ቆቦ ኮሙኒኬሽን kobo communication

ቆቦ ኮሙኒኬሽን kobo communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቆቦ ኮሙኒኬሽን kobo communication, Government Organization, ቆቦ, K'obo.

በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳድ ከንቲባ ጽ/ቤት የ9ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ ስራዎች አቅጣጫ ዙሪያ ከጠቅላላ ሰራተኛው  ጋር ውይይት አካሄደ።በመድረኩ የቆቦ ከተማ  አስተዳደ...
04/06/2026

በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳድ ከንቲባ ጽ/ቤት የ9ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ ስራዎች አቅጣጫ ዙሪያ ከጠቅላላ ሰራተኛው ጋር ውይይት አካሄደ።

በመድረኩ የቆቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉስ አብርሃ እንዳሉት በበጀት አመቱ እንዲፈፀሙ በእቅድ ከተያዙ ስራዎች በዘጠኝ ወራት የተሻለ ውጤቶች የተመዘገበ ቢሆንም መድረስ በሚገባን የስራ አፈፃፀም ያልደረስንባቸው ተግባራት እንዳሉ አስገንዝበዋል።

በቀሪ ወራትም ሁሉም የስራ ቡድን የተጀመሩ ስራዎች በማጠናቀቅ ወደ ስራ በመግባት በተለያያ መንገድ የሚጓተቱ ስራዎችን ካሉም በአጭር ጊዜ ወደ ወደስራ ተገብቶ ተጨባጭ የሆነ ወጤት እንዲያመጡ ኃላፊው በአፅንኦት ገልጸዋል።

የቆቦ ከተማ አሰ/ር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የ9 ወር ስራንና ዞናዊ የስራ አጸፃፀም ግብረ መልሰና ተቆማዊ  የአገልግሎት አሠጣጥን በመገምገም የቀጣይ ስራ አቅጣጫን አስቀመጡ  ግንቦት 26/201...
03/06/2026

የቆቦ ከተማ አሰ/ር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የ9 ወር ስራንና ዞናዊ የስራ አጸፃፀም ግብረ መልሰና ተቆማዊ የአገልግሎት አሠጣጥን በመገምገም የቀጣይ ስራ አቅጣጫን አስቀመጡ

ግንቦት 26/2018 ዓ.ም(ቆቦ ኮሙኒኬሽን ) የቆቦ ከተማ አስተዳድር ስራና ክህሎት ጽ/ቤቱ በስሩ ከሚገኙ ጠቅላላ ሰራተኞች ጋር የ2018 ዓ.ም የዘጠኝ ወር እቅድ ክንውን ያለበትን የሁኔታ ግምገማ አካሄደ ።

ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አህመድ ኑርየ እንደገለፁት ግምገማው ቁጥር መሰረት ያደረገ ሳይሆን የአሻጋሪ እቅዱን የስራ መመሪያ በማድረግ በእቅድ ተመርተን እያመጣነው ያለው ውጤት ምን ላይ ነው? በሚለው መተኮር አለበት ያሉ ሲሆን። ከዚህ በመነሳት ያለንበትን የአፈፃፀም ደረጃ በማየት በቀሪ ጊዚያት ለማከናዎን የሚያስችል የተግባር ግምገማ ላይ አተኩረን ልንሰራ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል ።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቁን በማስመልከት የቆቦ ከተማ አስተዳደር ምርጫው በሠላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የቀበሌና የከተማ አመራሮች   ምስጋና አቅርቧል። በሰሜን ወሎ ዞን ...
03/06/2026

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቁን በማስመልከት የቆቦ ከተማ አስተዳደር ምርጫው በሠላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የቀበሌና የከተማ አመራሮች ምስጋና አቅርቧል።

በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ ሀይለአብ ወንድሙ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን በማስመልከት ለቀበሌና ለከተማ አመራሮች በከተማ አስተዳደሩ እና ህዝቡ ስም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህ አፈጻጸም ከተማችን ቁርጠኛ አመራሮች የመጣ በመሆኑ ለውጤቱ መሳካት ሚና የነበራችሁ አመራሮች እና መላው የከተማችን ህዝብ ውጤቱ የጋራ ውጤታችሁ መሆኑን እየገለጽኩ።

በቀጣይ ለምናከናውናቸው የመንግስት ስራዎች በቁርጠኝነት ልንሰራ ይገባናል ያሉት አቶ ሀይአብ ወንድሙ በሁሉም ልማቶች ተደራሽ ለመሆን ሰላም ወሳኙ አጀንዳችን ሲሆን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከመንግሥት ጎን በመሆን ለሠላሙ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የዘንድሮው ምርጫ የአመራሮቻችንን ጥንካሬ እና ጉድለት የህዝባችንን ቆራጥነት ያየንበት አገር የማስቀጠል ነበር ሲሉ የቆቦ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ይመር ገልጸዋል ።

በመጨረሻም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አሰቀምጠው የምስጋና ፕሮግራሙ ተጠናቋል ።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የቆቦ ከተማ ፖሊስ  ጽ/ቤት አስታወቀ።በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ  7ኛ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የከተማው  ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ፈን...
02/06/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የቆቦ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ 7ኛ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ፈንታው ውዱ አሳውቀዋል።

አዛዡ እንደተናገሩት በከተማው የተካሄደው ምርጫ ያለምንም የጸጥታ ችግር በትላንትላው እለት ሲካሄድ ውሎ በሰላም ተጠናቋል ብለዋል።

ኮማንደር ፈንታው እንደገለጹት ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ለሰሩ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ለፌዴራል ፓሊስ፣ለከተማው የጸጥታ መዋቅር፤ለምርጫ አስፈጻሚዎች እና ለህዝቡ ምስጋና አቅርበዋል።

በቆቦ  ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ዜጎች በማለዳ ወጥተው ድምፅ እየሰጡ ነው።ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችም በምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል።
01/06/2026

በቆቦ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ዜጎች በማለዳ ወጥተው ድምፅ እየሰጡ ነው።

ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችም በምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው! በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ምርጫ ክልል መራጮች ካርድ ባወጡበት ምርጫ ጣቢያ ድምፅ እየሰጡ ነው።
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ምርጫ ክልል መራጮች ካርድ ባወጡበት ምርጫ ጣቢያ ድምፅ እየሰጡ ነው።

"ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው !!!"በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ መራጮች በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጽ እየሰጡ ነው።
01/06/2026

"ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው !!!"

በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ መራጮች በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጽ እየሰጡ ነው።

'' " ​በራያ ቆቦ ወረዳ በራያ ቆቦ ምርጫ ክልል በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች መራጩ ህዝብ ማለዳ ላይ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጻቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።
01/06/2026

'' "

​በራያ ቆቦ ወረዳ በራያ ቆቦ ምርጫ ክልል በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች መራጩ ህዝብ ማለዳ ላይ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጻቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በሰላምና በስኬት ለማጠናቀቅ የጸጥታ ኀይሉ ዝግጅት ማድረጉን የቆቦ ከተማ  ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። ‎‎በሰሜን ወሎ ዞን  ቆቦ ከተማ አስተዳደር ሰባተኛው ሀገራዊ እና ክ...
30/05/2026

7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በሰላምና በስኬት ለማጠናቀቅ የጸጥታ ኀይሉ ዝግጅት ማድረጉን የቆቦ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

‎በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳደር ሰባተኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን የከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

‎የቆቦ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ፈንታው ውዱ እንደገለጹት የከተማ የጸጥታ ሀይላችን ፖሊስ እና ከሰላም አስከባሪ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት ምርጫውን በስኬት ለማካሄድ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።

‎ምርጫው ሰላምዊ ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የጸጥታ መዋቅራችን በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል ያሉት ፖሊስ አዛዡ ገልጸዋል።

14 47ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰሜን ወሎ ዞን  በቆቦ ከተማ ተከበረ።14 47ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳድር፣ የሃይማኖት አባቶች እና ...
27/05/2026

14 47ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰሜን ወሎ ዞን በቆቦ ከተማ ተከበረ።

14 47ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳድር፣ የሃይማኖት አባቶች እና ምዕመናን በተገኙበት በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት ተከብሯል።

በበዓሉ አከከባበር ስነ-ስርዓት ላይ የቆቦ ከተማ አሰተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ ሀይለአብ ወንድ፣ የቆቦ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ይመር ተገኝተዋል።

በዓሉ ሶላት እና ተክቢራን ጨምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል ።

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖች በመርዳትና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ መልዕክት ተላለፏል።

Address

ቆቦ
K'obo

Telephone

+251333340389

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቆቦ ኮሙኒኬሽን kobo communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share