Hawasi quchumi gashooti loosu,loosiisiranotena loosiisanote biddisha

Hawasi quchumi gashooti loosu,loosiisiranotena loosiisanote biddisha Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hawasi quchumi gashooti loosu,loosiisiranotena loosiisanote biddisha, Government Organization, Hawassa.

25/12/2024
20/12/2024
20/12/2024
በሥራ ዕድል ፈጠራ ያለው አስተዋጽኦ ትልቅ ነው።
04/12/2024

በሥራ ዕድል ፈጠራ ያለው አስተዋጽኦ ትልቅ ነው።

የቁጠባ አሰባሰብና ብድር አመላለስ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሄደ።የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ ህዳር/4/2017/ዓም/ሐዋሳየሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ስራ፣ አሰሪና ሰራተኛ መምሪ...
13/11/2024

የቁጠባ አሰባሰብና ብድር አመላለስ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሄደ።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ህዳር/4/2017/ዓም/ሐዋሳ

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ስራ፣ አሰሪና ሰራተኛ መምሪያ ከኦሞ ባንክ ሐዋሳ ከተማ ዲስትሪክት ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጁት የቁጠባ አሰባሰብ፣ በብድር ስርጭትና አመላለስ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ያለመ የምክክር መድረክ ዛሬተካሂዷል።

መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የሐዋሳ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌቱ ማሞ ናቸው።

አቶ ጌቱ ማሞ በመድረኩ ባደረጉት ንግግርም የወጣቶችና የሴቶችን የስራ አጥነት ችግር ከመቅረፍ ረገድ ተስፋ የተጣለበት የቁጠባና ብድር ስርጭት ስራው የተረጋጋ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ምህዳር ከመፍጠር ረገድ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።

በመሆኑም በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ደረጃ የሚከናወነውን የቁጠባ አሰባሰብ፣ የብድር ስርጭት እና ብድር አመላለስ ስራ ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራው ዘርፍ ተገቢውን ሚና እንዲወጣ ፖለቲካዊ ትርጉም ሰጥቶ በላቀ ቁርጠኝነት መምራት እንደሚገባም ገለፀዋል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ስራ አሰሪና ሰራተኛ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታሪኩ ጥላሁን በበኩላቸው የወጣቶችን እና የሴቶችን የስራ አጥነት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት አንደ‍ኡ የፋይናንስ ምንጭ ከቁጠባና ብድር የሚገኘው ገንዘብ መሆኑን ጠቅሰው የፋይናንስ አማራጮችን ለማስፋት በቅንጅትና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ከዚህ ረገድ የምክክር መድረኩ የስራ እድል ፈጠራ ስራውን ከማስፋት አኳያ ያለውን ፋይዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት በለድርሻ አካላት የጋራ ተግባቦት የፈጠሩበት መድረክ መሆኑንም አቶ ታሪኩ ጠቁመዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በተለይ ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ 36 ሚሊየን 340 ሺህ ብር የተረጋጋ ቁጠባ ለመሰብሰብ መታቀዱን አቶ መስፍን ማርቆስ የኦሞ ባንክ ሐዋሳ ከተማ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ ገልፀዋል።

አቶ መስፍን አያይዘውም 49 ሚሊየን 496 ሺህ ብር ብድር ለማስመለስ መታቀዱን የገለፁ ሲሆን 73 ሚሊየን 761 ሺህ ብር ከቁጠባ እና ከመንግስት ድጋፎች ብድር ለመስጠት መታቀዱንም ጨምረው ገልፀዋል።

የሞሃ መጠጦች አክሲዮን ማህበር ከሐዋሳ ከተማ  የኮሪደር ልማት ለማልማት ቦታውን ተረከበየሐ/ከ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያጥቅምት 23 2017 ዓ/ምሐዋሳየሞሃ መጠጦች አክሲዮን ማህበር በዛሬው እለት የ...
02/11/2024

የሞሃ መጠጦች አክሲዮን ማህበር ከሐዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ለማልማት ቦታውን ተረከበ

የሐ/ከ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ጥቅምት 23 2017 ዓ/ም
ሐዋሳ

የሞሃ መጠጦች አክሲዮን ማህበር በዛሬው እለት የኮሪደር ልማት፣ የሼድ ግንባታ እንዲሁም የእድለኞችን ሽልማት የማስረከብ ፕሮግራም አካሄዷል።

የሐዋሳ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ብሩክ ሰለሞን በንግግራቸው ይህ የልማት ተሳትፎ ህብረተሰቡን ታሪካዊ የልማቱ አጋር መደገፉን ያሣያል ነው ብለዋል።

አክለውም መንግስት በራሱ አቅም ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ እንደ ሞሐ ለስላሳ መጠጦች አክሲዮን ማህበር መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸው አቶ ብሩክ ገልፀዋል።

የሞሃ መጠጦች አክሲዮን ማህበር ሥራ አስኬያጅ አቶ አማኑኤል ሙሄ በንግግራቸው የተጀመሩ የኮሪደር ልማት በጥራትና በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ተቋሙ የበኩሉን ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።

አክለውም ማህበሩ 40 የሚሆኑ ኮንቲነሮችን በአጭር ቀን ውስጥ ገንብቶ ለወጣቶች ለማስረከብ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ጨምረው ገልፀዋል።

የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎት ኢንተርኘራይዝ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊና የስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ከበደ የስራ ዕድልን ተጨባጭነት ለማረጋገጥ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማትና ከባለሀብቱ ጋር የተሰሩ ስራዎች ውጤት እያስገኘ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ከፍያለው አክለውም ላለፉት ዓመታት ለወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያሉንን አማራጮች በተደራጀ መልኩ በማስኬድ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የተፈጠረ ነውም ሲሉ አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም በሞሃ ለስለሳ እድለኞች ለሆኑ በርካታ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ከዚህም ውስጥ ID4 የቤት መኪና የሐዋሳ እድለኛ ቁልፉን ተረክቧል።

Address

Hawassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawasi quchumi gashooti loosu,loosiisiranotena loosiisanote biddisha posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share