Ethiopian Food and Drug Authority /EFDA/

Ethiopian Food  and  Drug Authority /EFDA/ Address up-to-date regulatory information about the safety, quality, efficacy, rationale use and performance of regulated products.

ራዕይ

በአፍሪካ ውስጥ በምግብ እና በጤና ምርቶች ቁጥጥር የልህቀት ማዕከል መሆን፡፡

ተልዕኮ

ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ምርቶች ደህንነት፣ ውጤታማነት፣ ጥራት እና ትክክለኛ አጠቃቀም በፈቃድ፣ በምርመራ፣ በምዝገባ፣ በላብራቶሪ ምርመራ፣ በድህረ-ገበያ ክትትልና በማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲሁም ወቅታዊ የቁጥጥር መረጃ በማቅረብ የህዝብ ጤናን መጠበቅና ማሻሻል፡፡

Africa Avenue, near wolosefer, Kirkos sub city, 02/03 kebelle, 02

http://www.fmhaca.gov.et/
E-mail [email protected]
Telegram
https://t.me/ethiopianfoodanddrugauthority
YouTube channel link

የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ ተሳታፊዎች በአርባ ምንጭ ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በቦታው ተገኝተው በመጎብኘት የእግር ...
04/09/2026

የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ ተሳታፊዎች በአርባ ምንጭ ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በቦታው ተገኝተው በመጎብኘት የእግር ጉዞ አካሄዱ።

ነሐሴ 28 / 2018 ዓ.ም አርባ ምንጭ ከተማ — የጉባኤው ተሳታፊዎች ከአርባ ምንጭ ከተማ ባህል ማዕከል እስከ ሲቻ አደባባይ የእግር ጉዞ ያደረጉ ሲሆን፥ በዚሁ ወቅት በከተማው አስተዳደር የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን መመልከት ችለዋል፡፡

በተከናወነው የኮሪደር ልማት መደመማቸውን በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡን የጉባኤው ተሳታፊዎች፥ ለቱሪስት መናኸሪያ ለሆነችው አርባ ምንጭ ከተማ የተገነባው የኮሪደር ልማት ልዩ ድምቀትና ውበት እንዳጎናጸፋት ተናግረዋል፡፡

ከዓመታት በፊት በዚሁ ከተማ ተመሳሳይ የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር እቅድ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ መካሄዱን ያስታወሱት ተሳታፊዎቹ፥ የዘንድሮውን ልዩ የሚያደርገው ከተማዋን ለነዋሪዎቿና ለጎብኚዎች ይበልጥ ምቹ የሚያደርጉ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታዎች በጥራትና በስፋት የተከናወኑበት በመሆኑ የተለየ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡

ባለስልጣኑ በምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር በ2018 በጀት ዓመት ላስመዘገባቸው ስኬቶች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያላሰለሰ ቁጥጥርና ድጋፍ አስተዋፆ ከፍተኛ እንደነበር ተገለፀ፡፡ነሐሴ 28/...
03/09/2026

ባለስልጣኑ በምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር በ2018 በጀት ዓመት ላስመዘገባቸው ስኬቶች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያላሰለሰ ቁጥጥርና ድጋፍ አስተዋፆ ከፍተኛ እንደነበር ተገለፀ፡፡
ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም አርባምንጭ፡- የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃጸም ግምገማ መድረክን በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወይዘሮ ወርቀሰሙ ማሞ ሲከፍቱ እንደተናገሩት የምክርቤቱ አባላት ከተቋሙ ጋር በትብብር በመስራታቸው በዓለም አደባባይ የተመሰከረለት ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ቁርጠኝነትና ዲሲፕሊን የታየበት ነው ያሉት ክብርት ሰብሳቢዋ በተገኘው ውጤት ሳይኩራሩ የሕዝባችንን ፍላጎት ለማርካት ሌሎች ተጨማሪ ስኬቶችን ለመጨበጥ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳሰበዋል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ በበኩላቸው እንደተናገሩት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሰራራዊና መዋቅራዊ ክፍተቶችን በማረም በተለይ ደግሞ የደረጃዎችና ሌሎች መዋቅራዊ ማስተካከያዎችን በማድረግ፣ የቁጥጥር ፍትሃዊነታችንን በማጠናከር፣ ላቦራቶሪዎቻችንን በማደራጀት፣ አሰራሮቻችንን ግልጽ በማድረግ፣ የህዝብ ጤና አደጋ ላይ ለሚጥሉ አሰራሮችን ለማረም ሰፊ እርምጃዎችን ወስደናል ብለዋል፡፡
የቁጥጥር ስራው ስራዎቹ ሲኖሩ ብቻ ከመስራት ወይም የሆነ ችግር ሲፈጠር ብቻ ከመስራት ቀድሞ አስቦ፣ አቅዶ፣ ችግሮችን ተንብዮ እርምጃ የሚወስድ የቁጥጥር ስርዓት መሸጋገር አለበት ብለን ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ የጥራት መሰረተ ልማትን ከመዘርጋት አንጻር ተቆጣጣሪ ብንሆንም የቁጥጥር ስራ ብንሰራ፤ እኛም ደግሞ በሌሎች ስታንዳርዶች ትክክለኛ የቁጥጥር ስራ ስለመስራታችን ማረጋገጥ ስለሚያስፈልግ በአለም አቀፍ ስታንዳርዶች ተቋማችንን ማስመዝገብ፣ ይህ የተገኘውን ደግሞ ደረጃ ማስቀጠል ትልቁ ባለፉት ዓመታት የትኩረት አቅጣጫችን ነበሩ ነው ያሉት፡፡

ባለፉት ዓመታት የጤና አገልግሎት ተደራሽነት በመስፋቱ የጤና ልማት ተጠቃሚ ሕዝባችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ አድጓል ያሉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ዶ/ር እንዳሻው ሽብሩ ለዚህም የቁጥጥር ዘርፉ ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም የማርበርግ ወርሽኝን በመከላከል ረገድ ክልሉ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተባብሮ በመስራት አገር የሚያኮራ ስኬት መመዝገቡን ገልፀዋል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ ለአርባምንጭ ጤና መመሪያ ከ710 ሺ ብር በላይ መድኃኒት፣ ከ280 ሺ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የህክምና መሳሪያዎች እንዲሁም በከተማው ለሚኖሩ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የሚሆን ከአንድ መቶ ሺ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች ደብተርና ስክሪፕቶ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ድጋፍ አድርጓል፡፡

02/09/2026
 #የበዓል  #ምግቦችን  #ሲገዙ  #እነዚህን  #ያስተውሉ
02/09/2026

#የበዓል #ምግቦችን #ሲገዙ #እነዚህን #ያስተውሉ

Public Alert Notice on a Suspected Counterfeit Products Mimicking Forxiga® (Dapagliflozin) as obtained from the National...
31/08/2026

Public Alert Notice on a Suspected Counterfeit Products Mimicking Forxiga® (Dapagliflozin) as obtained from the National Agency for Food and Drug Administration and Control (NAFDAC) of Nigeria.

011/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ። መልካም በዓል!
25/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ። መልካም በዓል!

ለትምባሆ ቁጥጥር ሥርዓት ዘላቂ የሆነ የፋይናንስ ምንጭ ማግኘት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።ነሀሴ 18/2018ዓ.ም -- አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ለትምባሆ ቁጥጥር ሥርዓት ራሱን የቻለና ዘላቂ የበጀት ...
25/08/2026

ለትምባሆ ቁጥጥር ሥርዓት ዘላቂ የሆነ የፋይናንስ ምንጭ ማግኘት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።

ነሀሴ 18/2018ዓ.ም -- አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ለትምባሆ ቁጥጥር ሥርዓት ራሱን የቻለና ዘላቂ የበጀት ኮድ መመደቡን አስመልክቶ የምስጋናና የእውቅና ፕሮግራም ተካሄደ።
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ከማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በትምባሆ ቁጥጥርና የትምባሆ ኢንዱስትሪ ጣልቃ ገብነትን በመቀነስ ረገድ አምስት ጊዜ ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘቷን አስታውሰው ትንባሆና አልኮል በጤና ላይ የሚያደርሱት የጤና ጉዳትና ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሱት ጫና ከፍተኛ ነው በመሆኑም ይህን ታሳቢ በማድረግ በትምባሆና አልኮል ምርቶች ላይ የሚጣለውን ኤክሳይስ ታክስ ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስቴር የበጀት ዝግጅትና አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍሬው ኃይሌ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው የጤናውን ዘርፍ ኃላፊነት በመገንዘብ አስፈላጊውን የስራ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ዘላለም መንግሥቱ በበኩላቸው ይህ ውሳኔ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርአያ የሚሆን ታሪካዊ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

መድረኩ ለትንባሆ ቁጥጥር ስራው እንዲሁም ለጥራት አስተዳደርና ስራ አመራር ቋሚ የበጀት ምደባ ግቡን እንዲመታ በሂደቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የገንዘብ ሚኒስቴርና የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች በተጨማሪም ለተቋሙ የስራ ክፍሎች እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይም በጀቱን ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውል የመከታተል ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተገልጿል፡፡

Address

Ethiopian Food And Drug Authority/EFDA/የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
Hawassa
5681

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Food and Drug Authority /EFDA/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Food and Drug Authority /EFDA/:

Shortcuts

Share