Central Ethiopia Regional State - Office Of The President

Central Ethiopia Regional State - Office Of The President This is the official Central Ethiopia RS Office of the president page where you can get recent info.
(1)

የኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የምትከፍትበት ዕለት - "ሰኞ ግንቦት 24 "በቀን መቁጠሪያው ላይ እንደ አንድ መደበኛ ቀን ብትታይም፣ በውስጧ ግን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሀገራ...
31/05/2026

የኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የምትከፍትበት ዕለት - "ሰኞ ግንቦት 24 "

በቀን መቁጠሪያው ላይ እንደ አንድ መደበኛ ቀን ብትታይም፣ በውስጧ ግን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሀገራቸውን መጻኢ ዕድል በገዛ እጃቸው የሚቀርጹበት ታሪካዊ አጋጣሚን አቅፋ ይዛለች።

ነገ በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በማቅናት ድምፃቸውን ያሰማሉ።

ይህ ሂደት የፖለቲካ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ሉዓላዊነት በተግባር የሚገለጽበት እና ዴሞክራሲያዊ መሠረቶች በሕዝብ እጅ የሚረጋገጡበት ታላቅ ሀገራዊ ክስተት ነው።

ለዘመናት በተለያዩ ታሪካዊ ምዕራፎች ያለፈችው ኢትዮጵያ ይህንን ታሪካዊ ሰኞ በአዲስ ተስፋ፣ በከፍተኛ ጉጉት እና በላቀ ሀገራዊ ስሜት ትቀበለዋለች።

ምርጫ ማለት በወረቀት ላይ ምልክት ማድረግ ብቻ አይደለም፤ ስለ ልጆቻችን ነገ፣ ስለ ሀገራችን ሰላም፣ ልማት እና ብልጽግና በነጻነት የምንወስንበት የዜግነት ከፍተኛ መገለጫ ነው።
የነገዋ ዕለት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ባሕል ውስጥ የባለቤትነት ስሜትን የምታረጋግጥ ታሪካዊ ቀን ናት።

ሥልጣን የሕዝብ መሆኑን፣ የመጨረሻው ውሳኔ ሰጪም ራሱ ሕዝቡ መሆኑን በተግባር የምናሳይበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

ነገ ሕዝቡ በሰላማዊ፣ በነጻ እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ሲያመራ ለዓለም የሚያስተላልፈው ታላቅ መልዕክት አለ፤ “ልዩነቶቻችንን በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ መፍታት የምንችል የበሰልን ሕዝቦች ነን” የሚል ክቡር ምስክርነት ነው።

ይህ ምርጫ ኢትዮጵያ በራሷ ልጆች ጥረትና ብስለት የራሷን ጉዳይ በራሷ ማስተዳደር እንደምትችል የምታሳይበት ታላቅ አጋጣሚ ነው።

በአፍሪካ ቀንድ የዴሞክራሲ ተምሳሌት ለመሆን የምናደርገውን ጉዞም የሚያጠናክር እርምጃ ነው።

ታሪክ ያስተምረናል፤ ታላላቅ ሀገራት የዛሬው የዴሞክራሲ ከፍታ ላይ የደረሱት በአንድ ጀምበር አይደለም።

በእንደዚህ ዓይነት ታሪካዊ ቀናት ሕዝቡ በሚያሳየው ብስለት፣ ታጋሽነት እና የሀገር ፍቅር ነው የዴሞክራሲ መሠረቱ እየጠነከረ የሚሄደው።

ስለዚህ የነገዋ ሰኞ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ልጅ የሀገሩን ታሪክ በደማቅ ቀለም የሚጽፍበት ወርቃማ ዕድል ናት።

የሕዝብ ድምፅ የበላይ የሚሆንበት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እውነተኛ አሸናፊ መሆኑን ለዓለም የምናሳይበት ታላቅ ቀን ናት።

ይህች ዕለት ለኢትዮጵያችን የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተማመን እና የብሩህ ተስፋ መጀመሪያ እንድትሆን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫም በስኬት፣ በሰላም እና በኩራት ተጠናቅቆ ሀገራችንን ወደ ላቀ ከፍታ እንዲያሻግራት ካርድ የያዙ ዜጎች ሁሉ ኃላፊነት ነው።

Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ምርጫ

ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለች፤ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በመምረጥ ሉዐላዊነታቸውን ለዓለሙ ማህበ...
31/05/2026

ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለች፤ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!

ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በመምረጥ ሉዐላዊነታቸውን ለዓለሙ ማህበረሰብ ያረጋግጣሉ። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ጥቅም እና ሉዐላዊ ጉዳይ ነው።

ይህ ታሪካዊ ዕለት የዜግነት ግዴታችንን በክብር የምንወጣበት እና የነገዋን ኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ የምንወስንበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

እያንዳንዱ ዜጋ ወደ ኮሮጆው የሚከተው የድምፅ ካርድ፣ የሀገርን ሰላም፣ ዕድገትና የህዝቦችን አንድነት የሚገነባ ጠንካራ የመሠረት ጡብ ነው።

አባቶቻችን "ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" ብለው በተረትና ምሳሌ እንዳስተማሩን፣ የ54 ሚሊዮን ዜጎች ድምፅ በአንድነት ሲዋሃድ የድህነትን፣ የመከፋፈልንና የኋላቀርነትን ጠንካራ ሰንሰለት በጥሶ መጣል የሚችል የማይበገር አገራዊ አቅም ይፈጥራል።

ምርጫ የሃሳብ ልዕልና የሚረጋገጥበት የሰለጠነ መድረክ እንጂ የጥልና የልዩነት ማራዘሚያ አይደለም። የፖለቲካ ልዩነቶቻችንን በምርጫ ካርድ እንጂ በግጭት የማንፈታበትን ዴሞክራሲያዊ ባህል በተግባር ልናሳይ ይገባል።

ዛሬ የምንመርጠው ተወዳዳሪን ወይም የፖለቲካ ፓርቲን ብቻ ሳይሆን፣ ለልጆቻችን በኩራት የምናስረክባትን ጽኑ እና የበለፀገች ሀገር መሠረት ጭምር መሆኑን መዘንጋት የለብንም።

ስለዚህ፣ ሁላችንም በማለዳ በነቂስ ወጥተን፣ በሰላምና በጨዋነት ድምፃችንን እንስጥ! ድምፃችን ዴሞክራሲያዊ መብታችን ብቻ ሳይሆን፣ መጻኢዋን ኢትዮጵያ የማነፅ ኃይላችን ነው።

ከምንም በላይ ሀገራችንን እናስቀድም፤ የፖለቲካ ውድድሩ ሲያበቃ ለዘለዓለም አብሮን የሚዘልቀው የማይናወጠው ኢትዮጵያዊነታችን ነውና።

የዓረፋ በዓልን በትውልድ መንደራቸው ለማክበር የሄዱ የስልጤ ዞን ተወላጆች የምርጫ ድምፅ ለመስጠት ወደ አዲስ አበባ እየተመለሱ ነውየዘንድሮውን የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በትውልድ ቀያቸ...
31/05/2026

የዓረፋ በዓልን በትውልድ መንደራቸው ለማክበር የሄዱ የስልጤ ዞን ተወላጆች የምርጫ ድምፅ ለመስጠት ወደ አዲስ አበባ እየተመለሱ ነው

የዘንድሮውን የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በትውልድ ቀያቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በጋራ ለማክበር ወደ ስልጤ ዞን ተጉዘው የነበሩ በርካታ የዞኑ ተወላጆች፣ ድምፅ ለመስጠት ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ውስጥ በሚገኙ 10ሩ ወረዳዎችና 5 የከተማ አስተዳደሮች በዓሉን ለማክበር የሄዱ የአካባቢው ተወላጆች ወደ አዲስ አበባ እየተመለሱ መሆናቸውን ለኢቢሲ ተናግረዋል።

ለመመለሳቸው ዋነኛው ምክንያት በነገው ዕለት በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በመሳተፍ የዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም እና ድምፅ ለመስጠት መሆኑን ተናግረዋል።

ተጓዦቹ ያለምንም እንግልት በሰዓቱ ደርሰው ድምፃቸውን መስጠት እንዲችሉ የዞኑ አመራርሮች እና የትራንስፖርት ዘርፍ አስተባባሪዎች በትብብር እየሠሩ ነው።

በዚህ ከፍተኛ የሕዝብ ፍሰት ምክንያት ከወራቤ እና ከተለያዩ የስልጤ ዞን ወረዳዎች ወደ አዲስ አበባ በሚወስዱ መንገዶች ላይ ከፍተኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እየታየ ይገኛል።

ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለችታሪካዊውን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለማከናወን የመጨረሻው ቀን ላይ እንገኛለን ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ ይከናወናል በዚህ ታሪካዊ ቀን ድም...
31/05/2026

ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለች

ታሪካዊውን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለማከናወን የመጨረሻው ቀን ላይ እንገኛለን

ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላው አገሪቱ ይከናወናል

በዚህ ታሪካዊ ቀን ድምፅዎን ሰጥተው ኃላፊነትዎን ለመወጣት እና አሻራዎን ለማሳረፍ ዝግጁ ነዎት?

ነገ በጠዋት ወጥተን በተመዘገብንበት ምርጫ ጣቢያ ድምፅ እንሰጣለን።

Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ምርጫ #ኢትዮጵያ #ምርጫ #በምርጫብቻ

ድምፅ ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲሄዱ ምን መያዝ ይጠበቅብዎታል?በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት የተመዘገበ ማንኛውም መራጭ በድምፅ መስጫው ዕለት ወደ ተመዘገበበት ምርጫ ጣቢያ ለመምረጥ...
30/05/2026

ድምፅ ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲሄዱ ምን መያዝ ይጠበቅብዎታል?

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት የተመዘገበ ማንኛውም መራጭ በድምፅ መስጫው ዕለት ወደ ተመዘገበበት ምርጫ ጣቢያ ለመምረጥ ሲሄድ ሊያሟላቸው የሚገቡ ሰነዶችን አሉ።

በዚህም መሠረት ማንኛቸውም መራጭ መታወቂያ ወይም ማንነትን የሚገልጽ ማስረጃ መያዝ ያለበት ሲሆን፣ የምዝገባ ሁኔታውን መሠረት በማድረግም የሚከተሉትን ሰነዶች ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፦

በአካል ወደ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ ለተመዘገቡ መራጮች በምዝገባ ወቅት ከተመዘገቡበት የምርጫ ጣቢያ የወሰዱትን የመራጭነት ካርድ ዋናውን እና ማንነትን በግልጽ የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ሰነድ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

በተመሳሳይ መልኩ ለመራጭነት የተመዘገቡት "የምርጫዬ" የሞባይል መተግበሪያን ወይም ድረ-ገጽን በመጠቀም ከሆነ ደግሞ የተሰጣቸውን የመራጭነት ካርድ በስልክ ወይም በታተመ ቅጂ (Print) ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸወዋል።

ማንኛውም መራጭ ማንነቱን የሚገልጽ ማስረጃና እነዚህን ሰነዶች በአግባቡ በመያዝ የዜግነት መብቱን መጠቀም ይችላል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ወልቂጤ ምርጫ ክልል ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚውሉ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ስርጭት ተካሂዷል። በወልቂጤ ምርጫ ክልል ሥር በአጠቃላይ 141 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ...
30/05/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ወልቂጤ ምርጫ ክልል ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚውሉ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ስርጭት ተካሂዷል።

በወልቂጤ ምርጫ ክልል ሥር በአጠቃላይ 141 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን ለእነዚህ ጣቢያዎች አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በተሽከርካሪዎች የማድረስ ሥራ በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

ለምርጫ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች ስርጭት ሂደት ሙሉ በሙሉ በጸጥታ አካላት ታጅቦ ስኬታማ በሆነ መንገድ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

የወልቂጤ ምርጫ ክልል ኃላፊ አቶ ሲሳይ ጀማል፣ የምርጫ ቁሳቁሶቹን በየምርጫ ጣቢያዎቹ የማድረሱንና ተደራሽ የማድረጉን ሥራ እስከ ዛሬ ምሽት ድረስ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች  ትርጉም !... የሉዓላዊነት እና የሀገረ መንግሥት ግንባታ ምሰሶኢትዮጵያ በታሪኳ አዲስ እና ደማቅ የዴሞክራሲ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ከ54...
30/05/2026

ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች ትርጉም !... የሉዓላዊነት እና የሀገረ መንግሥት ግንባታ ምሰሶ

ኢትዮጵያ በታሪኳ አዲስ እና ደማቅ የዴሞክራሲ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ድምፃቸውን ለመስጠት መመዝገባቸው ከተራ አሃዛዊ ስኬት እጅግ የዘለለ ጥልቅ ትርጉም አለው።

ይህ አሃዝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሀገሩ ያለውን ፅኑ አቋም የሚያሳይ ሕያው ምስክር ነው።

ታዲያ የዚህ ግዙፍ ሕዝባዊ ተሳትፎ ትርጉም ከሉዓላዊነት እና ከሀገረ መንግሥት ግንባታ አንፃር ሲመዘን ምንን ያመለክታል?

1. ሉዓላዊነትን በተግባር ማረጋገጥ
በተለምዶ ሉዓላዊነት ሲባል ድንበርን ከውጭ ጠላት መከላከል ብቻ ተደርጎ ይወሰዳል። ነገር ግን የዘመናዊ ሉዓላዊነት መሠረት የሕዝብ ሕጋዊ ይሁንታ ነው።

54 ሚሊዮን ዜጎች የሀገራቸውን ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ወደ ምርጫ ኮሮጆ ሲያመሩ ሉዓላዊ የውሳኔ ሰጪነት ሥልጣናቸውን በተግባር እያረጋገጡ ነው።

ይህ ግዙፍ ተሳትፎ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚያስተላልፈው አንድ ጥብቅ መልእክት አለ፡፡

ይኸውም የኢትዮጵያ የፖለቲካ አቅጣጫ የሚወሰነው በራሷ ልጆች እንጂ በውጭ ኃይሎች ጫና ወይም ጣልቃ ገብነት አለመሆኑን ነው።

ይህ የሕዝብ ድምፅ የውጭ ጫናዎችን የሚመክት የሉዓላዊነት የማይበገር ጋሻ ነው።

2. ለሀገረ መንግሥት ግንባታ (State-Building) የጀርባ አጥንት መሆን
ኢትዮጵያ ለዘመናት በተወሳሰቡ የፖለቲካ ሽግግሮች፣ የታሪክ ስብራቶች እና የውስጥ ግጭቶች ውስጥ አልፋለች።

ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት የተበታተኑ ማንነቶችን እና አግላይ የፖለቲካ ትርክቶችን ወደ አንድ ማዕከላዊ የሕዝብ ውክልና ማምጣት የግድ ይላል።

የምርጫ ሳጥን ደግሞ ትልቁ የማስተሳሰሪያ ድልድይ ነው። ዜጎች በዚህን ያህል ታላቅ ቁጥር ሲሳተፉ የጥይት ድምፅን በካርድ፣ ሽኩቻን በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት እየቀየሩት ነው።

ይህ የጋራ ርብርብ የተሰበረውን የማኅበራዊ ውል የሚጠግን፣ ማዕከል እና ዳርቻን የሚያስተሳስር፣ እንዲሁም የዴሞክራሲ ተቋማትን በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ታላቅ ተግባር ነው።

3. የውክልናው ታሪካዊ ኃላፊነት እና የሕዝብ አደራ
ከ54 ሚሊዮን መራጮች የሚገኝ ውክልና እጅግ ከባድ የሆነ የኃላፊነት ሚዛን አለው። ይህ ድምፅ ለአሸናፊዎች የሚሰጥ ነፃ ፈቃድ ሳይሆን ጥብቅ የትውልድ አደራ ነው።

በእንደዚህ ዓይነት ግዙፍ ሕዝባዊ መሠረት ላይ የሚዋቀር መንግሥት የሕግ የበላይነትን የማስከበር፣ የኑሮ ውድነትን የሚቀርፍ ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን የማረጋገጥ እና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባትን የመፍጠር ብቃት ያጎናፅፈዋል፡፡

በአጠቃላይ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች መኖራቸው ተወካዮችን ከመምረጥ የዘለለ ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ አለው።

ይህ አሃዝ የኢትዮጵያ ሕልውና የማይናወጥ መሆኑን የሚያሳይ ማኅተም ነው። ሀገራችንን የመፈወስ፣ መልሶ የመገንባት እና ወደ ላቀ ከፍታ የማሸጋገር ኃይል ሙሉ በሙሉ በዜጎቿ እጅ መሆኑን የሚያበስር የንቃት ጊዜ ነው።

እነዚህ 54 ሚሊዮን ድምፆች መንግሥትን ብቻ ሳይሆን፣ ሉዓላዊ፣ ጠንካራ እና የተዋሐደች የነገዋን ኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት አጥብቀው እየገነቡ ነው፡፡

በሆሳዕና ከተማ፣ የመራጮች ትምህርት መስጠት ሒደት በምስል፡- #ፋና
30/05/2026

በሆሳዕና ከተማ፣ የመራጮች ትምህርት መስጠት ሒደት በምስል፡-
#ፋና

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሌሞ 01 ምርጫ ክልል ስር ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተደረገ ነውሆሳዕና፡ ግንቦት 22/2018፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሌሞ 01...
30/05/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሌሞ 01 ምርጫ ክልል ስር ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተደረገ ነው

ሆሳዕና፡ ግንቦት 22/2018፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሌሞ 01 ምርጫ ክልል ስር ለሚገኙ 140 የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭት እያከናወነ መሆኑን የሌሞ 01 ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን አሻግሬ ገለፁ።

በሌሞ 01 ምርጫ ክልል ስር 140 የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚገኙ የገለፁት አስተባባሪው፤ የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭቱን በተሳካ ሁኔታ ለማሳለጥ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንደሚገኙም አብራርተዋል።

በምርጫ ጣቢያዎቹ 125,548 መራጮች የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን የጠቆሙት አስተባባሪው፤ 62,500 የሚሆኑት መራጮች በዲጂታል አማራጭ የተመዘገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሌሞ ወረዳ የደማላ ባልቡላ ምርጫ ጣቢያ ትምህርት ቤት የምርጫ ጣቢያው ሀላፊ አቶ ጥጋቡ ታፈሰ፤ ለምርጫ ጣቢያው የሚሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶችን ለመረከብ በስፍራው መገኘታቸውን ጠቅሰው፤ የምርጫ ክልሉ ቁሳቁሶችን በጊዜ ተደራሽ የማድረግ ስራውን በተገቢው ሁኔታ እያካሄደ መሆኑን አስረድተዋል።(
#ደሬቴድ

ኢትዮጵያ ትመርጣለች!Ethiopia ElectsEthiopia Votes Ethiopian Broadcasting Corporation
30/05/2026

ኢትዮጵያ ትመርጣለች!

Ethiopia Elects
Ethiopia Votes
Ethiopian Broadcasting Corporation

Address

Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Regional State - Office Of The President posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share