Sidaamu Qoqqowi Loosunna Dandoote Biiro ሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Hawassa
  • Sidaamu Qoqqowi Loosunna Dandoote Biiro ሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ

Sidaamu Qoqqowi Loosunna Dandoote Biiro ሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ Sidaamu Qoqqowi Loosunna Dandoote Biiro
የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ
Sidaama Regional State Labor And Skills Bureau

የክልሉ ምክር ቤት በህገ-መንግስቱ ላይ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት የአስፈፃሚ አካላት ለማደረጃጀት በተሰጠው ስልጣን በአዋጅ ቁጥር 003/2012 መሠረት የተደራጀው የቴክኒኪና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የሳይንስ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ነው፡፡

28/05/2026

Sidaamu Dagoomu Qoqqowu Mootimma Ogimmate Dandoonna Buuxote Ejeense Sai ontu diri giddo loossino loossa.

Onkoleessa 20/ 2018 M.D
Hawaasa
Ledote mashalaqqera:_

ያሉንን ጸጋዎች በሙሉ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራዉ ስራ ዘላቂ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል :_ አቶ ከፍያለዉ ከበደ ሀዋሳ ፤ ግንቦት 19/2018፤ የቢሮዉ የሕዝብ ግንኙነት የሲዳማ ክ...
27/05/2026

ያሉንን ጸጋዎች በሙሉ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራዉ ስራ ዘላቂ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል :_ አቶ ከፍያለዉ ከበደ

ሀዋሳ ፤ ግንቦት 19/2018፤ የቢሮዉ የሕዝብ ግንኙነት

የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ከክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ CALM_P4 ጋር በጋራ በመቀናጀት በፕሮግራሙ ድጋፍ ለተደራጁ ወጣቶች ስልጠና ተሰጠ።

የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትልና የሥራ ዕድል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለዉ ከበደ በመክፈቻ ንግግራቸዉ ክልሉ የበርካታ ጸጋ ባለቤት በመሆኑ ያሉንን ጸጋዎች በሙሉ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራዉ ስራ ዘላቂ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል።

አቶ ክፍያለዉ አክለዉም ያሉንን ጸጋዉች በአግባብ በመለየት በክልሉ ለሚገኙ ሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር በመቻሉ ከራሳቸዉ አልፈዉ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።

ቢሮዉ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመሰራት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎችን መስራት መቻላቸዉን የተናገሩት አቶ ከፍያለዉ በተለይም እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ከቢሮዉ ጋር በቅንጅት በመስራት ለወጣቶች ዘላቂ የሥራ ዕድል መፍጠር በመቻሉ በቢሮዉ ስም ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መንገሻ ፊጣሞ በበኩላቸዉ በዞናቸዉ ለሚገኙ ወጣቶች ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር በሰሩት ሥራ በርካታ ወጣቶችን ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ በንግግራቸው አመላክተዋል።

በሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አበባየሁ በየነ የሚፈጠሩ ማንኛዉንም ዕድሎችን ወጣቶችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመሰራቱ ለበርካታ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉንና በካልም ፕሮጀክት ከ31 ሚሊዩን ብር በላይ ድጋፍ በማድረግ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረዋል።

ለቢሮው ለበለጠ መረጃ:_
Telegram :_https://t.me/+fPA20GFng5kxZGU8
You Tube :_https://youtube.com/?si=I0V1pgFTOeftsKWv
TikTok:_https://www.tiktok.com/?_t=8qA4mUlWXQ6&_r=1
WhatsApp :_https://whatsapp.com/channel/0029VakybqAB4hdLaMYFqm3h
ዋትስ አፕ:_https://chat.whatsapp.com/G8X4mUl03Na1cWwMPECO3h
X:_https://twitter.com/NewsSidaama?t=0-VU7tDUzLGQliHbNDY_9w&s=09
Website:_https://g.co/kgs/MpxLFG1

በሲዳማ  ክልል የብልፅግና ፓርቲ  የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተካሂደዋል ።የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የብልጽግና ፓርቲ አባላት በሀዋሳ አለም ...
26/05/2026

በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተካሂደዋል ።

የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የብልጽግና ፓርቲ አባላት በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም በመገኘት በግንቦት 24/2018ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የመወዳደሪያ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶን በመምረጥ ሃላፊነታችንን እንወጣለን ስሉ ድጋፋቸውን አሳይተዋል።

!
ሀዋሳ፣ ግንቦት 18፣ 2018ዓ.ም የቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶረት
ለቢሮው ለበለጠ መረጃ:_
Telegram :_https://t.me/+fPA20GFng5kxZGU8
You Tube :_https://youtube.com/?si=I0V1pgFTOeftsKWv
TikTok:_https://www.tiktok.com/?_t=8qA4mUlWXQ6&_r=1
WhatsApp :_https://whatsapp.com/channel/0029VakybqAB4hdLaMYFqm3h
ዋትስ አፕ:_https://chat.whatsapp.com/G8X4mUl03Na1cWwMPECO3h
X:_https://twitter.com/NewsSidaama?t=0-VU7tDUzLGQliHbNDY_9w&s=09
Website:_https://g.co/kgs/MpxLFG1

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር !ብልጽግናን ይምረጡ !የምርጫ ምልክታችን የሲንዴ ነዶ ነው!
26/05/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር !

ብልጽግናን ይምረጡ !

የምርጫ ምልክታችን የሲንዴ ነዶ ነው!

የብልፅግና ፓርቲ  የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በደመቀ ሁኔታ በሲዳማ  ክልል እየተካሄደ ይገኛል።በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።የተ...
26/05/2026

የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በደመቀ ሁኔታ በሲዳማ ክልል እየተካሄደ ይገኛል።

በሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከማለዳው ጀምሮ በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም በመትመም ቃሉን በተግባር ለተረጎመው ብልፅግና ፓርቲ ድጋፋቸውን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

ድምፃችን የነገ ማንነታችን ውሳኔ ነው! በመሆኑም ምርጫችንን ለምናውቀው፣ በተግባር ለምናምነውና ሁልጊዜም ከጎናችን ለቆመው ፓርቲያችን እንሰጣለን!



25/05/2026
23/05/2026
ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠርና ግብርናን ለማዘመን እንደ ሀገር የተያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ ቢሮው በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል፦ አቶ መምህሩ ሞኬሀዋሳ፤ግንቦት13፣2018የቢሮ የህዝብ ...
21/05/2026

ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠርና ግብርናን ለማዘመን እንደ ሀገር የተያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ ቢሮው በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል፦ አቶ መምህሩ ሞኬ

ሀዋሳ፤ግንቦት13፣2018የቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶረት

የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ከእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመቀናጀት በግብርና ዘርፍ ለተደረጁ ወጣቶች ትራክተሮችን አሳልፎ የመስጠት መርሀግብር አካሄዱ።

በስነስርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ መምህሩ ሞኬ ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠርና ግብርናን ለማዘመን እንደ ሀገር የተያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ ቢሮው በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የእርሻ ዘርፍ ለክልሉ ኢኮኖሚ ዋና መሠረት ነው ያሉት አቶ መምህሩ ለግብርና የተሰጡ ስራዎች በርካታ በመሆኑ የዘመነ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በሁሉም እርሻ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ወሳኝ ነው ብለዋል።

መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተቀናጅተው መስራት ወሳኝ ነው ያሉት አቶ መምህሩ ዛሬ በISVCD ፕሮጀክት ድጋፍ የተገዙ ትራክተሮች የግብርና ዘመናዊነት የሚያሳድጉና ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግሯል ።

አክለውም ለወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር የአሰራር ስርዓትን በማሻሻል በ32 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገዙ 10 ትራክተሮችን በተለያዩ ወረዳዎች በ10 ማህበራት ለተደራጁ ለ148 ወጣቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማምረት ተጠቃሚ ለመሆን የተሰጡ መሣሪያዎችን በትክክል እና በግልጽ አስተዳደር እንዲተገበሩ አሳስበዋል።

የክልሉ የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትልና የስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ከፍያለው ከበደ ትራክተሮቹ በግብርና ዘርፍ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዝ የተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ድጋፍ በክልሉ የሥራ አጥነትን ለመቀነስ እና የእርሻ እንቅስቃሴን ለማዘመን እንደሚያገለግል አብራርተዋል።

አቶ ከፍያለው አክለውም የዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶች በሙያዊ ስልጠና ተደግፈው ወደ ስራ ገብተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተዘጋጀ ስርዓት መሆኑንም ተጠቅሟል።

የISVCD ፕሮጀክት ተወካይ አቶ ሰለሞን ዳኜ በበኩላቸው
ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክቱ ልዩ እቅድ ነድፎ እየሰራ ይገኛል ያሉት ስሆን ይህ ድጋፍም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በመጨረሻም የትራክተር ማስተላለፍ ስነ-ስርዓቱ በክልሉ የወጣቶች የሥራ ፈጠራ ፖሊሲ አፈፃፀም ውስጥ አስፈላጊ እርምጃ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶች በቀጣይ የሙያ ስልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኙ ቃል ተገብቷል።

ይህም በክልሉ የዘላቂ ልማት እና የሥራ እድል መፍጠር ግቦች ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ነው ተብሎ ይጠበቃል።

ለቢሮው ለበለጠ መረጃ:_
Telegram :_https://t.me/+fPA20GFng5kxZGU8
You Tube :_https://youtube.com/?si=I0V1pgFTOeftsKWv
TikTok:_https://www.tiktok.com/?_t=8qA4mUlWXQ6&_r=1
WhatsApp :_https://whatsapp.com/channel/0029VakybqAB4hdLaMYFqm3h
ዋትስ አፕ:_https://chat.whatsapp.com/G8X4mUl03Na1cWwMPECO3h
X:_https://twitter.com/NewsSidaama?t=0-VU7tDUzLGQliHbNDY_9w&s=09
Website:_https://g.co/kgs/MpxLFG1

ለኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር ለመፍጠር ተብሎ የተዘጋጀ ባዛርና ኤግዚቢሽን በሀዋሳ ከተማ ተከፈተ **********************ሀዋሳ ፤ ግንቦት13፤2018 የቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይ...
20/05/2026

ለኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር ለመፍጠር ተብሎ የተዘጋጀ ባዛርና ኤግዚቢሽን በሀዋሳ ከተማ ተከፈተ
**********************

ሀዋሳ ፤ ግንቦት13፤2018 የቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶረት

የሀዋሳ ከተማ አሰተዳደር ሥራ አሰሪና ሠራተኛ መምሪያ ለኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር ለመፍጠር ተብሎ የተዘጋጀ ባዛርና ኤግዚቢሽን መከፈቱን ቢሮ ገለፁ ።

በመክፈቻ ላይ የተገኙት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፍን አየለ ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለመፍጠር መንግስ በርካታ ስራዎች እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በከተማችን እየተመዘገበ ያለው የስራ ፈጠራ እንቅስቃሴ የብልፅግና ፓርቲ የልማት እሳቤን በተግባር የሚያሳይ ነው ያሉት አቶ መስፍን ወጣቶች መንግስት ያመቻቸላቸው እድል ተጠቅመው ተደራጅተው ወደ ስራ እድል መግባታቸው ለከተማው ኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ አለውም ብለዋል።

አቶ መስፍን አክለውም እንደነዚህ ያሉ ባዛርና ኤግዚቢሽኖች ማዘጋጀት የምርት ትውውቅና የገበያ ትስስር ከመፍጠር ባለፈ በኢንተርፕራይዞች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ በር የሚከፍት መሆኑን ተናግረዋል ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የስራ አሰሪና ሰራተኛ መመሪያ ሀላፊ አቶ ሽታ ኤቢሶ በበኩላቸው መምሪያው የስራ እድል ፈጠራን ለማስፋፋትና የኢንተርፕራይዞችን አቅም በማጠናከር በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም ባዛርና ኤግዚቢሽኑ ኢንተርፕራይዞች ያላቸውን የምርት አቅም ለገበያ እንዲያስተዋውቁ፣ አዳዲስ የንግድ ትስስሮችን እንዲፈጥሩ እና ተጠቃሚዎችን በቀጥታ እንዲያገናኙ እድል እንደሚፈጥር ጠቅሰው በመርሃ ግብሩ ላይ ከ50 በላይ የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞችን በግብርና ፤ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ ተሰማርተው እያመረቱ ያሉ ምርቶቻቸውን ማቅረባቸውንና ባዛሩም ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑን ተናግረዋል።

እዚህ ስፍራ የተገኛችሁ ኢንተርፕራይዞች ያላችሁን ምርት በስፋትና በጥራት በማምረት ለሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በፍጥነት ማቅረብ ከቻላችሁ በሀገራችን ላይ ድህነትን ታሪክ አድርገን ለማውራት የያዝነውን የብልጽግና ጉዞአችንን እናፋጥናለን ብለዋል አቶ ሽታ።

በመጨረሻም ኢንተርፕራይዞች ያቀረቡትን ምርቶች በማስተዋወቅ ልምዳቸውን አጋርተዋል ።

ለቢሮው ለበለጠ መረጃ:_
Telegram :_https://t.me/+fPA20GFng5kxZGU8
You Tube :_https://youtube.com/?si=I0V1pgFTOeftsKWv
TikTok:_https://www.tiktok.com/?_t=8qA4mUlWXQ6&_r=1
WhatsApp :_https://whatsapp.com/channel/0029VakybqAB4hdLaMYFqm3h
ዋትስ አፕ:_https://chat.whatsapp.com/G8X4mUl03Na1cWwMPECO3h
X:_https://twitter.com/NewsSidaama?t=0-VU7tDUzLGQliHbNDY_9w&s=09
Website:_https://g.co/kgs/MpxLFG1

Sidaamu Qoqqowi Loosunna Dandoote Biironna Woshshamaano Ejensooti Hawaas Garba Latisa Aganu Damooza Aate Qaale E'u.Hawaa...
19/05/2026

Sidaamu Qoqqowi Loosunna Dandoote Biironna Woshshamaano Ejensooti Hawaas Garba Latisa Aganu Damooza Aate Qaale E'u.

Hawaasi garba latisate projekite irkisatenni haamata qansoota loosu horaameyye assa dandiinannita coyidhinori biirote massagaano qoqqowu mootimmano ikko quchumu amadino quchuma latisate mixo gumaame assate aganu damooza aate sumuu yaansa xawissino.

Biiro Hawaasi quchuma latisatenni quchuma turizimmete hattono loosu kaayyo kalaqo mereersha assate aanteno biirote gede hasiissanno irko assate qixxaawaano ikkansa huwachishshino.

የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ እና ተጠሪ ኤጀንሲዎች የሀዋሳ ሀይቅ ዳሪቻ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክትን ለመደገፍ የወር ደሞዛቸው ለገሱ

ሀዋሳ፤ ግንቦት 11፤2018 የቢሮ የህዘብ ግንኙነት ዳይሬክቶረት

የሀዋሳ ሀይቅ ዳር ልማት ፕሮጀክት ስራ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ነው ያሉት የቢሮ አመራሮች የክልሉ መንግስትና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማችንን ለማልማት የያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ የወር ደሞዛችንን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

ቢሮው በሀዋሳ ከተማ ላይ የተጀመረውን የልማት ስራዎችን ለመደገፍ ከደሞዝ ባሻገር በቀጣይነት አሰፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም አንስተዋል ።

ለቢሮው ለበለጠ መረጃ:_
Telegram :_https://t.me/+fPA20GFng5kxZGU8
You Tube :_https://youtube.com/?si=I0V1pgFTOeftsKWv
TikTok:_https://www.tiktok.com/?_t=8qA4mUlWXQ6&_r=1
WhatsApp :_https://whatsapp.com/channel/0029VakybqAB4hdLaMYFqm3h
ዋትስ አፕ:_https://chat.whatsapp.com/G8X4mUl03Na1cWwMPECO3h
X:_https://twitter.com/NewsSidaama?t=0-VU7tDUzLGQliHbNDY_9w&s=09
Website:_https://g.co/kgs/MpxLFG1

Address

Hawassa
HTTPS://T.ME/SIDAMATVETST

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251912694805

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidaamu Qoqqowi Loosunna Dandoote Biiro ሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Sidaamu Qoqqowi Loosunna Dandoote Biiro ሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ:

Share