Jimma University Library System ጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመፅሐፍት

  • Home
  • Ethiopia
  • Jimma
  • Jimma University Library System ጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመፅሐፍት

Jimma University Library System ጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመፅሐፍት Introducing the library service
(5)

የጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመፃህፍት  የክፍል ሀላፊዎችና የቡድን መሪዎች በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢኒስቲትዩት የጅማ ዕፅዋት አፀድ ማዕከል በመገኝት በጋራ ያደረጉት የጉብኝትና የመዝናኛ ፕሮግራም...
02/11/2024

የጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመፃህፍት የክፍል ሀላፊዎችና የቡድን መሪዎች በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢኒስቲትዩት የጅማ ዕፅዋት አፀድ ማዕከል በመገኝት በጋራ ያደረጉት የጉብኝትና የመዝናኛ ፕሮግራም በፎቶ ።

ጥቅምት 23/2017

በጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመጻህፍት “Knowledge sharing workshop within library academic staff “  በሚል ርዕስ ለአራት ቀናት ሲካሄድ  የቆየው የዕውቀት ሽግግር...
17/10/2024

በጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመጻህፍት “Knowledge sharing workshop within library academic staff “ በሚል ርዕስ ለአራት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የዕውቀት ሽግግር ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ (ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም)
***********************************************
በስልጠና መድረኩ ላይ የአብያተመጻሐፍቱ ዳይሬክተር ወ/ሮ አዲስዓለም ጉሉማ በአካዳሚክ ስታፉ የተካሄደው ይህ በዕውቀት የተደገፈ የዕውቀት ሽግግር ስልጠና ዩኒቨርሲታው በየጊዜው ለሚያደርጋቸው የተለያዩ ጥናትና ምርምሮች ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግና አብያተመጻህፍቱም በስፋት እንደሚሰራበት ገልፀዋል ።

ካሳለፍነው ሰኞ ጥቅምት 4/2017 ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በድህ-ምረቃ ቤተ-መጻህፍት በተካሄደው በዚህ የዕውቀት ሽግግር ስልጠና Knowledge sharing workshop ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድህረ ምረቃ ት/ቤት ዳይሬክተር ዶ/ር በቃሉ ፈቀደ ደግሞ እንደነዚህ አይነት የእውቀት ሽግግር መድረኮች መካሄዳቸው በጣም አስፈላጊ እንደሆነና በቀጣይ አብያተመፅሐፍቱ በሌሎች ኮሌጆችና ኢንስቲትዩቶች ውስጥ ላሉ መምህራንና ለድህረ -ምረቃ ተማሪዎች ተከታታይነት ባለዉ መልኩ መስጠት እንደሚገባው አሳስበዋል።

በመጨረሻም በወርክሾፑ የመዝግያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የአካደሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝድንት ዶ/ር ታደሰ ሀብታሙ ላይብረሪው የዩኒቨርሲቲውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማሳለጥ እያደረገ በሚገኝው እንቅስቃሴ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ ይሄንን የእውቀት ሽግግር ስልጠና ሁሉም መምህራን እንድያገኙ በስፋት መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል ። ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም ላይብረሪው በሁሉም መስክ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ በዩኒቨርሲቲው እንደሚደግፍ ገልፀዋል::

በጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመጻህፍት የ2017 ዓ.ም ዓዲስ ዓመት ስራ ማነቃቂያ  ኘሮግራም ተካሄደ ።***********************************************በጅማ ዩኒቨርሲቲ አ...
03/10/2024

በጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመጻህፍት የ2017 ዓ.ም ዓዲስ ዓመት ስራ ማነቃቂያ ኘሮግራም ተካሄደ ።
***********************************************
በጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመጻህፍት በተካሄደው በዚህ የማነቃቂያ ፕሮግራም የቤተመፃህፉ ቡድን መሪዎች ፣ የቅርንጫፍ ቤተመፃህፍ ሀላፊዎችና አስተባባሪዎች የተገኙ ሲሆን የአብያተመጻህፍቱ ዳይሬክተር ወ/ሮ አዲስዓለም ጉሉማ የ2016 ዓ ም የተሰሩ ስራዎችና የተገኙ አመርቂ ውጤቶች እንዲሁም በ 2017 ዓ. ም የስራ ዘመን ለማሳካት የተያዙ እቅዶችን የተመለከተ ገለፃ አድርገዋል ። በመጨረሻም ከተሳታፊዎቹ ጋር በተደረገ ሰፊ ውይይት ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል ።
መስከረም 23/2017 ዓ.ም

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚገኝው  የህፃናት ቤተ-መጻህፍ ከመቶ በላይ የልጆች መፅሐፍ ተበረከተ ( ነሐሴ 21/ 2016 )****************...
27/08/2024

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚገኝው የህፃናት ቤተ-መጻህፍ ከመቶ በላይ የልጆች መፅሐፍ ተበረከተ ( ነሐሴ 21/ 2016 )
*********************;************************
በአሜሪካና በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የሚገኙ የጅማ ከተማ ተወላጅ የሆኑ ዲያስፓራዎች ወደ ሀገር ቤት የላኩትን ግምቱ 60 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የትምህርት መርጃ መፅሐፍ በአደራ የተቀበለዉ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ በሁለተኛ ዙር በጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከ7 ዓመት በላይ ለዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ሰራተኛ ልጆች ምቹ የማንበቢያ ስፍራ ለሆነው የህፃናት ቤተ-መጻህፍ ከመቶ በላይ የሚሆኑ የልጆች መፅሐፎችን አበርክቷል ።

በመፅሐፍ ርክክቡ ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተ - መጻህፍት ዳሬክተር ወ/ሮ አዲስዓለም ጉሉማ የመፅሐፍ ስጦታው ለልጆች የሚመጥን መረጃን የማግኝት ክፍተትን ለመሙላትና የንባብና የመረጃ አጠቃቀም ባህላቸውን ለማጎልበት በማሰብ እንደሆነ ገልፀዋል ።

ወ/ሮ አዲስዓለም አያይዘውም አብያተመጻህፍቱ በአደራ ከተቀበላቸው መፅሐፎች በመጀመሪያ ዙር ከ260 በላይ የሚሆኑ የትምህርት መርጃ መፅሐፎችን ለሰጦ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መስጠቱን አስታውሰው የቀሩት መፅሐፎችም በተገቢው ቦታቸው ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በመጨረሻም በጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሰለሞን ቱሉ መፅሐፎቹን ለላኩና ላስተባበሩ ጅማ ከተማ ለተወለዱ ዲያስፓራዎች ፣ ለጅማ ከተማ ባለሀብቶችና ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ምስጋና አቅርበው መፅፎቹን ተርክበዋል ።

ማርቆስ ባህሩ

Address

Jimma

Telephone

+251471112119

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jimma University Library System ጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመፅሐፍት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Jimma University Library System ጅማ ዩኒቨርሲቲ አብያተመፅሐፍት:

Share

Category