የጥላሁን ስንታየሁ ጦማር Tilahun Sintayehu

የጥላሁን ስንታየሁ ጦማር Tilahun Sintayehu በዚህ ገፅ ልዩ ልዩ ኪነ ጥበባዊ ምህዳሮች ይቃኙበታል ኢትዮጵ?

መንግስት ግን ቂጥ አለው?በጥላሁን ስንታየሁዛሬ ትንሽ የአእምሮን ማጀት የሚፈትሽ ጥያቄ ይዤ የተነሳሁ ይመስለኛል፡፡ ስለ መንግስትቂጥ…. አዎ ጥያቄው ለእኔ አልያም ለአንተ እርባና ባይኖረውም ...
16/10/2021

መንግስት ግን ቂጥ አለው?
በጥላሁን ስንታየሁ
ዛሬ ትንሽ የአእምሮን ማጀት የሚፈትሽ ጥያቄ ይዤ የተነሳሁ ይመስለኛል፡፡ ስለ መንግስት
ቂጥ…. አዎ ጥያቄው ለእኔ አልያም ለአንተ እርባና ባይኖረውም ለአንድ ለተበሳጨ፣ ግራ
ለተጋባ፣ የአእምሮው ጓዳ በጥያቄ ለተሞላ፣ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ላለ ግለሰብ ግን
የህልውና ጥያቄ ነው፡፡…. ጠያቂው ይጠይቃል መንግስት ግን ቂጥ አለው?.... ይሄ ጥያቄ
ፈገግ አስብሎም ግራም አጋቶኝ አድሯል፡፡…. በተደጋጋሚ ወደ ህሊናዬ እየመጣ እንቅልፍም
ነስቶኛል፡፡ መንግስት ልብ አለዎይ? አቅም አለውዎይ? ጉልበት እና ብርታ አለውዎይ?
ወታደራዊ ሀይል አለዎይ? ዜጎቹን መጠበቅ ይችላዎይ? ተብሎ ይጠየቃል እንጅ እንዴት
ቂጥ አለው ወይስ የለውም ተብሎ ይጠየቃል?
ለመንግስትስ የቂጥ መኖር አለመኖር የህልውናው ጉዳይ ይሆን? ብቻ አላውቅም ዘንድሮ
ህልውና የምትለዋ ቃል ምግብ እና መጠጣችን ሆናስ አይደል!...... መንግስትስ ቂጥ
ቢኖረው ሚዲያዎቻችን ምን ብለው የሚዘግቡ ይመስላችኋል? እኔ ግን እንዲህ እና
እንዲያ እያሉ የሚያወጉ ይመስለኛ፡-
# ኢቢሲ ፡- የጆ ባይደን መንግስት በሀገራችን ላይ እያደረሰ ያለው ጫና ለአሸባሪው ቡድን
ከለላ ለመስጠት እና የመንግስትን ቂጥ ሆን ብሎ ለማኮሰስ እንደሆነ የአዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ሙሁራን ገለጹ፡፡
# ፋና ፡- ዜጎች የመንግስት ቂጥ እንዳይነካ እና እንዳይደፈር ለማድረግ በግንባር ቀደምነት
ከፊት ተሰልፈው መስራት እንዳለባቸው እና የመንግስትን ቂጥ ላላስፈላጊ እንግልት እና
መጎሳቆል ሊዳርጉ የሚችሉ ነገሮች ሲያጋጥሟቸው ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ
የዜግነት ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
# ትግራይ_ቲቪ ፡- የፋሽሽቱ የዓብይ አህመድ መንግስት በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸመ
ያለው እልቂት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያበቃ በማለት የትግራይ ሰራዊት በወሰደው
መጠነ ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ የፋሽሽቱ መንግስትን የግራ እና የቀኝ ቂጥ ለአንዴ እና
ለመጨረሻ ጊዜ መደምሰስ ተቻለ፡፡
ብቻ ሚዲያዎቻን እንዲህ እያሉ የሚዘግቡ የመስለኛል፡፡ ግን መንግስት ቅጥ አለው? ብቻ
አላውቅም ሊኖረውም ላይኖረውም ይችላል፡፡ ካለውስ በየትኛው አቅጣጫ? በስተ ሰሜን
ወይስ በስተ ደቡብ? በስተ ምስራቅ አልያስ በስተ ምዕራብ? የመንግስት ቂጥ መገኛው
በየትኛው አቅጣጫ ነው? ትልቅ ነው ወይስ ትንሽ? እኔ ግን ትልቅ ብቻ ግዙፍ የሚባለው
አይነት ይመስለኛ፡፡ አለ አይደል ከመቀመጫው የሚበልጥ መቀመጫ ይመስለኛ፡፡ ብቻ
እንጃ ጠያቂው ግን ይጠይቃል፡፡
አብዮት ነው፡፡ ጢንቢራቀው እስኪወጣ ድረስ ስክር ብሎ ሰክሯል፡፡ ከግራ ወደ ቀኝ፣ ከቀኝ
ወደ ግራ፣ ከላይ ወደ ታች፣ ከታች ወደ ላይ ብቻ እግሩ መርገጥ እስከቻለበት ድረስ እረገጠ
ሄድ መለስ ይላል፡፡ እኛ ገና ልጅ ሳለን እማዬ እና አባዬ የአብዮትን ወንድም እና እህቶች ፣
እናት እና አባቱን የደርግ አብዮት እንደገደላቸው ያጫውቱን የነበረው ትዝ ይለኛል፡፡ የደርግ
አብዮት ጨካኝ ነው፡፡ የሰፈራችንን አብዮት ሰካራም እና ዘር የለሽ አድርጎታል፡፡
ይወናጨፋል፣ ይውረገረጋል፣ በደመና አልቦታል እሱም ድምጹን ከፍ አድርጎ ``ደም……
መና`` ይላል፡፡ አየሩ ደመና ነው፡፡ ደሙም ደም-መና ነው፡፡…. ``ደም-መና`` ሲል ወደቀ፡፡
መሬቱ ላይ ያለው ድንጋይ አናቱን አገኘው፡፡ ደሙ ፈሰሰ እሱ ግን ደሙን እየጠረገ ተነስቶ
ቆመና….``መሬ…ቱ ባይኖር….ኖሮ….. ወድቄ ነበር፡፡`` አለ፡፡ በግራ እጁ አንዲት አነስተኛ
ሰንጢ ቢጤ ጨብጧል፡፡ ወደ ፊት ሰንዘር ያደርጋታል፡፡
የቀኝ እጁን አውራ ጣት ጥፍር ለማያየው ሰው ለማሳየት እየሞከረ ``ይታይሃል ይሄ ቀለም
የሰኔ አስራ አራቱ ማህተም ነው፡፡…. በቅጡ እንኳን አልደረቀም፡፡…. አይገርምህም ቀለሙ
ሳይለቅ…. ስንት ዜጋ…. ላይመለስ ለቀቀ….ዜ……..ጋ………ዜ…….ጋ……ዜ….``
አብዮት ላይ እልህ፣ ቁጭት፣ አልሸነፍ ባይነት….. ብቻ የተዘበራረቀ ስሜት ይስተዋላል፡፡
እንባው ከቃላቶቹ ቀድሞ ይወርዳል፡፡ እልሁን እና ቁጭቱን አስተውሎ ለተመለከተው ሰው
አንድ ብርጌድ ጦር የመመለስ አቅም ያለው ይመስላ፡፡ አብዮት ንግግሩን ቀጠለ፡፡
``እኔ…. ተስፋ ቆርጫለሁ…. ተስፋዬስ ማን ሊሆን ይችላል?....... እግዜሩ? አይመስለኝም
እሱስ ተስፋ ላለመቁረጡ ምን ዋስትና አለን?..... ምንም፡፡…… መንግስትስ ማን
ነው?..... የአብዮትን ዘር ማዘር አብዮቱ በላቸው፡፡…… የተረፉት ዘሮቼን በሰሜን እና
በወለጋ እንደ ቆሎ ቆሏቸው!!...... እህ…..እህ….``
እንባው ቁልቁል እየወረደ ንግግሩን ቀጠለ፡፡
``እናቱን መንግስት……. ድንጋይ ተንተርሶ ድንጋይ በልቶ ይደር…… እናቱን……..ድሆ
ይሂድ…. አጥንቱ ይመንምን….. ወንበሩ እሾህ አሜኬላ ያብቅል…. የንግስናው በትር ከዘር
ማዘሩ እጅ ይውጣ!..... እናቱን….. ይሄን መንግስት በዚህ ሰንጢ ቂጡን መውጋት
ነበር….. አዎ የመንግስትን ቂጡን መውጋት ቢቻል እንዴት ያስደስታል፡፡ …… ዙፋን ላይ
የተቀመጠበትን ቂጡን መውጋት!!...... ዙፋን እዳያሰኘው አድርጎ ቂጡን
መጨቅጨቅ…….``
አብዮት ይህንን ሲል መሳቅም አሰኝቶኝ ነበር፡፡ ግና ሰሜቱን፣ ህመሙን፣ ቁጭቱን ስመለከት
ለማያገኘው የመንግስት ቂጥ የማይመለስ ግለሰብ የእኔን ቂጥ ቢወጋኝስ ብዬ ፈራሁ፡፡ ዳሩ
ቂጥ እንጅ ዙፋን የለኝ፡፡ አብዮት ንግግሩን ወደ ጥያቄ ቀየር አደረገው፡፡
``መንግስት ግን ቂጥ አለው?.... ካለውስ የግራውን ወይስ የቀኙን ቂጥ ልውጋው?......
የመንግስትን ቂጥ ለሚጠቁመኝ ዎረታውን እከፍላለሁ፡፡….. አናንተ ጠቁሙኝ እንጅ
መውጋቱን ለእኔ ተዉት….. ዙፋን ላይ መቀመጥ ቀርቶ በአካባቢው መቆም እንዳያሰኘው
አድርጌ እወጋዋሉ፡፡…. ቂጥ አልባ እስኪሆን ድረስ እጨቀጭቀዋለሁ፡፡…… የዛኔ መቀመጥ
ሲያቅተው ዜጋውን ቆሞ ይጠብቃል፡፡…… ከቂጡ ደም ሲንፎለፎል ለሌሎቹም ደም ጥብቅና
የቆማል፡፡``
አብዮት ወደ ፊት መራመድ ጀመረ፡፡ እኔም የመንግስትን የቂጥ ህልውና ለጭንቅላቴ
እየጠየኩ ባለሁበት ቆሜ ቀረሁ፡፡ እውነት መንግስት ግን ቂጥ አለው?

ጥቅምት 4/2014 ዓ.ም
ሆሳዕና

አንበሳዎቻችን ስለ ፒኮክ ሲሰሙ.....
27/04/2020

አንበሳዎቻችን ስለ ፒኮክ ሲሰሙ.....

17/04/2020
ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 442 ሰዎች መካከል ዘጠኙ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወ...
10/04/2020

ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 442 ሰዎች መካከል ዘጠኙ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 65 ከፍ ብሏል።
__________

ዛሬ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሁሉም ግለሰቦች የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።
ከግለሰቦቹ መካከል ሰባቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፤ አንድ ኤርትራዊ ቀሪዋ ደግሞ የህንድ ዜግነት ያላት ናት።

አራቱ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው፡፡

ሁለቱ የቱርክ፤ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ደግሞ የእንግሊዝ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሁሉም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል።

የ20 ዓመቷ ህንዳዊት የአሜሪካ እንዲሁም የ40 ዓመቱ ኤርትራዊ ደግሞ የዱባይ ጉዞ ታሪክ ያላት ናቸው።

በጽኑ ህሙማን ክፍል ከሚገኙት ሁለት ግለሰቦች መካከል አንዱ የጤና መሻሻል በማሳየቱ ከክፍሉ ወጥቷል።

እስካሁን ባለው ሂደትም በኢትዮጵያ ለሶስት ሺህ 232 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ጠቁመው፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 57ቱ የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።

አራት ግለሰቦች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።https://www.facebook.com/470282680043130/posts/755958328142229/

08/04/2020

............ሚስቴን በዶላር....................../በጥላሁን ስንታየሁ/..............
ከበሮ መደለቅ ፣ ጡሩንባ ማስነፋት ፣ ሸራ ጫማ ተጫምቶ
የእስኒከርን ያክል መበጣጠስ ፣ ውሀ ተጎንጭቶ የውስኪን ያህል
ማግሳት ፣ በእግር እየዳከሩ መኪና ሰለቸኝ ማለት ፣ድቃቂ
ሳንቲም በእጅ ላይ እያንቃጨሉ በዶላር ላይ ማላገጥ የእውነት
ቀላል ነገር ነው፡፡ ምክንያቱ ካንተ የሚጠበቀው ማስመሰል ብቻ
ነው፡፡ በቃ ማስመሰል መመሳሰል አለቀ፡፡ ሌላውን ለዚህ ወረኛ
ህዝብ ተወው ያልሆንከውን ሆንክ ያላደረከውን አደረክ ተብሎ
ይነገርልሀል፡፡ አንተ ብቻ ለመበጣጠስ ለመሽቀርቀርና
ለመንጠራራት ያብቃህ፡፡
"ህይወት ባለ ብዙ ውጣ ውረዳም ባለ ብዙ ጣጣም ባለ ብዙ
ኮተታምና ድሪቷም ናት፡፡ ገንዘብ ከሌለህ አትሰማህም፡፡ አሁንማ
ዘርህንም ጠያቂ ሆናልሀለች፡፡"
የሚሉኝን ሰወች አልሰማቸውም፡፡ እንዴ ምንድነው እንደዚህ ዘሎ
የሰው ትዳር ላይ ጉብ ማለት?... በቃ አስመስላለሁ፡፡ ማስመሰል
ብርቅ ነው እንዴ?...ደግሞ ለሐበሻ እድሜ ልኩን በማስመሰል
አይደል እንዴ የሚኖረው? መንግስት አስመሳይ ህዝቡ አስመሳይ
ተራራው ወንዙ ሳይቀር አስመሳይ ነው፡፡ ምድረ እስስት ሁላ!!!
ቅቡን እንጅ ወርቁን
ለማያይ ህዝብ የምን መጨነቅ ነው??
በተለይ እኛ ሰፈር ሁሉም ምቀኛ ነው፡፡ እንዳገባ አይፈልጉም
ነበር፡፡ እንግዲህ ምን ያምጡ? ቤዛን አገባኀት፡፡
ከነ ግሳንግሷ ፣ ከነ ብልግናዋ ፣ ከነ ልጇ ከነ ኩራቷ ፣ ከነ
ጥጋቧ፣ ከነ ግማትና ጥንባቷ፣ ከነ ውሻነቷ፣ ከነ የዶላር ፍቅሯ ፣
ከነ ምናምኗ አገባኀት!!!!.....እንግዴ ምን ታመጡ????....ገና
ደግሜ ደጋግሜ አገባታለሁ!!! ፍቅሬ ምክንያት የለውም፡፡ ለሷ
ያለኝ ፍቅር ይሄ አሁን እናንተ የምትሉትን ዝባዝንኬ ነገርን ሁሉ
እዳልሰማ እንዳላይ አድርጎኛል፡፡ ስትፈልጉ የማትመጥነውን
አንዲት ውርጋጥ ለጭራቅ ጭራ ቀረሽን ሴት አገባ ብላችሁ
አንቀፅ ጠቅሳችሁ ክሰሱኝ፡፡....አይደለም ጭራቅ ለምን
ዳይኖሰር አትሆንም እናንተን ምን አገባችሁ? በቃ አገባኋት!!
ግብትብት አደረኳት.....ገና ከጠዋት ሴት ከሰሀት ወንድ በፈረቃ
እያፈራረቀች እንድትወልድልኝ አደርጋታለሁ፡፡

ደግሞ እናንተ እኮ አታፍሩም በገዛ ንብረቴ የማስረገዝም ሆነ
የማስወለድ መብት የለህም በሉኝ አሏችሁ፡፡

ከሁሉ የወ/ሮ ታየች አልባሰ መሰላችሁ!

"ልጅቷ የመጀመርያ ባሏ ፈረንጅ ስለ ነበር ዶላር ትወዳለች፡፡
አመሏን አይችለውም:: ጨርቁን አስጥላ አደባባይ ካላሶጣችው
ከምላሴ ፀጉር ይብቀል፡፡"
አሉ፡፡ እንኳን!!.አይደለም ምላሶ ላይ ለምን እንጥሎ ላይ
አይበቅልም እኔ ምናገባኝ!?... እስኪ አሁን ማን ነው ዶላር
የሚጠላ??? አዎ ቤዛ ዶላር ትወዳለች እኔንም ትወደኛለች፡፡
መጥላት እንጅ መውደድ መች ነው ሀጢያት ሆኖ
የሚያውቀው??... ቤዛ እኮ ደግ ናት የማትፈልጋቸውን ነገሮች
በሙሉ ለእኔ እና ለእኔ ቢጤ በመመጽወት የምትታወቅ ደግ ሴት
፣ ላለው የምታበድር ፣ ድሀን ከመጥላት ውጭ የማትጎዳ ፣
ባሏን እና ዶላርን ማበላለጥ እስከቻለችው ድረስ ብቻ አስበልጣ
ዶላርን በብዙ ባሏን በመጠኑ የምትወድ የዋህ ሴት ናት፡፡ ዶላር
ካገኘች ሁል ጊዜ ፋሲካ ናት፡፡ አትጨቃጨቀኝም፡፡
ቤዚን ከማግባቴ በፊት የሚያጨቃጭቀን ነገር አንድ ብቻ ነበር
አሜሪካን በጣም መውደዷ እና ፍቅሯ ከልክ ያለፈ መሆኑ ብቻ፡፡

"አሜ....አሜዬ....አሚኳ.....ሆዴ.....አሚይዬዬዬ"

እያለች አሜሪካ ተብዬዋን ስታሞካሻት እና ስታቆለጳጵሳት ደስ
አይለኝም፡፡ ትንሽ እበሳጭና ቁርስ፣ ምሳ፣ ራትን እዘላለሁ ከዛ
ጨጓራዬን ሲያመኝ የእኔ ውድ አንጀቴን እንዳርሰው ብላ
ሚጥሚጣ በጥብጣ ትሰጠኛለች፡፡ ከዛም ለሳምንታት ከእህል
ውሀ እርቃለሁ፡፡ ይሄ ሁሉ አሜሪካን ማቆለማመጧና ማቆለጳጰሷ
ያመጣብኝ ጦስ ነው፡፡ እኔ ደስ የሚለኝ...
"ጥሌ....ጥልዬ.....ጥሉካ.....ካካዬ...ሆዴ....ጥጥ...ጥሜ...ጥሬ...ጥ...ጥንብ"

በቃ አለ አይደል እንደዚህ እያለች ብታሞካሸኝ አለም አስር
ትሞላ ነበረ፡፡ አሁን....አሁን የወ/ሮ ታየች ምክር እየገባኝ
መጥቷል፡፡ ምን ያደርጋል መስማት ባለብኝ ጊዜ ያልሰማሁትን
ምክር ማስታወስ በሌለብኝ ጊዜ አስታወስኩት፡፡ ልክ እንደ
መንግስታችን ገዳማውያን አባቶች ተው ባሉት ጊዜ ቢተው ኖሮ
እዚህ ሁሉ ሮሮ ውስጥ ባልገባ ነበር፡፡ እኔም ምን አለ ተው
ሲሉኝ ብተው??...ጭራሽ አፏን ሞልታ
"የልጃችን የክርስትና አባት የሚሆነው የመጀመርያ ባለቤቴ
ነው፡፡"....አለችኝ፡፡

የኔዋ ቤዛ ያች ደግና ንፉጓ ፣ ያች የዋኀና ክፉዋ ፣ ያች
መላአክና ሰይጣኗ ያች መልከ መልካሟና ጥይፏ የእኔ ትንባሆ
ፊት ቤዛ....ለእኔ ደግ ለሰወች ግን ክፉ መስላ ትታየን
የነበረችው ቤዛ፡፡ ያች "የዶላር ምንዛሬ ስንት ገባ?"...እያለች
ትጨቀጭቀኝ የነበረችው ቤዛ ይህንን ሰይጣናዊ በቅንፍ ቤዛዊ
ንግግር ተናገረችኝ፡፡
ገንዘብ በጣም ተወዳለች ሁል ጊዜ በ ኢቢሲ የቢዝነስ ዘገባን
ስትከታተል ነው የማገኛት፡፡ እንደውም ሳስበው ያረገዘችው
ዶላር ሳይሆን አይቀርም፡፡ አይ.....አይ....ልጁ ዶላር ከሆነ
አባቱሳ?? ዩሮ?? ወይስ ፓውንድ??....እእእ በጭራሽ!!....ባገባ
ባገባ ቤዛን አገባ ነበር??..ብርቄ ፣ ከበቡሽ ፣ አስናቀች ፣አበበች
፣ ተዋበች፣ አስዋበች እነዚህን የመሳሰሉ ኮረዳዎች ሞልተው
እድሜዋን ስትጠየቅ "ሃያ አምስት ዶላር" እያለች ምትቀባጥር
በዘመነ ርግዝናዋ "መቶ ሽህ ዶላር አማረኝ"
እያለች ባሏን ስኳር እና ደም ግፊት የምታሲዝ ሴት ላግባ???
የማን እርግማን ነው??.....የአባዬ ወይስ የእማዬ?..የኢትዮጵያ
ወይስ የአሜሪካ? ፣ ፓለቲካዊ ወይስ ማህበራዊ?? ወይስ
ኢኮኖሚያዊ??...ይሄማ ኢኮኖሚያዊ እርግማን መሆን አለበት
እንደሱ ባይሆን የኢኮኖሚ ቀውስ አይገጥመኝም ነበር፡፡ በቃ
አሁንስ ሰለቸኝ ቤዛን ልፈታት ነው፡፡ አዎ ፈታኋት፡፡ ይች ዶላራም
እኔ የምቀምሰው ዶናት አጥቻለሁ እሷ ዶላር ያምራታል አዎ
እሷን
ፈትቸ ብርቄን አገባኋት፡፡ የወ/ሮ ታየችን ልጅ አገባኋት፡፡ ገንዘብ
የተባለ በአይኗ አንኳን ለማየት የማትፈልገውን ብርቄን
አገባኋት፡፡......ገንዘብ አትወድም እኔን ግን ትወደኛለች፡፡ ስራ
ሰርታ ደሞዝ አትቀበልም፡፡ ነፃ አገልግሎት ታዘወትራለች፡፡
በገንዘብ የተገዛን ምግብ አትበላም፡፡
ገበሬ አድርጋኛለች፡፡ አርሳሉ፣ እዘራለሁ ፣ እተክላለሁ አበስላለሁ
ትበላለች፡፡ በገንዘብ የተገዛ ልብስ አትለብስም ጥጥ
አመርታለሁ እሸምናለሁ አለብሳታለሁ፡፡ ሸማኔ አድርጋኛለች፡፡
በገንዘብ የሚመጣ ጤና አትፈልግም፡፡ የባህል ሀኪም
ሆኛለሁ፡፡ .....በቃ ሁሉን እንድሆን አደረገችኝ ግን ምክንያቷ ምን
ይሆን??....ጎበዝ ጉድ ሆንኩልህ ብርቄ የኔዋ ብርቄ.....
፡..................................
:.................ጥላሁን ስንታየሁ...........

Address

Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጥላሁን ስንታየሁ ጦማር Tilahun Sintayehu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category