የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Hosanna
  • የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በስልጤ አለም ገበያ

የተወደዳችሁና እጅግ የተከበራችሁ ልማት ወዳድ የራግዲና ማዞሪያ ከተማ ባለሀብቶች ፣ ወጣቶች ፣ሴቶች ፣ ሺማግሌዎች ፣የግንበታ ተቋራጮች ፣አንደንድ ከከተማዋ ውጭ የሆኑ በወረዳው የተለያዩ ቀበሌ...
26/09/2023

የተወደዳችሁና እጅግ የተከበራችሁ ልማት ወዳድ የራግዲና ማዞሪያ ከተማ ባለሀብቶች ፣ ወጣቶች ፣ሴቶች ፣ ሺማግሌዎች ፣የግንበታ ተቋራጮች ፣አንደንድ ከከተማዋ ውጭ የሆኑ በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ ባለሀብቶች ፣የህብረተሰብ ተሳትፎ አስተባባሪ ኮሚቴዎች እና መለው የከተማው ነዋሪዎች ለከተማዋ ልማት እንደ አቅማቹ መጣን በወጣቹት ብር የጠየቃቹትን ፈጽመናል ለሌላ ልማት ተዘጋጁ እንኳን ደስ አለቹ !!!
ከተማችን የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎችን በማጠናከር ዘላቂ የሆነ ዕድገቷን ተረጋግጣለች !!!
ከተሞች የወረዳችን ኢኮኖሚ ዋና መናህሪያ በመሆናቸው እድገታቸው በተባለው ልክ ሊረጋገጥ ወይም ሊሳካ የሚችለው በመንግስት ጥረት ብቻ አለመሆኑ ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡
በመሆኑም የከተማችን እድገት ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማረጋገጥ የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎችን በማጠናከር ህብረተሰቡን የልማቱ አካል ከማድረግ ባለፈ ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ተከታታይነት ያላቸው ስራዎችን በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡
ነዋሪዎች በከተማችን የሚያነሷቸውን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው እያሰሩ ነው !!!በ2014ዓ/ም ከህብረተሰቡ የተሰበሰበው ብር ለከተማው የውሃ ተቋም የትራንስፎርመር ግዢ እንዲውል ህብረተሰቡ በመስማማቱ የትራንስፎርመር ፣የመስመር ዝርጋታ እና የቆጦሪ ክፊያ የተከፈለ ብሆንም መብራት ሀይል እንደ ሀገር ገጠመኝ በለው የትራንስፎርመር እጥረት የተነሳ ሰይመጣ በመቆየቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ መቆየቱ ይተወቃል ።ይህንን ችግር ለመፍታት የሳንኩራ ወረዳ አስተዳደር ፣የወረደው ፓርቲ እናት የአስተዳደር ጽ/ቤት የኢትዮጵያ መብራት ሀይል ሆሳዕና ዲስትሪክት እና ሀዋሳ ቅርንጫፍ ድረስ በመንቀሳቀስ ችግሩ እንዲፈታ በማድረጋቸው ዞሬ ችግሩ ተቀርፎ የተጠየቀው አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መግኛት ተችሏል ።ለዚህ ምስጋናችን የላቀ ነው ።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለቹ እንኳን ደስ አለን !!!

የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ዓመታዊ የማትጊያ መርሃ ግብር አካሄደ።*************************የመምሪያው ባለሙያዎችና የስራ ሀላፊዎች በጦራ ከተማ አስተዳደር ...
26/08/2023

የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ዓመታዊ የማትጊያ መርሃ ግብር አካሄደ።
*************************

የመምሪያው ባለሙያዎችና የስራ ሀላፊዎች በጦራ ከተማ አስተዳደር ችግኝ በመትከልና ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የጦራ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ጎብኝተዋል።

ነሃሴ 20/2015/የስልጤ ዞን ኮሙዩኒኬሽን-ወራቤ።
…………………………………………

መምሪያው በ2015 የስራ ዘመን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ባለሙያዎችና አስተባባሪዎች በመልታሜ ሎጅ የማትጊያ መርሃ-ግብር በድምቀት አካሄዷል።

የማትጊያው የምልመላ መስፈርቶች እና ቀጣይ ፈጻሚው ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ በመምሪያው ቤቶችና ልማት አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊና የምልመላ ኮሚቴ አባል በሆኑት በአቶ ዳሪ ከድርና
የመምሪያው ከተሞች ፕላንና አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊና የምልመላ ኮሚቴ አባል በሆኑት አቶ አብድልመናን ሀጂ ሀሰን አጠር ያለ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በእለቱ በተዘጋጀው የማትጊያ መርሃ-ግብር ላይ የስራ ሂደቶች፣ ፈጻሚዎች፣ ሴቶችና ልዩ ተሸላሚዎች በሰባት ዘርፎች ለፈጸሟቸው ተግባራት የተዘጋጀላቸውን የማበረታቻ ሽልማት ተቀብለዋል ።

በማትጊያና እውቅና አሰጣጣጥ መርሃ ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ዳኒኤል ድሌ ተቋሙ በ2015 አመት በርካታ የልማት ስራዎችን ያከናወነበት እንደርበር ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ የልማቱ አጋዥ እንዲሆን በተደረገው ጥረት 52 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንና በዚህም በዞኑ የሚገኙ ከተሞች ለከተማነት የሚያስፈልጓቸውን መሰረተ ልማቶች ማለትም የማብራት ዝርጋታ፣ የኮብልእስቶን ንጣፍ፣ የመንገድ ከፈታ፣ የዲች ግንባታ ስራዎች ማከናወን መቻሉንም ዋና ሀላፊው ገልጸዋል።

ቀደም ሲል በክልል ደረጃ ይዘጋጅ የነበረው የከተሞችን የ10 አመት እስትራቴጂክ ፕላን በመምሪያው ባለሙያዎች በጥራት ማዘጋጀት የተጀመረበት፣ በሁሉም ዘርፍ 1ሺህ 2 መቶ ኢንቨስተሮች ወደ ዞኑ መሳብ እንደተቻለና ከ3 መቶ 33 ሄክታር በላይ መሬት ለተለያዩ አገልግሎቶች ተላልፎ የተሰጠበት እንዲሁም በህገ-ወጥ መንገድ የተያዘ 1 መቶ 35 ሄክታር መሬት የማስመለስ ስራ የተሰራበት ልዩ አመት ነው ሲሉም አቶ ዳንኤል ተናግረዋል።

የአንድ ተቋም ውጤት የግለሰቦች ያጋራ ጥረትና ትጋት ውጤት ነው ያሉት አቶ ዳኒኤል መምሪያው በ2015 ላሳካቸው ሁለንተናዊ ግቦች ሁሉም ሰራተኞች ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡

ፈጻሚዎች በቀጣይም ይበልጥ የሀሳብና የተግባር አንድነት ፈጥረው ተቋሙን ወደ ላቀ አፈጻጸም ለማሻገር መረባረብ ይጠበቅባቸዋል ሲሉም ሀላፊው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በእለቱ ሽልማት የተበረከተላቸው ባለሙያዎችም ለዞኑ ኮሙዩኒኬሽን በሰጡት አስተያየት የተቋሙን እስትራቴጂክ እቅዶች ተከትለው የአመቱን ተግባር መፈጸማቸውን ገልጸው ላከናወኑት ተግባር በዚህ መልኩ እውቅና መሰጠቱ ቀጣይ የተሻለ አቅደው ለመፈጸም የሚያነሳሳ እንደሆነ ተናግረዋል።
ዜናው የስልጤ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን መምሪያ ነው

በመኖሪያ ህብረት ስራ ማህበር  ለተደራጁ 06  ማህበራት መሬት የማስተላለፍ ሥራ ተካሄደ!በስልጤ ዞን በሳንኩራ ወረዳ በመኖሪያ ህብረት ስራ ማህበር  ለተደራጁ የመምህራንና ከመከላከያ በክብር ...
07/08/2023

በመኖሪያ ህብረት ስራ ማህበር ለተደራጁ 06 ማህበራት መሬት የማስተላለፍ ሥራ ተካሄደ!

በስልጤ ዞን በሳንኩራ ወረዳ በመኖሪያ ህብረት ስራ ማህበር ለተደራጁ የመምህራንና ከመከላከያ በክብር ሽኝት ለተደረገላቸው 06 ማህበራት መሬት ማስተላለፉን የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት አስታወቀ!!

ዓ/ገበያ፣ነሃሴ1/2015- ሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

በርክክቡ ስነስርዓቱ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ በድሩ ሰንገሮ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የወረዳው አስተዳደር ሁሉንም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በእቅድ እየተንቀሳቀ መሆኑን ተናግረዋል።

ዛሬ ርክክብ እያደረግን ያለነው የማህበራት የመሬት ጥያቄ የወረዳው የረዥም ጊዜ ጥያቄ እንደነበር ገልጸው በማህበር ተደራጅታችሁ ዛሬ መሬት እየወሰዳችሁ ያላችሁ መምህራንና ከመከላከያ በክብር የተሸኙ አባላት እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አያይዘው ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በረግዲና ማዞሪያ ከተማ መሬት የተቀበሉ ማህበራት በርካታ ሂደቶችን አልፎ የማጥራት ሥራ ተሰርቶ በካቢኔ ውሳኔ ካገኘ በኋላ እየተሰጠ ያለ መሆኑን አንስተዋል።

በእስካሁኑ በነበረው ሂደት በወረዳው መንግስት በኩል በርካታ ስራዎች ተሰርቷል ያሉት አስተዳዳሪው ዛሬ መሬት የተላለፈላቸው የማህበር አባላት ፈጥነው ወደ ማልማት መግባት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

በሌላበኩል ያለአግባብ ለመጠቀም ብሎም ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት ተገቢ አለመሆኑን አፅንኦት ሰጥተው መልዕክት አሳስበዋል ።

በዕለቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ሃላፊና የቤቶች ልማትና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቶ ዳሪ ከድር እንደገለፁት የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት በህብረት ስራ ማህበራት በማደረጃት የዜጎችን የቤት ችግር መቅረፍ ወሳኝ ተቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል።

በመሆኑ የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ መምሪያ ከዚህ በፊት በርካታ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱንና በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በመግለፅ ለማህበራቱ በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ሙባሪክ እ/ሱንከሞ በበኩላቸው ከምንም በላይ በሰው ጭንቅላት ላይ ለሚሰሩ መምህራን፣ የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር ደፋቀና ብለው በክብር ሽኝት ለተደረገላቸው ከመከላከያ በክብር ተመላሽ አባላት እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

ኃላፊው አያይዘው በዚህ የርክክብ መርሃ ግብር 06 ማህበራት መሬት የሚሰጣቸው መሆኑን ገልጸው በዚህም 05 የመምህራን ማህበራት 57 ወንድ 09 ሴት በድምሩ 66 መምህራን እና ከመከላከያ በክብር ተመላሾች ወንድ 14 ሲሆኑ በድምሩ 71 ወንድ 9 ሴት 80 አባላት መሬት የሚሰጣቸው መሆኑንም ገልፀዋል።

በተካሄደው የመሬት ርክክብ ስነስርዓት የፍራፍሬ ችግኝ ተከላ መርሃግብር የተካሄደ ሲሆን ለማህበራቱ የጋይድ ማፕ ርክክብ በማካሄድ መድረኩን ማጠናቀቅ ተችሏል ።

በርክክብ መርሃግብሩ የሳንኩራ ወረዳ ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ፣ የሳንኩራ ወረዳ አስተባባሪ አካላት፣ የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ሃላፊና የቤቶች ልማትና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ፣ የወረዳው ካቢኔ፣ የምክርቤት ቋሚ ኮሚቴዎች፣ የመምህራን ማህበር ሰብሳቢ፣ የረ/ማዞሪያ ከተማ ማዘጋጃ ቤቱ ኃላፊና ባለሙያዎችና የማህበር አባላት ተገኝተዋል ።

የሳንኩራ ወረዳ አስተዳደር ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺ 4መቶ 44ኛው የኢድ-አል አደሀ/አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ ፤ ለእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የሰላም የፍቅ...
27/06/2023

የሳንኩራ ወረዳ አስተዳደር ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺ 4መቶ 44ኛው የኢድ-አል አደሀ/አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ ፤ ለእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የሰላም የፍቅርና የጤና ይሁንላችሁ በማለት የመልካም ምኞቱን ገለፀ

የሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በድሩ ሰንገሮ ለ1ሺ 4መቶ 44ኛው የኢድ-አል አድሃ ረፋ በዓል ለመላዉ የወረዳዉ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

ከሁሉ በማስቀደም እንኳን ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1444ኛው አመተ ሂጅራ የኢድ-አል-አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን ብለዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አቅመ ደካማ የሆኑ ወገኖችን በመርዳት ፣ ማዕድ በማጋራትና እርስ በእርስ በመተባበርና በመደጋገፍ እንዲሁም በአብሮነት በዓሉን ማክበር እንደሚገባ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ለመላው የዕምነቱ ተከታዮች በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል ይሆንላችሁ በማለትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዒድ አል አድሃ የመስዋዕት በዓል እንደመሆኑ መጠን ነቢዩ ኢብራሂም ለጌታው የነበረውን ፍጹም እምነት በቆራጥነት ያሳየበት ልዩ ቀን ነው።

ፈጣሪ አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) ልጅህን መሥዋዕት አቅርብልኝ ብሎ በጠየቀው ጊዜ ኢብራሂም አንድዬ ልጁን እስማኤልን ወደ መሠዊያው ወስዶታል።

ፈጣሪም የኢብራሂምን ፍጹም እምነት ተመልክቶ ሙክት እንደሰጠውና በልጁ ምትክ ሙክቱ ስለተሰዋ የሚከበር በዓል ነው።

የገዛ ልጁን ለመሠዋት ዝግጁ ከመሆን የበለጠ ቆራጥነት የለምና ፣ ዒድ አል-አድሃ “የመስዋዕት በዓል” እየተባለ ይጠራል።

ከልጅ በላይ የቀረበና የሚወደድ ነገር እንደሌለ የወለደ ሰው ሁሉ ያውቀዋልና ለመልካም ዓላማ ሲሉ እጅግ ውድ የሆነ ሀብታቸውን ልጃቸውን ሲሰጡ ቅር አላላቸውም ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል

በመጨረሻም የዘንድሮው የኢድ አል አደሀ አረፋ በዓል ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ የመረዳዳትና የመደጋጋፍ ባህላችንን በማጠናከር አቅመ ደካማ ከሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመተሳሰብ የምናከብረው ሊሆን እንደሚገባ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ዋና አስተዳዳሪው በድጋሚ ለህዝበ ሙስሊሙ እንኳን ለአረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን መልካም በዓል ብለዋል።

////////ኢድ-ሙባረክ//////

ዜናው ሳንኩራ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ነው

እንኳን ደስ አላቹ  ዘርፈ ብዙ የሆኑ የከተማዋን ችግሮችን እንዲፈታ ተስቦ የተዘጋጀው የራግዲና ማዞሪያ ከተማ የቀጣይ 10 ዓመት  መሠረታዊ ፕላን በአጭር ጊዜ ተሰርቶ በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል ፀድ...
26/06/2023

እንኳን ደስ አላቹ
ዘርፈ ብዙ የሆኑ የከተማዋን ችግሮችን እንዲፈታ ተስቦ የተዘጋጀው የራግዲና ማዞሪያ ከተማ የቀጣይ 10 ዓመት መሠረታዊ ፕላን በአጭር ጊዜ ተሰርቶ በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል ፀድቆ እንዲመጣ በማድረግ ወደ ትግበራ ተገባ !!!
ከተሞች ለአንድ ሀገር ልማትና እድገት ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የለውጥ ምሶሶዎች፣ የአስተዳደር፣ የገበያና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመሆናቸው ተገብውን ልዩ ትኩረት በመስጣት ፕላኑ እንዲዘጋጅ ተደርጓል።
ከተማን ከተማ ከሚያሰኘው ነገር አንዱ ከተማን በፕላን መምራት ስሆን በከተሞች ቀጣይነት ያለው ፍትሀዊ የመሬት ሀብት ተጠቃሚነት እንዲኖር በማድረግ ከመልካም አስተዳደርና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞው የሚመጡ አስተዳደራዊ ችግሮች ለመፍታት በስነ ምግባር ፣ ከብልሹ አሰራር በጸዳ፣ እውነት ሳይሸራረፍ ለህሊናው በመኖር ህዝቡን በታማኝነት ለማገልገል ትክክለኛ የከተማ ፕለን መስራት አስፈለጊ በመሆኑ በዚህ ልክም ለማዘጋጀት ጥረት ተደርጓል።
በቀጣይም ለተግባራዊነቱ ሁሉም ባለድርሻ አከለት በቅንጅት መስራትን ይጠይቃል ።
በዛው ዕለት ፕላን የሚወርድበት መሣሪያ (ቶታል እስቴሽን) እና በለሙያ ከስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በማምጣት የደረቅ ቆሻሻ መጣያ ፣ የቄራ ፣ የኢንቨስትመንት ፣ የኢንዱስትሪ እና በመኖሪያ ህብረት ሰራ ለተደራጁ ለቤት መስሪያ የሚሆን መሬት በፕለኑ መሠረት የማመላከት ስራ ተሰርቷል !!!

በህገ-ወጥ ግንባታዎች የሚደረጉ የመሬት ወረራዎችን አጥብቆ በመከላከልና በመቆጣጠር ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹና ተስማሚ መሆን እንዲችሉ አጥብቆ መስራት እንደሚገባ ተገለፀበስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረ...
21/06/2023

በህገ-ወጥ ግንባታዎች የሚደረጉ የመሬት ወረራዎችን አጥብቆ በመከላከልና በመቆጣጠር ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹና ተስማሚ መሆን እንዲችሉ አጥብቆ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የ2015/16 ዓ.ም የአረንጓዴ ልማት አሻራ እና የመሬት አጠቃቀም ወረዳዊ የንቅናቄ መድረክ በረግዲና ማዞሪያ ከተማ አካሂዷል፡፡

የወረዳ አመራር አካላትን ፣ የከተማ ቀመስ የገጠር ማዕከላት(ስከች ፕላን ያለቸው )ቀበሌ አስተዳዳሪዎችና ስራ አስኪያጆች እና የረግዲና ማዞሪያ ከተማ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተካሄደው የንቅናቄ መድረክ በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች በህገ-ወጥ ግንባታ ምክንያት እየተስተዋሉ ያሉ የመሬት ወረራ ችግሮችን በመከላከል ከተሞች የነዋሪውን ማህበረሰብ ማህበራዊና ኢኮነሚያዊ ዕድገት ባረጋገጠ መልኩ መልማት እንዲችሉ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡

በከተሞች በተስተዋሉ ህገ-ወጥ ግንባታዎች ምክንያት የተከሰቱ የመሬት ወረራዎችን በማጥራት ስርዓት ለማስያዝ እና የአረንጓዴ ልማት የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዙሪያ የተዘጋጁ የውይይት ሰነዶች የጽ/ቤቱ ም/ል ኃላፊ በሆኑት በአቶ ሀምደላ ኤርጎሻና በአቶ ሀያቱ ኑሪ በኩል ለንቅናቄ መድረኩ ተሳታፊዎች ቀርቦ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

የንቅናቄ መድረኩን የመሩት የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙባሪክ ኢማም ሱንከሞ በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ህግና ስርዓትን ተከትሎ መልማት እንዲችሉ በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን ይሁንና ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ያልተገባ ጥቅም ማግኘት የሚፈልጉ አካላት ሀላፊነት ካለባቸውና ከባለሀብቶች ጋር በመሆን ህገ-ወጥ ግንባታን በተጠኑ መንገዶች በመፈጸም የመሬት ወረራ እያካሄዱ
ይገኛል ብለዋል፡፡

በየደረጃው እየተስተዋለ ያሉ ህገ-ወጥ ተግባራትን በመከላከል ሂደት አሰራርና መመሪያን ተከትሎ ህጋዊ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ያስረዱት አቶ ሙባሪክ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና ተስማሚ ለማድረግ በሚሰራው ስራ አሁን ላይም እንቅፋት መሆኑን ጠቅሰው ተግባሩ እያስከተለ ያለውን ቀውስ በማስቆም ሂደት ከቀበሌ ጀመሮ እያንዳንዱ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል ፡፡

ህገ-ወጥነትን ተከላክሎ ስርዓት ማስያዝ የማህበራዊና ኢኮነሚያዊ መሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን በማፋጥን የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው ያሉት የሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በድሩ ሰንገሮ በበኩላቸው በህገ-ወጥነት የሚደረጉ የመሬት ወረራዎችን ለማስቆም ትኩረት ተሰጥቶ እየሰራ ቢሆንም ተግባሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለፁ ሲሆን በየደረጃው እየተስተዋለ ያለው ችግር ከተሞች ለነዋሪው ማህበረሰብ ምቹና ተስማሚ እንዲሁም ፈጣን ዕድገት የሚመዘገብባቸው እንዳይሆኑ የሚያደርግ መሆኑን አቶ በድሩ አስረድተዋል፡፡
በወረዳ ደረጃ የተጀመረው ሁሉ አቀፍ ልማታዊ ዕደገት በተጨባጭ በማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚቻለው ህገ-ወጥነትን በሁሉም መልኩ ተከላክሎ ማስቆም ሲቻል ብቻ መሆኑን ያስረዱት አቶ በድሩ ከተሞች ጤናማ የዕድገት ደረጃ ማስመዝገብ እንዲችሉ እያንዳዱ ማህበረሰብ ኃላፊነትና ግዴታ ያለበት መሆኑን ጠቅሰው በህገ-ወጥ ግንባታዎች የሚደረጉ ወረራዎችን አጥብቆ በመከላከልና በመቆጣጠር ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹና ተስማሚ መሆን እንዲችሉ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አሳስበዋል፡፡
በዕለቱም የ2015 /16 የአረንጓዴ ልማት አሻራን በማስመልከት የችግኝ ተከላ ተካሂዷል፡፡

በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የረግዲና ማዞሪያ ከተማ ለነዋሪዎቿ ምቹና ተስማሚ መሆን እንድትችል "ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ቃል  የወረዳ አመራር አካ...
21/06/2023

በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የረግዲና ማዞሪያ ከተማ ለነዋሪዎቿ ምቹና ተስማሚ መሆን እንድትችል "ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ቃል የወረዳ አመራር አካላትና የከተማው ነዋሪዎች በተገኙበት የ2015 /16 የአረንጓዴ ልማት አሻራ ፕሮግራምን በማስመልከት የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡

የረ/ማዞሪያ ከተማ የቀጣይ 10 ዓመት ፕላን ዝግጅት ለማድረግ የሰርቬይንግ የሶሾ ኢኮኖሚ መረጃ መሰብሰብ ተጀመረ!በሳንኩራ ወረዳ የረ/ማዞሪያ ከተማ ፕላንን በአጭር ሰዓት ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሚ...
15/03/2023

የረ/ማዞሪያ ከተማ የቀጣይ 10 ዓመት ፕላን ዝግጅት ለማድረግ የሰርቬይንግ የሶሾ ኢኮኖሚ መረጃ መሰብሰብ ተጀመረ!

በሳንኩራ ወረዳ የረ/ማዞሪያ ከተማ ፕላንን በአጭር ሰዓት ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሚያስችል የሰርቬይንግና የሶሾ ኢኮኖሚ መረጃ ለማሰባሰብ የሚያስችል ጥናት ለማካሄድ በማለም ነው በዛሬው ዕለት የውይይት መድረክ የተካሄደው

በውይይት መድረኩ የተገኙት የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የሶሾ ኢኮኖሚ የጥናት ባለሙያ አቶ አሊ መሐመድ የመረጃ ማሰባሰቢያ ፎርማት ለተቋማት በሰጡበት ወቅት እንዳሉት ይህ የተጀመረው የመረጃ ማሰባሰብ ሥራ ለከተማው ዕድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወት በመሆኑ በትኩረት ትክክለኛና ተአማኒነት ያለውን መረጃ በተገቢው ተሞልቶ በአጭር ሰዓት መድረስ እንዳለበት ገልፀዋል

የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ሙባሪክ ኢማም ሱንካሞ እንደገለፁት የፕላን ክለሳ የሚጀምረው የአስተዳዳራዊ ወሰን በመከለል ሲሆን ይህም ተግባር ከቅርብ ቀናት በፊት አልቆ ለባለድርሻ አካት ቀርቦ መፅደቁ የሚተወስ ሲሆን ከዚህ ተግበር በመቀጠል የሰርቬይንግ እና የሶሾ ኢኮኖሚ መረጃዎች አስፈላጊ በመሆኑ ይህም ተግባር የስልጤ ዞን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በከተሞች ፕላን ዩኒት ዘርፍ የቅያሳ መሳሪያና ባለሙያዎችን በመላክ ስራው በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

የሶሾ ኢኮኖሚ መረጃዎች መጠይቅ የደረሳቸው ተቋማት በተጠየቀው ጊዜ ጥራቱን የጠበቀ መረጃ በመስጠት ለመረጃ ተደራሽነቱ ትብብር ማድረግ እንዳለባቸው ኃላፊው አያይዘው ገልጸዋል፡፡

መድረኩን የመሩት የሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተማም ፊጣሞ እንደገለጹት የሚሰራው ፕላን ለቀጣይ አስር ዓመታት እንደመሆኑ መጠን
ፕላኑ ለከተማው ዕድገት የሚመጥን በመሆኑ መረጃ የተጠየቁ ተቋማት ትክክለኛና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

የረግዲና ማዞሪያ ከተማን ለኑሮና ኢንቨስትመንት ምቹና ሳቢ ማድረግ የሁሉንም ባለድርሻ አካለት ጥረት የሚጠይቅ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በፕላን ዝግጅቱና በሌሎችም የከተማ ልማት ስራዎች በቅርብ እያደረገ ላለው ድጋፍ በራሴ እና በወረዳው ህዝብ ስም ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

15/03/2023
በስልጤ ዞን በሳንኩራ ወረዳ የረግዲና ማዞሪያ ከተማ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማትና እና ማኔጅመንት ዋና የስራ ሂደት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ 721/2004 አንቀጽ...
25/01/2023

በስልጤ ዞን በሳንኩራ ወረዳ የረግዲና ማዞሪያ ከተማ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት የመሬት ልማትና እና ማኔጅመንት ዋና የስራ ሂደት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ቁጥር ከ ሀ እስከ ሰ በደንብ ቁጥር 123/2007 አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ ከ1 እስከ 3 እና መመሪያ ቁጥር 8/2007 አንቀጽ 23 በተዘረዘረዉ መሰረት ለንግድ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የተዘጋጀ መሬት በግልጽ የሊዝ ጨረታ ለተጫራቾች ለማስተላለፍ በቀን 19/04/2015 ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል ሆኖም ዛሬ በቀን 17/05/2015 በወጣው ማስታወቂያ መሰረት የጨረታው መዝጊያ ጊዜ መራዘሙን አስተውቋል ፡፡ በመሆኑም በማስታወቂያው መሰረት የሰነድ ሽያጭ እስከ 22/05/2015 መራዘሙን የገለጸ ስለሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከተራዘመበት ቀን እስካ 22/05/2015 ድረስ በማዘጋጃ ቤቱ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ ለመኖሪያ የማይመለስ 300(ሶስት)መቶ ብር እንዲሁም ለንግድ የማይመለስ 400(አራት )መቶ ብር መግዛት የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል ።ጨረታው የሚዘጋው በቀን 22/05/2015 ከቀኑ 11:30 ሲሆን የሚከፈተው በቀን 23/05/2015 በጠዋቱ 3:00 ሰዓት በማዘጋጃ ቤቱ አደራሽ መሆኑን ይገልጻል ።
በተጨማሪም ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ በማ/ቤቱ ስልክ ቁጥር 0945849500/0939889656 /0932581411 ወይም በአካል በመቅረብ እና ከሚሸጠዉ የጨረታ ሰነድ ጋይድ ማፕ ማግኘት የሚችል ይሆናል፡፡

ማዘጋጃ ቤቱ !!!

Address

Hosanna

Telephone

+251978870008

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share