃለያ የመመዘኛ ፈተና ተሰጠ።

(ግንቦት 16 ቀን 2018፤ ኮምቦልቻ)

በገቢዎች ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ትብብር ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ዕጩ ተመራቂዎች የተዘጋጀው የታክስና የጉምሩክ ህጎች ተከታታይ ስልጠና ማጠቃለያ የመመዘኛ ፈተና ተሰጥቷል።

ለወሎ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ፣ ኢኮኖሚክስና ሕግ ትምህርት ክፍል ዕጩ ተመራቂዎች ለተከታታይ ሳምንታት ሲሰጥ የቆየው የታክስና የጉምሩክ ሕጎችና አሠራሮች ስልጠና በስኬት መጠናቀቁ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2018 ከጧቱ 3:30 ሰዓት ስልጠናውን ላጠናቀቁ ተማሪዎች የመመዘኛ ፈተና በዩኒቨርሲቲው ግቢ ተሰጥቷል።

ይህ በስነ ምግባር የታነፀና የሕግ ተገዥነትን የሚያከብር ትውልድ ለማፍራት የተዘጋጀው ሥልጠና ፍፃሜን አስመልክቶ፣ ነገ ግንቦት 17 ቀን 2018 በደሴ ከተማ ደማቅ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ይከናወናል።

በመድረኩም የወሎ ዩኒቨርሲቲ የስራ ኃላፊዎች፣ የሁለቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይታደማሉ።

ተቋምን በልህቀት፤ ገቢን በስኬት!

 #መልካም የእረፍት ቀን!
24/05/2026

#መልካም የእረፍት ቀን!

 #የስራ አስኪያጅ መልዕክት
23/05/2026

#የስራ አስኪያጅ መልዕክት

Address

Ethiopia Kombolcha City
Kembolcha
251

Telephone

+251335512352

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kombolcha Customs Branch -ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Kombolcha Customs Branch -ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ ቤት:

Share