Sidaamu Dagoomu Qoqqowu Mootimma Ispoortete Komishiine

Sidaamu Dagoomu Qoqqowu Mootimma Ispoortete Komishiine Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sidaamu Dagoomu Qoqqowu Mootimma Ispoortete Komishiine, Government Official, Sidaama, Hawassa.

20/05/2023
ደማቅ አቀባበልና እውቅና ለእንቁ አትሌት መቶ አለቃ በላይነህ ዲንሳሞየሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ   ለመቶ አለቃ አትሌት በላይነህ ዲንሳሞ የሚመጥን የእውቅናና የአቀባበል መርሃ ግብር...
20/05/2023

ደማቅ አቀባበልና እውቅና ለእንቁ አትሌት መቶ አለቃ በላይነህ ዲንሳሞ

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ ለመቶ አለቃ አትሌት በላይነህ ዲንሳሞ የሚመጥን የእውቅናና የአቀባበል መርሃ ግብር አዘጋጅቷል።

መቶ አለቃ አትሌት በላይነህ ፣ በ1980 ዓ.ም በሮተርዳም ከተማ በተካሄደው የዓለም ማራቶን ክብረ ወሰንን በማሻሻል ጭምር ማራቶንን በከፍተኛ ትጋትና ጽናት ማጠናቀቅ የቻሉ፤ ይህንንም ውጤት ለአስር ዓመታት በስማቸው ማቆየት ያስቻሉ የሀገራችን ብርቅዬ አትሌት ናቸው።

በወቅቱ የስርዓት ለውጥ፣ የሀገር አለመረጋጋት ከመኖሩ እና ሌሎች ወዘተ ምክንያቶች ጋር ተዳምሮ ይህንኑ ብርቅዬ አትሌት ማስታወስ ሳይቻል በርካታ ዓመታት አልፏል። እውቅናም ይሁን አቀባበል አልተደረገላቸውም ነበር። ብዙ ውዝፍ ነገሮች ያለበት ነው።

አሁን ደግሞ እንደሀገርና ክልል ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ፣ አትሌት በላይነህም በራሱ ጥረት የግል ታሪካቸውን የሚያሳይ ''የተፈተነ ጽናት'' የሚለውን መጽሃፍ በመጻፍ ለትውልድ ማቅረብ በመቻሉ እና የሲዳማ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለዚህ ጀግና ለክብራቸውና ለታሪካቸው የሚመጥን አቀባበል እንዲደረግ ፣ እውቅና እንድሰጣቸው እና ከአትሌቱ ህይወት ታሪክና ገድል ወጣቱ መማር የሚችልበት መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባ በመወሰናቸው የእውቅናና የአቀባበል ፕሮግራም ተሰናድቷል።

በመሆኑም ግንቦት 12/2015 ዓ.ም በሳውዝ ስታር ሆቴል ዕለተ ቅዳሜ ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ የእውቅናና የአቀባበል መርሃግብር ተዘጋጅቷል። በፕሮግራሙ ላይ የክልል መ/ቤት አጠቃላይ አመራሮች ፤ የወረዳ አስተዳዳሪና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባላት ፣ አፌ ጉባኤዎች እና የክፍለ ከተማ አስተዳዳሪዎች ፤ ነጋዴዎች/ባለሃብቶች ፤ አንጋፋ አትሌቶችና አሰልጣኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለጀግናው አትሌት አቀባበል ይደረጋል ፣ እውቅናም ይሰጣል።

እናመሰግናለን !!

 ከ22ኛ ሳምንት የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ጀምሮ  እስከ 27ኛው ሳምንት ድረስ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን የሚያስተናግደዉ የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም የምሽት ገፅታ ምልከ...
03/05/2023



ከ22ኛ ሳምንት የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ጀምሮ እስከ 27ኛው ሳምንት ድረስ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን የሚያስተናግደዉ የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም የምሽት ገፅታ ምልከታ ተካሂዷል።

ቀጣይ የሊጉን ጨዋታዎች ተቀብሎ ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ የሚገኘዉ የሀዋሳ ዩንቨርስቲ የሜዳዉ አሁናዊ የምሽት ገፅታ (የፓዉዛ ብርሀን) ምልከታ የተደረገ ሲሆን በምሽት ለሚካሄዱም ጨዋታዎች ዝግጁ መሆኑ ተረጋግጧል።

(የሜዳዉን የምሽት ገፅታ በፎቶዎቹ ላይ ይመልከቱ)

Telegram t.me/Hatricksport
Website www.Hatricksport.net
Twitter twitter.com/Hatricksport
Instagram instagram.com/Hatricksport

ነገ ከጧቱ  12 : 00 ስዓት አይቀርም ....ሁል ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ በንክክ የማይተላለፉ በሽታዎችን እንከላከላለን ...።
29/04/2023

ነገ ከጧቱ 12 : 00 ስዓት አይቀርም ....

ሁል ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ በንክክ የማይተላለፉ በሽታዎችን እንከላከላለን ...።

*** መልካም ዜና ለሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ***       " የአንድ ስዓት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ"             # # # #... ለሚሊዮኖች...  # # # #   በሚል መሪ ቃል በ...
29/04/2023

*** መልካም ዜና ለሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ***

" የአንድ ስዓት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ"

# # # #... ለሚሊዮኖች... # # # #
በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ማረምያ ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ በደማቅ ሁኔታ እንደሚካሄድ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ስፖርት ኮሚሽን አስታውቀዋል ።
በዕለቱ ስለ አካል ብቃት ጥቅምና ዕለቱን አስመልክቶ በክብር እንግዶች መልዕክት ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል ።

ሁሉ የከተማችን ነዋሪዎች የአከባቢው ማህብረሰብ ተገኝተዉ እንድሳተፍም ተጋብዘዋል።

22/08/2015 ዓ.ም.
ሲዳማ ስፖርት ኮሚሽን
ሀዋሳ

"Fichee cambalaallate dodeemmo kilaweyya irkiseemmo" yaanno uminni 5 kiilo meetire doddansho assinoonni.Sidaamu Da/Qo/Mo...
18/04/2023

"Fichee cambalaallate dodeemmo kilaweyya irkiseemmo" yaanno uminni 5 kiilo meetire doddansho assinoonni.

Sidaamu Da/Qo/Mo/Woga/Tu/Ispoortete biiro Dotteessa 10/2015 M.D Hawaasa.

Layinki perezidaantichi kalaa Beyyene Baraasihu Fichee cambalaalla Sidaamaho ha'nuranna ayirrado dona ikkasinni ilamayenni ilamara sa"anno gede assatenni jawa daga ikkitinota Sidaamu daga albilcho sufisiisa agartannota coyrino.

Qoqqowu Woga, Turizimenna Ispoortete Biiro Sooreessi kalaa Jago Aganyohu Ficheenke baxille, mittimma, ayirrisammannita ikkase aleenni Sidaamu dagannino sa'e Alamete dona ikkasenni baalunku budesenna balchoomase amaddino garinni sufanno gede assate baalunku qeechi agarannota kulu techo barra assinanni dodansho 5 kiiloomeetireti Sidaamu lekkate kaase kilawe irkinsannite ikkitinota kulino.

Labbalunni Taamiraati Duuggehu meyaatewidoonni Alimaazi Yohaannisiti 5 kiilomeetirera umire ikkite qeeltino.

"ለፊቼ ጫምባላላ እሮጣለሁ ክለቤን እደግፋሁ" በሚል መር ቃል የ5 ኪ.ሜ ሩጫ የሲዳማ እግር ኳስ ክለብን ለመደገፍ ተደርገዋል።

17/04/2023

# # #... ቀኑ ደረሰ ...ደረሰ ...!!!
ነገ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት " ከሱሙዳዉ ፊት ለፊት አይቀርም ... "ለፊቼ - ጫንባላላ እሮጣለሁ ክለቤን እደግፋለሁ " በሚል መሪ ቃል ለሚደረገዉ ሩጫ የከተማና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንደሚገኙ ከመገለጹ በላይ ታዋቂ አትለቶች እንደሚገኙና በሩጫዉ እንደሚሳተፉ ተገልፀዋል።

በዉድድሩ መረሃ ግብር በ5ኪ.ሜ.እና በ2 ኪ.ሜ.የሚደረግ ሲሆን በዉድድሩ ቀዳም ደረጃ ይዘዉ ለሚያጠናቅቁ የሽልማት ስነስርአት እደሚካሄድም ተገልፆዋል ።

በዕለቱ የፊቼ -ጫንባላላ የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ዋዜማን ምክንያት በማድረግ ሌሎች አጓግና አስደሳች ስፖርታዊ ዉድድሮች እንደሚካሄድም ተመልክተዋል ።

" ለፊቼ እሮጣለሁ ክለቤንም እደግፈለሁ "!!!

ሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ስፖርት ኮሚሽን
10/08/2015 ዓ.ም.

17/04/2023

የጌታን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ኃጥአት ከሰማይ ሰማያት ወርዶ የሰው ልጆች የሚኖሩበትን ምድራዊ መከራን ከእኛ ጋር ተቀብሎ፣ ስለ እኛ ኃጥያት ተዋርዶ፣ ተገርፎ፣ ተሰቅሎና ተቀብሮ በሶስተኛም ቀን ሞትን አሸንፎ ተነስቶ እኛ ከዘላለማዊ ሐጥያት በደሙ ዋጅቶ አድኖን ህይወትና መንገድ ሆኖን እስከ አለም ፍፃሜ ከእኛ ጋር እንደምሆን ተስፋ ሰጥቶን ወደ አባቱ እቅፍ ያረገበት ቀን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ ። ኢየሱስ ክርስቶስ በደላችንን ሁሉ ይቅር ብሎን ከአባቱ ከአብ ጋር አሰታርቆናል ። ፋስካ በዓልን ስናከብር እኛም የበደሉንን ይቅር በማለት፣ ያጡትን በመርዳት፣ የተራቆቱትን በማልበስ፣የተራቡትን በማብላት፣በተሰማራንበት የስራ መስክ ታማኝ አገልጋዮች ልንሆን ይገባል። መልካም በዓል ይሁንልን !!

Address

Sidaama
Hawassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidaamu Dagoomu Qoqqowu Mootimma Ispoortete Komishiine posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Sidaamu Dagoomu Qoqqowu Mootimma Ispoortete Komishiine:

Share