04/06/2026
የሐረሪ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በ“ሰቆጣ ቃልኪዳን ማስፋፊያ ፕሮጀክት” አማካኝነት በአሚር ኑር ወረዳ በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን እና በፆታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶችን (GBV) ለመከላከል ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
ተማሪዎች ከማንኛውም ዓይነት ጥቃትና ስጋት ነፃ በሆነ አካባቢ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ እንዲገነባ ቢሮው ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል።
ስልጠናው የፆታ ተኮር ጥቃት ምንነት፣ ዓይነቶች፣ መንስኤዎችና የመከላከል ስልቶችን በስፋት የዳሰሰ ሲሆን፣ አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ የወሲብ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቃቶች በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚያስከትሉት አሉታዊ ተፅዕኖ በዝርዝር ተብራርቷል።
በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከል ለማስወገድ ጤናማና ንቁ ማህበረሰብ ለመገንባት ያለመ ነው።
በስልጠናው በተለይም የሴት ልጅ ግርዛት በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚያስከትለው ከፍተኛ የጤና፣ የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ጉዳት በስፋት ተብራርቷል።
በአሚር ኑር ወረዳ ከሚገኙ አራት ቀበሌዎች በሴቶችና ህፃናት ላይ የጥቃት ተከላካይ ኮሚቴ በስልጠናው ተሳትፈው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን እና የፆታ ተኮር ጥቃቶችን ለማስወገድ በትብብር እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
“በፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን መከላከል የሁላችንም ኃላፊነት ነው፤ የሴቶችና የህፃናት መብት ሲከበር ጤናማና የተረጋጋ ማህበረሰብ ይገነባል።”