በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት /East Azernet Berbere PP

  • Home
  • Ethiopia
  • Hossana
  • በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት /East Azernet Berbere PP

በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት /East Azernet Berbere PP ፈጣን፣ወቅታዊና ተዓማኒነት ያለው መረጃ ለሁለንተናዊ ብልጽግና

የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከ...
03/06/2026

የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ።

ግንቦት 26/ 2018 ዓ.ም
____________________________________________

‎7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ግልጽ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የላቀ ሚና ለተጫወቱ ከክልልና ከዞን ማዕከል ጀምሮ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች፣ አባላት ፣ ደጋፊዎች ፣ የፀጥታ አካላት፣ሴቶች ፣በጎ ወጣቶች እንዲሁም መላው መራጭ ህዝብ በነቂስ ወጥታችሁ ምርጫው ላይ የተሳተፋችሁ አካላት በሙሉ ከልብ የመነጨ ክብርና ምስጋና ይገባችሀል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፏል ።

‎ምርጫ በማንኛውም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ የሕዝብ ሉዓላዊ ፈቃድ የሚገለጽበት፣ የዜጎች እውነተኛ የፖለቲካ ተሳትፎ የሚረጋገጥበት እና የሀገር የጋራ ራዕይ፣ ዕድልና አቅጣጫ የሚወሰንበት ታላቅ ሀገራዊ ሂደት ነው።

‎ይህ ታላቅ ሂደት በሰላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ የተደረገው ጥረት የአንድ ተቋም ወይም የአንድ አካል ብቻ ድካም ውጤት አይደለም ይልቁንም የብዙኃኑ ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ልፋት፣ የማይናወጥ ትብብር እና የጋራ ቁርጠኝነት የታየበት ስኬት ነው።

‎የዘንድሮዉ የምርጫው ሂደት በሕግና በሥርዓት እንዲመራ፣ የመራጮች መብት እንዲከበር፣ የምርጫ ጣቢያዎች ፍጹም ሰላማዊ አገልግሎት እንዲሰጡና የሕዝቡ ንቁ ተሳትፎ በተሟላ ሁኔታ እንዲረጋገጥ ሌት ተቀን በትጋት ለደከሙ አካላት በሙሉ የላቀና ልዩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎‎በተጨማሪም በቅድመ-ምርጫ፣ በምርጫው ዕለትና በድህረ-ምርጫ ሂደቶች ሁሉ ሰላምና መረጋጋት ሳይናጋ እንዲቀጥል የዜጎች ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን እና የሕግ የበላይነት እንዲከበር የማይተካ ሚና ለተጫወቱት የጸጥታ ኃይሎቻችን የላቀ አክብሮትና ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

የመቻቻል ባህልን በማሳደግና የሰላም እሴቶችን በማክበር፣ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ብቻ ለተወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎችና ደጋፊዎቻቸው በሙሉ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ታላቅ አክብሮታቸውን ገልፀዋል።

‎የምርጫው ሂደት ግልጽና ታማኝ እንዲሆን የሕዝብ ዓይንና ጆሮ በመሆን ያገለገሉትን የሚዲያ ተቋማትና ጋዜጠኞች ያመሰገኑት ክብርት ነኢማ ሙኒር ሚዲያው እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን በወቅቱ በማድረስና ሂደቱን በኃላፊነት በመዘገብ ላሳዩት የላቀ ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

በተለይ የህብረተሰቡ ምሰሶ ለሆኑት የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ልዩ አክብሮታቸውን የገለጹት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ የሕዝብን አንድነት በማጥበቅና የምርጫው ሂደት በአዎንታዊ መንፈስ እንዲሳካ በማድረግ ረገድ ላበረከቱት የማይተካ አስተዋጽኦ ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉም ገልፀዋል ።

ከሁሉም በላይ የክብሩ መደብና የታሪኩ ባለቤት ለሆነው ለተከበረው የስልጤ ዞን ሕዝብ ልዩና የላቀ ምስጋና ያቀረቡት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ በምርጫው ዕለት የዜግነት ኃላፊነቱን ለመወጣት ካለሊቱ 11:30 ጀምሮ እስከ ምሽት 6:00 ድረስ ሳይሰለች፣ ብርድና ንፋስ፣ ፀሐይና ሙቀት እየተፈራረቁበት በሰላማዊና በሥርዓታማ ሰልፍ በመቆም፣ የዴሞክራሲ መብቱን በከፍተኛ ኃላፊነት በመጠቀም ለምርጫው ስኬት የላቀ ታሪክ የጻፈው ውዱ ሕዝባችን ከምንም በላይ ታላቅ ምስጋና እና ክብር ይገባዋል ብለዋል።

‎የሕዝባችን የማይናወጥ ሰላም ፍቅር፣ የጸና የአንድነት መንፈስ እና ልባዊ የሕግ አክባሪነት ለዚህ ታሪካዊ ስኬት ዋነኛውና የማይናጋው መሠረት ነው።

‎ይህ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁ የዞናችን ሕዝብ የዴሞክራሲ ባሕልን እያዳበረና እያጠናከረ መምጣቱን፣ ለዘላቂ ሰላም ያለውን ፍጹም ቁርጠኝነት እና ለሀገር ግንባታ ያለውን ንቁ ተሳትፎ በግልጽ ያሳየበት ታላቅ ማረጋገጫ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህንን ያገኘነውን በጎ ተሞክሮ እና መልካም ልምድ ይበልጥ በማስቀጠል ለላቀ ሰላም፣ ለተፋጠነ ልማትና ለአጠቃላይ ብልጽግና በጋራ እንደምንሠራ ያለን እምነት ፍጹም ጽኑ ነው።

በመጨረሻም ይህ 7ኛው አጠቃላይ ምርጫ በሙሉ ሰላምና በላቀ ስኬት እንዲጠናቀቅ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ አሻራችሁን ላሳረፋችሁ በሙሉ በድጋሚ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
በቀጣይም ለሕዝባችን ጽኑ ሰላም፣ ለዞናችን ሁለንተናዊ ዕድገት እና ለሀገራችን የጋራ ብልጽግና በትጋት በአንድነት እንድንቆም በፓርቲያችን ስም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብለዋል።
የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት

ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ መርጣለች! ሀገራችን ባከናወነችው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ረዣዥም የመራጮች ሰልፍ መስተዋሉ፣ ዜጎች በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ስለ...
03/06/2026

ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ መርጣለች!

ሀገራችን ባከናወነችው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ረዣዥም የመራጮች ሰልፍ መስተዋሉ፣ ዜጎች በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ስለመሆናቸው ጉልህ ማሳያ ነው።

የዕድሜ መግፋት ፣ የጤና ሁኔታ መታወክ፣ አራስነት፣ ከቤት መቆየትን የግድ ያለው አሰገዳጅ ክስተት ሳይበግራቸው ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው ይበጀኛል ያሉትን መርጠዋል።

አንድ ድምፅ ዋጋ እንዳለው በመረዳት ከሌሊት እስከ ሌሊት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

በምርጫው ዕለት የታዩ ረዣዥም የመራጮች ሰልፎች የሕዝብ የፖለቲካ ፍላጎት እና የዴሞክራሲ ተሳትፎ መጉላትን የሚያሳዩ ናቸው።

ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ መርጣለች ፤ የህዝብ ተሳትፎና የዲሞክራሲ ጉዞ​ምርጫ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታዋን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ታሪካዊ ፋይዳ አለው ።7ኛውን ...
02/06/2026

ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ መርጣለች ፤ የህዝብ ተሳትፎና የዲሞክራሲ ጉዞ

ምርጫ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታዋን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ታሪካዊ ፋይዳ አለው ።

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮች ማልደው ተነስተው በየምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት ቀጣይ እጣ ፈንታቸውን እና ሀገሪቱን ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት የሚመራውን መንግስት ለመምረጥ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመምረጥ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ምዝገባ ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን የድምፅ መስጠት ሂደቱ ላይም ሕዝቡ ያሳየው ተሳትፎ እጅግ ከፍተኛ እና ታሪካዊ ነበር።

​የዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገሪቱ የፖለቲካ እና የልማት ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ሲሆን፥ ህዝቡ በነፃነትና በንቃት በመሳተፍ የዜግነት ድርሻውን ተወጥቷል።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተስተዋለው የመራጮች ሰልፍ ህዝቡ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ያለውን ጽኑ ፍላጎት ያሳየበት ሆኗል። በተለይም የሴቶች፣ የወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች የመጀመሪያ ጊዜ መራጮች ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑ ተስተውሏል።

ይህ ምርጫ ከፖለቲካዊ ውሳኔነቱ ባሻገር በሀገሪቱ የኢኮኖሚ መረጋጋት፣ በማህበራዊ ልማትና በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ላይ ቀጣይነት ያለው እድገት ለማምጣት መሰረት የሚጥል ነው።

ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማካሄዷ በራሷ፥ የዲሞክራሲ ጉዞዋ ወደ ኋላ የማይመለስ መሆኑንና በትክክለኛ መስመር ላይ እየተጓዘች ለመሆኗ ትልቅ ማረጋገጫ ነው።

ድምጼ ለሀገሬ ትልቅ ፋይዳ አለው--የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ መሬጮች!የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ነዋሪዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በየምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተ...
02/06/2026

ድምጼ ለሀገሬ ትልቅ ፋይዳ አለው--የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ መሬጮች!

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ነዋሪዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በየምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የሚኖሩ መራጮች እንዳሉት፦የኔ ድምጽ የሀገር ዕጣ ፋንታን የሚወስን እና የሚሆነውን መንግስት ለመወሰን ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።

መራጮቹ አክለውም እንደገለጹት ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ምርጫ ወሳኝ በመሆኑ የአዘርነት በርበሬ ወረዳ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ለቀጣይ የሚመራቸውን መንግስት እንደመረጡ ነው የተናገሩት።

የምርጫ ሂደቱም ሰላማዊ፣ፍትሃዊና ፍጹም ዲሞክራሲ በሆነ መልኩ ሲካሄድ እንደዋለ በመግለጽ ማህበረሰቡም በወሰደው ካርድ ይበጀኛል ያለውን መንግስት እንደመረጠ ገልጸዋል።

ግንቦት 25/2018

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲን ወክለው በአዘርነት በርበሬ  ምርጫ ክልል እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ ረሻድ ከድር በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በመገኘት የምርጫ ድምጻቸውን ሰጡ።በአዘርነት በር...
01/06/2026

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲን ወክለው በአዘርነት በርበሬ ምርጫ ክልል እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ ረሻድ ከድር በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በመገኘት የምርጫ ድምጻቸውን ሰጡ።

በአዘርነት በርበሬ የምርጫ ክልል የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)ን በመወከል ለክልል ምክር ቤት ዕጩ ሆነው የቀረቡት አቶ ረሻድ ከድር በዛሬው ዕለት በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ቂልጦ01 የምርጫ ጣቢያ በመገኘት የምርጫ ድምጻቸውን ሰጥተዋል፡፡

ግንቦት 24/2018
---------------------------------------------------------

የአዘርነት በርበሬ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ቂልጦ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጽ ሰጡ!በስልጤ ዞን የአዘርነት በርበሬ ምርጫ ክልል የብልጽ...
01/06/2026

የአዘርነት በርበሬ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ቂልጦ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጽ ሰጡ!

በስልጤ ዞን የአዘርነት በርበሬ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ቂልጦ ምርጫ ጣቢያ ላይ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

የአዘርነት ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ዶ/ር ብሩክ ከዲር፣ የአዘርነት ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ወ/ሮ ታኢባ ኑሪ ፣ የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከይሬ ሀቢብ እንዲሁም የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ የሆኑት አቶ ሙዲን ሙዘሚል በቂልጦ ምርጫ ጣቢያ ላይ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

ሀገራችንን ኢትዮጵያ ቀጣይ አምስት አመት የሚመራትን መንግስት በወሰዱት ካርድ ይበጃል ያሉትን መንግስት መምረጣቸውን ገልጸዋል።

ግንቦት 24/2018

ኢትዮጵያ እየመረጠች ትገኛለች!የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ማህበረሰብ ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ በነቂስ ወጥቶ በየምርጫ ጣቢያው ላይ በመገኘት ድምጻቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።በስልጤ ዞን የም...
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ትገኛለች!

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ማህበረሰብ ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ በነቂስ ወጥቶ በየምርጫ ጣቢያው ላይ በመገኘት ድምጻቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ማህበረሰብ በአዘርነት በርበሬ ምርጫ ክልል፥ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ በመገኘት ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ድምጻቸውን በመስጠት ላይ ናቸው።

በ7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ላይ ማህበረሰቡ የሚሆነውን መንግስት በካርዱ ድምጽ በመስጠት አሸራውን እያሳረፈ ሲሆን በምርጫ ክልሉ በየ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የምርጫ አሰጣጥ ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ ነው።

ግንቦት 24/2018

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለቀጣይ አምሰት ዓመት ይበጀናል ያሰተዳድረናል ያሉትን ፓርቲ እየመረጡ  ሰለመሆናቸው በሰልጤ ዞን ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የቂልጦ ከተማ መራጮች ገለፁ።መራጮቹ ረጃ...
01/06/2026

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለቀጣይ አምሰት ዓመት ይበጀናል ያሰተዳድረናል ያሉትን ፓርቲ እየመረጡ ሰለመሆናቸው በሰልጤ ዞን ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የቂልጦ ከተማ መራጮች ገለፁ።

መራጮቹ ረጃጅም ሰልፎችን ጠብቀው በታሪካዊው ምርጫ ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በድምጻችን ብቻ የሀገራችንን የዲሞክራሲ ስርዓት ልምምድ እናጠነክራለን ያሉት መረጮቹ ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤት ዕጩዎችን አየመረጡ መሆናቸውን አሰታወቀዋል።

በአዘርነት ምርጫ ክልል ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ቂልጦ ምረጫ ጣቢያ ለክልል ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲን ወክለው ድምጻቸውን የሰጡት ወ/ሮ ታኢባ ኑሪ ምርጫ ህዝብ በካርዱ ይሆነኛል ያለውን ፓርቲ የሚመርጥበት ነው ብለዋል።

አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሰለመሆኑ አሰረድተዋል።

ሌላኛው በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ሆነው የቀረቡት የኢፈድሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይርክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከፍተኛ ህዝብ የተሳተፈበት ሰለመሆኑ ጠቁመው ኢትዮጲያ የዲሞክራሲ ሰርዓት ልምምድ ላይ ነች ብለውል።

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ድምፅ ሰጡ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ድምፃቸውን ሰተዋል። ኢትዮጵያ እየመረጠች ...
01/06/2026

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ድምፅ ሰጡ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ድምፃቸውን ሰተዋል።

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ማህበረሰብ በነቂስ ወጥቶ በምርጫ ጣቢያዎች ላይ በመገኘት ድምጹን እየሰጠ ይገኛል።በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ማህበረሰብ በአዘርነት በርበሬ ...
01/06/2026

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ማህበረሰብ በነቂስ ወጥቶ በምርጫ ጣቢያዎች ላይ በመገኘት ድምጹን እየሰጠ ይገኛል።

በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ማህበረሰብ በአዘርነት በርበሬ ምርጫ ክልል፥ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ በመገኘት ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ድምጹን በመስጠት ላይ ይገኛል።

ማህበረሰቡ የሚሆነውን መንግስት በካርዱ ድምጽ በመስጠት አሸራውን እያሳረፈ ሲሆን በምርጫ ክልሉ በየ ምርጫ ጣቢያዎች ቦታ ላይ የምርጫ አሰጣጥ ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ ነው።

ግንቦት 24/2018

Address

Worabe
Hossana

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት /East Azernet Berbere PP posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share