Harbu City Government Communication /ሀርቡ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን/

  • Home
  • Ethiopia
  • Harbu
  • Harbu City Government Communication /ሀርቡ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን/

Harbu City Government Communication /ሀርቡ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን/ Information communication

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሻሻ ድምፅ ሰጡ *******************ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋ...
01/06/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሻሻ ድምፅ ሰጡ
*******************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ እና ለአማራ ክልል ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲ እጩ ፋንቱ ተስፋዬ ድምጻቸውን ሰጡ።በቃሉ አንድ ምርጫ ክልል በኮምቦልቻ ከተማ ቢራሮ ክፍለ ከተማ በቦር...
01/06/2026

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ እና ለአማራ ክልል ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲ እጩ ፋንቱ ተስፋዬ ድምጻቸውን ሰጡ።

በቃሉ አንድ ምርጫ ክልል በኮምቦልቻ ከተማ ቢራሮ ክፍለ ከተማ በቦርቸሌ ቀበሌ ጅነአድ የምርጫ ጣቢያ በመገኘት ለአማራ ክልል ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ በቦታው ተገኝተው ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር  ዶ/ር አብዱ ሁሴን በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል ተገኝተው   ድምጻቸውን ሰጡ።
01/06/2026

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር አብዱ ሁሴን በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል ተገኝተው ድምጻቸውን ሰጡ።

01/06/2026
"ኢትዮጵያ" እየመረጠች ነውበደቡብ ወሎ ዞን ሀርቡ ከተማ አስተዳደር ዜጎች እየመረጡ ነው
01/06/2026

"ኢትዮጵያ" እየመረጠች ነው

በደቡብ ወሎ ዞን ሀርቡ ከተማ አስተዳደር ዜጎች እየመረጡ ነው

በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ለነገው ታሪካዊ ዕለት እየተሰናዱ ነውግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ዞን ስር በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተቋቋሙ ...
31/05/2026

በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ለነገው ታሪካዊ ዕለት እየተሰናዱ ነው

ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም

በደቡብ ወሎ ዞን ስር በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች፣ ድምጽ ለመስጠት ለሚወጣው ህዝብ አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት እያጠናቀቁ ይገኛሉ።

ጣቢያዎቹ ቁሳቁሶችን ከማሟላት ጀምሮ ለድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ምቹ ሆነው ተሰናድተዋል።

South Wollo Zone Gov. Communication Dept.

በደቡብ ወሎ ዞን በሀርቡ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ጣቢያዎች ዝግጁ ሁነዋል። ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ሰባተኛው አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ በደቡብ ወሎ ዞን በሀርቡ ከተማ ሁሉም የ...
31/05/2026

በደቡብ ወሎ ዞን በሀርቡ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ጣቢያዎች ዝግጁ ሁነዋል።

ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ሰባተኛው አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ በደቡብ ወሎ ዞን በሀርቡ ከተማ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በመዘጋጀት ላይ ናቸው።

ቦርዱ የምርጫ ቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ ጥቆማ ማድረጊያና ምላሽ መስጫ ሥርዓት አቋቋመየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዜጎች ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጋር የተያያዙ ችግሮችንና ክስተቶችን ደኅንነቱ በተጠ...
30/05/2026

ቦርዱ የምርጫ ቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ ጥቆማ ማድረጊያና ምላሽ መስጫ ሥርዓት አቋቋመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዜጎች ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጋር የተያያዙ ችግሮችንና ክስተቶችን ደኅንነቱ በተጠበቀና ፈጣን በሆነ መንገድ ጥቆማ የሚያደርጉበትን “ከምርጫ ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩ ችግሮች ሪፖርት ማድረጊያ እና ምላሽ መስጫ ሥርዓት” ዘርግቷል።
ይህ ሥርዓት ምርጫ ቦርድ፤ የሚመለከታቸው ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት መረጃዎችን አስቀድመው እንዲያገኙ፣ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ እንዲሁም ሰላማዊና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድ ለማገዝ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ምን ዓይነት ችግሮችን ጥቆማ ማድረግ ይችላሉ?
• በምርጫ ሂደቶች ላይ የሚፈጠሩ መስተጓጎሎች፣
• በድምፅ አሰጣጥ ወይም በቆጠራ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች፣
• በምርጫ ጣቢያዎች አቅራቢያ የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች፣
• በመራጮች ላይ የሚደርስ ማስፈራራት ወይም ትንኮሳ፣
• በምርጫ ቁሳቁስ ላይ የሚደርስ ጉዳት፣
• ዐመፅ ወይም ዛቻዎች፣
• ውጥረት የሚፈጥሩ የሐሰት መረጃዎች፣
• እንዲሁም ምርጫውን ሊያስተጓጉል የሚችል ወይም ማንኛውም ሌላ አጠራጣሪ ድርጊት ጥቆማ ማድረግ ይችላሉ።

መቼ ጥቆማ መስጠትይኖርብዎታል?
• የምርጫ ሂደቶች ሲስተጓጎሉ ሲመለከቱ፣
• ከላይ የተጠቀሱትን ክስተቶች በቀጥታ ከተመለከቱ፣
• የዐመፅ ወይም የግጭት ሥጋት ካለ፣
• እንዲሁም አስቸኳይ ዕርምጃ የሚያስፈልጋቸው ማንኛውም ምርጫን የሚያውኩ ክስተቶች ከተመለከቱ።

ችግሮችን አስቀድሞ ሪፖርት ማድረግ ሁኔታዎች እንዳይባባሱ ለመከላከልና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ይረዳል።

እንዴት ጥቆማ መስጠት ይችላሉ?

በሚከተሉት መንገዶች ጥቆማ መስጠት ይችላሉ፦
• በነፃ የስልክ መስመር 6214 ላይ በመደወል
• አጭር የጽሑፍ መልዕክት ወደ 7555 በመላክ
ሪፖርት ሲያደርጉ የሚከተሉትን መረጃዎች ለማካተት ይሞክሩ፦
• ምን እንደተከሰተ
• የት እንደተከሰተ
• መቼ እንደተከሰተ
• ማን እንደተሣተፈበት (የሚታወቅ ከሆነ)

ማን ጥቆማ መስጠት ይችላል?
ማንኛውም ሰው ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክስተቶችን ጥቆማ መስጠት ይችላል፤ ከእነዚህም መካከል፦
• ዜጎች፣
• የምርጫ ታዛቢዎች፣
• የፖለቲካ ፓርቲዎች፣
• የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣
• የሴቶችና የወጣቶች ማኅበራት፣
• ምርጫ አስፈጻሚዎች፣
• የቦርዱ ሠራተኞችና ኃላፊዎች ጥቆማ

ጥቆማ ከተሰጠ ካደረጉ በኋላ ምን ይከናወናል?
1. ጥቆማዎ እኛ ጋር ከደረሰ በኋላ ይመረመራል፣
2. የቀረበው መረጃ ትክክለኛነት ይረጋገጣል፣
3. እንደ አስፈላጊነቱ ምርጫ ቦርድ እና የሚመለከታቸው ተቋማት በቅንጅት ምላሽ ይሰጣሉ።
4. የተወሰደው ዕርምጃ ወይም የተሰጠው ምላሽ ለጥቆማ አቅራቢው ሊገለጽ ይችላል፣

የእርስዎ ጥቆማ መስጠት ለምን አስፈለገ?
የሚያቀርቡት ጥቆማ ለሚከተሉት ጉዳዮች ይረዳል፦
• የምርጫውን ግልጸኝነት ለማሻሻል፣
• ሰላማዊ እና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድ ለማገዝ፣
• መራጮችን እና የምርጫ አስፋጻሚዎችን ደኅንነት ለመጠበቅ፣
• ዐመፅ እና ግጭቶችን ለመከላከል፣
የምርጫውን ሂደት ሊያስተጓጉል የሚችል ማንኛውንም ችግር ካዩ ወይም ካጋጠመዎት እባክዎን ወዲያውኑ ጥቆማ ይስጡ!
እያንዳንዱ ጥቆማ ይበልጥ ደኅንነቱ የተጠበቀ የምርጫ ሂደት እንዲኖር አስተዋፅዖ ያበረክታል።

የመገናኛ መንገዶች
ነፃ የስልክ መስመር 6214
አጭር የጽሑፍ መልዕክት 7555
አድራሻ: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ| አዲስ አበባ
ድረ-ገጽ www.nebe.org.et

" 'መንገድ ተዘግቷል' በሚል የሚራገበው ፕሮፖጋንዳ የጽንፈኛ ኃይሉ የተለመደ የሐሰት ወሬ ነው" እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር) ከአሚኮ ጋር...
30/05/2026

" 'መንገድ ተዘግቷል' በሚል የሚራገበው ፕሮፖጋንዳ የጽንፈኛ ኃይሉ የተለመደ የሐሰት ወሬ ነው" እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር) ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ የጸጥታ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል።

የምርጫ ቁሳቁስ በክልሉ በሚገኝ የምርጫ ክልሎች ያለምንም ጸጥታ ስጋት እንዲደርስ መደረጉንም አስታውቀዋል። መራጩ ሕዝብም በምርጫው ዕለት ያለ ምንም ስጋት ድምፁን መስጠት እንዲችል በየጣቢያዎቹ በቂ የጸጥታ ስምሪት ተደርጓል ነው ያሉት።

የጸጥታ ኀይሉ ሰላምን የማስከበር እና ደኅንነትን የማረጋገጥ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ መኾኑንም አስገንዝበዋል።

ከጸጥታ መዋቅሩ በተጨማሪ መላው ማኅበረሰብ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በንቃት እየተሳተፈ መኾኑን አብራርተዋል። በተለይም ወጣቶች አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ለጸጥታ አካላት በመጠቆም ትልቅ እገዛ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

"መንገድ ተዘግቷል" በሚል የሚራገበው ፕሮፖጋንዳ የጽንፈኛ ኃይሉ የተለመደ የሐሰት ወሬ ነው፤ በዚህ ወቅት መደበኛ ሥራዎችም ኾኑ ወቅታዊ ተግባራት በአግባቡ እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በዚህ ወቅትም በክልሉ የምርጫ ቁሳቁስ እና የአፈር ማዳበሪያ በተፈለገው አካባቢ ያለምንም ችግር እንዲደርስ እየተደረገ መኾኑን ተናግረዋል። ኅብረተሰቡም ለተለመደ የመንገድ ተዘግቷል የጽንፈኛ ኀይል የማደናገሪያ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ጀሮ ሳይሰጥ የእለት ከእለት ተግባሩን ያለምንም ስጋት እንዲከውን አሳስበዋል።

***********
አሚኮ

Address

Harbu

Telephone

+251909257361

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harbu City Government Communication /ሀርቡ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share