በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Harbu
  • በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት To give information about agricultural practice to the farmers and development agents in the kebele and woreda as well as Ethiopian communities.

 (ግንቦት_27/2018 ዓ.ም)*****************🍉በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ በሁለተኛ ዙር የመስኖ ልማት የለማው ሀብሃብ በአሁኑ ወቅት ለተጠቃሚው ማህበረሰብ እና ለተለያዩ ገበያዎ...
04/06/2026

(ግንቦት_27/2018 ዓ.ም)
*****************
🍉በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ በሁለተኛ ዙር የመስኖ ልማት የለማው ሀብሃብ በአሁኑ ወቅት ለተጠቃሚው ማህበረሰብ እና ለተለያዩ ገበያዎች በስፋት እየቀረበ ይገኛል።

የመስኖ ልማቱ ለአርሶ አደሮች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ከመፍጠሩ ባሻገር፣ መሬታቸውን በተሻለ ሁኔታ የመጠቀምና የመንከባከብ ባህላቸውን በማጠናከር የግብርና ምርታማነትን እያሳደገ ይገኛል።

🌱 መስኖ_ለምግብ_ዋስትና
🍉 ሀብሃብ_ለገቢ_ማሳደጊያ
👨‍🌾 ለአርሶ_አደሮች_የተሻለ_ኑሮ




#ሀብሃብ #ምርታማነት

21/05/2026
 - ።************* #​የምርት ዘመኑ ዋና ዋና ግቦች፡-✅ የመሬት ስፋት፡ 22 ሺህ 103 ሄክታር መሬት በሰብል ይሸፈናል።✅ የተቀመጠ ምርት ግብ፡- ከ685,000 ኩንታል በላይ ምርት...
09/05/2026

- ።
*************
#​የምርት ዘመኑ ዋና ዋና ግቦች፡-
✅ የመሬት ስፋት፡ 22 ሺህ 103 ሄክታር መሬት በሰብል ይሸፈናል።
✅ የተቀመጠ ምርት ግብ፡- ከ685,000 ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።
✅ ትኩረት፡ በክላስተር የማምረት ልምድ፣ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የእርሻ መካናይዜሽን ይሰጣሉ ።

#​መድረኩን በንግግር የከፈቱት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሃመድ ኑር እንደገለጹት፣ የሀገርን ኢኮኖሚ ለማጠናከር ምርትና ምርታማነትን በእጥፍ ማሳደግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ ከአነስተኛ መሬት ከፍተኛ ምርት ለማግኘት ከተለመደው አሠራር ወጥቶ በዘመናዊ መንገድ ማምረት እንደሚገባ አሳስበዋል።

​የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም እንድሪስ በበኩላቸው፣ ለምርት ዘመኑ ስኬታማነት፦
​የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ አቅርቦት፣​የምርጥ ዘር አጠቃቀም፣
​እና የትራክተርና መሰል የመካናይዜሽን አሠራሮች በስፋት ተግባራዊ እንደሚደረጉ አረጋግጠዋል።

​ለታቀዱ ግቦች ስኬት ሙያዊ ድጋፍና ቀጣይነት ያለው ክትትል ወሳኝ መሆኑም በመድረኩ ተመላክቷል።

​"በጋራ በመሥራት የምግብ ዋስትናችንን እናረጋግጣለን!!"

  (ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም)*************​በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የግብርና ኤክስቴንሽን አደረጃጀት አባላቶች በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ ያተኮረ የመስክ ምልከታና የልምድ ...
07/05/2026

(ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም)
*************
​በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የግብርና ኤክስቴንሽን አደረጃጀት አባላቶች በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ ያተኮረ የመስክ ምልከታና የልምድ ልውውጥ በዛሬው ዕለት በሁሉም ቀበሌዎች አካሂደዋል ።
​በመርሃ ግብሩም አባላቱ እርስ በርስ ያላቸውን ጠንካራ ተሞክሮዎችና ውጤታማ አሰራሮች የተጋሩ ሲሆን፣ በቀጣይ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች የተሻለ መነቃቃትና የስራ ቁርጠኝነት እንዲፈጠር አስችሏል።
​የመስክ ምልከታና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብሮች በግብርና ልማት ስራዎች ላይ የተሻሉ ተሞክሮዎችን ለማስፋፋትና የተቀናጀ የስራ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው።

#ግብርና #ልማት #አርጎባ #ኢትዮጵያ

 #በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ  የግብርና ኤክስቴንሽን አደረጃጀቶችን ለማጠናከርና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በተቀረጸው ፕሮግራም መሠረት ቀበሌዎች በዛሬው ዕለት  የግብርና ልማት ቡድን መሪዎ...
05/05/2026

#በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የግብርና ኤክስቴንሽን አደረጃጀቶችን ለማጠናከርና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በተቀረጸው ፕሮግራም መሠረት ቀበሌዎች በዛሬው ዕለት የግብርና ልማት ቡድን መሪዎችን እና የግብርና ልማት ቀጠና ተጠሪዎችን በቀበሌ ማዕከል በማሰባሰብ የስራ አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል ።

ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም

  !! 🍌🍌🥭🥭 #​በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ በመይጢ መስኖ ላይ ሰፊ የፍራፍሬ ልማት በክላስተር ለመሸፈን የታቀደው ፕሮግራም አበረታች ውጤት እያሳየ ይገኛል።​በአሁኑ ወቅት የማሳ ዝግጅት ...
30/04/2026

!! 🍌🍌🥭🥭

#​በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ በመይጢ መስኖ ላይ ሰፊ የፍራፍሬ ልማት በክላስተር ለመሸፈን የታቀደው ፕሮግራም አበረታች ውጤት እያሳየ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት የማሳ ዝግጅት ስራዎች በጥራት እየተከናወኑ ሲሆን፣ የሙዝ እና የማንጎ ችግኞችን ለአርሶአደሩ የማቅረብ ስራ በስፋት ተጀምሯል።

ይህ የክላስተር አመራረት የፍራፍሬ ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ገቢ ከመቀየር ባለፈ፣ ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ይታመናል።

​ #ልማት #አርጎባ #መስኖ #ፍራፍሬ #ግብርና #ኢትዮጵያ

 !በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የግብርና ዘርፉን ለማዘመን እና ምርታማነትን ለማሳደግ የተደራጀ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።በወረዳው በአጠቃላይ 22,103 ሄክታር የሚታረስ መሬት ሲኖር፣ በ20...
29/04/2026

!

በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የግብርና ዘርፉን ለማዘመን እና ምርታማነትን ለማሳደግ የተደራጀ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
በወረዳው በአጠቃላይ 22,103 ሄክታር የሚታረስ መሬት ሲኖር፣ በ2018/19 የምርት ዘመን የማሽላ ዘር ስራ በስፋት እየተከናወነ ነው።
በተለያዩ የማሽላ ክላስተር እርሻዎች ላይ የግብርና ፓኬጆችን በተሟላ ሁኔታ በመተግበር፣ ምርታማነትን በማሻሻል የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር እና የአርሶ አደሮችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ግብ ተይዞ እየተሰራ ነው።

  /ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም /በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ለ2018/19 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በሦስት ሁለገብ ሕብረት ሥራ ማህበራት በኩል ለአርሶ አደሮች እየተሰራጨ ይ...
23/04/2026

/ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም /

በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ለ2018/19 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በሦስት ሁለገብ ሕብረት ሥራ ማህበራት በኩል ለአርሶ አደሮች እየተሰራጨ ይገኛል።
ግብዓቱ በወቅቱ መቅረቡ አርሶ አደሮች የግብርና ፓኬጆችን አሟልተው እንዲተገብሩ አቅም ስለሆነ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናው የተረጋገጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያስችላል ።

 !   !!
12/04/2026

!


!!

Address

Harbu

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share