ሀዲያ ዞን ብልፅግና ፓርቲ - Hadiya zone prosperity

ሀዲያ ዞን ብልፅግና ፓርቲ - Hadiya zone prosperity Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሀዲያ ዞን ብልፅግና ፓርቲ - Hadiya zone prosperity, Political Party, Hossana.

ለ6ኛው ሀገር አቀፍ የሀይማኖት ተቋማት የሰላም ኮንፈረንስ መሳካት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የሀዲያ ዞን እና የሆሳዕና ከተማ የወጣት አደረጃጀቶች ለኮንፍረንሱ እያደረጉት ያለ ዝግጅት በምስ...
10/02/2026

ለ6ኛው ሀገር አቀፍ የሀይማኖት ተቋማት የሰላም ኮንፈረንስ መሳካት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የሀዲያ ዞን እና የሆሳዕና ከተማ የወጣት አደረጃጀቶች ለኮንፍረንሱ እያደረጉት ያለ ዝግጅት በምስል ፦

ለ6ኛው ሀገር አቀፍ የሀይማኖት ተቋማት የሰላም ኮንፈረንስ መሳካት  የወጣት አደረጃጀቶች ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።(ሆሳዕና፣ የካቲት 03/2018) 6ኛው ሀገር አቀፍ የሀይማኖት ተቋማት የሰ...
10/02/2026

ለ6ኛው ሀገር አቀፍ የሀይማኖት ተቋማት የሰላም ኮንፈረንስ መሳካት የወጣት አደረጃጀቶች ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።

(ሆሳዕና፣ የካቲት 03/2018) 6ኛው ሀገር አቀፍ የሀይማኖት ተቋማት የሰላም ኮንፈረንስ "ሀይማኖቶች ለሰላም፣ ለአብሮነት እና አንድነት" በሚል መሪ ቃል ከነገ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሆሳዕና ከተማ ይካሄዳል።

ሁነቱን አስመልክቶ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የሀድያ ዞንና የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ወጣት አደረጃጀቶች በሆሳዕና ከተማ የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኘው የክልሉ ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወጣት አብዱ ድንቁ እንደተናገረው ሰላም ለወጣቱ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ወሳኝ በመሆኑ በዘላቂ ሰላም ግንባታ ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል።

የክልሉ ወጣቶች ከክልሉ መንግስት ጋር ለሰላም በጋራ በመቆማቸው በተፈጠረው አዎንታዊ ሰላም የክልሉ ከተሞች የኮንፈረንስ ማዕከላት፣ የቱሪዝም መዳረሻና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እየሆኑ መምጣታቸውን አመላክቷል።

የክልሉ ወጣት አደረጃጀቶችም በ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ቀን በዓል ያሳዩትን ተምሳሌዊ ተግባር በ6ኛው ሀገር አቀፍ የሀይማኖት ተቋማት የሰላም ኮንፈረንስም በተለመደው እንግዳ አቀባበል እንዲደግሙት ወጣት አብዱ አሳስቧል።

በሰላም ኮንፍረንሱ ከ200 በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንደሚሳተፉ የጠቆመው ወጣት አብዱ በአዳራሽና በአደባባይ የሚካሄደውን መርሃ-ግብር እንዲያስተባብሩ የሥራ መመሪያም ተሰጥቷቸዋል ብሏል።

ከሰላም ኮንፍረንሱ ጋር በተያያዘም ወጣቶች በደም ልገሳ፣ በከተማ ጽዳትና በተለያዩ በጎ ፈቃድ ተግባራት እየተሳተፉ መሆኑን የፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቱ ጠቁሟል።

6ኛውን ሀገር አቀፍ የሀይማኖት ተቋማት የሰላም ኮንፈረንስ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር አዘጋጅታውታል።

ምንጭ - Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau

10/02/2026
 !!Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና
10/02/2026

!!

Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና

09/02/2026
ክልሉን የኢንቬስትመንት የስበት ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ሆሳዕና፣የካቲት2/2018) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮ...
09/02/2026

ክልሉን የኢንቬስትመንት የስበት ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና፣የካቲት2/2018) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄና ፎረም በቡታጅራ ከተማ ተካሂዷል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት ክልሉን የኢንቬስትመንት የስበት ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

በሚቀጥሉት ተከታታይ አመታት በተቀመጠው የፖሊሲ ማሻሻያ ላይ በመመስረት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን እውን ለማድረግ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪውን ስኬታማ ለማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥን ማቀላጠፍ እና ምቹ የኢንቬስትመንት አካባቢ መፍጠር ተገቢ ነው ብለዋል።

በክልሉ ባለሀብቶች ለኢንቬስትመንት የተረከቡትን መሬት ወደ ልማት እንዲያስገቡ መስራት ይገባል ብለዋል።

ሰፋፊ ኢንቬስትመንቶችን ማሰብ እና ወደ ተግባር ማስገባት አስፈላጊ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

ባለሀብቱ የሚያነሳቸውን ማነቆዎች ቆጥሮ መፍታት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።

ባለሀብቱ ለሚያቀርባቸው የሀይል ፣የብድር፣፣የመንገድ ፣የቴሌኮም ፣የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት ተገቢ ነው ብለዋል።

የሚመለከታቸው ተቋማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ በስራ መመሪያቸው አመላክተዋል።

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት የበርካታ ዜጎችን ህይወት መለወጥ ይገባል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢንዱስትሪና ከተማ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል በበኩላቸው ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ማነቆ የሆኑ ጉዳዮችን በመፈተሽ መፍታት ይገባል ብለዋል።

ክልሉን የኢንቬስትመንት ማዕከል ለማድረግ ከይገባኛል ነጻ የሆነ የኢንዱስትሪ ዞን የመሬት አቅርቦት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ለኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጉልህ ድርሻ እንዳለውም አቶ ስንታየሁ ጠቅሰዋል።

መሬት ወስደው ወደ ልማት ያልገቡ ባለሀብቶችን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑም ኃላፊው ጠቁመዋል።

ምንጭ - Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau

በሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2018 ዓ.ም የ6 ወር የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የብልጽግና ህ...
09/02/2026

በሀዲያ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2018 ዓ.ም የ6 ወር የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የብልጽግና ህብረት አመራሮች ምዘና ተካሄደ፤

ሆሳዕና፡ የካቲት 2/2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2018 ዓ.ም የ6 ወር የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የብልጽግና ህብረት አመራሮች ምዘና ተካሄዷል።

የግምገማውና የምዘናው አላማም በየሴክተሩ የተሰሩ ጠንካራ ስራዎች ለማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም ለተሻለ ውጤት ጠንክሮ ለመስራት እንዲሁም የአባላትን ቁመና በመፈተሽ በቀጣይ በሚሰሩ በመንግስትና በፓርቲ ስራዎች ወጥ አረዳድና አመለካከት በመያዝ ለሁለንተናዊ ብልጽግና የበለጠ ለመትጋትና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መድረኮቹ ተጠናቀዋል።

መንግስት ለግሉ ዘርፍ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የአምራች ኢንዱስትሪውን ማነቃቃት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተመላከተ (ሆሳዕና፣የካቲት2/2018) ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ...
09/02/2026

መንግስት ለግሉ ዘርፍ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የአምራች ኢንዱስትሪውን ማነቃቃት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተመላከተ

(ሆሳዕና፣የካቲት2/2018) ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በተገኙበት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄና ፎረም በቡታጅራ ከተማ እየተካሔደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንቬስትመንት እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አባስ መሐመድ (ዶ/ር )"አምራች ኢንዱስትሪ የሉአላዊነት እና የብልጽግና መሰረት "በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሔደ ባለው የምክክር መድረክ ላይ እንደገለጹት
መንግስት ለግሉ ዘርፍ አስቻይ ሁኔታዎችን በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲጎለብት እየሰራ ነው ብለዋል።

ፖሊሲና ህግ ከማመቻቸት በተጨማሪ የህዝብ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ መስኮች ላይ ኢንቬስት በማድረግ ዋና ዋና የመሰረተ ልማቶችን በማረጋገጥ ረገድ የመሪነት ሚናውን እየተወጣ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

መንግስት ለግሉ ዘርፍ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ነው ያሉት ዶ/ር አባስ በተለይ አምራች ኢንዱስትሪውን ለማነቃቃት እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑንም ኃላፊው በአብነት ጠቅሰዋል።

አዲሱ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እንዲሁም በኢነርጂ አቅርቦት ላይ እየተደረገ ያለው ጥረት ተስፋ ሰጪ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

የግሉ ዘርፍ ይህን መልካም እድል ተጠቅሞ ከተለመደው አዝጋሚ ጉዞ በመላቀቅ በቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ በማተኮር በፍጥነት፣በጥራት እና በብዛት በማምረት በገበያው ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል።

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና መጀመሩ ብሎም ለአለም የንግድ ድርጅት አባልነት እየተቃረብን መሆኑን ተከትሎ ይህ አዲሱ የንግድ ከባቢ መጻኢ እድል መልካም አጋጣሚ ስለመሆኑም ኃላፊው አመላክተዋል።

ክልሉ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የበርካታ ጸጋዎች ባለቤት ነው ያሉት ዶ/ር አባስ በዘርፉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ተናግረዋል።

አምራች ኢንዱስትሪው የሁሉም ልማት መሰረት ነው ያሉት ኃላፊው የግብርና የግብአት እና የቴክኖሎጂ ምንጭ መሆኑንም አብራርተዋል።

የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ካላደገ ሉአላዊነት ፣ዘላቂ ብልጽግና እንዲሁም ኑሮን ማዘመን አይታሰብም ሲሉም ኃላፊው በንግግራቸው ጠቅሰዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ለቴክኖሎጂ ሽግግር ወሳኝ ነው ብለዋል።

የስራ እድል ፈጠራ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጥራት ያለው የስራ እድል ተጠቃሚነት እየጎለበተ መምጣቱንም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

የውጭ ቀጥታ ኢንቬስትመንት በመሳብ ረገድ ክልሉ በለውጥ ጎዳና ላይ ስለመሆኑ በአብነት የጠቀሱት ሚኒስትሩ ይህም ለኤክስፖርት እና ለሀገር ውስጥ ምርት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስረድተዋል።

በቡኢ ከተማ አስተዳደር በ5 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ግንባታው እየተካሔደ የሚገኘውን የብሉ ኤለፋንት ፋይበር ቦርድ ካምፓኒ በክልሉ የፈርኒቸር ኢንዲስትሪዎች እንዲስፋፋ ያደርጋል ሲሉም ጠቁመዋል።

የኢንቬስትመንት ፕሮጀክቱ እውን የሆነው ክልሉ የበርካታ ጸጋዎች ባለቤት በመሆኑ እና ለግሉ ዘርፍ የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት በመቻሉ ነው ብለዋል።

ለኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ዘላቂ ሰላም እና የመሰረተ ልማት ተደራሽነት ነው ያሉት ሚኒስትሩ በክልሉ ለአምራች ኢንዱስትሪው የመሬት አቅርቦት ማመቻቸት መቻሉን ሚኒስትሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

በግብርና ዘርፍ የተጀመረው ልማት ለኢንዱስትሪ ግብአት አቅርቦት ወሳኝ ስለመሆኑም አመላክተዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በበኩላቸው መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲነቃቃ ዘርፈ ብዙ ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል።

በዞኑ 19 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸውን ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል።

በዞኑ 15ሺ 794 ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ሲሉም ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል።
Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau

የሀዲያ ዞን የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2018 ዓ.ም የ6 ወር የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የብልጽግና ህብረት አመራሮች ምዘና ተካሄደ፤ሆሳዕና፡ የካቲት 2/2018 ዓ.ም...
09/02/2026

የሀዲያ ዞን የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2018 ዓ.ም የ6 ወር የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የብልጽግና ህብረት አመራሮች ምዘና ተካሄደ፤

ሆሳዕና፡ የካቲት 2/2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2018 ዓ.ም የ6 ወር የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የብልጽግና ህብረት አመራሮች ምዘና ተካሄዷል።

የግምገማውና የምዘናው አላማም በየሴክተሩ የተሰሩ ጠንካራ ስራዎች ለማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም ለተሻለ ውጤት ጠንክሮ ለመስራት እንዲሁም የአመራሩን ቁመና በመፈተሽ በቀጣይ በሚሰሩ በመንግስትና በፓርቲ ስራዎች ወጥ አረዳድና አመለካከት በመያዝ ለሁለንተናዊ ብልጽግና የበለጠ ለመትጋትና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የጋራ መግባባት ላይ ተደረሶ መድረኩ ተጠናቋል።

የሀዲያ ዞን የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2018 ዓ.ም የ6 ወር የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የአባላት ምዘና ተካሄደ፤ሆሳዕና፡ የካቲት 2/2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵ...
09/02/2026

የሀዲያ ዞን የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2018 ዓ.ም የ6 ወር የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የአባላት ምዘና ተካሄደ፤

ሆሳዕና፡ የካቲት 2/2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን የዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2018 ዓ.ም የ6 ወር የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የአባላት ምዘና ተካሄዷል።

የግምገማውና የምዘናው አላማም በየሴክተሩ የተሰሩ ጠንካራ ስራዎች ለማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም ለተሻለ ውጤት ጠንክሮ ለመስራት እንዲሁም የአባላትን ቁመና በመፈተሽ በቀጣይ በሚሰሩ በመንግስትና በፓርቲ ስራዎች ወጥ አረዳድና አመለካከት በመያዝ ለሁለንተናዊ ብልጽግና የበለጠ ለመትጋትና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መድረኮቹ ተጠናቀዋል።

Address

Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሀዲያ ዞን ብልፅግና ፓርቲ - Hadiya zone prosperity posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share