01/06/2026
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፤ ታዛቢዎች ያለምንም ገደብ በነጻነት መታዘባቸውን ገለጹ!!!
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስከ ቀን 7 ሰዓት ድረስ ያለውን የትዝብት ሂደት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ካሰማራቸው አጠቃላይ 3 ሺህ 149 (2,258 ተቀማጭ እና 891 ተንቀሳቃሽ) ታዛቢዎች መካከል 99 በመቶ ያህሉ ያለምንም ገደብ ወደ ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች በመግባት ስራቸውን በነጻነት ማከናወናቸውን አስታውቋል።
ህብረቱ በ2 ሺህ 258 ጣቢያዎች ላይ ባደረገው የክትትል ግኝት መሰረት፤ በ97 በመቶዎቹ (2,183 ጣቢያዎች) ታዛቢዎች በደረሱበት ወቅት የምርጫ አስፈጻሚዎች በቦታው ተገኝተው የነበረ ሲሆን፣ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱም በ99 በመቶዎቹ ጣቢያዎች ከጠዋቱ 1 ሰዓት በፊት መጀመሩን (42 በመቶው ከማለዳው 12 ሰዓት በፊት፣ 57 በመቶው ደግሞ ከ12 እስከ 1 ሰዓት ባለው ጊዜ) አረጋግጧል። በአንጻሩ 1 በመቶ (32 ጣቢያዎች) የሚሆኑት ከጠዋቱ 1 ሰዓት በኋላ ሂደቱን የጀመሩ ሲሆን፣ በ3 ጣቢያዎች ላይ ግን መግለጫው እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የድምፅ አሰጣጥ ስራው አለመጀመሩን በማመልከት የምርጫውን ቀደምት ሂደት አጠቃላይ ገጽታ በስኬትና በተግዳሮት ሚዛን አስፍሯል።
FDREGovermentCommunication