19/11/2025
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰው (ዶ/ር) የ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ምልከታ አደረጉ ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በክልሉ አስተናጋጅነት የሚካሄደዉን የ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዛሬ ምልከታ አድርገዋል ።
በዓሉን ለመሳተፍ ወደ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶች ለመቀበል እየተሰሩ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ያሉበት ደረጃ ተዘዋዉረው የጎበኙት ክብር ፕሬዝዳንቱ የተሰሩ ስራዎቹም በመልካም አፈፃፀም ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ትልቅ ሀገራዊ በዓል በመሆኑ ህብረ ብሔራዊነት በማጠናከር የተጀመሩ ቀሪ ተግባራት በአጭር ጊዜ በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ።