Awi Zone Finance and Economic Cooperation office

Awi Zone Finance and Economic Cooperation office facebook
(1)

15/08/2025
የመንግስትን በጀት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ መጠቀምና በፍትሃዊነት መመደብ እንደሚገባ ተጠቆመ ። የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅና መረጃን ለመያ...
15/08/2025

የመንግስትን በጀት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ መጠቀምና በፍትሃዊነት መመደብ እንደሚገባ ተጠቆመ ።

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅና መረጃን ለመያዝ የሚያግዝ አዲስ ቴክኖሎጂ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አስተዋውቋል።

መምሪያው በ2018 በጀት ዓመት የአመራሩና የፈፃሚዎች አቅም በማሻሻል፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ ፣ ለደንበኞች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት፣ የንብረት አስተዳደር ስርዓትን በማዘመን የመንግስት ሀብት በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል ማድረግና ብክነትን መከላከልና የበጀት አመዳደብ አስተዳደርን ፍትሃዊ በማድረግ ወጪ ቆጣቢ ሀብት አጠቃቀም መከተል እንደሚገባ በዕቅድ ተመላክቷል።

መረጃ ለመያዝ የሚያገለግል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ(ሶፍት ዌር) የመንግስት በጀት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለመጠቀምና ጊዜና ጉልበት መቆጠብ የሚያስችል እንደሆነ ሶፍት ዌሩን ያበለፀጉት አቶ ፀዳሉ መኮነን ገልፀዋል።

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ አቶ መለሰ አዳል እንደገለፁት በጀት በቀመሩ መሠረት በፍትሃዊነት መመደብና በቁጠባ መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመው በፋይናንስ አሰራርን ተከትሎ የማይመራ አካል ተጠያቂ የሚሆንበት ስርዓት ማዘጋጀቱን ተናግረዋል ።

አገልግሎት አሰጣጥን ለማፋጠንና መረጃዎች በጥራት ለመያዝ እንዲሁም ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል የሚያስችል ሶፍት ዌር መሆኑን አቶ መለሰ ጠቁመዋል።

በእቅድ ትውውቅ የተገኙት የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉዓለም ደሴ እንደገለፁት በጀትን በአግባቡና በአሰራር የማይጠቀሙ አካላት ተጠያቂ መሆን እንደሚገባቸው ጠቅሰው በጀት ህግና ስርዓትን ተከትሎ በፍትሃዊነት መመደብ እንደሚገባ ገልፀዋል ።

በመንግስት በጀት ምዝበራ እንዳይካሄድ በየጊዜው ኦዲት መደረግና ንብረት አጠቃቀም በጥንቃቄና በቁጠባ እንዲጠቀሙ የፍትህ አካላት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባቸው አቶ ሙሉዓለም ተናግረዋል።

እንደ ሀገር እየተተገበረ ያለው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት ፋይዳው የላቀ ነው -መለሰ አዳልየአዊ ብሄ/አሰ ገንዘብ መምሪያ የመንግስት አገልግ...
13/06/2025

እንደ ሀገር እየተተገበረ ያለው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት ፋይዳው የላቀ ነው -መለሰ አዳል

የአዊ ብሄ/አሰ ገንዘብ መምሪያ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ንቅናቄና የሀሰተኛ የትምህርት ዝግጅት ማጣራት ማስጀመሪያ መድረክ ከሰራተኞቹ ጋር አካሂዷል።

የአዊ ብሄ/አሰ ገንዘብ መምሪያ ሀላፊ መለሰ አዳል፣ መምሪያው ሪፎርሙ በቀዳሚነት ተግባራዊ ከሚሆኑባቸው ተቋማት አንዱ እንደሆነ ገልፀዋል።ሪፎርሙ ሰራተኛውን በአመለካከት፣በክህሎትና በእውቀት የመፈፀም አቅም በማሳደግ ለህዝቡ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመሰጠት ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

ሪፎርሙ የዜጎችን እርካታ ለማረጋገጥ ደግሞ እያደገ ከመጣው ቴክኖሎጅ ጋር አብሮ የሚራመድና የመፈጸምና የማስፈጸም ብቃቱ የጎለበተ ሲቪል ሰርቫንት መፍጠር እንደሚገባም ነው አቶ መለሰ ያብራሩት።

የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃና የስራ ልምድ ሀገርን ወደ ኋላ የሚጎትት አደገኛ በሽታ በመሆኑ የማጣራት ስራ የሪፎርሙ አንዱ አካል እንደሆነ ተናግረዋል። የሌሎችም ተቋማት ማሳለጫ ወይም ማዕከል የሆነው ገንዘብ ተቋም ሪፎርሙ ውጤታማ እንዲሆን በግንባር ቀደምነት መፈፀም ይገባል ነው ያሉት።ለዚህም ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የሪፎርሙን ሰነድ ያቀረቡት የአዊ ብሄ/አስ ሲቪል ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ተ/ሀላፊ አስረስ ቢተው ፥ከዚህ በፊት የነበረው ሪፎርም በመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በሚታዩ ብልሹ አሰራሮች ምክንያት ዜጎች ከመንግስት የሚፈልጉትን አገልግሎት በአግባቡ እንዳያገኙ ማድረጉን አንስተዋል።

አዲሱ ሪፎርም እንደ ሀገር በሲቪል ሰርቪስ መዋቅሩ የሚታዩ ዘርፈ ብዙ የብቃትና አገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን በመሙላት የዜጎችን እርካታ ለማረጋገጥ ታስቦ የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል።

የመምሪያው ሰራተኞች በሰጡት አስተያየት በመድረኩ ባገኙት ግንዛቤ እና ቀጣይም በሪፎርም አተገባብር ላይ የተሟላ ግንዛቤ በመያዝ ለተግባራዊነቱ ርብርብ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

የገንዘብ መምሪያ ም/ሀላፊ አሞኘ ቢተው በበኩላቸው የመንግስት አገልግሎትና አሰተዳደር ሪፎርም ለአመታት በህዝብ ሲጠየቅ የነበረውን የሪፎርም ማሻሻያ የመለሰ መሆኑን ተናግረዋል።

የሰራተኞች ምዘና፣ የሀሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ማጣራት፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠትና ዲጅታላይዜሽንን ተግባራዊ ማድረግ የሪፎርሙ አካል መሆናቸውን ም/የመምሪያ ኃላፊው ገልጸዋል ።

የታቀደው ሀብት ለታለመለት አላማ ከማዋል አንፃር የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን የአዊ ብሄ/አስ ገንዘብ መምሪያ ገለጸ። የአዊ ብሄ/አሰ ገንዘብ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የ9ወራት ዕቅድ አፈ...
26/04/2025

የታቀደው ሀብት ለታለመለት አላማ ከማዋል አንፃር የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን የአዊ ብሄ/አስ ገንዘብ መምሪያ ገለጸ።

የአዊ ብሄ/አሰ ገንዘብ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የ9ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ግምገማ ከወረዳዎች እና ከአጋር ተቋማት ጋር መድረክ አካሂዷል።

የአዊ ብሄ/አስ ገንዘብ መምሪያ ሀላፊ አቶ መለሰ አዳል የብሄ/አስ 2017 አጠቃላይ በጀት 5.6ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ መጽደቁን አስታውሰዋል። መምሪያው ሀላፊነቱ በዋናነት የመንግስትን ሃብት ማስተዳደር መሆኑን ገልጸዋል። ሃብቱ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን በአግባቡ እየተከታተሉ እንደሆነም ተናግረዋል ።

ስለሆነም ባለፉት 9ወራት የተያዘውን በጀት ለታለመለት አላማ ከማዋል አንፃር የተሻለ አፈፃፀም መኖሩን ገልፀዋል።አንፃራዊ ሰላም ባለባቸው በሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የአፈጻጸም ሁኔታ በአብዛኛው የሚያበረታታ መሆኑንም ነው ሀላፊው ያነሱት።

በእርዳታ እና በድጋፍ የሚመጡ የበጀት ድጋፎችን በአግባቡ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከመጠቀም እና ሥራ ላይ ከማዋል አንጻር ክፍተቶች መታየታቸው በግምገማው ተነስቷል። የውዝፍ ሂሳቦችን በሚፈለገው መልኩ ተመላሽ ማድረግ ላይ አሁንም እጥረቶች መኖራቸው ሀላፊው አመላክተዋል ።

በበጀት አመቱ 31ሚ 427ሽ ለመመለስም ታቅዶ እስካሁን 88% በመቶ መፈጸም ተችሏልም ብለዋል።

በየጊዜው ከበጀት አስተዳደር፣ ከኦዲት፣ ከግዥ፣ የፋይናንሰ ወጪ ቁጥጥር ሰርአት ክትትልና ድጋፍ እና ሌሎች ጉዳዮችን በቅርበት በመከታተል ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ደብሪቱ ደስየ ለከተማዋ የተመደበው በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በማድረግ ረገድ ድጋፍና ክትትል እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። ክልሉ የላከው 19ሚ ብር ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ አውለዋል።የፕሮጀክት አፈፃፀሞች ስራ ዕድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ ውጤታማ እንደሆነ ተናግረዋል ።

በኦዲት ግኝት 14 ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱንም ተናግረዋል። ከፍትህ አካላት ጋር በመሆን የማስመለስ ስራ እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በመድረኩ በጥንካሬ የተገኙት ልምዶች እና አሠራሮችን ለቀጣይ ተግባራት በተሞክሮነት የሚወሰዱበት ፣በድክመት የተገመገሙት ደግሞ እንዲስተካከሉ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የአዊ ብሄረሰብ አሰተዳደር ገንዘብ መምሪያ በ26/05/2017/ዓ/ም የ6ወር የእቅድ አፈፃፀም ሪፓርት  የወረዳና የከተማ አሰተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤቶች የማኔጅመንት አባላትን  እና የብሄ/አሰ/የ...
04/02/2025

የአዊ ብሄረሰብ አሰተዳደር ገንዘብ መምሪያ በ26/05/2017/ዓ/ም የ6ወር የእቅድ አፈፃፀም ሪፓርት የወረዳና የከተማ አሰተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤቶች የማኔጅመንት አባላትን እና የብሄ/አሰ/የፋይናንስ ቋሚ ኮማቴ ስብሳቢ የሆኑት የተከበሩ አቶ የኔው አላምረው በተገኙበት የ6ወር የእቅድ አፈፃፀም፣በተለየ መንገድ ከ2004ዓ/ም ጀምሮ በውጭና በውስጥ አዲተሮች የተሰራን ስራና የመምሪያው አሰተግባሪ ቡድን የወረዳና የከተማ የ6ወር አፈፃፀም የደገፈበትን እና አወዳድሮ ደረጃ የ ሰጠበትን ወጤት በማቅረብ ወይይት የተደረገ ሲሆን በጣም የተሻለ ስራ የሚሰሩ ወረዳና ከተሞች ያሉ ቢሆንም የአየሁ ጎጉሳ ወረዳና የዚገም ወረዳዎች በተደጋጋሚ ተደግፈው ከችግር ያልወጡ ስለሆነ የወረዳ አሰተዳደሩ ኮር አመራር እየገመገመ ካልመራው ቀጣይም ከችግር የማይወጡ መሆኑን የገመገምን ቢሆንም በተቃራኒው በጣም የተሻለ ስራ የሰሩና የመምሪያውን ድጋፍ በቅንነት የተቀበሉ፣ በ6ወሩ የእቅድ አፈፃፀም ግምገሜና በአጠቃላይ የስራ አፈፃፀማቸው 1ኛ ደረጃ የሆነው የቻግኒ ከተማ አሰ/ገንዘብ ፅ/ቤት ዲስክ ቶብ እና የአንደኛነት የምስክር ወረቀት 2ኛ ደረጃ የያዘ ባንጃ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት 20ደሰታ ወረቀትና የምስክር ወረቀት 3ኛ ደረጃ የያዘ የጎንጎ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት 10ደስታ ወረቀትና የምስክር ወረቀት የብሄረሰቡ ምከትል አሰተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አይተነው ታዴ በቦታው ተገኝተው ሽልማቱን እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ የሰጡን ስለሆነ በቀጣይም ጠንቅሮ የሰራ የተሻለ የሚሸለም መሆኑን እናሳውቃለን።

የአዊ ብሄረሰብ  አስተዳደር ገንዘብ  መምሪያ  የ2017 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም  ግምገማ  አካሄደ ።ለተሳታፊዎች  የስራ መመሪያ  የሰጡት  የአዊ ብሄረሰብ  አስተዳደር...
03/02/2025

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ ።
ለተሳታፊዎች የስራ መመሪያ የሰጡት የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አይተነው ታዴ በየደረጃው የሚገኙት የገንዘብ ተቋማት ውስን የመንግስት ሀብት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ አይተነው አያይዘውም ሀብት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ለማድረግ ለህዝብ አገልግሎት ለመሰጠት የሚመጡ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቅሰው አዳዲስ የኦን ላይን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የገዢ ስርዓት በመፈጸም ሌብነትንና ብልሹ አሰራር መከላከል እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ አቶ መለሰ አዳል የተገመገሙና በጥያቄ መልክ የተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ለቀጣይ በሂደት በየደረጃው የሚፈቱ መሆኑን ገልፀው ያጋጠማውን የበጀት ችግር ለመፍታት ለሚመለከተው አካል ጠቅሰው እንደአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ገቢ እያሰባሰቡ ጊዜያዊ መፍትሔ መፈለግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
በፀጥታ ምክንያት የመንግስት ሀብት እንዳይመዘበር ማደረግ ይገባል ያሉት መምሪያ ኃላፊው በአንዳንድ ወረዳዎች ላይ ወቅታዊ የፀጥታ ችግሮችን ስበብ በማድረግ የሚያጭበረብሩ ሠራተኞች እንዳይኖሩ መከታተል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመንፈቅ ዓመት የተግባራት አፈፃፀም ከእቅድ በታች በመሆኑ ለቀጣይ ቁልፍና አብይት ተግባራትን በሚካክስ መንገድ መስራት እንደሚገባ አቶ መለሰ በአፅንኦት አስገንዝበዋል።
የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አሞኜ ቢተው በበኩላቸው በፀጥታ ጉዳይ የወጣው ወጭ መረጃ በአግባቡ ማጠናከር እንደሚገባቸው ገልፀው ሁሉም ወረዳዎች የሂሳብ መመሪያ ተከትለው መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።
በፅንፈኛው የተዘረፉት ሀብቶች በአግባቡ መረጃ መያዝ እንደሚገባቸው የጠቀሱት አቶ አሞኜ ተጨባጭ መረጃ በሌለው የመንግሰት ሀብትና ንብረት እንዳይመዘበር ማደረግ እንደሚገባ አንስተዋል።
በግምገማው ላይ የተሳተፉት የአዊ ብሄረሰብ ምክር ቤት ኢኮኖሚ ልማት በጀትና ፋይናንስ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ የኔው አላምረው እንደገለፁት በአንዳንድ ወረዳዎች የተሰሩ መልካም ስራዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ሀብትን ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ግልፅ ጫራታ በስፋት መጠቀም እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
የግምገማው ተሳታፊዎች በመንፈቅ ዓመቱ በጥንካሬ የፈፀሙትን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ውስንነቶች በማረም ለቀጣይ እንደሚሰሩ ጠቅሰው በክፍተት የገመገሙትን በቀሪ ጊዜ ለመፈጸም መግባባት ላይ ተደርሷል።
በቀሪ ወራት የሚከናወኑ ተግባራት በመምሪያ ኃላፊዎች የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ግምገማው ተጠናቋል ።
በ2017 ዓ/ም በ6 ወር የተሻለ ተግባራት ለፈፀሙት ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በአይነት ሽልማትና እውቅና ተሰጥቷል።

አዊ/ብሔ/አሰ/ገንዘብ መምሪያ የ2017በጀት ዓመት  የበጀት አሰተዳደርና የመግስተት ትብብር፣ የፋይናንስ ውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት፣ የግዥና ንብረት አሰተዳደር ዙሪያ ፣ የግዥ ኦዲት ክትትል ሥርዓ...
06/12/2024

አዊ/ብሔ/አሰ/ገንዘብ መምሪያ የ2017በጀት ዓመት የበጀት አሰተዳደርና የመግስተት ትብብር፣ የፋይናንስ ውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት፣ የግዥና ንብረት አሰተዳደር ዙሪያ ፣ የግዥ ኦዲት ክትትል ሥርዓትእና የኦዲት የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ሥልጣናና አማረ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሻሻለው የመግስት ተቋማት የለውጥ አመራር አደረጃጀትና አሰራርእና ሠራተኞች የሥራ አፈፃፀም ምዘና መመሪያ ቁጥር 49/2014 ሥልጠና ሁሉም ባለሙያዎች ጋር ሥልጠና መስጠት ተችሏል ፡፡

Address

Injibara

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awi Zone Finance and Economic Cooperation office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share