Awi Administrative Zone Revenue Department /አዊ አስተዳደር ዞን ገቢዎች መምሪያ/

  • Home
  • Ethiopia
  • Injibara
  • Awi Administrative Zone Revenue Department /አዊ አስተዳደር ዞን ገቢዎች መምሪያ/

Awi Administrative Zone Revenue Department /አዊ አስተዳደር ዞን ገቢዎች መምሪያ/ ይህ የአዊ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ፌስቡክ ገጽ ነዉ

07/02/2026
03/02/2026

ባለፉት ወራት 45 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰበሰበ

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት እስከ ጥር 22/2018 ዓ.ም ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ 45 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የቢሮው የግብር ትምህርትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ታዘባቸው ጣሴ ገለጹ፡፡

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የክልሉ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በመሰብሰብ የክልሉ ህዝብ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለማሰጠት በርትቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 ዓ.ም ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ 100 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ ጥር 22/2018 ዓ.ም ከመደበኛ ገቢ 40 ነጥብ 2 እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ 5 ነጥብ 4 በድምሩ 45 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወይም የእቅዱን 45.6 በመቶ መሰብሰብ እንደቻለ ተናግረዋል፡፡

የተሰበሰበው ገቢ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው ገቢ አኳያ ሲነፃፀር 15 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር እድገት እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ሰሜን ሽዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ፣ ወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ገቢዎች መምሪያ፣ወልዲያ ከተማ ገቢዎች መምሪያ፣ማዕከላዊ ጎንደር ገቢዎች መምሪያ፣ኦሮሞ ብሔረሰብ ገቢዎች መምሪያ፣ አዊ ብሔረሰብ ገቢዎች መምሪያ እና ደብረ ብርሃን ከተማ ገቢዎች መምሪያ በቅደም ተከተላቸው የእቅዳቸውን ከ50.6 እስከ 47.04 በመቶ ባለው ውስጥ በመፈፀም በተሻለ አፈፃፀም ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ ገቢዎች መምሪያ፣ ደሴ ከተማ እና ሰሜን ጎንደር ገቢዎች መምሪያ ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ የሚያሻቸው በአፈፃፀም በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዞኖች እንደሆኑ አብራርተዋል።

ቢሮው የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግ የኤሌክትሮኒክ ታክስ አስተዳደር ስርዓት (ኢ-ታስ) የተሰኘ ሲስተም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስለምቶ እየተገበረ ሲሆን በክልሉ ካሉ 257 የታክስ ማዕከላት ውስጥ 225 ሲስተሙን መጠቀም መጀመራቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በ2018 የታቀደው የገቢ እቅድ በስኬት እንዲሳካ ቢሮው የገቢ እቅዱን ለከፍተኛ አመራሩ፣ ለአጋርና ባለድርሻ አካላት እና ከገቢ ተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ተደጋጋሚ መድረክ ተፈጥሮ የእቅዱ ባለቤት እንዲሆኑ የማድረግ ስራ መሰራቱን ተናረዋል፡፡

በአጠቃላይ ውጤቱ በጥንካሬ የሚገለፅ ቢሆንም ግን አሁንም በቀጣይ የደረሰኝ አቆራረጥ ላይ ብዙ ስራ መስራት እንዳለበት ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፡- ሲሳይ አስማማው
ፎቶ፡- ማስተዋል ሁነኛው

አስተያየት እና ጥያቄ ቢኖርዎ ከዚህ ገፅ በተጨማሪ እነዚህን አድራሻዎች ይጠቀሙ
በፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/AmraNews
https://www.facebook.com/profile.
በቴሌግራም:- Amhara Region revenue bureau
በዩትዩብ:- https://www.youtube.com/ ገቢያችን
እንዲሁም አስተያየትና ጥቆማ በ 9504 ይደውሉ
መደበኛ ስልክ ቁጥሮች 058 220 57 49/ 09 47

Awi Revenue Staff ቴሌግራም ገጽ የተወሰደ
12/12/2025

Awi Revenue Staff ቴሌግራም ገጽ የተወሰደ

27/11/2025

ለሚመለከተው ሁሉ
ገቢ ለመሰብሰብ በሚል ምክኒያት የተዘረጉ ኬላዎች የተነሱ መሆኑን እናሳውቃለን።

19/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus Disease) በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት የደም መፍሰስና ትኩሳት ህመም ሲሆን በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንስሳት ላይ ይከሰታል።

የበሽታው ምልክቶች ለቫይረሱ በተጋለጥን ከ2 እስከ 9 ባሉት ቀናት ውስጥ የሚታዩ ሲሆን፤ ምልክቶቹ:-
ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ስር ደም መፍሰስ፣
ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፣
የጡንቻ እና የጀርባ ህመም፣
ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፣
ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ በጣም ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ ናቸው።

የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች
ከበሽተኛ ደም፣ ሽንት፣ እንባ እና ሌሎች ፈሳሾች ጋር የሚፈጠር ቀጥተኛ ንክኪ፣
በታመመ ወይም በሞተ ሰው የሰውነት ፈሳሽ የተበከሉ ቁሶች (እንደ ልብስ፣ አልጋ ልብስ፣ መርፌ እና ሌሎች መገልገያዎች) ጋር በሚኖር ንክኪ፣
በተጨማሪ በበሽታው ከተያዙ የሌሊት ወፎች ወደ ሰዎች ይተላለፋል።

የበሽታው መከላከያ መንገዶች

የተዘረዘሩት ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ፣
ከታመመ ሰው ጋር ንክኪ ካለዎት እና ትኩሳት ካለ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ፣
ሞት በሚከሰትበት ጊዜ አስከሬኑን በባለሙያ ማዘጋጀት እና መቅበር፤ አላስፈላጊ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን ማስቀረት እና ንክኪ ያላቸውን ቁሶች ማስወገድ፣
ከታመመ ሰው ደም እና ፈሳሽ ንክኪ ራስን መጠበቅ፣

ለታመመ ሰው እንክብካቤ በምናደርግበት ጊዜ የመከላከያ ዘዴዎችን ማለትም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የእጅ ጓንት መጠቀም፣
እጅን በሳኒታይዘር ወይም በሳሙናና በውሃ በአግባቡ መታጠብ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

12/11/2025
04/11/2025

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓም በእንጅባራ ከተማ በአዊ አስተዳደር ህንፃ በተሻሻለዉ የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በስልጠናዉ የወረዳ/ከተማ አስተዳደር ገቢ ጽ/ቤት ሃላፊዎች፣ ስራ ሂደት አስተባባሪዎች፣ ሙያተኞች እና የመምሪያዉ ሙያተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ስልጠናዉ እንደቀጠለ ይገኛል።

Address

Injibara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awi Administrative Zone Revenue Department /አዊ አስተዳደር ዞን ገቢዎች መምሪያ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share