Hamar Woreda Government Communication Service

Directions Contact the organization

Hamar Woreda Government Communication Service Information is a vital for all society

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ከደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመዲመካ፣ መስከረም 26/2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሬ...
06/10/2026

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ከደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ዲመካ፣ መስከረም 26/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ከደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

​በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር መካከል ሀገራዊ መረጃ ተደራሽ ማድረግ፣ የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስፋፊያ እና ትውልድ ግንባታ ላይ ያተኮሩ የህትመት ሚዲያ ውጤቶች በዞኑ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት መፈራረሙን የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት አስታውቀዋል።

ይህ ስምምነት በዋናነት ያነጣጠረው በዞኑ የሚገኙ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎችን፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችን፣ የልማት ስራዎችን እንዲሁም የህዝቡን ባህልና እሴት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የህትመትና መልቲሚዲያ ውጤቶች ሰፊ ሽፋን በመስጠት ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑ ተመልክቷል::

ትላልቅ የሚዲያ ድርጅቶች ጋር ተቀናጅቶ መስራት በዞኑ የሚገኙ ማህበረሰቦች ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃዎችን እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈ፣ የትውልድ ግንባታ ሥራዎችን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ይታወቃል።
South Omo Zone Government Communications

✍️ በሐመር ወረዳ ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ለመሸፈን 50 ኩንታል የቦቆሎ እህል ግዢ ተፈፅሞ በወረዳው በተዘጋጀ የእህል ማከማቻ መጋዘን ገቢ ተደረገ።✅✅ መስከረም፦ 26/2019 ዓ.ም    ...
06/10/2026

✍️ በሐመር ወረዳ ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ለመሸፈን 50 ኩንታል የቦቆሎ እህል ግዢ ተፈፅሞ በወረዳው በተዘጋጀ የእህል ማከማቻ መጋዘን ገቢ ተደረገ።

✅✅ መስከረም፦ 26/2019 ዓ.ም
#ዲመካ

✍️ በደቡብ ኦሞ ዞን የሐመር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ለመሸፈን 50 ኩንታል የቦቆሎ እህል ግዢ በመፈፀም በወረዳው በተዘጋጀ የእህል ማከማቻ መጋዘን ገቢ ተደርጓል።

✍️ የሐመር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ዛንጋ ኛይታ እንደገለፁት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተጋላጭ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በራስ አቅም ለማገዝ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

✍️ በዚህም መሠረት በወረዳው ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በ460 ሺህ ብር 50 ኩንታል ቦቆሎ ግዢ መፈፀሙን ዋና ኃላፊው ገልጸዋል።

የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉመስከረም 26/2019 ዓ.ም  የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ጠቅላይ ሚኒስት...
06/10/2026

የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

መስከረም 26/2019 ዓ.ም

የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን ለመምራት በድጋሚ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ በመልዕክታቸው÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በድጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየምዎ በታንዛኒያ ሕዝብ እና መንግሥት ስም እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ድጋሚ መመረጥ ላሳዩት የአመራር ጥበብ እና ለኢትዮጵያ እድገት ላላቸው ራዕይ የተሰጠ መተማመኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ታከብራለች ያሉት ፕሬዚዳንቷ ÷ መንግሥታቸው ከኢትዮጵያ ጋር በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት፣ በጋራ እና በቀጣናዊ ፍላጎቶች ዙሪያ በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ከአጀንዳ ተቀባይነት ወደ አጀንዳ ሰጪነት የተሸጋገረው የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ**************ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት ስትከተለው የቆየችውን የውጭ ግንኙነት አካሄድ በመቀየር፣ በዓለም አቀፍ...
06/10/2026

ከአጀንዳ ተቀባይነት ወደ አጀንዳ ሰጪነት የተሸጋገረው የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ
**************

ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት ስትከተለው የቆየችውን የውጭ ግንኙነት አካሄድ በመቀየር፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች ከአጀንዳ ተቀባይነት ወደ አጀንዳ ሰጪነት የሚያሸጋግራት አዲስ የዲፕሎማሲ መስመር እየተከተለች ትገኛለች።

ከዚህ ቀደም ሀገራችን በዋናነት ለውጭ ጫናዎች እና ትችቶች ምላሽ በመስጠት ላይ ያተኮረ፣ ከተወሰኑ አጋሮች ጋር ብቻ የተሳሰረ እና በእርዳታ ላይ የተንጠለጠለ አካሄድ ትከተል እንደነበር ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ግን ይህንን አሠራር በመቀየር በሥድስት ዋና ዋና መርሆች ላይ የተመሰረተ ገቢር-ነበብ የዲፕሎማሲ ፖሊሲ በመተግበር ላይ ትገኛለች።

እነዚህ ዋና ዋና የዲፕሎማሲ መርሆችም ቅድመ-መከላከል እና መሪነት፣ ሚዛናዊ የውጭ ግንኙነት፣ በብሔራዊ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ትስስር፣ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር፣ ሉዓላዊነትና የባሕር በር ጥያቄ እንዲሁም የአፍሪካ ድምፅ መሆን ናቸው።

በመሆኑም ይህ አዲስ የዲፕሎማሲ መስመር ኢትዮጵያ ተቀናቃኝ ከሆኑ የዓለም ኃይሎች ጋር ሚዛኗን ጠብቃ እንድትሠራ፣ የባሕር በር ጥያቄዋን ከውስጥ አጀንዳነት ወደ ዓለም አቀፍ የምክክር ነጥብ እንድታሸጋግር እና በዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ አህጉራዊ ተሰሚነቷ እንዲጎለብት አድርጓታል።

በቅርቡ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ፣ ሀገራችን ለአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ችግሮች የመፍትሔ ምንጭ መሆኗን አስመስክሯል።

በተጨማሪም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ያቀረቡት ጥሪ፣ በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ጉባኤ እና በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዘንድ ሰፊ ድጋፍ ማግኘቱ የሚታወስ ነው።

በአጠቃላይ የመደመር መንግሥት የተከተለው ይህ ገቢር-ነበብ የዲፕሎማሲ አካሄድ ኢትዮጵያን ከአጀንዳ ተቀባይነት ወደ አጀንዳ ሰጪነት፣ ከምላሽ ሰጪነት ደግሞ ወደ ቅድመ-መከላከል በማሸጋገር ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተሰሚነቷ ይበልጥ እንዲጠናከር አድርጎታል።

በሜሮን ንብረት

‎ #የመደመርመንግሥት

"መደመር የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማሰቢያ ቋንቋ መሆን እንደሚችል አረጋግጠናል።"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #የመደመርመንግሥት      ‎
06/10/2026

"መደመር የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማሰቢያ ቋንቋ መሆን እንደሚችል አረጋግጠናል።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#የመደመርመንግሥት
‎

06/10/2026
የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያ የቀጣይነት ጉዞ እና የሀገራዊ አንድነት ማብሰሪያ********************ኢትዮጵያ በሕዝብ ነፃ ፍላጎት እና በዴሞክራሲያዊ ውሳኔ ላይ የተመሠረተ አዲስ የታ...
06/10/2026

የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያ የቀጣይነት ጉዞ እና የሀገራዊ አንድነት ማብሰሪያ
********************

ኢትዮጵያ በሕዝብ ነፃ ፍላጎት እና በዴሞክራሲያዊ ውሳኔ ላይ የተመሠረተ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በይፋ ጀምራለች።

ቀደምት የሥልጣን ሽግግሮች በግጭትና በፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት ሀገራዊ ኪሳራን አድርሰዋል። ዛሬ ግን ሀገራችን ከእነዚያ የታሪክ ስህተቶች በመማር፣ የሕዝብን ድምፅ እና የሐሳብ አሸናፊነትን ያስቀደመ አዲስ የመንግሥት ምሥረታ እውን አድርጋለች።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በነፃነት እና በነቂስ ወጥተው በሰጡት ድምፅ በትናንትናው ዕለት 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምሥረታ ጉባኤ አዲሱን የመደመር መንግሥት በይፋ መሥርቷል።

በዚሁ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሰየሙት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፣ ያሳለፍነው የምርጫ ሂደት ውዥንብሮችን እና ፈተናዎችን አልፎ የሕዝብን ሕልውና ያፀና እንዲሁም የዴሞክራሲ ባህል መሠረቱን ያጠነከረ ታሪካዊ ክስተት መሆኑን ገልጸዋል።

አዲሱ የመደመር መንግሥት የሕዝብን አደራና እምነት ሙሉ በሙሉ ተረክቦ የተነሳ በመሆኑ፣ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማስቀጠል የሚያስችል ጠንካራ አቅም አለው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው “በዚች ሀገር አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ አይኖርም” ሲሉ እያንዳንዱን ዜጋ እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ መንግሥታቸው በትጋት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

ይህ የሕዝብ ውሳኔ ሰጪነት እና የሀገር ሉዓላዊነት ማረጋገጫ የሆነው መንግሥት፣ ባለፉት ዓመታት የዜጎችን የዘመናት ጥያቄዎች የመለሱ በርካታ ታላላቅ የልማት ስኬቶችን አበስሯል።

የሀገራችንን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለዜጎች ምቹ የኑሮ ሁኔታን እና የሥራ ዕድል የፈጠሩት የገበታ ለሀገር፣ የገበታ ለትውልድ እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ትልቅ አዎንታዊ ተፅዕኖ አሳድረዋል።

የሌማት ትሩፋት እና በበጋ መስኖ ስንዴ ምርት የተመዘገበው ታሪካዊ ስኬት ሀገራዊ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አልፎ ምርቱን ወደ ውጭ መላክ የሚያስችል አቅም ፈጥሯል።

የኢትዮጵያውያን የጋራ አቅምና የፅናት ምልክት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሀገራችንን በቀጣናው የኃይል ምንጭ በማድረግ ለኢኮኖሚው ትልቅ ማነቃቂያ እየሆነ ይገኛል።

የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ በባሕር በርና በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ያላትን ፍትሐዊና ተፈጥሯዊ ፍላጎት በግልጽ ብሔራዊ ጥቅም አድርጎ በማስቀመጥ፣ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሠረተ ውይይት በማድረግ ውጤታማ ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎችን አከናውኗል።

አዲሱ የመደመር መንግሥት በሕዝብ ሙሉ ድጋፍ እና በተመዘገቡት ታላላቅ የልማት ስኬቶች ታግዞ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር፣ የታላቋን ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋና ከፍታ የመገንባት ጉዞውን አጠናክሮ ቀጥሏል።

#የመደመርመንግሥት

በብሌን ደምበሎ

! ! ! ‎

"ሌሎች እሳቤዎች ኢትዮጵያን ከመቀየር ይልቅ፣ ለኢትዮጵያ ሲባል የሌሎችን እሳቤ አቃንቶ መቀበል ተገቢ አካሄድ ነው።"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #የመደመርመንግሥት         ‎
06/10/2026

"ሌሎች እሳቤዎች ኢትዮጵያን ከመቀየር ይልቅ፣ ለኢትዮጵያ ሲባል የሌሎችን እሳቤ አቃንቶ መቀበል ተገቢ አካሄድ ነው።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#የመደመርመንግሥት ‎

ያለፈውን ማወቅ፣ የአሁኑን ማስተካከል እና ለነገው መዘጋጀት፡- የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የሽግግር መንገድ******************ሀገራት ለዘመናት የገነቧቸው ተቋማዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራ...
06/10/2026

ያለፈውን ማወቅ፣ የአሁኑን ማስተካከል እና ለነገው መዘጋጀት፡- የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የሽግግር መንገድ
******************

ሀገራት ለዘመናት የገነቧቸው ተቋማዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መዋቅሮች በለውጥ ማዕበል ውስጥ ማለፋቸው የተለመደ የታሪክ አጋጣሚ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ያለፉትን ስብራቶች መርምረን፣ በፍጥነት እና በፈጠራ መንገድ ሪፎርም እያደረግን፣ የሚመጣውን ዓለም ለመቃኘት እየተዘጋጀን ነው” በማለት ያስተላለፉት መልዕክት፣ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ቀጣዩን አቅጣጫ ግልጽ የሚያደርግ ጥልቅ ርዕይ ያዘለ ነው።

ይህ ጥሪ በውስጡ ያለፈውን ማወቅ፣ የአሁኑን ማስተካከል እና ለነገው መዘጋጀት የሚሉ ሦስት ዋና ዋና የሽግግርና የዕድገት መሠረቶችን በግልጽ ያንጸባርቃል።

ማንኛውም ዘላቂ መፍትሔ የሚጀምረው ችግርን በሆደ ሰፊነት እና በግልጽነት ከመቀበል በመሆኑ፣ ሀገራችን በታሪኳ ያጋጠሟትንና በየጊዜው የተከመሩትን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስብራቶች መመርመር ወሳኝ ጉዳይ ነው።

እነዚህን ስብራቶች ሳይቀበሉ እና ሳይመረምሩ ወደፊት ለመራመድ መሞከር በተሰበረ መሠረት ላይ ሕንፃ የመገንባት ያህል አደገኛ ነው። በመሆኑም ያለፉ ስብራቶችን በጥልቀት መመርመር የችግሩን ሥረ-መሠረት አውቆ ዳግም እንዳይከሰት አስተማማኝ ተቋማዊ አጥር ለመገንባት ያስችላል።

በሌላ በኩል በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታዩ ፈጣን ለውጦች እና የቴክኖሎጂ ምጥቀቶች በባህላዊና በዘገምተኛ የአሠራር ዘይቤ እንድንጓዝ አይፈቅዱም። ለዚህ ነው ሪፎርማችን የፍጥነትና የፈጠራ ታላቅ መርሆዎችን መሠረት ማድረግ ያለበት።

ይህ አሠራር የሕዝብን ጥያቄ እና የሀገርን ፍላጎት በወቅቱ ለመመለስ ጊዜ የማይሰጡ ውሳኔዎችንና አሠራሮችን ተግባራዊ ማድረግን የሚጠይቅ ነው። በተለይም የተለመዱና ውጤት ያላመጡ አሠራሮችን በመተው በቴክኖሎጂ የተደገፉ፣ አዳዲስ የፖሊሲ ሐሳቦችንና የዲጂታል አሠራሮችን ሥራ ላይ ማዋል ይገባል።

በኢኮኖሚው፣ በትምህርቱ፣ በፍትህና በተቋማት ግንባታ የሚደረጉት እውነተኛ የሪፎርም ሥራዎች ሀገራችንን ከቆመችበት ወደፊት የሚያስፈነጥሩ ዋና ዋና ሞተሮች ናቸው።

በአሁኑ ወቅት ዓለም በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤ አይ)፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ፣ በታዳሽ ኃይል እና በጂኦ-ፖለቲካዊ ለውጦች በፍጥነት እየተቀየረች ትገኛለች። በመሆኑም የቀደመውን ስብራት ጠግኖ በነበረበት መቆም አይቻልም። ኢትዮጵያ የነገዋ ዓለም አካል ልትሆን የምትችለው አሁኑኑ ለነገው ዓለም ስትዘጋጅ ብቻ ነው።

የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂዎች፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ ጥረቶች፣ የግብርናና የኢንዱስትሪ ማሻሻያዎች እንዲሁም በሰው ኃይል ልማት ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ሀገራችንን ለነገው ዓለም የሚያዘጋጁ ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው።

በአጠቃላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት ለመላው የሀገራችን ሕዝብ የተላለፈ ጥሪ ነው። ያለፈው ስብራት እንዳያቆመን እና ተስፋ እንዳያስቆርጠን፣ የዛሬው ፈጣንና ፈጠራዊ ሪፎርም ጥንካሬ ሆኖን ለነገው የብልፅግና ዓለም በጋራ መዘጋጀት አለብን፤ ምክንያቱም ሀገር የምትገነባው ስብራቶችን ወደ ጥንካሬ፣ ፈተናዎችን ደግሞ ወደ ዕድል በመቀየር ነው፡፡

! ! !

በአድማሱ አራጋው

‎ #የመደመርመንግሥት

Address

South Omo
Humbo Tebela

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hamar Woreda Government Communication Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Hamar Woreda Government Communication Service:

Shortcuts

Share