08/05/2026
ሕግ በያዘዉ ጉዳይ ሕዝብ አይዳኝም! የክስ ሂደትንም ሆነ ፍርድን ያለፍ/ቤት ትዕዛዝ መግለጽ አይቻልም!
(ጨርሰዉ ሳያነሱ አስተያየት አይስጡ!)
ከወራት በፊት ወ/ሮ በረከት ወርቁ (ገበሬዋ) በሕገወጥ የሰዎች ዝዉዉር፤ ሐሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀት፤ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ተቋምን እንዲሁም የአገር መከላከያ ሠራዊትን መታወቂያ አዘጋጅታ በመገልገልና ሌሎችም ወንጀሎች በቁጥጥር ስር ዉላ በእስር ቆይታ በዋስትና መለቀቋ ይታወቃል። በዚያም ዋስትና ተፈቅዶ ከዉጭ ሆና እንድትከታተል በመደረጉ እንኳን ለቤትሽ አበቃሽ ብለን ብላችሁም ነበር።
በሂደት ጉዳዩ ከሌሎች ጋር በግብረ አበርነት የተፈጸሙ ከባባድና አገርን የሚጎዱ ወንጀሎች በመሆናቸዉ ክስ ቀርቦባት ከሰሞኑን ፍ/ቤት ስትጠራ ይህኑ በተመለከተ ትላንት ህዝብ ይስማልኝ ስትል መልክት አስተላልፋለች።
እንዲህ ባሉ ጉዳዮች ጥንቃቄ እያደረገች አይመስልም። ክስ አቅራቢዉን አካል ወይም መንግስትን መወንጀል ተገቢ አይደለም። ለምን በዋስ ተለቀኩም ይመስላል። በመንግስት በፀጥታና በፍትህ ተቋማት ዜጎች እምነት እንዳይኖራቸዉ ከሚያደርግ ንግግር መቆጠብ ተገቢ ይሆናል። ሕግ በያዘዉ ጉዳይ ሕዝብ አይዳኝም። ይሄ በራሱ ወንጀል ነዉ። ፀልዩልኝ ማለት አንድ ነገር ነዉ። ከወንጀሌ ጎን ቁሙ ማለት ግን ተገቢ አይደለም። ሕግ ትክክል የማይሆነዉ በግል ተጠያቂ ሲኮን አደለም።
ማንም ሰዉ በዋስ የሚወጣዉ ማስረጃ እንዲያጠፋ፤ የፍትህ ሥርዓቱን እንዲያቀል ሳይሆን ጉዳዩን ጥፋተኛ መሆኑ ሳይረጋገጥ በእስር ላይ ከሚቆይ ዉጭ ሆኖ እንዲከታተል ለማድረግ ነዉ።
በሚዲያ ላይ የክስ ሂደትንም ሆነ ፍርድን ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ መግለጽ አይቻልም። በግልጽ ሂደቱንም ሆነ ፍርዱን በሚዲያ እንዲተላለፍ ትዕዛዝ ካልሰጠ በቀር ፖሊስም ሆነ አንዱ ወገን አይችልም። ፍርድ ተሰጥቶ ቢሆን እንኳ ፍ/ቤት በሚዲያ ይተላለፍ ብሎ ካላዘዘ አይቻልም! በፖሊስ በኩል ሌላም ጊዜያት በተግባር የሚታየዉ ግን ለየቅል ነዉ። ለተከሳሹም ይሆናል። (የሕጉን ድንጋጌ ከታች ይመልከቱ)
ይህ እንዳለ ሆኖ በዋስትና ከተወጣ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ጉዳዩን እንደ ማንኛዉም ዜጋ በመከታተል ፈንታ "በእስር በነበረችበት ጊዜ በጤናዋ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል። ከደም መርጋት ጋር የተያያዘና ለህይወቷም አስጊ ነው ዉጭ ሄዳ መታከም አለባት ተብሏል።" ሲሉ
ባንዳንድ ሚዲያዎች ፎቶ እንዲሰራጭና እንዲነገርላት በማድረግ በዚህም በዋስ ዉጭ ሆና እንድትከታተል ከተደረገዉ ወንጀል ተጠያቂነት ለማስቀረት የተደረገ መሆኑን የሚመለከታቸዉ በመረዳታቸዉ ሕክምና በሚል ከአገር የማምለጥ ፕሮግራሙ ሳይሆን ቀረ! ጤናዋም በዛዉ ተመለሰላት። እኛም ይህኑ ጠቅሰን ተናግረን ነበር።
ሌላዉ ከመጸለይ ጉዳዩን የሕዝብ አንደምታ ለመፍጠር መሞከርም ተገቢ አይደለም። ሐሰተኛ የአገር ደህንነትና የአገር መከላከያ ሠራዊት መታወቂያ አበጅቶ መገልገል በራሱ ለዚሁ ማሕበረሰብ ይሄንኑ ሕዝብ ለማስፈራራት፤ ከዚሁ ሕዝብ አላግባብ ተጠቃሚ ለመሆን የተሞከረ ከመሆን በዘለለ ምን ዓላማ ይኖረዋል? ታዲያ መልሶ ይሄን ሕዝብ ድረሱ እወቁልኝ ማለት ምን ማለት ነዉ?
መደገፍ በጌታ እንጂ በጌታ ነኝ እያሉ ባለስልጣናት ስር በመሸጎጥ በግለሰቦች ተቀባይነት ለማግኘት በጌታ ነኝ እየተባለ ኢሬቻና ሌላ ኃይማኖት የባዕድ አምልኮ በዓል ዋነኛ ካዳሚ ከመሆንና ስርዓት ከመፈጸም ኢየሱስ ላይ መደገፍ ነበር። እዚ ዉስጥም መግባት አይኖርም ነበር! ኢየሱስ የነፍስ ብቻ ሳይሆን የስጋም ነዉ! እንዲ ካለ ስጋትና ጥፋት ታዳጊ ነዉ። አሁንም ወደ እርሱ እንጂ ወደ ህዝብ ይቅርብሽ በሏት!
አገሬን ብዬ መጥቼም አይባልም። ከኔ በፊትም በኋላም አገሪቱ ሰዉ የላትም አልነበራትም እንደማለትም ነዉ። ከኔ በፊት ሰዉ አልነበረም ይመስል ሕዝባዊ ለማድረግ መሞከርም ተገቢ አደለም።
ሰው ሀገር ለፍቼ ያመጣሁትን.. በማለትም ሁሉም አገር ሰዉ ያለበት እንጂ እዚ ያለዉ እንስሳ ወይም ግዑዝ ነዉ ማለት እንዳይመስል መጠንቀቅና ወደ አገር የሚመጡ ሌሎች ዳያስፖራዉንም በአገሪቷ እንቅስቃሴ እንዳያረጉ መቀስቀስም እንዳይሆንባት ለምትናገረዉ በማስተዋል ቢሆን መልካም ነዉ።
ሲጀምር ሰዉየዉ (ጠቅላዩ) የበለጠ እንዳይሰራ ከዚያ ከዚህ ከተለያየ በኩል ካሉት ጥቃቅን ችግር ፈጣሪዎች የተለያዩ አካላትና ግለሰቦች በላይ እዚሁ በጉያዉ ያሉቱ ደጋፊና ወዳጅ መስለዉ የሚነግዱት ከተለዩት የአገሪቱ ጠላቶች የከፉ ናቸዉ።
ዉስጥ ያሉት ከነኛ ይከፋሉ። አጋጣሚን እየተጠቀሙ ያለ ጥይት ከተማን የሚያጮሁ፤ ሕዝቡን በኢኮኖሚ የሚጎዱና የሚያጯጩኹ የዉስጥ ሽብርተኞች ናቸዉ።
አገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንድትጎዳ መንግስት አልቻለም እንዲባል እያመቻቹ ካሉት ዋነኞቹ ከዉስጥ እንዲህ ያሉ ዉንብድና እየፈጸሙ ያሉቱ ናቸዉ። ሕዝብን የማደህየት እንጂ እነሱማ ምርጫ አላቸዉ።
ስለዚህ ይቺን በረከት ወርቁ የተባለች እህትን ከሰሞኑን ክስ መቅረቡን ተከትሎ ጥፋት የለኝም ካለች አለ ካለዉ አካል ጋር እዛዉ በአግባብ መከታተል እንጂ ዋስትናዋን ከልክለዉ መልሰዉ ወደ እስር ቤት እንዳያስገቧትና ወደ ሌላ ተጨማሪ ወንጀል እንዳትገባ ጥንቃቄ እንድታደርግ ምከሯት!
የፍርድ ሂደትን፤ በቀጠሮ ላይ ያለ ጉዳይን መግለጽ.. በራሱ ወንጀል ነዉ። ከፍርድ በኋላም ሚዲያ ላይ ያለ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ በፎቶም ሆነ በጽሑፍ መግለጽ ይህም ወንጀል ነዉ። (የሕጉን ድንጋጌና ክልከላዎች በተግባር ካለዉጋ ለግንዛቤም ከታች አስቀምጠናል ይመልከቱ)
ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ደሞ እንዲህ ባሉ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር እየተለጠፉ በሚመዘብሩ ግለሰቦች ላይ መንግስት በሚወስዳቸዉ እርምጃዎች እንደ አገር እንደ ሕዝብ ከጎኑ በመቆም አብረዉ ሊያግዙት በጋራ የመጠበቅ ኃላፊነት የራሱም ነዉ። ከራስ ፈቃድ ባለፈ በሕግም አስገዳጅ ነዉ። ከሚጎዱት ሳይሆን ከእዉነት ጋር መተባበር አገርን ራስን መጠበቅ ኃጢአት አደለም!! በቀጣይም እንዲህ ባሉት ላይ በመላ አገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ባለሥልጣናትና መሰል ግንኙነት ፈጥረዉ በሚመዘብሩት ላይ መንግስት በሚወስደዉ እርምጃዎች ከጎኑ መቆም አግባብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። ሻሎም!
የአርቲስት ገነት ንጋቱን ክስ በተመለከተ በካዉንስሉ በኩል ስለሆነዉና በዚህ ላይ ስለጠቅላላዉ ጉዳይ መረጃዉን ይዘናል። ይጠብቁን!